Tewahido

Tewahido የእውነት አባት ምን ይላሉ

ርቀት ያልገደበው የሁለቱ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ግንኙነት ።በመምህር አቤል አሰፋ የምሥራቅ ካቶሊኮስ እና የማላንካራ ሜትሮፖሊታን የሆኑት የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓት...
25/09/2026

ርቀት ያልገደበው የሁለቱ ኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት ግንኙነት ።

በመምህር አቤል አሰፋ

የምሥራቅ ካቶሊኮስ እና የማላንካራ ሜትሮፖሊታን የሆኑት የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ በሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ለማጠናከር ከመስከረም 14–18 ቀን 2019 ዓ.ም በኢትዮጵያ ይፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

​በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግብዣ መሠረት ቅዱስነታቸው በታላቁ የቤተክርስቲያንናችን የመስቀል ደመራ በዓል በመገኘት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጋር በመሆን ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ያስተላልፋሉ ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት በዚህ ጉብኝት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አቀባበል ተደተደርጎላቸዋል። በዚሁ ካቴድራል ሥርዓተ ጸሎት አድርሰዋል ። ቅዱስነታቸው በአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

​ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት በሕንድ እና በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን መንፈሳዊ አንድነት በጎላ ሁኔታ የሚያሳይ ነው። ሁለቱም የእህትማች አብያተ ክርስቲያናት የኦሬንታል ኦርቶዶክስ ቤተሰብ አባላት እንደመሆናቸው መጠን፣ በተመሳሳይ ዶግማ እና ምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን አንድ ሆነው በባህላቸው እና ቋንቋቸው የተለያዩ ናቸው።

​የሁለቱ አብያተክርስቲያናት ግንኙነት ታሪካዊ መሠረት አለው። ከዚህ ታሪካዊ ግንኙነት በይፋዊቱ የሚጠቀሰው በ1965 (እ.ኤ.አ) ካቶሊኮስ ባስሊዮስ ኦገን ፩ኛ በአዲስ አበባ በተካሄደው ታሪካዊ የኦሬንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች ጉባኤ ላይ ተሳታፊ ነበሩ። በ2013 (እ.ኤ.አ) ካቶሊኮስ ባስልዮስ ማርቶማ ጳውሎስ ፪ኛ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፩ኛ የፓትርያርክነት በዓለ ሢመት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር። በ2016 (እ.ኤ.አ) ደግሞ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ወደ ሕንደኬ ኬርላ ተጉዘው ሐዋርያዊ ጉብኝት አድርገዋል።

​የብፁዕ ወቅዱስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ ጉብኝት ይህንን ርቀት ያልገደበው የወንድማማችነት እና የእህትማችነት ግንኙነት ያስቀጥላል።

የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቋንቋ ባህል እና ትውፊት ቢለያዩም በዶግማ ባላቸው አንድነት በአንድ መንበር ቀድሰው ምስጢረ ቁርባንን የሚካፈሉ እምነት አንድ ያደረጋቸው አብያተክርስቲያናት ናቸው።

የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ
ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ጸሎት ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው አይደለም። ከዚህ ዓለም ድካም ባረፉት በቀድሞው የቤተክርስቲያናችን ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የቀብር ሥነ ሥርዓት ወቅት ተገኝተው ጸሎተ ፍትሐት ማድረጋቸው ይታወሳል።

ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ማርቶማ ማቴዎስ ፫ኛ " በዓለም ዙሪያ ባደረግኳቸው ሐዋርያዊ ጉዞዎች ሁሉ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሞቅ ያለና ልብን የሚነካ አቀባበል ያደረገልኝ የለም። ዛሬም በካቴድራሉ የተደረገልኝ አቀባበል፣ የቀረበው ዝማሬና ክብር ልባችንን በጥልቅ ነክቶታል" ሲሉ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተደረገላቸው አቀባ

❤የጋብቻው ፊርማ ሥነ ሥርዓት ተከናወነ❤በአስትሮኖሚ ዘርፍም ሆነ በመንፈሳዊው ዓለም ተወዳጁና ታዋቂው ምሁር ሰው አክባሪው ቅኑ ወንድም  መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ እንኳን ለዚህ ታላቅ ...
18/09/2026

