Selehadin Albani

30/05/2025

የማይቀርበት የንቃት 8 ፕሮግራም እሁድ ግንቦት 24 ወደናንተ ታዳሚዎቹ ለመድረስ ስንድቱን ጨርሷል፣ እርሶም እሁድን ከወዳጅ ቤተሰቦ ጋር በመሆን በዚህ ፕሮግራም ላይ እንዲያሳልፉ ተጋብዘዋል።

يد مبتورة .. وجسد متهالك .. جالس على كرسي كأحد ملوك الأرض .. بقلب جعفر ابن أبي طالب .. سلاحه بين عضديه .. وبفؤاد موسى عل...
18/10/2024

يد مبتورة .. وجسد متهالك .. جالس على كرسي كأحد ملوك الأرض .. بقلب جعفر ابن أبي طالب .. سلاحه بين عضديه .. وبفؤاد موسى عليه السلام .. يضرب بعصاه الفضاء .. يرفض ان تصعد روحة قبل أن يدفع ويدافع بآخر رمق .

أي ثبات يا مجاهد .
هكذا رجال العقيدة .
ربح البيع يا يحيى .
آن لك ان تحيا .
مقبل غير مدبر .. تقبلك الله يا أبا ابراهيم

ይህ እንግድህ የህያ ሲሰዋ ከእርሱ ጋር የተገኙ ንብረቶች ናቸው።የአዝካር እና የተለያዩ ትንንሽ ኪታቦች ሙስበሀየሚፃፃፍባቸው ብእርና ወረቀትየእጅ ሰአት የጥፍር መቁረጫ ትንሽየ የእጅ ባትሪ ሶፍ...
18/10/2024

ይህ እንግድህ የህያ ሲሰዋ ከእርሱ ጋር የተገኙ ንብረቶች ናቸው።
የአዝካር እና የተለያዩ ትንንሽ ኪታቦች
ሙስበሀ
የሚፃፃፍባቸው ብእርና ወረቀት
የእጅ ሰአት
የጥፍር መቁረጫ
ትንሽየ የእጅ ባትሪ
ሶፍት
ትንሽየ ጥሬ ገንዘቦች
እና ጥይት የጨረሰች ታጣፊ ክላሽ😢

በቃ ይህቺው ነበረች የሸሂዱ ህይወት!
የእርሱ ህይወት ከዚህ የተለየችም ሆና አታውቅም!
የፍልስጤም መሪ ቢሆንም ከዚህች የተለየ አንድት ንብረት እንኳ በእጁ አልነበረውም።

በዘመኔ የሶሀቦችን ህይወት ኖረው እንደ ሶሀቦች የሚሞቱ ህዝቦችን አይቻለሁ እነርሱም ጋዛ ምድር ይገኛሉ!!!

ይህ ሰው ሲያስቀና!!!
Seidsocial

19/12/2023
27/08/2022
11/09/2021

ለክቡሯን ደንበኞቻችን
ከመስከረም 2 ጀምሮ 3 ብር 50 ስንሸጥ የነበረውን ትንሹን ድብ 3 ብር ያደረግን ሲሆን እንዲሁም 6 የነበረውን ፍላውር ዳቦ 5 ብር ያደረግን መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልፃለን

🍞 ድርጅቱ 🍞

18/05/2021

የመስከረም ኦሮሙማ!
★★★/🌟/★★★

(ኦሮሙማ ፀረ–ኦርቶዶክስ ነው‼ ዲያቆን አባይነህ ካሴ)

መስከረም አበራ ያደረገችውን ትንታኔ ሰማሁት። የሰራችውን የትርጉም ግድፈት ላስቀምጥ።

አንደኛ ኦሮሙማ የሚለው ቃል ተከፍሎም ሆነ በድምሩ ኦሮምኛ ቃል እንጅ ዐረብኛ ቃል አይደለም። ኦሮሙማ የሚለው ቃል በሽዋ ኦርቶዶክስ ኦሮሞዎች፣ በባሌ ሙስሊም ኦሮሞዎች እንዲሁም በወለጋ ፕሮቴስታንት ኦሮሞዎች ዘንድ ያለው ትርጉም አንድና ወጥነት ያለው የኦሮምኛ ቃል ነው።

ሁለተኛ የኦሮምኛን ትርጉም አረብኛ መዝገበ ቃላት ላይ ሄዶ መፈለግ በእውነቱ ቤት ውስጥ የጠፋውን መርፌ መብራት ያለው አስፓልት ጋር ሔዶ እንደመፈለግ ነው።

