Finote Selam Information Communication Technology

Finote Selam Information Communication Technology Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Finote Selam Information Communication Technology, Computer Company, 0587751377, Finote Selam.

26/08/2024

ለአዲሶቹ ተከታዮቼ ምስጋና! በመቀላቀልዎ ደስ ብሎኛል! Ybsh Love, Alex Hope

25/08/2022

🇪🇹🇪🇹ሀርድ ዲስክን ለሁለት መክፈል🇪🇹🇪🇹 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
የላፕቶፐ ወይም የዴስክቶፐ ኮምፒውተራችሁን ሀርድ ዲስክ Hard Disk እንዴት ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ መክፈል እንችላለን?
🟣🟢🔵Step by step:-🟣🔵🟢
ለምሳሌ Local disk C: ካለን ለሁለት ለመክፈል
🌺1 right click on My computer
🌺2 ከዛ Manage የሚለውን እንነካለን
🌺3 ከዛ ከሚመጡት ምርጫዎች ውስጥ disk management የሚለውን እንመርጣለን
🌺 4 ከዛ ለመክፈል የምንፈልገውን ዲስክ C:በመምረጥ right click እናደርጋለን
🌺 5 ከዛ shrink volume የሚለውን እንመርጣለን ትንሽ ሰከንድ ይቆያል
🌺 6 ከዛ የምንፈልገውን መጠን በመፃፍ shrink የሚለውን click አድርጎ መጠበቅ
መጠንቀቅ ያለብን ነገር:- ቁጥሩ በሜጋ ባይት ነው የሚገባው ለምሳሌ 50GB መክፈል ብትፈልጉ 1GB ማለት 1024 MB ነው ይህ ማለት 50*1024=51,200 ይሆናል ስለዚህ 51,200 ብለን ማስገባት ይጠበቅብናል።
🌺 7 ከዛ በጥቁር ቀለም ከታች (unlocated) የሚለው ላይ right click ማድረግ
🌺 8 click on "new simple volume
🌺9. ከዛ next next next እያሉ እስከመጨረሻው መቀጠል::
ይሄን ስናደርግ ምንም አይነት መረጃ አይጠፋብንም። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 💚💛❤️እንዲለቀቅላችሁ የምትፈልጉትን በኮሜት አሳውቁ💚💛❤️

24/08/2022

🇪🇹🇪🇹IDM Downloader🇪🇹🇪🇹 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
IDM download ስታደርጉ ለተቸገራችሁ ምርጥ መፍትሄ
ይህ IDM ማንኛውን በኮምፒውተር ላይ በመጫን የፈለጉትን ነገር ማውረድ ይችላሉ
የአጫጫን Steps
1ኛ idman629build2.exe ይጫኑ
2ኛ Patch የሚለውን ፎልደር ውስጥ በመግባት የኮምፒውተር OS bit 32 ከሆነ 32 Bit patch build 2.exe
64 ከሆነ ደግሞ በተመሳሳይ ይጫኑበት
በይበልጥ ግን How to install የሚለውን ያንብቡት።
Serial number አይጠይቃችሁም ከዚህ በኋላ

11/08/2022

🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴
ስልካቹ Stack ወይም እየደረቀ ካስቸግሮት እነዚህን 10 ነጥቦችን ይተግብሩ፦
🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆🦆
1.በብዛት የመትጠቀሙበት አፕሊኬሽን ብቻ Install አርጉ ማለትም እልሰፈላጊ የሆኑ አፕዎችን ማጥፋት ወይንም Uninstall ማረግ
2.Screen Animation እና ተንቀሳቃሽ Wallpaper Disable ማረግ ወይም ማጥፋት
3.RAM Management የሆኑ አፕሊኬሽኖችን በጭራሽ Install አያርጉ
4.የአፑን Cache Memory አፅዱ ይሄም Setting » Storage » Cache Data
5.ትንሽ ነፃ ቦት ማስቀረት
Setting » Storage
6.Widgetቱን አስወግዱ
7.ሁል ጊዜ ጥዋት ጥዋት ስልካትን Restart ወይም Reboot አርጉ
8.ሁሉንም የስልኩን አፕሊኬሽን Update ማረግ
9.Bloatwareኡን ማጥፋት ይሄም Setting » All Apps » በመግባት Disable ማርግ
10.Custom ROM Install ማርግ.እነዚህን ከላይ ያሉትን ነጥቦች በመተግበር ስልካትን ፈጣን ያርጉት።

