Ethiopians life in cape town

Ethiopians life in cape town መረጃ የፍትህ ደምጽ በዚህ ሚዲያ ላይ እናቀርባለን ይህ ፔጅ መቀመጫው ደቡብ አፍሪካ ስሆን ጠቅላለ በአለም ዙሪያ ያለውን መረጀውችን የምያከትት ስሆን ለሁልም አግልግሎቶች መልዕክቶች መጠቅም ይቻላል!!!

06/09/2026

ከመሞታችሁ በፊት አንድ ህልም ይሳካላችሁ 🙏

ከቁንጅና ውድድሩ ወጣ እንበልና : ድምፅ ያልሰጣችሁ ድምፅ እየሰጣችኃትአንዱ ክርክር የለበሰችው አልባሳት ጉዳይ ነው: አለም አቀፍ መድረክ ላይ "ኢትዮጵያን የማይወክል ልብስ ለበሰች" የሚሉ የ...
04/09/2026

ከቁንጅና ውድድሩ ወጣ እንበልና : ድምፅ ያልሰጣችሁ ድምፅ እየሰጣችኃት


አንዱ ክርክር የለበሰችው አልባሳት ጉዳይ ነው: አለም አቀፍ መድረክ ላይ "ኢትዮጵያን የማይወክል ልብስ ለበሰች" የሚሉ የፕላኔቱ ሰዎች እያየሁኝ ነው

👇🏾

የለበሰችው ልብስ ከኢትዮጵያዊነት መገለጫ አንዱ የሆነውን ልብስ ነው

ምን ብትለብስ ነበር ኢትዮጵያዊ የሚያስብላት?

እንደዚህ አይነት "መገለጫ" ተብዬ መገለጫዎች ሰፋ ማለት አለባቸው : መቀበል እና ማድነቅ መቻል አለብን:: There is no specific “የኢትዮጵያ ልብስ እና መገለጫ" as far as my knowledge is concerned

👇🏾

ነጩን ልብስ ስንለብስ ያምራል: የደቡብ ኢትዮጵያ አልባሳትም የእኛ ናቸው: የኮንሶ እና ዳሰነች ልብሶችም መገለጫዎቻችን ናቸው: የሰሜን ኢትዮጵያ ልብሶቻችንም መድመቂያዎቻችን ናቸው: የኦሮሚያ አልባሳትም የእኛ ናቸው: የጉራጌ ልብሶች እና ባህልም የምንወደው ነው

ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን !


መገለጫችንም የተለያየ ነው

🙌❤️

01/09/2026

SamiDaily7 follow አድርጉ

ተማሪ ሮቤል ጌታቸው በ 2018 E.C የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አስደማሚ ውጤት አስመዘገበበሀዲያ ዞን የሚገኘው የሊችጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት (Lichgogo Board...
26/08/2026

ተማሪ ሮቤል ጌታቸው በ 2018 E.C የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አስደማሚ ውጤት አስመዘገበ

በሀዲያ ዞን የሚገኘው የሊችጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት (Lichgogo Boarding School) ተማሪ የሆነው ሮቤል ጌታቸው ገብሬ በ 2018 E.C የ 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 590.08 ያመጣ ሲሆን፡ ይህ ውጤት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከከፍተኛው ውጤት በ 1 ነጥብ ብቻ የሚለይ ድንቅ ስኬት ነው።

የተማሪው የፈተና ውጤት ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

1. እንግሊዝኛ (English): 99.00

2. ሒሳብ (Mathematics): 95.00

3. አጠቃላይ የብቃት መለኪያ ፈተና (Scholastic Aptitude Test): 98.33

4. ፊዚክስ (Physics): 100.00

5. ኬሚስትሪ (Chemistry): 98.75

6. ባዮሎጂ (Biology): 99.00

• ጠቅላላ ድምር ውጤት (Total): 590.08

• አማካይ ውጤት (Average): 98.35

በፊዚክስ ትምህርት ሙሉ 100 በመቶ ያስመዘገበው ተማሪ ሮቤል ጌታቸው፣ ላሳየው ከፍተኛ የትጋትና የጽናት ፍሬ እንኳን ደስ አለህ እንላለን።

እንዲሁም ለዚህ የላቀ ውጤት መገኘት መሰረት የሆነውንና ጥራት ያለው ትምህርት ሲሰጥ የቆየውን የሊችጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት ማህበረሰብ፣ መምህራንና የቤተሰብ አባላትን ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።

Vi EAES

👏👏👏

በአንድ ብር አንድ ቡና የጠጣ ሰው አለ? ዓ.ም እና ቦታ ጥቀሱ✍️
26/08/2026

በአንድ ብር አንድ ቡና የጠጣ ሰው አለ? ዓ.ም እና ቦታ ጥቀሱ✍️

19/08/2026

አንድ ልጅ መንገድ ላይ ተጠይቆ ለሀገርህ ትሞታለህ ወይ ተብሎ እንዲስል መለሰላቸው አዎ ለሀገር ይሞታል ከዚህ በላይ ሞት አለ ወይ አሁንም ሞተናል 🙏እኮ እየኖረን አይደለም ⚠️🤣

18/08/2026

ኢትዮጵያ ላይ ከጦርነት ውጪ ምን ያስደስታችኋል 🙏?

17/08/2026

ዜግነት የመምረጥ መብት ብኖራችሁ የት ሀገር ዜገ መሆን ትፈልጋላችሁ? 🙏 ለምን?

መልካም ወጣት ከ******
14/08/2026

መልካም ወጣት ከ******

12/08/2026

ደቡብ አፍሪካ ሰነድ አልባ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለመመለስ ያወጣችውን ወጪ ኢትዮጵያ እንድትከፍል ጠየቀች‼️

ደቡብ አፍሪካ በተያዘው ዓመት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ካወጣችው ከ18 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የተወሰነውን ወጪ እንዲሸፍኑ ለኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ማላዊ ጥያቄ አቀረበች።

የደቡብ አፍሪካ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ጥያቄው መቅረቡን ይፋ ያደረገው ማክሰኞ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ለፓርላማው የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሰጠው ማብራሪያ ወቅት ነው።

የቋሚ ኮሚቴው ዋና ዳይሬክተር ቶሚ ማኮዴ እንደገለጹት፣ ሚኒስቴሩ ለዚህ ተግባር ቀደም ሲል የመደበው በጀት 60 ሚሊዮን ራንድ ብቻ ቢሆንም፣ እስካሁን 292 ሚሊዮን ራንድ ስደተኞችን ለመመለስ ወጪ አድርጓል።

ማኮዴ ስደተኞችን የመመለስ መርሃ-ግብር «በጀት ያልተያዘለት ኃላፊነት» መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴርም ሆነ ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ለዚህ ያህል ሰፊ እንቅስቃሴ በጀት እንዳልመደቡ ተናግረዋል።

አክለውም የትራንስፖርት ክፍያው ወጪው ከፍተኛ እንዲሆን ዋና ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

Address

Cape Town

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopians life in cape town posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopians life in cape town:

Shortcuts

Share