ANRS North Shoa Zone ICT Core Process

ANRS North Shoa Zone ICT Core Process Information and Communication Technology Team

"የነገው ቀንን" ስናስብ  አሁን ያለንበትን ቴክኖሎጅ ተቋማት መከተል እንዳለባቸው ለማስገንዘብ በማሰብ ነው። ጳጉሜ 05 ቀን 2017 ዓ.ም  በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት የቴክኖሎ...
10/09/2025

"የነገው ቀንን" ስናስብ አሁን ያለንበትን ቴክኖሎጅ ተቋማት መከተል እንዳለባቸው ለማስገንዘብ በማሰብ ነው።

ጳጉሜ 05 ቀን 2017 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ቡድን "ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ" በሚል መሪ ሐሳብ ጳጉሜ 5 ቀን "የነገው ቀንን" ለመንግስት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብር አካሄደ።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግዛቸው ነገሰ በመርሐ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያውያን ቀደምት ከምንታወቅበት ስልጣኔ ወጥተን ወደ ኋላ የቆየንበት ጊዜ ቢኖርም አሁን ላይ ዲጂታል ዘርፋን መከተል አለብን።

ተቋማት ከቴክኖሎጅው ጋር መታረቅ ይኖርባቸዋል ያሉ ሲሆን፤ አሁን ያለንበትን የዲጂታል አለም ይዘን የሞያው ባለቤቶች ልንሰራበት ይገባል ብለዋል።

ከቴክኖሎጂው ጋር ለመሄድ ቀኑን አስበን ብንውልም የሚመለከታቸው ኃላፊዎች ትኩረት ሊያደርጉበት ይገባልም ብለዋል።

በመድረኩ አከባበር ላይ የተገኙት የሰሜን ሸዋ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሜሮን አበበ እና የመንግስት ኮሙኑኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ተማለደ በላይሁን ስለቴክኖሎጂው ጠቀሜታ አስተያየት በመስጠት የዲጂታል ሽግግር አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽህፈት ቤት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ በአቶ ደመላሽ በላይ በበኩላቸው "የነገው ቀን" ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚል ሰነድ ለተሳታፊዎች አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ለተሳታፊዎች መጪው ጊዜ የቴክኖሎጂ ነውና ዲጂታል ኢትጵያን እውን ማድረግ የሁላችንም ድርሻ በመሆኑ በፍጥነት የዞናችንን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረግ ይጠበቅብናል ያሉት ቡድን መሪው፤ በመድረኩ የጥያቄና መልስ ውድድር በማድረግ እውቅና በመስጠት የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሩ ላይ የዞኑ አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
ዘገባው የ(ሰሸዞመኮ) ነው

በሰሜን ሸዋ ዞን የ2017 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የዘርፍ ስራ አፈጻጸምን በመገምገም የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ይፋ ሆነ፦ ውይይቱን በቨርቺዋል ቪዲዮ ኮንፈረንስ ያካሄደው የሰሜን ሸዋ ...
18/07/2025

በሰሜን ሸዋ ዞን የ2017 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የዘርፍ ስራ አፈጻጸምን በመገምገም የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ይፋ ሆነ፦

ውይይቱን በቨርቺዋል ቪዲዮ ኮንፈረንስ ያካሄደው የሰሜን ሸዋ ዞን አስ/ጽ/ቤት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን ወጣቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማብቃት የትኩረት አቅጣጫ እንዲሆን አስቀምጧል

በሰሜን ሸዋ ዞን የ2017 በጀት ዓመት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ ተካሂዷል። በዚሁ የስራ ግምገማ መድረክ ላይ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተክለየስ በለጠ እንዲሁም የቀወረዳና ከተማ አስተዳደር የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በቨርቺዋል ቪዲዮ ኮንፈረንሲንግ ላይ ተገኝተዋል።
ምክትል አስተዳዳሪው አቶ ተክለየስ በለጠ እንደተናገሩት በዚህ ወቅት የኢ/ቴ ቡድኖች ለዞኑ እድገት ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

እንዲሁም በቀጣይ እቅድ ትግበራ ላይ አስፈላጊ የሆኑ ድጋፎችን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
አቶ ተክለየስ በለጠ አክለውም የቴክኖሎጂው ዘርፍ የአንድን ሀገር እድገት ለማፋጠን ቁልፍ ሚና እንዳለው ገልጸው፣ ዞኑም ይህንኑ ተገንዝቦ እየሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በሪፖርቱ ላይ የኢትዮ ኮደር አጠቃላይ የእቅድ አፈፃፀም፣
የኔትወርክ አስተዳደር የስራ ዘርፍ፣ የኢኮቴ ጥናትና ስልጠና የስራ ዘርፍ ለም ዘርፍ ፣ የሲስተም ልማትና አስተዳደር የስራ ዘርፍ የተከናወኑና ያልተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርቧል። በተጨማሪም በእያንዳንዱ የስራ ዘርፍ በቀጣይነት ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይትም ተደርጓል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የወረዳና ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶችና ያገኙዋቸውን መልካም አጋጣሚዎች ያካፈሉ ሲሆን በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ባለሙያወች ተለምተው ለአገልግሎት የበቁ ሶፍትዌሮች ቀርበዋል።
ለቀጣይ ሊተኮርባቸው የሚገቡ ጉዳዮች ላይም ሃሳባቸውን አካፍለዋል። የ2018 የኢ/ቴ እቅድ የዞኑን የልማት እንቅስቃሴ ለማሳለጥ የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።
በእነዚህ ዘርፎች የታዩትን ጠንካራ ጎኖች በማስፋትና ክፍተቶችን በመሙላት ለ2018 የዕቅድ ዘመን የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

