30/07/2021
"ገብቶ የሚያግዘን እንጂ ስልክ እየደውለ ላስተምራችሁ የሚል ወታደርን አንፈልግም" ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ
"ኢትዮጵያ ውስጥ እየኖረ እኔን ወታደራዊ ምክር ልምከርህ የሚል ወታደር ካለ በፍጹም አልሰማውም። እኛ አሁንላይ ምክር የሚመክረን ወታደር ሳይሆን ሰራዊታችንን ተቀላቅሎ የሚያደራጀን የሚያዋጋን ወታደር ብቻ ነው።
"ኢትዮጵያ እየኖረ ለኔ ምክር የሚሰጠኝ እሱ የማንን ጎፈሬ ሊያበጥር ነው?
ባዴን/ብልጽግና አመራር አስቀየመኝ፤ ስቸገር ረስተውኛል አሁን እንዴት ፅ አልኳቸው ገለ መሌ አይሰራም። እኔም በወያኔ 9 አመት ሙሉ ታስሬ አንድም ቀን አልጠየቁኝም፤ እራሳቸውም አስረውኛል። አሁን ላይ የምታገለው ለካድሬ ሳይሆን ለራሴ፤ ለሰፊው የአማራ ሕዝብ ለሀገሬ ኢትዮጵያ ነው። ከውጭ ሆኖ ምክር አንፈልግም ገብታችሁ አግዙን።"
ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