Sky First

Sky First ይህ ገጽ ለታማኝ ዜናዎች እና ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ ለመሆን የተዘጋጀ ነው።


https://t.me/SkyFirstMedia YouTube.com/-sf
(1)

በምርጫው ድምፅ የተሰጠባቸውን ወረቀቶች ዋጋ አልባ የሚያደርጓችው ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው ?1. የመራጩ ማንነት በስም የተገለጸ ከሆነ፣2. ለምክር ቤቱ ሊመረጥ ከሚቻለው ተመራጮች ቁጥር በላይ...
05/31/2026

በምርጫው ድምፅ የተሰጠባቸውን ወረቀቶች ዋጋ አልባ የሚያደርጓችው ምክንያቶች የትኞቹ ናቸው ?

1. የመራጩ ማንነት በስም የተገለጸ ከሆነ፣
2. ለምክር ቤቱ ሊመረጥ ከሚቻለው ተመራጮች ቁጥር በላይ ላላቸው ዕጩዎች ምልክት የተደረገበት ከሆነ፣
3. ምንም ምልክት ያልተደረገበት ከሆነ፣
4. መራጩ ማንን አንደመረጠ መለየት የሚያስቸግር ከሆነ፣
5. ሕጋዊ የድምፅ መስጫ ወረቀት ያልሆነ ወይም በምርጫ ጣቢያው ያልተሠራጨ የድምፅ መስጫ ወረቀት ከሆነ ዋጋ አልባ ይሆናል፡፡

Sky First

||  የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳሰቢያየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመዘገብ የሰለጠኑና ልዩ ባጅ የተሰጣቸውን 68 መገናኛ ብዙኃን ድርጅቶች እና 1,815 ጋዜጠኞችን ...
05/31/2026

|| የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመዘገብ የሰለጠኑና ልዩ ባጅ የተሰጣቸውን 68 መገናኛ ብዙኃን ድርጅቶች እና 1,815 ጋዜጠኞችን መመዝገቡን ገልጿል።

ሆኖም ጋዜጠኞች በየአካባቢው ዘገባ በሚሠሩበት ወቅት « በቦርዱ መዘገብ ስለመቻላችሁ ደብዳቤ ሊጻፍላችሁ ይገባል » በሚል ከዘገባ ሥራ የማስቆም ሁኔታዎች በውስን አካባቢዎች ላይ መስተዋላቸውን አመልክቷል። ይህ ተግባር የተሳሳተ መሆኑን የገለጸው ቦርዱ፤ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የተመዘገበ መሆን ብቻ ምርጫን ለመዘገብ እንደሚያስችል አሳውቋል።

በየምርጫ ጣቢያው 200 ሜትር ንቅፈ-ክበብ ውስጥ መዘገብ የሚችለው ከቦርዱ የዕውቅና ባጅ ያለውና የሚሠራበት የመገናኛ ብዙኃን ተቋም መታወቂያ የያዘ ብቻ መሆኑን አስታውቋል።

#ምርጫ2018

05/31/2026

"የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የቀረው ህዝብ ኢትዮጵያ ምንድን ናቸው ሁሉንም አካታች የሆነ ልማት ነው ሚያስፈልገው " - ሰለሞን ሹምዬ

Sky First

||  "የጸጥታ ኃይሉ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው" — እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር)​የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) ወቅታዊ ጉዳዮችን እና የክልሉን ሰላም አስመልክ...
05/31/2026

|| "የጸጥታ ኃይሉ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው" — እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር)

​የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር) ወቅታዊ ጉዳዮችን እና የክልሉን ሰላም አስመልክተው ከአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ጋር ቆይታ አድርገዋል። በቆይታቸውም የክልሉ ጸጥታ ኃይል እና ሌሎች የጸጥታ መዋቅሮች ሕዝቡ በነጻነት ድምጹን መስጠት እንዲችል ከኅብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየሠሩ እንደኾነ ገልጸዋል።

​የምርጫ ቦርድ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሕዝቡን ሰላም ለማስከበር የጸጥታ ኃይሉ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ይገኛል። የምርጫ ቁሳቁስ በሁሉም አካባቢዎች በሚፈለገው ሁኔታ እንዲደርስ የተደረገ ሲሆን፣ ማኅበረሰቡ ከጸጥታ ሥጋት ነጻ ኾኖ ድምጹን እንዲሰጥ አስተማማኝ ሁኔታ የመፍጠር ኀላፊነት በአግባቡ እየተተገበረ ነው። ምርጫው ስኬታማ ይኾን ዘንድ በምርጫው ዕለትም ኾነ ከምርጫ በኋላ የጸጥታ ኃይሉ ኀላፊነቱን እንደሚወጣና በቀጣይም የክልሉን ሕዝብ ሰላም የማረጋገጥ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