ሶስተኛ የኦሮሞ ፖለቲካ በመሰረታዊነት የአራት እምነት ተከታይ ኦሮሞዎች ጥምረት ፖለቲካ ነው። የሽዋ ኦርቶዶክስ፣ የደ/ምሥራቅ ሙስሊሞች፣ የምዕራብ (ወለጋ) ፕሮቴስታንቶች እና የዋቀፈና ኦሮሞዎች የወል ፖለቲካ ነው። ይህን ህዝብ ኦሮሙማ በሚል የራሳቸው ቃል አሰባስበውታል።

ኦሮሙማ የኦሮምኛ ቃል ሲሆን ኦሮሞ የሚለው ግስ ወደ ኦሮሞነት ሲራባ በአማርኛው –ነት የሚል ድህረ ቅጥያ (ሰፊክስ) እንደሚጨመርበት ሁሉ ኦሮሙ–ማ የሚል ድህረ ቅጥያ ይጨመርበትና ኦሮሙማ (ኦሮሞነት) የሚል ቃል ይወጣዋል። የድሪባ መገርሳን ማብራሪያ እዚህ ላይ ላምጣ

-umma ምን ምን ላይ በአፋን ኦሮሞ ቃላቶች እንደሚራቡ እንይ
1. Nama (ሰው)….. namummaa (ሰውነት)
2. Aantee (ወገን)…….aantummaa(ወገንተኝነት)
3. Bilisa (ነፃ)..... bilisummaa (ነፃነት)
4. Oromoo (ኦሮሞ) ....Oromummaa (ኦሮሞነት)

ከላይ የተጠቀሱት ምሳሌዎች -umma ጥቅል ስሞችን ለማራባት ይጠቀማሉ::

የመስከረም ትርጓሜ ህፀፆቹ ከኦሮሙማ ትርጉም መፋለስ ጋር ብቻ አይገናኝም። የዚህ ትንታኔ ዓላማ

1️⃣ ኦሮሞዎችን በሃይማኖት መከፋፈል ነው።

2️⃣ ሙስሊም ኦሮሞዎችን ማጥቃት ነው

በ2007ቱን የብሔራዊ የህዝብና የቤት ቆጠራ መረጃ መሰረት እስልምና ከኦሮሞ ህዝብ 47.55 % በመያዝ መሪ ኃይማኖት ነው። ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ሙስሊም 51% ያክሉ የሚገኘው በኦሮሚያ ነው። 53% ያክሉ የኦሮሞ ህዝብ የሚገኘው በሙስሊም በዝ የኦሮሚያ ቀጠናዎች ነው። ከኦሮሚያ ሙስሊም በዝ ቀጠናዎች ከፍተኛውን የኦሮሞ ሙስሊም የያዙት ደግሞ ሐረርጌ፣ አርሲ፣ ጅማና ባሌ ናቸው።

ስለዚህም የመስከረም አበራ እና መሰሎቿ ፍላጎት በአሃዝ ትልቁን የኦሮሞ ህዝብ ነጥሎ በማጥቃት ከውስጥ ድሪፍት በመፍጠር በተራዘመ ትግል በሰሜኑ የኦርቶዶክስ ኦሮሞ፣ በምስራቅና ደቡቡ የሙስሊም ኦሮሞ፣ በምእራቡ የፕሮቴስታንት ኦሮሞ መካከል ስንጥቅ በመፍጠር፣

…………«ለማን ነው የምትታገሉት? የኦሮሞን ኮዝ የሙስሊም ኮዝ ላደረጉት ኦሮሞዎች ነው ወይ የምትታገሉት? እንዴት የሽዋ ኦርቶዶክስ ኦሮሞ ለሸኽ ጃራና ለጃዋር የእስላም ኦሮሞ ኮዝ ይታገላል? ትግላችሁን ሙስሊም ኦሮሞዎች ነጠቀዋችኋል፣ ለራሳቸው ግብ ተጠቅመውባችኋል» ዓይነት ቅስቀሳ በማድረግ ሙስሊም በዙን ቀጠና ከውጭም ከውስጥም ለማጥቃት የታለመ ትንታኔ ነው።

3️⃣ የእስልምና ጥላቻ ነው።

የኦርቶማራው ኃይል «ኦሮሞን ለመምታት እስልምናን መምታት፣ እስልምናን ለመምታት ኦሮሞን መምታት‼» የሚል የከረመ ስትራቴጂ አላቸው። በጥቅሉ ኦሮሙማነትን በፀረ–ኦርቶዶክስነት ፈርጆ የተነሳ ኃይል ሽዋን የማማበበል እቅዱን በተሰላ የኡማ (ሙስሊም ህዝብ) የዐረብኛ ትርጓሜ ኮንፊዩዝ ለማድረግ ይሞክራል። በዚህም ትንታኔ የኦሪት የአህዛብና ህዝብ ትንታኔን በመደላድልነት ይጠቀማል።
።።።።
Abduljelil Sheh Ali Kassa
====================

Address

K'olito
142

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Selehadin Albani posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Selehadin Albani:

Share