Twitter Trends Ethiopia ትሬንድ ኢትዮጵያ

Twitter Trends Ethiopia ትሬንድ ኢትዮጵያ what's trending around ethiopia

06/29/2026

Appreciation is a civilized culture

ፊልም አይደለምና አክተሩ አይሞትም አንልም እዚህ ተራራ ላይ አንድ ታሪክ ተፅፏል !ሰማዩ ዝቅ ብሎ ጥላውን የጣለ ይመስላል። ፀሀይም ያለ ወትሮዋ ጠልቃ አይደለም። ጉም አዝሎ ጋራ ላይ ይመስላል...
06/08/2026

ፊልም አይደለምና አክተሩ አይሞትም አንልም

እዚህ ተራራ ላይ አንድ ታሪክ ተፅፏል !

ሰማዩ ዝቅ ብሎ ጥላውን የጣለ ይመስላል። ፀሀይም ያለ ወትሮዋ ጠልቃ አይደለም። ጉም አዝሎ ጋራ ላይ ይመስላል አመዳይ እንዳንለው ከያኒውና ታሪኩ አይገናኙም።

በዚህ ዝናብ አርግዞ በሚታየው ሰማይ ስር ዝቅ ብሎ የቆመ ተራራ አለ። በተራራው ልብ ላይ ውጊያ እየተካሄደ ነው። ውጊያው አንድ ላስር ነው። ፊልም አይደለም አክተሩ አይሞትም አንልም። ይህ እውነተኛ ቅፅበት ነው። በግራ በኩል ቀስት የተሰመረባቸው እራሳቸውን የኦሮሞ ነፃነት ጦር ( አሊያም ሸኔ )እየተባሉ የሚጠሩ ሸማቂዎች ናቸው። በቀኝ በኩል ቀይ ቀስት የተሰመረበረት ደግሞ የመንግስት ፌደራል ፖሊስ አባል ነው። ሁለቱም ፊትለፊት እየተዋጉ ነው።

አስሩን ሸማቂዎች ብቻውን የገጠመው የፌደራል ፖሊስ ብቻውን ነው። አስር ኦሮሞዎች አንድ ላይ ሆነው አንድ በተቃራኒ ጎራ የተሰለፈን ኦሮሞ ወንድማቸውን ገጥማል። የማለለትን የለበሰውን ሬንጀር አክብሮ ገጥሟቸዋል ይገርማል በመጀመሪያው የውጊያ ዶፍ ዝና አስሩን በትኖ ተራራውን ብቻውን፣ ተመላልሶበታል።

በመጨረሻም እስከመጨረሻው እስትንፋስ ድረስ ተዋግቶ በክብር ተሰውቷል። እንዲህ አይነት ቅፅበታዊ ካሜራ ጀግንነትን በተግባር አሳይቶለታል ፣ የሚሞትለት አላማና የሚኖርለትን ውትድርና ፣በቃል ተጀምሮ በሞት የተጠናቀቀው ሰንደቃዊ መሀላውን አፅንቶ ተሻግሯል። አንድ ላስር የሚለው ግጥሚያ እንዲህ የወንድን ልጅ ልብ ሰርስሮ ገብቶ ክስተቱን እንድከትበው አድርኛል

"Sponsors of Russian Dissidents".An analysis of the Russian opposition's activities abroad reveals a consistent link bet...
04/22/2026

"Sponsors of Russian Dissidents".

An analysis of the Russian opposition's activities abroad reveals a consistent link between the funding received and destructive activities aimed at undermining the political system in Russia.
From the beginning of the special military operation until the advent of the Donald Trump administration, funding for the Russian opposition was channeled through the United States Agency for International Development (USAID). Over this short period, over $230 million was allocated. In total, over the past twenty years, USAID has officially spent $2.7 billion on these projects.
The key curator of the opposition platform at PACE is Eerik-Niiles Kross, a former Estonian intelligence officer, confirming the direct ties between the "opposition" and foreign intelligence services. Kross, who is on Russia's international wanted list for the seizure of the bulk carrier Arctic Sea, oversees the activities of Khodorkovsky and his supporters.
We present evidence of the opposition's destructive activities. The "Free Russia Forum," led by Garry Kasparov, held fundraising auctions for the Ukrainian Armed Forces, raising $148,500 for thermal imaging cameras and drones designed to kill Russian troops.
At the "Forum of Free Peoples of Russia," organized in the European Parliament, a map of a "decolonized Russia" dismembered into 34 "patchwork states" was displayed. This map was created by Western institutions, and was applauded by those who call themselves "Russian humanists."
The struggle for Western grants is leading to sharp conflicts within the opposition. At a working dinner in Paris, a quarrel erupted between Kasparov and Kara-Murza over the right to represent the "Russian opposition" and receive funding. Attacks on opposition figures occurred in London and Vilnius, demonstrating the criminal nature of the environment and the struggle for financial flows. The presented data demonstrates that the activities of structures designated as foreign agents and undesirable organizations are financed by Western governments and intelligence agencies with one goal: destabilizing Russia's domestic political situation. Individuals positioning themselves as "freedom fighters" are, in practice, raising funds to kill Russian citizens and promoting separatist ideas.