​በአሁኑ ወቅት የጠላት የሰው ኃይል እና የፕሮፖጋንዳ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክሟል። ይህ ሊኾን የቻለው የጸጥታ ኃይሉ ከሚያደርገው ሕግ የማስከበር ተልዕኮ ባሻገር፣ ኅብረተሰቡ የታጣቂዎችን የጥፋት ድርጊት ተረድቶ ከመንግሥት ጎን በቁርጠኝነት በመቆሙ እንደሆነ ኃላፊው አብራርተዋል።

​መንግሥት አሁንም ቢኾን የሰላም አማራጭን ተቀብለው ለሚመጡ ኃይሎች በሩ ክፍት መኾኑን ያረጋገጡት ዶክተር እሸቱ፣ ይህንን ዕድል በማይቀበሉ አካላት ላይ ግን ሕጋዊ እርምጃ የመውሰዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል። በመጨረሻም በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ማኅበረሰቡ ከመንግሥት ጎን በመቆም የተለመደ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

Via: አሚኮ
Sky First

||  በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቦምብ ፍንዳታ ተከስቶ የተማሪዎች ህይወት አለፈ!​በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ትላንት ምሽት የአርሴናል እና ፒኤስጂ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በፕሮጀክተ...
05/31/2026

|| በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቦምብ ፍንዳታ ተከስቶ የተማሪዎች ህይወት አለፈ!

​በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ትላንት ምሽት የአርሴናል እና ፒኤስጂ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ በፕሮጀክተር እና በቴሌቪዥን እየተላለፈ በነበረበት ወቅት በተከሰተ የቦምብ ፍንዳታ የተማሪዎች ህይወት ማለፉና በርካቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ታውቋል።

​ጨዋታው ተጀምሮ የመጀመሪያው 45 ደቂቃ ሊያልቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ከፍተኛ የፍንዳታ ድምጽ ተሰምቷል። ተማሪዎች መጀመሪያ ላይ የሮኬት አይነት ድምጽ እንደሰሙና በመቀጠል እንደመብረቅ ድፍን አድርጎ በጭስ እንደታፈኑ ገልጸዋል። አዳራሹ በሰው ተጨናንቆ ስለነበር ተማሪዎች በድንጋጤ እርስ በርስ ለመውጣት ሲጋፉ በተፈጠረው መረጋገጥ የጉዳቱ መጠን ሊጨምር ችሏል።

​የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት እና የዓይን እማኞች ሁለት ተማሪዎች ሆስፒታል ከገቡ በኋላ ህይወታቸው ማለፉን አረጋግጠዋል። አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች ደግሞ የሟቾች ቁጥር ሶስት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል። በአደጋው ሳቢያ ሶስት ተማሪዎች ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ ከሰላሳ ያላነሱ ተማሪዎች ላይ ደግሞ ቀላልና መካከለኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። አብዛኞቹ ተጎጂዎች በካምፓሱ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

​የሟች ተማሪዎች አስክሬን ዛሬ ጠዋት ወደ ቤተሰቦቻቸው በሽኝት ተልኳል። በአሁኑ ወቅት በካምፓሱ ውስጥ የሀዘን ድባብ ቢኖርም ሁኔታው መረጋጋቱ ተገልጿል። የፖሊስ አባላትም ወደ ካምፓሱ በመግባት የፍንዳታውን መንስኤ ለማጣራት ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉ።

​"ሁለቱንም እግሬን ነው የተመታሁት፣ እስካሁን እግሬ ላይ የገባው የፍንዳታው ፍንጥርጣሪ አልወጣልኝም..." — በወቅቱ ጉዳት የደረሰበት ተማሪ
​ለተጎዱት ተማሪዎች ፈጣን ማገገምን፣ ለሞቱት ደግሞ መጽናናትን ለቤተሰቦቻቸው እንመኛለን።

||  በየአካባቢያችሁ ያለው የምርጫ ዋዜማ ድባብ ምን ይመስላል?ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሰባተኛው የኢትዮጵያ  አጠቃላይ ምርጫ ሊካሄድ  ሰአታት ብቻ ቀርተውታል። በነ...
05/31/2026

|| በየአካባቢያችሁ ያለው የምርጫ ዋዜማ ድባብ ምን ይመስላል?

ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሰባተኛው የኢትዮጵያ አጠቃላይ ምርጫ ሊካሄድ ሰአታት ብቻ ቀርተውታል። በነገው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 ሊካሄድ ቀን በተቆረጠለት በዚህ ምርጫ ፤ የ42 የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት እና የግል ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ 10,438 ዕጩዎች ተመዝግበዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ እንደሚያሳየው 28,632 ተፈናቃዮችን ጨምሮ 54 ሚሊዮን ገደማ ድምጽ ሰጪዎች ተመዝግበዋል። ሰኞ የሚካሄደው ምርጫ በ614 የምርጫ ክልሎች ላይ እንደሚከናወንም ቦርዱ ገልጿል።

በአማራ ክልል 5 ምርጫ ክልሎች እና በጋምቤላ ክልል 4 የምርጫ ክልሎች በስተቀር በሁሉም የምርጫ ክልሎች የምርጫ ማስፈጸሚያ ቁሳቁሶች መዳረሳቸውን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

በዚህ ሁኔታ ላለፉት ወራት ሲካሄድ የነበረው የምርጫ ቅስቀሳን ጨምሮ ሌሎች ከምርጫ ጋር የተያያዙ ስራዎች ተጠናቀው ዛሬ የጥሞና ቀን መሆኑንም ተገልጿል።
ኢትዮጵያ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ከአንድ ቀን ያነሰ ጊዜ ብቻ በቀረበት ባሁን ወቅት በየአካባቢያችሁ ያለው የምርጫ ዋዜማ ድባብ ምን ይመስላል?ሀሳብ አስተያቶቻችሁን አካፍሉን።

#ምርጫ2018

||  ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት ሳይጠናቀቅ እንደሚካሄድ ተገለጸየኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋናውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት ሳይጠናቀቅ ለ...
05/31/2026

|| ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት ሳይጠናቀቅ እንደሚካሄድ ተገለጸ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋናውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የ2018 በጀት ዓመት ሳይጠናቀቅ ለማካሄድ ማቀዱን አስታውቋል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ይኽንን የገለጹት የሃይማኖት ተቋማት እና የሲቪክ ማኅበራት አጀንዳዎች በቀረቡበት የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ነው።

የምክክር ሂደቱን የሚያሳልጡ 192 አመካካሪ ባለሙያዎች ተመርጠው ሥልጠና መውሰዳቸውን ዋና ኮሚሽነሩ ጠቁመዋል። በቀጣይም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰላምና ምክክር ላይ በሚሠሩ ተቋማት ተጨማሪ ሥልጠና እንደሚሰጣቸው ገልጸዋል።

በጉባኤው ላይ በአጠቃላይ አራት ሺሕ ተሳታፊዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። የምክክር ሂደቱም አምስት መቶ ተሳታፊዎችን በያዙ ስምንት ንዑሳን ጉባኤዎች ተከፋፍሎ የሚካሄድ ሲሆን የውይይቶቹ ማጠቃለያ ምክረ ሐሳብም ይቀርባል።

ኮሚሽኑ የጉባኤውን ዝርዝር መረጃ የዝግጅት ሥራውን እንዳጠናቀቀ ይፋ እንደሚያደርግ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ጨምረው ገልጸዋል።

 #ሄይቲ፡ በነጻነቷ ምክንያት ከአንድ መቶ ለሚበልጥ ዓመታት የተቀጣችው ሀገር​በፈረንሳይኛ አቆጣጠር በ1791 በሄይቲ የነበሩ ጥቁር ባሪያዎች በታሪክ ማንም አድርጎት የማያውቀውን ተአምር ፈጸሙ...
05/31/2026

#ሄይቲ፡ በነጻነቷ ምክንያት ከአንድ መቶ ለሚበልጥ ዓመታት የተቀጣችው ሀገር

​በፈረንሳይኛ አቆጣጠር በ1791 በሄይቲ የነበሩ ጥቁር ባሪያዎች በታሪክ ማንም አድርጎት የማያውቀውን ተአምር ፈጸሙ። መሣሪያ አንስተው በመታገል በወቅቱ የአለማችን እጅግ ኃያላን የነበሩትን ሶስት የአውሮፓ ኢምፓየሮችን—ማለትም ፈረንሳይን፣ ስፔንን እና ብሪታንያን—በአንድ ጊዜ አምርረው በመዋጋት ድል ነሷቸው።

​በ1804 ሄይቲ በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ የጥቁር ሕዝቦች ሪፐብሊክ ለመሆን በቃች።
​ነገር ግን የታሪክ መጻሕፍት ሆን ብለው የሚደብቋቸው እውነታዎች አሉ