04/08/2022

🇪🇹ከመስከረም እስከ ጳጉሜ የተሰየሙት ወራት ስያሜአቸውን እንዴት አገኙ?🇪🇹
🌷መስከረም
የግዕዝ ስርወ ቃሉ መስ እና ከረም
ትርጉም፡- መስ፣ አለፈ፣ ከረም፣ ክረምት፣ ክረምት አለፈ ማለት ነው።
🌷ጥቅምት
የግዕዝ ስርወ ቃሉ ጠቀመ
ትርጉም፡- ሠራ፣ ጠቃሚ፣ ጊዜ ማለት ነው።
🌷ኅዳር
የግዕዝ ስርወ ቃሉ ኀደረ
ትርጉም፡- አደረ፣ ሰው በወርሃ አዝመራ ማሳ ውስጥ ለጥበቃ ማደሩን ይገልፃል።
🌷ታኅሳስ
የግዕ ስርወ ቃሉ፣ ኀሠሠ
ትርጉም፡- መረመረ፣ ፈለገ፣ በመኽር ወቅት የሰብል ምርመራ ያመለክታል።
🌷ጥር
የግዕዝ ስርወ ቃሉ ነጠረ
ትርጉም፤- ጠረረ፣ ብልጭ አለ፣ ነጻ በራ የጸሀይን ግለት ወቅት ያሳያል።
🌷ይካቲት
የግዕዝ ስርወ ቃሉ ከቲት
ትርጉም፡- (የህልን) መክተቻ ማለት ነው።
🌷መጋቢት
የግዕዝ ስርወ ቃሉ መገበ
ትርጉም፡- በቁሙ የሚመግብ (በጎተራ የተከተተው የሚበላበት) ማለት ነው።
🌷ሚያዚያ
የግዕዝ ስርወ ቃሉ መሐዘ
ትርጉም፡- ጎረመሰ ጎበዘ ሚስት ፈለገ (ወርኀ ሰርግ መሆኑን ሲያጠይቅ)
🌷ግንቦት
የግዕዝ ስርወ ቃሉ ገነበ
ትርጉም፡- ገነባ፣ ሰራ፣ ቆፈረ፣ ሰረሰረ(ለእርሻ የመሬቱን መዘጋጀት ያሳያል።
🌷ሰኔ
የግዕዝ ስርወ ቃሉ ሰነየ
ትርጉም፡- አማረ ማለት ነው።
🌷ሐምሌ
የግዕዝ ስርወ ቃሉ ሐመለ
ትርጉም፡ ለቀመ(ለጎመን)
🌷ነሀሴ
የግዕዝ ስርወ ቃሉ አናህስየ
ትርጉም፡- አቀለለ፣ ተወ የክረምቱን እያደረ መቅለሉን ያመለክታል።
🌷ጳጉሜ
ስርወ ቃሉ ግሪክ ሲሆን ኤጳጉሚናስ
ትርጉም፡ ተጨማሪ ወርህ ማለት ነው፡፡ 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
ምንጭ፡
የአብነት ትምህርት ቤት የቴሌግራም ገጽ

31/07/2022

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 8 ምርጥ ቪዲዮ ማውረጃ ሶፍትዌሮች ለስልኮቻችን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
1 YouTube Go
2. Instube YouTube Downloader
3. Videoder
4. TubeMate
5. KeepVid
6. SnapTube Downloader
7. EasyTube
8. NewPipe