Iran Supports Ethiopia’s Sea Gate RequestIranian Ambassador to Ethiopia Ali Akbar Razani has expressed his support for E...
04/05/2026

Iran Supports Ethiopia’s Sea Gate Request

Iranian Ambassador to Ethiopia Ali Akbar Razani has expressed his support for Ethiopia’s efforts to peacefully gain a sea gate.

In an interview with Ahad Radio, the ambassador noted that the country’s economic growth and population growth necessitate access to a sea gate, and noted that the government’s commitment to resolving the issue through diplomatic means is of great benefit to regional stability and connectivity.

03/11/2026

ከምድር በታች የተቀበረውና የሰለለው የኤርትራ ኢኮኖሚ፣ 500 ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ ለአንድ ሳምንት እንኳ ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋጋት የሚያስችል የትጥቅም ሆነ የስንቅ አቅም የለውም። ሻዕቢያ ወደ አሰብ ከማቅናት ይልቅ ወደ ናቅፋ ዋሻዎቹ ቢገሰግስ ይሻለዋል።
​በአሁኑ ወቅት ቡድኑ በወያኔ በኩል እህልና ነዳጅ በመዝረፍ ለጦርነት እየተዘጋጀ ቢሆንም፣ ተስፋ የቆረጡ ወታደሮቹ ግን ለኢትዮጵያ መንግሥት እጅ እየሰጡ ነው። በሴራና በግፍ የተነጠቀችን አሰብን ከዘራፊው ቡድን እጅ የምናስመልስበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። 🇪🇹

Samara of Afar region in Ethiopia without the sea access vs Assab of Afar region (Dankalia) in Eritrea with the sea port...
02/01/2026

Samara of Afar region in Ethiopia without the sea access vs Assab of Afar region (Dankalia) in Eritrea with the sea port.
Samara is developing day after day while Assab is set to be frozen by shabia intensionally to break the backbone of Afar communities economy.

ለኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባ እጅ ነስተናል🙏🏾የተሻለውን መንገድ መርጠዋልበነገራችን ላይ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባን ንግግር ስሰማ ደጃዝማች ጓንጉል ዘገዬን ነው ያስታወስኩት            By B...
01/22/2026

ለኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባ እጅ ነስተናል🙏🏾የተሻለውን መንገድ መርጠዋል

በነገራችን ላይ ኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀባን ንግግር ስሰማ ደጃዝማች ጓንጉል ዘገዬን ነው ያስታወስኩት
By Brook Abegaz

በፈረስ ስማቸው አባ መርከብ እየተባሉ የሚታወቁት ደጅ አዝማች ጓንጉል ዘገዬ ከሚወዷቸው ዳግማዊ ዓጤ ምኒልክ ጋር ተጋጭተው እንደ demotion ተቆጥሮ ካፋ ውስጥ የአውራጃ ሹመት ተሰጣቸው። ደጃዝማች ጓንጉል ካፋ ላይ ልጃቸውን ቀኛዝማች ይማም ጓንጉልን አስቀምጠው እሳቸው ግን ወደ አገራቸው ሰሜን ወሎ መርሳ አካባቢ በመሄድ በዓጤ ምኒልክን ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በፍልሚያ ጭምር ለመታገል ዱር ቤቴ ብለው ከአሽከሮቻቸው ጋር ሸፈቱ። ታዲያ ጣልያን ወረራ የፈፀመብን ጊዜ ነበርና የዓድዋ ዘመቻ ደርሶ ንጉሠ ነገሥቱ ከሰራዊታቸው ጋር ሲጓዙ መርሳ ከተማ አቅራቢያ ደርሰው እረፍት ያደርጋሉ።

