06/08/2026
"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በመስቃን ወረዳ አስተዳደር ጎይባን ቀበሌ በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አማካኝነት የችግኝ ተከላ ተካሄደ።
========
ሐምሌ_30/2018
"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በመስቃን ወረዳ አስተዳደር ጎይባን ቀበሌ በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አማካኝነት የችግኝ ተከላ ተካሄደ።
የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ በመስቃን ወረዳ ጎይባን ትምህርት ቤት
"አንድ ችግኝ ዛሬ፣ ሺህ ተስፋዎች ነገ!"
በመስቃን ወረዳ ጎይባን ትምህርት ቤት በተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የሳኢቴ፣ ኮሚንኬሽን ባለሙያ፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ቤቱ አመራሮች በንቃት በመሳተፍ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
ይህ እንቅስቃሴ አካባቢያችንን አረንጓዴ ለማድረግ፣ አየርን ለማጽዳት፣ አፈርን ለመጠበቅ እና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለ አካባቢ ለመፍጠር የሚያስችል ጠቃሚ ተግባር ነው።
🌳 ዛሬ የተተከለውን ችግኝ በፍቅር እንንከባከብ፤ ነገን በአረንጓዴ ተስፋ እንገንባ!