31/07/2022

🥕 የሚሞቅ ላፕቶፕን ማቀዝቀዣ 4 መንገዶች🥕
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
አንዳንድ ጊዜ ላፕቶፖች ከመደበኛው የሙቀት መጠናቸው ሊያልፉና በትክክል ስራቸውን መከወን ሊያቅታቸው ብሎም በሙቀቱ መነሾ ሊበላሹ ይችላሉ፡፡ በውድ ዋጋ የገዛናቸው እነዚህ ላፕቶፖች ደግሞ ተገቢውን አገልግሎት ሳይሰጡ ከጥቅም ውጭ በመሆናቸው ለተጨማሪ ጊዜ፣ ጉልበትና ወጪ ልንዳረግ እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን ችግሩ መፍትሄ የለውም ማለት አይደለም፡፡ እነዚህ 4 መንገዶች በመጠቀም ላፕቶፓችሁን ማቀዝቀዝ ትችላላችሁ፡፡
1. የምናስቀምጥበትን ቦታ መምረጥ 🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
በርካታ ሰዎች ላፕቶፓቸውን አልጋቸው ላይ አስቀምጠው የመጠቀም ልምድ አላቸው፡፡ በዚህ ጊዜ አንዳንድ ነገሮች ከላፕቶፑ የሚወጣው ሙቀት እንዳይወጣ ይልቁንስ ሙቀቱ ወደ ላፕቶፑ እንዲመለስ በማድረግ የላፕቶፑ ውስጠኛው አካል በሙቀት እንዲጎዳ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ ስለዚህም ላፕቶፕ በምንጠቀምበት ጊዜ እንደ ጠረጴዛ ያሉ ጠፍጣፋ ነገሮች ላይ በማደረግ መጠቀም ይመከራል፡፡
2. አቧራውን ማፅዳት 🌷🌷🌷🌷🌷
ላፕቶፓችን ባሉት ቀዳዳዎች አቧራ ገብቶ በመድፈን ላፕቶፑ ከመጠን በላይ እንዲሞቅ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህም ላፕቶፓችንን በየጊዜው በተለይ ፋኑ ያለበትን አካባቢ የአየር መንፊያ በመጠቀም በየጊዜው በማፅዳት የላፕቶፓችንን እድሜ ማራዘም እንችላለን፡፡
3. የኃይል አጠቃቀም 🌷🌷🌷🌷🌷
በብዛት በላፕቶፕ ላይ ስንሰራ ላፕቶፓችንን ቻርጅ ላይ በመሰካት ስንጠቀም ከፍተኛ የሆነ ሀይል እንዲጠቀም ስለሚያደርግ ላፕቶፓችን ከመጠን በላይ እንዲሞቅ ያድርገዋል፡፡ ይህንን ለመከላከልም በላፕቶፓችን ታስክ ባር ላይ ያሉ ሀይል ለመቆጠብ የሚያስችሉ አማራጮች በመምረጥ ሀይል እንዲቆጥብ በማድረግ ላፕቶፓችን ከመጠን በላይ እንዳይሞቅ ማድረግ ይቻላል፡፡
4. ሙቀቱን መከታተል 🌷🌷🌷🌷🌷🌷
የላፕቶፓችንን ሙቀት ለመቆጣጠር የሚያስችሉን የተለያዩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ እንግዲህ ላፕቶፓችን ከመጠን በላይ እየሞቀ ከተቸገርን እነዚህን በነፃ የሚገኙ እንደ Real Temp ያሉ ሶፍትዌሮች በመጫን ሲፒዩ ስራ በሌለው ጊዜ ከ30 ዲግሪ ሴልሺየስ እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ እንዲሁም በጣም የተጨናነቀ ስራ በታዘዘበት ጊዜ ደግሞ ከ70 ዲግሪ ሴልሺየስ እስከ 80 ዲግሪ ሴልሺየስ ባለው የሙቀት መጠን ውስጥ እየሰራ መሆኑን መከታተል ያስፈልጋል፡፡🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ምንጭ፡
☂️https://rockymtnruby.com
☂️https://www.reliancedigital.in

🌹🌹ላይፋይ /LiFi/ ምንድን ነው? 🌹🌹🥕🥕🥕🥕🥕🥕🥕🥕🥕🥕    #ዋይ ፋይን ይተካል የተባለው ቴክኖሎጂ ላይ ፋይ ወይም ላይት ፊደሊቲ መደበኛ የዋይ ፋይ ስርዓቶችን ሊተካ የሚችል እና አዲስ አው...
30/07/2022