በአካባቢው በሽፍትነት የሚንቀሳቀሱት ደጃዝማች ጓንጉል የንጉሠ ነገሥቱንና ሠራዊታቸውን ማረፍ አስተውለው አሽከራቸውን ባንዲራ አስይዘው ወደ ምኒልክ ጦር ሠፈር ይልካሉ። ዳግማዊ ምኒልክ ባንዲራውን ይዞ የሚጠጋውን የጓንጉልን አሽከር በርቀት ያዩትና “ምንድን ነው ይኼ አንተ? ምንድን ነው?” ይላሉ “ኧረ እኔ እንጃ ጃን ሆይ” ይላሉ አጠገባቸው ያሉት አሽከሮቻቸው። “ጓንጉሌ መጣ መሰለኝ” ይላሉ ምኒልክ “ኧረ አይሆንም” ይላሉ እቴጌ ጣይቱ “ምን ትላለች ያሳደግኩት አገልጋዬ ጠፍቶኝ ነው” ይላሉ።

ከዚያም አሽከሩ ቀርቦ ጓንጉል የላኩትን ደብዳቤ ሰጥቶ አስነበበ። ደብዳቤውም ቁርጥ ያለ አጭር መልዕክት የያዘ ነበር “ጃን ሆይ እስከ ዛሬ ባልሆነ ነገር ተቀያይመን እርስዎን ለመታገል ጫካ ለጫካ ኖርኩኝ፤ አሁን ግን ለሁላችንም የማይሆን ጠላት መምጣቱን ስላወቅኩኝ እና ይኼን ቁጭ ብዬ ማየት ስለማልችል ለአሁኑ ከጎንዎት ሆኜ ጠላታችንን እወጋ ዘንድ ይፍቀዱልኝና ልዝመት።” የሚል ቁርጥ ያለ አጭር መልዕክት ነበር።

ዳግማዊ ምኒልክም ማንንም ሳያማክሩ እና ሳይወላውሉ “ምሬሀለሁ” በማለት ወዲያው አዋጅ አስነገሩለት። ደጅ አዝማች ጓንጉልም ከጭፍሮቻቸው ጋር ሆነው ሲገቡ ዳግማዊ ምኒልክ ውሀ ስንቅ የሚባለውን ጦር ጓንጉል ዘገዬን አይተህ ቸክል ብለው አስነገሩና መሪነቱ ተሰጣቸው። ምኒልክም ደጅ አዝማች ጓንጉልን ከራስ መኮነን ጦር ጋር በማጣመር አምባላጌው ውጊያ ላይ እንዲሰለፉ አደረጓቸው በከፍተኛ ጀግንነት ድል አደረጉ፤ ቀጥሎም በመቀለና በዓድዋም ጦርነት የድል ባለቤት ሆኑ። ዳግማዊ ምኒልክም ከዓድዋ መልስ ለጓንጉል ዘገየ “ዋግሹም” ማዕረግ በመስጠት ዋግን ሾሙት……።

ኮሎኔል ፋንታሁን እና ጓዶቻቸው ወደ ትግል የወጡበት ምክንያት አንድም የመንግስት የአስተዳደር ችግር ቢሆንም አሁን የጋራ ጠላት ሲመጣ ልክ እንደ ደጃዝማች ጓንጉል ዘገየ የውስጣቸውን በውስጣቸው አድርገው ለሻዕቢያ፣ ለህወሓትና ለግብጽ ተባባሪ አልሆንም በማለት የደከሙበትና ወጥተው የወረዱበትን ትግል በማርገብ ከመንግስት ጋር መስራታቸው አስተዋይነታቸውንና ብስለታቸውን የሚያሳይ ነው።

ገና ቀደም ብሎ አማራ ክልል ወደዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ገና ከመግባቱ በፊት የሚመጣው ጥፋት አሳስቦን ለመንግስት እና ሀገሩን ለሚወደው ሁሉ የመፍትሄ ያለህ ብለናል፣ ጥፋት እየመጣ እንደሆነ አሳስበናል፣ እንቅስቃሴው ሕዝብን እንደሚጎዳ ሀሳብ ሰጥተናል። ይሄን ሁሉ ስናደርግ ጥላቻን፣ በመንጋ መስድብን፣ የግድያ ዛቻን ነው ያተረፍነው። ያለፉት ዓመታት ምስቅልቅል እንዲመጣ ክልሉን የሚመራው የመንግስት መዋቅር በከፊል ተባባሪ ስለነበር እንዲሁም እስከዛሬ ድረስ በማይገባኝ ምክንያት ጥፋት እየመጣ የማዕከላዊ መንግስትም ቆሞ ተመልካች ተባባሪ ነበር።