❤የጋብቻው ፊርማ ሥነ ሥርዓት ተከናወነ❤
በአስትሮኖሚ ዘርፍም ሆነ በመንፈሳዊው ዓለም ተወዳጁና ታዋቂው ምሁር ሰው አክባሪው ቅኑ ወንድም መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ እንኳን ለዚህ ታላቅ የጋብቻ ፊርማ ሥነ ሥርዓት አደረሳችሁ።
የመምህራችን የጋብቻ ሥነ-ሥርዓት በጉጉት ሲጠበቅ የቆየ ነው የጋብቻ የፊርማ ሥነ-ሥርዓታቸውን በታላቅ ደስታ አካሂደዋል።
መጪው እሁድ መስከረም 10 ቀን ደግሞ ሥርዓተ ተክሊሉና ዋናው የሰርግ ሥነ-ሥርዓቱ ይፈጸማል።
ለመምህራችንና ለባለቤታቸው፡
* የፍቅር፣ የሰላምና የጤና
* የሙሽርነት ደስታ የሚበዛበት
* እግዚአብሔር አምላክ በበረከቱ የሚጎበኝበት ያማረ ጋብቻ እንዲሆንላቸው ከወዲሁ መልካም ምኞቴን እገልጻለሁ
👉 መልካም የጋብቻ ዘመን! 🙏🎉

 #ውድ  #የጴንጤ ሴት እህቶች👭እባካችሁ እኛን ተዉና ቢያንስ ጌታን ፈርታችሁ አለባበሳችሁን አስተካክሉ🙏👐 ጨርሳችሁ አንብቡ!! #የኔ ውድ እህት👩‍❤️‍👩 ወንድ ሲያይሽ ለዝሙት እንድነሳሳ የሚ...
18/09/2026

#ውድ #የጴንጤ ሴት እህቶች👭እባካችሁ እኛን ተዉና ቢያንስ ጌታን ፈርታችሁ አለባበሳችሁን አስተካክሉ🙏👐 ጨርሳችሁ አንብቡ!!

#የኔ ውድ እህት👩‍❤️‍👩 ወንድ ሲያይሽ ለዝሙት እንድነሳሳ የሚያደርግ ልብስ ለብሰሽ ቸርች የምትሄጂ ከሆነ ራስሽን ፈትሽ!! በውስጥሽ የሆነ ችግር አለ ማለት ነው። ቸርች ውስጥ አንቺን የቸርች መርዎች ብሉሽ ስለምትይ የቸርች መርዎች ከተናገርናት ከጌታ ቤት(ቸርች) ትጠፋለች በሚል ፍራቻ አይነግሩሽም። ነገር ግን እህቴ እኔ ግልፁን እነግርሻለሁ ለቸርች የማይመጥን ልብስ ለመልበስ ብለሽ #እግዚአብሔር ልብን እንጅ ልብስን አያይም # እያልሽ የምታመካኝ ከሆነ ፍፁም ስህተት ውስጥ ነሽ👐 እውነት ነው! እግዚአብሔር የልብ አምላክ ስለሆነ ልብን ነው የሚያየው። ሆኖም ግን ልቡ ለጌታ ንፁህና ትክክል የሆነ ሰው ስጀመርም ለጌታ ቤት የማይመጥነውን ልብስ አይለብስም🙅‍♂️
#በእርግጥ ሁሉም ሰው አንቺ የማይሆን ልብስ ስለለበሽ ብቻ አይደለም ለዝሙት የሚነሳሳው። ሽፍንፍን ብለሽም ችግር ውስጥ የሚገባ ችግር ያለበት ሰው አለ። አንቺ ግን በስነ ስርአት ገላሽንና መቀመጫሽን እንዲያሳይ አድርገሽ መስታወት ፊት 100 ጊዜ ዞር ዞር💃 ብለሽ ቸርች ከመጣሽና ሰዎች አንቺን አይተው ባንቺ የሚሰናከሉ ከሆነ የምረን ነው የምልሽ ጌታ በዚያ በፍፁም አይከብርም🙌
#የኔ ውድ እህት አስተውይ ቸርች ማለት ሰዎች ከአለም ነገር፣ ከሀጢአት፣ እግዚአብሔርን እንዳያገኙ ካራቃቸው ነገር... ወዘተ እየሮጡ ለማምለጥ ሸሽተው የሚመጡበት ቦታ ነው። እንደገናም ቸርች ማለት ሰዎች ለመታነፅ፣ለመቀየር፣ ከሱስና ከዝሙት ለመላቀቅ የሚመጡበት ቦታ ነው። እና ልክ ቸርች መጥተው ሳምንት በትክክል ቆይተው ቀጣዩ ቀን ላይ አንቺን አይተው ስንክል የምሉ ከሆነ እውነተን ነው የሚልሽ በፍፁም ትክክል አይደለሽም😌 1ኛ ቆሮንቶስ 8÷13 ላይ ያለውን ክፍል አንብበሽ ከሆነ ጳውሎስ እንዲህ ይላል #ስለዚህም መብል ወንድሜን የሚያሰናክለው ከሆነ፥ ወንድሜን እንዳላሰናክለው ለዘላለም ከቶ ሥጋ አልበላም # ይላል። ጳውሎስ 👉 እንኳን ልብስ መብል እራሱ ሰውን የሚያሰናክል ከሆነ መብልን አልበላም እያለ አንቺ ለምን ሰውን የሚያሰናክል ልብስ ትለብሺያለሽ!?🤔 በጣም የሚያማምሩ ረጃጅም ቀምሶች አሉ እነሱን ብትለብሺ🙏 አውቃለሁ ሰው ኢየሱስን በማመን እንጂ ረጅም ቀምስ በመልበስ እንደማይፀድቅ። ቢሆንም ግን በአለባበስ፣በስርአትና በንግግራችን... ወዘተ ሰዎች ጌታን በኛ ውስጥ ማየት አለባቸው። እውነት ለመናገር ጌታን የማያውቁ ለሎች ቤተ እምነቶች ነበር አለባበስን ከኛ ማየት የነበረባቸው😥 #አይታወቅም አንቺም ያንን ልብስ የምትለብሽው ምናልባትም የተለያዩ የፋሽን ቪድዮዎችን በማየትና አቻ ጓደኞችሽን በመመልከት በማወቅም ሆነ ባለ ማወቅ ልሆን ይችላል። ነገር ግን ከአሁን በኃላ Please ብታስተካክይ🤲
#ደግሞ ሁሉንም የጴንጤ እህቶች እያልኩ አይደለም🙅‍♂️ እኔ እንደውም በአለባበስና በስርአት በጣም የማደንቃቸውና ለሎችም እነሱን ቢመስሉ የምላቸው ብዙ እህቶች ቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ አሉ። ጌታ የተመሰገነ ይሁን🙏ለምሳሌ በሶሻል ሚድያ የምናውቃት ዘማርት #ሰላም ደስታን # ብታዩ አለባበሷ ጌታን የሚያሳይና የሚያከብር ነው😅 ስለዚህ አለባበሳችሁ ጥሩ የሆነ እህቶች በዚያው እንድትቀጥሉ እናበረታታለን👏 የማይሆን አለባበስ የምትለብሱ ግን ጌታን ፈርታችሁ አለባበሳችሁን አስተካክሉ! ቸርች ፋሽን