🌹🌹ላይፋይ /LiFi/ ምንድን ነው? 🌹🌹
🥕🥕🥕🥕🥕🥕🥕🥕🥕🥕
#ዋይ ፋይን ይተካል የተባለው ቴክኖሎጂ ላይ ፋይ ወይም ላይት ፊደሊቲ መደበኛ የዋይ ፋይ ስርዓቶችን ሊተካ የሚችል እና አዲስ አውታረ መረብ ፕሮቶኮል ነው፡፡ ቴክኖሎጂው የሬድዮ ሞገዶችን ከመጠቀም ይልቅ መረጃን ለማስተላለፍ እና ለመቀበል ላይ ፋይ ሌኢዲ አምፖሎችን እና የላይት ሲግናሎችን ይጠቀማል እንዲሁም ለሰዎች የማይታዩ እንደ አልትራቫዮሌት ያሉ የኤሌክትሮማግኔቲክ ምልክቶችን እና ከሚታየው ብርሃን በተጨማሪ የኢንፍራሬድ ሞገዶች ይጠቀማል፡፡
ላይ ፋይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራው በ2011 ፕሮፌሰር ሃራልድ ሃስ በተባለ ግለሰብ ነው፡፡ Yole Development እና PISEO የተባሉት ኩባንያዎች እንደሚሉት ከሆነ ላይ ፋይ ጠንካራ እምቅ ቴክኖሎጂን ይወክላል፡፡ ይሁን እንጂ ሁለቱም ኩባንያዎች ቴክኖሎጂው በአጭር ጊዜ ደረጃውን የጠበቀ አሠራር በፍጥነት እንዳያድግ፣ ምርቶችና አገልግሎቶችን ደግሞ ላይ ፋይን ከመሰራት ሊከላከሉ የሚችሉ ሁለት ዋና ተግዳሮቶች ናችው ይላሉ፡፡
ይሄ ቴክኖሎጂ በዛሬው የገመድ አልባ አውታረ መረቦች ላይ ያልተለመደ እድገት ነው፡፡ ላይ ፋይ የ ዋይ ፍይ፣ 3ጂ እና 4ጂ ፍጥነት እና የመተላለፊያ ይዘትን ይጨምራል፡፡ የዋይ ፋይ አቅም ውሱን እና የተጠቃሚዎች ቁጥር ሲጨምር ይሞላል፤ ይህም እንዲበላሽ፣ ፍጥነት እንዲቀንስ እና ግንኙነቱን እንዲቋረጥ ያደርጋል፡፡
ላይ ፋይ የባንዱ ድግግሞሽ 200,000 GHz ሲሆን ዋይፋይ ግን ከፍተኛው 5 GHz ነው ስለዚህ ላይ ፋይ 100 እጥፍ ፈጣን ሲሆን ብዙ ተጨማሪ መረጃዎችን በሰከንድ ማስተላለፍ ይችላል፡፡ በ2017 በአይንድሆቨን ዩኒቨርስቲ የተደረገ ጥናት ምርጡ ዋይ ፋይ 300 Mbit/s በማይደርስበት ጊዜ ከኢንፍራሬድ ብርሃን ጋር 2.5 ሜትር ራዲየስ ያለው ላይ ፋይ 42.8 Gbit/s የማውረድ ፍጥነት አግኝቷል፡፡
☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️☘️ የላይ ፋይ ጥቅሞች
☂️ ፍጥነት
የአሁኑ የዋይ ፋይ ፍጥነት በ11 እና 300Mbit/s መካከል ያለው ሲሆን የ ላይ ፋይ ፍጥነቱ በመጨረሻዎቹ ጥናቶች መሰረት በጣም ተለዋዋጭ ነው፡፡ በሰፊው ተቀባይነት ያለው ፍጥነት 10 Gbit/s ነው ነገር ግን 224 Gbit/s ሊደርስ እንደሚችል እና 1.5 GB ፊልም በ አንድ ሺህ ሰከንድ ሊያወርድ እንደሚችል ተረጋግጧል፡፡
☂️ ዋጋ እና ዘላቂነት
ከዋይ ፋይ እስከ 10 እጥፍ ርካሽ ነው፣ ጥቂት አካላትን ይፈልጋል እና አነስተኛ ጉልበት ይጠቀማል፡፡ ማድረግ ያለብዎት መብራት ማብራት ብቻ ነው!
☂️ ተደራሽነት
ምክንያቱም ቀላል ላይ ፋይ ኢሚተር ብቻ በመጫን ማንኛውም አይነት ብርሃን በቀላሉ ወደ የበይነመረብ ግንኙነት ነጥብ ሊቀየር ይችላል፡፡
☂️ደህንነቱ
ብርሃን እንደ ሬዲዮ ሞገዶች በግድግዳዎች ውስጥ አያልፍምና ሰርጎ ገቦች በገመድ አልባ አውታረ መረብ የላይ ፋይ ግንኙነቶችን እንዳይጠልፉ ይከላከላል፡፡
☂️ የመተላለፊያ ይዘት
የብርሃን ስፔክትረም ከሬዲዮ ስፔክትረም 10,000 እጥፍ ይበልጣል፡፡ ይህም የላይ ፋይ በሴኮንድ የሚይዘው እና የሚያስተላልፈውን የውሂብ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
☂️ የበለጠ አስተማማኝ
ላይ ፋይ መልዕክቱን ያለምንም መቆራረጥ ያስተላልፋል፣ ይህም ግንኙነት ከዋይ ፋይ የበለጠ የተረጋጋ ያደርገዋል፡፡
☂️ ጣልቃገብነት አለመኖር
የኤሌክትሮኒክስ መብራት በሬዲዮ ግንኙነቶች ላይ ጣልቃ አይገባም፣ ከሌሎች ስርዓቶች ጋር ወይም ከአውሮፕላኖች፣ መርከቦች፣ ወዘተ አይገናኝም፡፡
☂️ ሽቦ አልባ መሆን
ላይ ፋይ ብርሃንን ስለሚጠቀም እና ከራውተሩ ጋር ስለሚሰራጭ ገመዶች ሳያስፈልገው ይሰራል፡፡ በተጨማሪም በሰው ዓይን የማይታየው የኢንፍራሬድ ብርሃን ወይም በሚታየው የኤልኢዲ መብራት በጣም ዝቅተኛ በሆነ መጠን መቆራረጥ እንዳይፈጠር ማድረግ ይችላል፡፡