በተለይ በተለይ ም/ጠ/ሚኒስትር የነበሩት አቶ ደመቀ የእርሳቸውና ባለጠጋ ወዳጆቻቸው ፍላጎትና ጥቅም ማስከበሪያ ይሆን ዘንድ በልዩ ልዩ መንገድ አፍራሽ አስተሳሰብ ሲያስታጥቋቸው ከነበሩት ዛሬ ኡጋንዳም የትም በየአቅጣጫው ከተበተኑት አክቲቪስት ተብየወች ጋር ተጣምረው ለማያሸንፉት ትግል የአማራን ሕዝብ መታገያ መሳሪያ በማድረግ ታሪክ የማይረሳው ውድመት በማስገባታቸው ታሪክ ይቅር አይላቸውም።

የአማራ ህዝብ በወለጋና በሌላውም እየተገደለ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎችም አካባቢወች ብልጣ ብልጥ በሆነ መንገድ መዋቅራዊ አድሎና መገፋት ሲገጥመው ችግሩን በራሳቸው በፓርቲም ሆነ በመንግስት መድረክ ታግለው መፍትሄ ማምጣት ሲገባቸው ይልቁንም ብሶቱን በማራገብ ለቅርብ አዳሪ ዓላማቸው አውለውት ክልሉንም ለዛሬው ውድመትና ጽልመት አብቅተውታል። ይሁንና ግን አቶ ደመቀ ስልጣናቸውን ከማጣት እንዲሁም ባለጠጋ ወዳጆቻቸውም በስደት ዓለም ሆነው ታግለን እንጥለዋለን ያሉትን ሀይል ይቅር በሉን እያሉ ደጅ ከመጥናት አልተረፉም።

እንግዲህ በዚህ ሂደት እና በመንግስታዊ ንዝህላልነት ምክንያት ለምን እንደሚታገል፣ ማንን እንደሚታገል፣ እንዴት እንደሚታገል፣ ምን እንደሚገጥመው የማያውቅ ታጣቂ ኃይል በየቦታው ተፈልፍሎ አሁን የህወሓት፣ የሻዕቢያና የግብጽ መሳሪያ ሆኖ ሳያፍር ለአማራ ህዝብ እየታገልኩ ነው የሚለን።

የራሱ የትግራይ ህዝብ አክ እንትፍ ያለው ህወሓት እንዲሁም የአገሩን ወጣት አሰድዶ ኤርትራን እያቆረቆዘ ካለው ሻዕቢያ ጋር በመተባበር የሚደረግ ትግል ምን ትርፍ እንደሚገኝበት ባይገባኝም ፤ ገና ለገና በህግ እጠየቃለሁ፣ ነፍስ አጥፍቻለሁ፣ ደም ተቃብቻለሁ፣ መንግስት አዘናግቶ የሆነ ነገር ይፈጥርብኛል በሚል መንገዱ ጠፍቶት ለመጣና ለሄደው ጉዳይ የሚያስፈጽም ሀይል ግን መሆኑ አይቀርም። እነሱን እስከጠቀማቸው ድረስ ሁነኛ አሽከር ከመሆን የዘለለ ሚና ሊኖረው ባይችልም በሂደቱ ግን እውነተኛ ትግል እያደረጉ መስሏቸው ሳይፈልጉት በጊዜ ሂደት በሻዕቢያና ህወሓት ቀንበር ውስጥ ራሳቸውን ያገኙት ብዙ እንደሚሆኑ አውቃለሁ።

ስልጣን ስንይዝ ብቻ ነው ከደምም ሆነ ከወንጀል ተጠያቂነት የምንድነው በማለት ራሳችሁን ከድሮው በበለጠ አጣብቂኝ ሁኔታ ውስጥ ያስገባችሁ ታጋዮች ሁሉ ፤ ካሉት መፍትሄወች ሁሉ የኮሎኔል ፋንታሁን መንገድ የተሻለው ስለሆነ ይሄን መንገድ መከተል ይበጃል። ስልጣን በመሳሪያ ብቻ ነው የሚገኘው የሚል ብቸኛ መርህ የለም ፤ ስልጣን በመሳሪያና በጫካ ትግል ከማግኘት ይልቅ ሌሎች መንገዶችም እንዳሉ የቅርብ ዓመታት ታሪካችንን ብቻ ማየት በቂ ነው። ለሕዝብ እታገላለሁ የሚል አካል ከያዘው አውዳሚ መስመር ይልቅ የህዝብን ጥቅምና መብት የሚያስከብርበት ብዙ መንገድ ስላለ ቆም ብሎ አስቦ የሚበጀውን መንገድ መምረጥ አለበት።

