10/04/2017
ሪሲቨሮች ማብራሪያ ➌
👉Supermax 9200 CA HD👈
👍Like ወይም Share በማድረግ አሪፍ አሪፍ መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ።
🔱______________🔱
💫አንዳንድ ዲኮደሮች ላይ ብዙ ሰው የማያውቃቸው ነገር ግን በጣም ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች ምን ምን ናቸው?
ለዛሬ ያቀረብነው Supermax 9200 CA HDን ነው ተከታተሉን
ይህ ሪሲቨር ኦርጅናል ሲሆን ነገር ግን ከሱ ጋር በመመሳሰል የተሰሩ ሪሲቨሮችም አሉ አነሱም supermax 9200 super plus, supermax 9200 super tech ናቸው፡፡ ይህ ሪሲቨር (SM9200 CA HD) ሪሞት ቢጠፋብን ለማስተካከል አስቸጋሪ ነው (ሪሲቨሩ ላይ በተኖች የሉትም) ስለዚህ ሪሞት እንዳይጠፋ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው፡፡
ሌላው ብዙ ሰዎችን ቻናል እየደበቀ ያስቸገራቸው ጉዳይ sat የሚል ነገር ሪሞቱ ላይ የለም ፡፡ ነገር ግን በቀላሉ "ቀይ" በተን በመጫን all satellite በማለት ማስተካከል ይቻላል፡፡ ከዚ ውጭ ተመሳስለው በተሰሩት ሪሲቨሮች ላይ sat የሚል ስላለ አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ እንደመግቢያ ይህን ካልን ወደ ዋናው ማብራሪያ እንሂድ
__________________________________
📺፩. ቻናል አጫጫን
__________________________________
የsupermax 9200 CA HD የቻናል አፈላለግ በ3 አይነት መንገድ ቀርቧል፡፡
➊Menu....installation ...Antena setting ....satellite.....(e.g) nilesat....start search.....blindsearch....Do you want to delete program exist?....no .....(ቻናሎችን በጥልቀት ለማሰስ ስንፈልግ) ነገር ግን ከዚህ በፊት ቅደም ተከተል የያዙ ቻናሎች ካሉ ይዘበራረቃሉ፡፡
➋Menu....installation ...antenna setting .......satellite ...eg. nilesat...ok....ከታች በመውረድ ...satellite...(ሙሉውን ቻናሎች ለመጫን ስንፈልግ)
➌ Menu.....installation ...antenna setting ...Transponder...Ok ....ቀይ በተን... የምንፈልገውን ፍሪኩየንሲ መሙላት.....OK (አንድን ቻናል ብቻ መጫን ስንፈልግ) ከዚህ በኋላ ከዚሁ ሳንወጣ ከታች startsearch ላይ ወደ ጎን በማለት transponder ...ok
( ወይም ሌላኛው መንገድ menu...installation ...channel manager...transponder)
______________________________________
እዚ ላይ ማወቅ የሚጠበቁብን ጉዳዮች:-
✔Multiscan....ከናይልሳት በተጨማሪ ብዙ ሳተላይት ለመጫን ስንፈልግ
✔Blind search....አንድን ሳተላይት በጥልቀት ለመጫን ስንፈልግ (ከዚህ በፊት ያለውን ቅደም ተከተል ያዛባል፡፡)
✔Transpoder......አንድ ቻናል ብቻ ለመጫን ስንፈልግ እንጠቀማለን፡፡
_______________________________________
________________________________
📺፪. ቻናል ቅደም ተከተል አያያዝ
________________________________
ቻናል ቅደምተከተል ለማስያዝ በ3 ዓይነት መንገድ ቀርቧል፡፡
➊OK on channels.....ሰማያዊ በተን...ወደ ቀኝ...ወደ ቀኝ ...move...ok... (3 ጊዜ ሰማያዊ በተን)....ቁጥር መስጠት...እንዲቀመጥበት የሚፈልጉትን ቁ...Ok.....(የሚፈለጉትን ቻናሎች በ1ጊዜ ማርክ አድርጎ ለመውሰድ ሲፈለግ)
➋Ok on channels ....ሰማያዊ በተን....ወደ ቀኝ..ወደ ቀኝ (2ጊዜ) ....ok...ወደላይና ወደታች ማንቀሳቀስ....የሚፈለገው ቦታ ላይ ሲደረስ (ቁጥር) ---ok( አንድ በአንድ)
➌ከሌላ ሪሲቨር ቅደም ተከተል ከያዘ ላይ በፍላሽ የቻናል ዝርዝር መውሰድ...