💟  #ሚስጥረ ስላሴ በጥቂቱ ❣️📌ምስጢረ ሥላሴ፦ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው። እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና...
17/09/2026

💟 #ሚስጥረ ስላሴ በጥቂቱ ❣️

📌ምስጢረ ሥላሴ፦ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው። እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው፤ ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን አንድ ሕያው አምላክ ነው።

የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል፦ እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው። የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው።

እግዚአብሔር በስም ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው። እነዚህም፦ #አብ #ወልድ መንፈስ ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም፤ አንዱ በሌላው ስም አይጠራም። "ዘፍጥረት1፡ 2 " "ምሳሌ30፡4" ።

>እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው፦ ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው። እነሱም፦
መውለድና ፤ማስረጽ 💟የአብ
መወለድ፡ 💟የወልድ
💟መስረጽ፡ 💟የመንፈስ ቅዱስ ፤ የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ። "መዝሙር2፡7"
እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።

ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።

ለመንፈስቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው። የሦስቱ የእግዚአብሔር ስሞችትርጉም

አብ፦ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸነው።

ወልድ፦ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው። "መዝሙር2፡7" መንፈስቅዱስ፦ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ; ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው። "ኢዮብ26፡13"

የቅድስት ሥላሴ ረድኤት
በረከታቸው አይለየን አሜን

 #ሻሸመኔበምዕመናን ብርቱ ርብርብ በዉብ ኪነ ሕንፃ ጥበብ የታነፀው ባለ7 ጉልላቱ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መሰከረም 11 እና 12 /2019 ይመረቃል!
16/09/2026

#ሻሸመኔ
በምዕመናን ብርቱ ርብርብ በዉብ ኪነ ሕንፃ ጥበብ የታነፀው ባለ7 ጉልላቱ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን መሰከረም 11 እና 12 /2019 ይመረቃል!

16/09/2026

ራሷን ለክርስቶስ ሙሽራ ያደረገች የዚህን ዓለም ጣዕም የናቀች ስለ እግዚአብሔር ስትል ደሟን ያፈሰሰች ስለ መንግሥተ ሰማያት መራራ ሞትን የታገሰች አንገቷን ለሰይፍ የሰጠች ቅድስት አርሴማ በረከቷ ይደርብን

ሻሸመኔ የአማላጇን፣ የወዳጇን፣ የጠባቂዋን  የቅዱስ ሚካኤል ቤተመቅደስ  መስከረም10,11እና12 ቀን 2019  ዓ/ም ታስመርቃለች ። ቅዱስ ሚካኤልን ያሉ ከመላው ኢትዮጵያ ሻሸመኔ ላይ ይከትማ...
14/09/2026