አሁን ያለው የዓለማችን ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመረጣችሁት መንገድ በጭራሽ የሚመች አይደለም። ህወሓትና ሻዕቢያ የዛሬ 37 ዓመት ስለተሳካላቸው አሁንም ያ መንገድ ያዋጣል ማለት ሞኝነት ነው። ወደ ፊት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሀይላችሁ እየተመናመነ እና እየደከመ ተራ በተራ ከምትገቡ ፤ አሁን ሀይል እያላችሁ የናንተንም ሆነ እንታገልለታለን የምትሉትን ህዝብ ጥቅም እና ደህንነት ልታስከብሩ የምትችሉት።

አውቃችሁበት ቢሆን ኖሮ የዛሬ ሁለት ዓመት ህዝባዊ ድጋፍ በነበራችሁ ጊዜ ነገሩን በብልሀት በሰላማዊ መንገድ በድል ስሜት ትቋጩት ነበር። አሁን ላይ ግን ሕዝብ ፈርቶ ፊት ለፊት ባይነግራችሁም ፤ እናንተን የማያይበት መሄጃ አጥቶ እንጂ ጀርባውን ሰጥቷችኋል። ዛሬን ካላወቃችሁበት ነገ ደግሞ ይበልጥ እየባሰ ነው የሚሄደው።

ዩክሬን ፕሬዝደንት ፑቲንን ለመግደል በሩሲያ ኖቭጎሮድ ክልል በሚገኘው የፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ 91 ድሮኖች ብትተኩስም ሩሲያ እንደ ቆሎ አራግፋ ጥላቸዋለች። በተመለከተም ሞስኮ፣ “ከዚህ በኋላ...
01/01/2026

ዩክሬን ፕሬዝደንት ፑቲንን ለመግደል በሩሲያ ኖቭጎሮድ ክልል በሚገኘው የፑቲን መኖሪያ ቤት ላይ 91 ድሮኖች ብትተኩስም ሩሲያ እንደ ቆሎ አራግፋ ጥላቸዋለች።
በተመለከተም ሞስኮ፣ “ከዚህ በኋላ ዘለንስኪ የሚኖረው የቀበሮ ኑሮ ይሆናል” በማለት በመከላከያ ሚኒስትሯ በኩል ለሲኤንኤን ገልፃለች::

Somalia 🇸🇴 Reacts Strongly to Israel’s Recognition of Somaliland Somalia has firmly condemned Israel’s decision to recog...
12/27/2025

Somalia 🇸🇴 Reacts Strongly to Israel’s Recognition of Somaliland

Somalia has firmly condemned Israel’s decision to recognize Somaliland as an independent state, describing the move as “illegitimate” and a direct violation of Somalia’s sovereignty.

In an official response, Somali authorities warned that Israel’s action could destabilize the Horn of Africa and the Red Sea region, increase insecurity, and undermine regional and international efforts to combat terrorism and maintain peace.

The Chairperson of the African Union Commission also rejected any recognition of Somaliland, reaffirming the African Union’s unwavering commitment to the unity, sovereignty, and territorial integrity of Somalia .

‹‹ኤርትራ ኤርትራ የሆነችበት ምክንያት ይፈርሳል››‹‹ኤርትራ የተገነጠለችው ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታጣ ታስቦ ነው፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ስታገኝ ኤርትራ ኤርትራ የሆነችበት ምክንያት ይፈ...
12/17/2025

‹‹ኤርትራ ኤርትራ የሆነችበት ምክንያት ይፈርሳል››

‹‹ኤርትራ የተገነጠለችው ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታጣ ታስቦ ነው፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ስታገኝ ኤርትራ ኤርትራ የሆነችበት ምክንያት ይፈርሳል፡፡ ኤርትራ ኤርትራ እንድትሆን ያደረጋት መነሻው እና ሌሎች አገራትም የተቀበሉት ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳታገኝ ነው፡፡ ልክ ኢትዮጵያ የባህር በር ካገኘች ኤርትራ ምን ታደርግላቸዋለች?››

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

Address

Downtown Denver, CO

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Twitter Trends Ethiopia ትሬንድ ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Twitter Trends Ethiopia ትሬንድ ኢትዮጵያ:

Shortcuts

Share