31/05/2023
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የ2015 ክህሎት ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ።
ክህሎት ለተወዳዳሪነት በሚል መሪ ሀሳብ ከግንቦት 14/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የ2015 ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል።
ውድድሩ ፍፃሜውን ሲያገኝ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመውጣት ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች ከአንድ መቶ ሺህ እስከ 80 ሺህ ብር ድረስ የማበረታቻ ሽልማት፣ ዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስራ ሁለት ወርቅ፣ አራት ብር እና ሦስት ነሀስ በማግኘት በአጠቃላይ ውጤት አንደኛ በማግኘት የ2015 ክህሎት ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዘጠኝ ወርቅ፣ ስአስር ብር እና ሰባት ነሀስ በማግኘት በአጠቃላይ ውጤት ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ ሰባት ወርቅ፣ ስምንት ብር እና ሦስት ነሀስ በማግኘት ሦስተኛ ደረጃን በማግኘት ውድድሩን አጠናቋል።