በተለይም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ፣ የኢትዮ ኮደር ወጣቶችን እና ተማሪዎችን በስፋት በማሰልጠን ከዲጂታል አለሙ ጋር እንዲተዋወቁና የቴክኖሎጂ ክህሎታቸው እንዲያድግ ማድረግ "ግድ ይላል" በሚል አጽንኦት ተሰጥቶበታል። ይህም የዞኑን የሰው ሀይል በቴክኖሎጂ ለማብቃትና የዲጂታል ኢኮኖሚውን ተጠቃሚ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑ ተጠቁሟል።

በመጨረሻም የዞኑ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ደመላሽ በላይ በበኩላቸው፣ በግምገማው የተለዩትን ጥንካሬዎች አጠናክሮ ለማስቀጠልና የታዩትን ድክመቶች በማረም የ2018 ዓ.ም ዕቅድን ከወዲሁ በላቀ ርብርብ ለማሳካት ሁሉም ባለ ድርሻ አካል በቡድንና በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅ አስገንዝበው ውይይቱ ተጠናቋል።
ሰሸዞአስ
11/11/2017 ዓ.ም

እንኳን ለ2017 ዓ.ም  አደረሳችሁ!🌿 አዲሱ ዓመት🌿     ✔የጤንነት     ✔ የሠላም     ✔ የፍቅር 🤝     ✔ የአንድነትና       ✔ የመከባበር ዓመት ያድርግልን!መልካም አዲስ ዓመ...
11/09/2024

እንኳን ለ2017 ዓ.ም አደረሳችሁ!

🌿 አዲሱ ዓመት🌿
✔የጤንነት
✔ የሠላም
✔ የፍቅር
🤝 ✔ የአንድነትና
✔ የመከባበር ዓመት ያድርግልን!
መልካም አዲስ ዓመት 2017!!!🌼እ🌻ን🌼ቁ🌻🌼ጣ🌻ጣ🌻ሽ🌼🌼🌼

በርካቶችን አለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ባለቤት እያደረገ የሚገኘው የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደር ኢኒሸቲቭ በአራት የስልጠና ዘርፎች (በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣...
02/09/2024

በርካቶችን አለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ባለቤት እያደረገ የሚገኘው የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደር ኢኒሸቲቭ በአራት የስልጠና ዘርፎች (በዌብ-ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) በኦንላይን እየተሰጠ ነው።

ስልጠናውን በተሰጡት 8 ሳምንታት ያጠናቀቁ ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት እየተበረከተላቸው ይገኛል እርስዎም ይህንን እድል እንዲጠቀሙ ተጋብዘዋል።

የምዝገባ ሊንክ https://www.ethiocoders.et/

02/09/2024
የማህበራዊ ትስስር ገጽዎን ደህንነት የሚያስጠብቁባቸዉ መንገዶች የትኞቹ ናቸዉ?  ለህዝብ እይታ አለማቅረብ  ደህንነት ማስጠበቅ #አድራሻና የጉዞ እቅድን ከማጋራት መቆጠብ #ህዝባዊ የሆኑ የዲጂ...
28/08/2024

የማህበራዊ ትስስር ገጽዎን ደህንነት የሚያስጠብቁባቸዉ መንገዶች የትኞቹ ናቸዉ?

ለህዝብ እይታ አለማቅረብ
ደህንነት ማስጠበቅ
#አድራሻና የጉዞ እቅድን ከማጋራት መቆጠብ
#ህዝባዊ የሆኑ የዲጂታል ቁሶችን ስንጠቀም ተገቢዉን ጥንቃቄ ማድረግ
ሶፍትዌር መጠቀም

የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደር ኢኒሸቲቭ ስልጠና ይፋ ከተደረገ ጀምሮ በርካቶች በዚህ ሊንክ  https://www.ethiocoders.et/ እየተመዘገቡ ስልጠናውን በመውሰድ ላይ ናቸው።እርስዎ...
27/08/2024

የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደር ኢኒሸቲቭ ስልጠና ይፋ ከተደረገ ጀምሮ በርካቶች በዚህ ሊንክ https://www.ethiocoders.et/ እየተመዘገቡ ስልጠናውን በመውሰድ ላይ ናቸው።እርስዎም ይህንን ወርቃማ እድል እንዲጠቀሙበት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የመመዝገቢያ ሊንክ https://www.ethiocoders.et/