​የአሜሪካ ካርታ የተቀየረው በሄይቲ ምክንያት ነው ናፖሊዮን ቦናፓርት በአሜሪካ አህጉር ላይ ታላቅ የፈረንሳይ ኢምፓየር ለመመስረት አቅዶ የነበረው ሙሉ እቅድ በሄይቲ ሽንፈት ምክንያት ባከነ። በዚህም የተነሳ ፈረንሳይ የነበራትን የሉዊዚያና ግዛት (Louisiana Territory) ለዩናይትድ ስቴትስ በርካሽ ዋጋ ለመሸጥ ተገደደች። ዛሬ የምናያት አሜሪካ ታላቅ ሀገር መሆን የቻለችው በሄይቲ የነበሩ ጀግኖች ናፖሊዮንን ስላሸነፉት ነው።

​ኢኮኖሚያዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ማዕቀብ የቅኝ ገዥ ኃይላት በሄይቲ ስኬት እጅግ ከመደናገጣቸው የተነሳ፣ ነጻነቷን ካወጀችበት ቅጽበት ጀምሮ ሀገሪቱን ከአለም ኢኮኖሚ እና ዲፕሎማሲ አገለሏት።

​ፈረንሳይ የሄይቲን ነጻነት እውቅና ለመስጠት 150 ሚሊዮን የወርቅ ፍራንክ እንድትከፍል አስገደደቻት። ይህ ገንዘብ የሀገሪቱን የዓመት ገቢ በአሥር እጥፍ የሚበልጥ የነበረ ሲሆን፣ የተከፈለውም የቀድሞ የባሪያ አጋፋሪዎች “ለንብረታቸው (ለሰዎቹ) መጥፋት” ካሳ እንዲሆናቸው ተብሎ ነው። ሄይቲ ይህንን ለመክፈል ከፈረንሳይ ባንኮች በከፍተኛ ወለድ ለመበደር ተገደደች።

​ሄይቲ ይህንን የጭቆና ዕዳ ከፍላ ያጠናቀቀችው በ1947 ዓ.ም. ነበር። ማለትም ነጻነቷን ካገኘች ከ122 ዓመታት በኋላ

​እስቲ አስቡት፤ ሄይቲ ጦርነቱን አሸነፈች፣ ነገር ግን ባሪያ ለመሆን ባለመፈለጓ እና ነጻነቷን በማስከበሯ ብቻ ለአንድ መቶ ክፍለ ዘመን ያህል ዋጋ እንድትከፍል ተደረገች።
​ዛሬ በሄይቲ የሚታየው ድህነት በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን፣ ሆን ተብሎ በሴራ የተቀነባበረ ነው።

​ይህ ታሪክ እያንዳንዱ ጥቁር ሕዝብ ሊያውቀው የሚገባ እውነት ነው፤ ምክንያቱም ጥቁር ሕዝቦች ሰንሰለታቸውን በጥሰው ለመውጣት ሲቆርጡ ዓለም ምን ያህል ጨካኝ ምላሽ እንደምትሰጥ ማሳያ ነውና።

​ለመሆኑ ዓለም ለሄይቲ ምን ዕዳ ያለባት ይመስላችኋል?

Sky First

|| የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከነገ እሁድ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዕገዳ ጣለ የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከነገ እሁድ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀ...
05/30/2026

|| የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከነገ እሁድ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዕገዳ ጣለ

የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከነገ እሁድ ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ዕገዳ መጣሉን ዛሬ ቅዳሜ አመሻሹ ላይ ባወጣው መግለጫ አሳወቀ። ይህ ዕገዳ 7ኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ ከሚካሄድበት ከሰኞ ግንቦት 24 ቀን ዋዜማ ጀምሮ እስከ ማግስቱ ቀን ድረስ የሚቆይ ቢሆንም፣ ኮሚሽኑ በሰጠው መግለጫ ላይ ግን ስለ ምርጫው በቀጥታ የጠቀሰው ነገር የለም።

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው፣ ከነገ ማለዳ ጀምሮ እስከ ማክሰኞ ድረስ ልዩ የይለፍ ፈቃድ ካላቸው ተሽከርካሪዎች በስተቀር ማንኛውም የመንግሥት፣ የግል፣ የንግድ እንዲሁም የባለሦስት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች በሙሉ “እንቅስቃሴያቸውን እንዲያቆሙ” በጥብቅ ታዟል። ይህንን የኮሚሽኑን መመሪያ ጥሰው በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ “ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ” እንደሚወሰድ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ዶክተር ካሩ ማሳሰባቸውን ኮሚሽኑ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ገልጿል።

Sky First

መድፈኞቹ ጉድ ሆነዋል
05/30/2026

መድፈኞቹ ጉድ ሆነዋል

Address

US
Atlanta, GA
404

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sky First posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Sky First:

Share