አወሳሰድ ፦ menu ...USB manager...software .....ቢጫ በተን....channel list ok.
ወደ እኛ ሪሲቨር መጫን ስንፈልግ menu ...USB manager ...software ....Novatek...OK
________________________________________
📺፫. ሶፍትዌር አጫጫን
________________________________________
አብዛኛዎቹ HD የቻይና ሪሲቨሮች የራሳቸው website ያላቸው ሲሆን google search tab ላይ የሪሲቨሮቹን ሞዴል በመፃፍና በመፈለግ ዳውንሎድ ማድረግ፡፡ አብዛኛውን ጊዜ www.newprog.net ላይ የሁሉንም supermax ሞዴሎች ሶፍትዌር ማግኘት ይቻላል፡፡ ቀጥሎም ዳውንሎድ የተደረገውን ፋይል በፍላሽ በመውሰድ ኮምፒውተር ላይ extract በማድረግ .bin በንፁህ ፍላሽ መጫን ፡፡
menu...usb manager...software...supermax 9200 CA HD...ok
N.B በዚህ ሰዓት ጭኖ ሳይጨርስ መብራት ከጠፋ ሪሲቨሩ ችግር ይደርስበታል ይጠንቀቁ፡፡
________________________________________
📺፬. BISS key አገባብ
________________________________________
SM 9200 CA HD ላይ biss key ለማስገባት በመጀመሪያ ሶፍትዌር መጫን አለበት፡፡ በመቀጠል ሪሞቱ ላይ slow የሚለውን ከነካን በኋላ 4 ጊዜ 1ን እንጫናለን (1111) ማለት ነው፡፡ በዚህ ሰዓት biss key ለማስገባት ዝግጁ ሆኗል ማለት ነው(patch enable) ከዚህ በኋላ በቢስ የተቆለፈው ቻናል ላይ አድርገን ሪሞቱ ላይ page- ስንል የመሙያው ቦርድ ይመጣልናል፡፡
★ከሌላ ከተሞላ ሪሲቨር softcam key ወስዶ በመጫን መሙላትም ይቻላል፡፡
________________________________________
📺፭. ፍላሽ ላይ መቅዳትና ማጫወት
________________________________________
✿አንድን ፕሮግራም ለመቅዳት መጀመሪያ ፍላሽ ከሰካን በኋላ ሪሞቱ ላይ ትንሽ ቀይ ነጥብ ስንነካ መቅረፅ ይጀምራል፡፡ ስንጨርስ exit በማለት መውጣት እንችላለን፡፡ የተቀረፀውን ለማየት menu...USB manager --movie--pvr--Ok ብለን ማጫወት አንችላለን፡፡
✿ እየተጫወተ ያለን ቪዲዮ ማሳለፍ ቢያስፈልግ "0"ን በመጫን ሰዓት እና ደቂቃ መሙላት ይቻላል፡፡ በቀስቶቹም እያፈጠኑ ማሳለፍ ይቻላል 2x...4x...8x በማድረግ፡፡ በዚሁ "0" ቻናል ላይ ከሆንን የስክሪኑን የብርሀን መጠንና ቀለም ማስተካከል እንችላለን፡፡
✿ሌላውና ወሳኙ ነገር አንድን ፕሮግራም ለመከታተል ፈልገን ጊዜ ባይኖረን ወይም እንቅልፋችን ቢመጣ ጥሩ አቅም(GB) ያለው ፍላሽ ከሰካን በኋላ menu--system setting ---timer adjust--- እንገባና አሁን ያለውን የሪሲቨሩን ሰዓት timer setup ላይ እናያለን፡፡ እንደገና በመመለስ--- event timer እንገባና "አረንጓዴ በተን" እንጫናለን፡፡
-ቻናሉን (channel )
-የሚጀምርበትን (start) ካሁኑ
ሰዓት ትንሽ አሳልፈን መሙላት
-የሚጨርስበትን (stop) ሰዓትን
- ቅረፅ (record)....yes
- STB off ...yes...ብለን
እንጨርሳለን፡፡
___________________________________________
📺፮. ቻናሎች በቀጣይ የሚያሳዩ
Как чистить диск флэш-памяти