ማስታወቂያለስልጠና ፈላጊዎች በሙሉበኢትዮጵያ መንግስትና እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መካከል በተደረገ ስምምነት "5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሸቲቭ" በሚል የስልጠና ፕሮግራም ተዘጋጅቷ...
23/08/2024

ማስታወቂያ
ለስልጠና ፈላጊዎች በሙሉ
በኢትዮጵያ መንግስትና እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መካከል በተደረገ ስምምነት "5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሸቲቭ" በሚል የስልጠና ፕሮግራም ተዘጋጅቷል፡፡ የስልጠና ፕሮግራሙ የሚያተኩረው
• Programming Fundamentals,
• Data Science Fundamentals and
• Android Developer Fundamentals በሚሉ ይዘቶች ላይ ሲሆን ምዝገባው የሚካሄደው በኦን ላይን ነው፡፡
በኦን ላይን ለመመዝገብ ድጋፍ የምትፈልጉ ተመዝጋቢዎች ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 በሚገኘው የአብክመ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን በመገኘት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ምዝገባውን በሚከተለው ሊንክ በመግባት ማከናወን ትችላላችሁ፡፡
https://ethiocoders.et
ኮሚሽኑ

Acquire the essential digital skills necessary to establish a promising career in the ever-evolving technology industry with our comprehensive, fully-funded courses.

Search using "Site:" to find content from a specific websiteከአንድ ድረገፅ አድራሻ ብቻ ለመፈለግ============A Google search can retur...
06/07/2022

Search using "Site:" to find content from a specific website
ከአንድ ድረገፅ አድራሻ ብቻ ለመፈለግ
============
A Google search can return millions of results. Cut that down significantly by searching just a single site with Google’s Site: feature. Open Google in your browser and type “site:” and then the website you wish to search. Like this: “site:amazon.com” but leave off the quotation marks.

Tip in a tip: You can enter “site:amazon.com search term” in your browser’s address bar and no need to go to Google. Again, no quotation marks needed.

የሰሜን ሸዋ ዞን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን ስልጠና ሰጠበጫጫ ከተማ ለ2 ቀናት የ9 ወር እቅድ አፃፀም ግምገማና በሪፖርት ሲስተም ላይ የተለማ ሶፍትዌር ስልጠና ከዞኑ የከተማ አ...
27/05/2022

የሰሜን ሸዋ ዞን የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን ስልጠና ሰጠ

በጫጫ ከተማ ለ2 ቀናት የ9 ወር እቅድ አፃፀም ግምገማና በሪፖርት ሲስተም ላይ የተለማ ሶፍትዌር ስልጠና ከዞኑ የከተማ አስተዳደርና የገጠር ወረዳ የመጡ የኢንፎርሜሽን ኮሙኑኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪዎችን ስልጠና ሰጥቷል።

በእለቱ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንግዳሸት በጋሻው ለዘርፉ ትኩረት መስጠት የሁሉም አመራር ኃላፊነት ሲሆን ቴክኖሎጂውን በሚገባ በመተግበር አካባቢያችንን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባናል ካሉ በኋላ በዓመቱ ታቅደው ያልተፈፀሙ ተግባራትን በመለየት በቀሪ ጊዚያቶች ማጠናቀቅ እንደሚገባና በሪፖርቲንግ ሲስተም በዞኑ ባለሙያዎች የተለማውን ሶፍት ዌር ወደ ተግባር መቀየርና አገልግሎት ላይ እንዲውል ማድረግ በእጅጉ ስራን የሚያቀል፣ ጊዜን የሚቆጥብ፣ ወጪን የሚቀንስ ነው በማለት አሳስበዋል።
የዞኑ የኢንፎርሜሽን ኮሙኑኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ደመላሽ በላይ በእለቱ የቀረቡ ጥያቄዎችን ከመለሱ በኋላ በወረራው ንብረት የወደመባቸውን የወረዳ ኔት ማዕከላትን መልሶ በማቋቋም በሙሉ አቅም ማስገባት የፌደራል፣ የክልሉም ኃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ ሳንሰለች ጥያቄው በተደጋጋሚ ቀርቦ እልባት እንዲያገኝ ይደረጋል ብለዋል።

ሌላው ከመድረኩ የተገነዘብንው ባለሙያዎች በውድመቱ ቢሮ፣ ግብአት ሳይኖራችሁ አካባቢያችሁን ለመጥቀም የምታደርጉት ተነሳሽነትና ጥረት በእጅጉ የሚበረታታና ሌሎችም ከእናንተ ተሞክሮ መውስድ እንደሚገባቸው አይተናል በማለት ቀሪ ዝርዝር ተግባራትን በበጀት አመቱ ውስጥ በማጠናቀቅ ውጤታማ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

Address

Debre Birhan

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251116811215

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS North Shoa Zone ICT Core Process posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ANRS North Shoa Zone ICT Core Process:

Share