23/06/2022

💜❤️ይህንን ያውቁ ኖሯል?❤️💜
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
1.) GOOGLE --------Global Organization Of Oriented Group Language Of Earth .
2.) YAHOO ---------Yet Another Hierarchical Officious Oracle .
3.) WINDOW -------Wide Interactive Network Development for Office work Solution
4.) COMPUTER----- Common Oriented Machine Particularly United and used under Technical and Educational Research.
5.) VIRUS ----------Vital Information Resources Under Siege .
9.) IMEI-------------International Mobile Equipment Identity .
10.) ESN------------ Electronic Serial Number .
11.) UPS------------uninterrupted power supply .
12). HDMI-------- High-Definition Multimedia Interface
13.) VPN---------- virtual private network
14.) APN---------- Access Point Name
15.) SIM---------- Subscriber Identity Module
16.) RAM--------- Random access memory.
17.) ROM--------- Read only memory.
18) VGA--------- Video Graphics Array
19) USB----------Universal serial Bus
20) WLAN--------Wireless Local Area Network
21.) LCD---------Liquid Crystal Display.
22.) O.S----------Operating system.
23.)GPS--------- Global Positioning System
24.)DVD-------- Digital Video Disk / digital versatile disc
25.)DTP---------Desk top publishing.
26.)CDMA------Code Division Multiple Access
27.) WCDMA-----Wide-band Code Division Multiple Access
28.)E-Mail-------- Electronic Mail
29.) WI-FI------- Wireless Fidelity
30.) DELL------- Digital electronic link library.
31.) ACER-------Acquisition Collaboration Experimentation Reflection
32.) INTERNET-----International Network
33.) HP---------------Hewlett Packard
34.) PDF ------------- portable document format.
35.) ATM ------------- Automated Teller machine

Address

0587751377
Finote Selam
48

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Finote Selam Information Communication Technology posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Finote Selam Information Communication Technology:

Share