ሻሸመኔ የአማላጇን፣ የወዳጇን፣ የጠባቂዋን የቅዱስ ሚካኤል ቤተመቅደስ መስከረም10,11እና12 ቀን 2019 ዓ/ም ታስመርቃለች ። ቅዱስ ሚካኤልን ያሉ ከመላው ኢትዮጵያ ሻሸመኔ ላይ ይከትማሉ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን

  የሆነች እናትበሃሳቧ ድንግል በስጋዋ ድንግል በሕሊናዋ ድንግል ማንም ሰው ጳጳስን ሐዋርያትን ነቢያትን ሊወልድ ይችላል አምላክን የመውለድ ጸጋ የተሰጣት ብቸኛዋ እናት።ማርያም ብቻ....✝ 1...
13/09/2026

የሆነች እናት
በሃሳቧ ድንግል በስጋዋ ድንግል
በሕሊናዋ ድንግል ማንም ሰው ጳጳስን ሐዋርያትን ነቢያትን ሊወልድ ይችላል አምላክን የመውለድ ጸጋ የተሰጣት ብቸኛዋ እናት።

ማርያም ብቻ....✝
1.አምላክን የወለደች ክብርት እናት - ማርያም ብቻ!
2.ከመውለዷ በፊትም ሆነ በኋላ ድንግል የሆነች - ማርያም ብቻ!
3.ከሰው ወገን ተለይታ መርገም ያልነካት - ማርያም ብቻ!
4.የእግዚአብሔር ሀገር ከተማ የተባለች - ማርያም ብቻ!
5.በድምጿ መንፈስ ቅዱስን የምትሞላ ንግስት- ማርያም ብቻ!
6.ጽንስ በማሕፀን የዘለለላት ብጽዕት - ማርያም ብቻ!
7.ያለፈውም የሚመጣውም ትውልድ የሚያመሰግናት - ማርያም ብቻ!
8.ፀሐይን ተጎናፅፋ ጨረቃን የተጫማች ልዩ እናት - ማርያም ብቻ!
9.በጌታ ሞት ያዘነውን ዓለም እንድታፅናና ጌታ የሰጠን
ሥጦታችን - ማርያም ብቻ!
10.በስጋዋ፣ በነፍስዋና በሕሊናዋ በሶስት ወገን ድንግል የሆነች - ማርያም ብቻ!
11.ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች - ማርያም ብቻ!
12.ከፍጥረት ሁሉ ተለይታ አምላኳን "ልጄ" የምትል - ማርያም ብቻ!
13. ፍቅርዋ በልቤ የሚቀጣጠል አማላጅነትዋን ነፍሴ
የሚመሰክርላት እናቴ - ማርያም ብቻ!
14.ከሰው ወገን 'ቤዛዊተ ዓለም' የሚል የጸጋ ስም ያላት -
ማርያም ብቻ!
15.በንጉሱ ቀኝ ቆማ የምትማልድ ንግስት - ማርያም ብቻ!
16.ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን የሚላት - ማርያም ብቻ!
17.አባ ኤፍሬም ያወደሳት፣ አባ ሕርያቆስ ያመሰገናት፣ ቅዱስ ያሬድ የተቀኘላት እመቤት - ማርያም ብቻ!
18.ከሰው ወገን በስጋ ከሞት ተነስታ ያረገች ንጽሕት እናት -
ማርያም ብቻ!
19.የመላእክት እህታቸው፣ የሰማዕታት አክሊላቸው፣ የመነኮሳት መመኪያቸው - ማርያም ብቻ!
20.ዘንዶው በሰው ልብ እንዳትቀረፅ ሊውጣት የሚፈልግ፣
ዘርዋንም ሊዋጋ የሚሻቸው ባለ ሁለት ክንፍ እመቤት - ማርያም ብቻ!
21.ጌታ ከፍጥረት ሁሉ ለይቶ "እናቴ" የሚላት - ማርያም ብቻ!
22.እንደ ማንኛውም ሰው ጸጋ ተካፍሎ ሳይሆን ጸጋ ሞልቶ ያላት የጸጋ ግምጃ ቤት - ማርያም ብቻ!
23.መለኮት ስጋዋንና ነፍስዋን ነስቶ የተዋሐደላት - ማርያም ብቻ!
24.በቤተመቅደስ አድጋ ከመላእክት ጋር እየተጫወተች፣ ሰማያዊ ሕብስትና ጽዋዕ የተመገበች ንጽሕት - ማርያም ብቻ!
25.ከፍጥረት ሁሉ ተለይታ መንግስተ ሰማያትን የወረሰች ብቸኛዋ ወራሽ ንግስት - ማርያም ብቻ! .....♥ ማርያም ብቻ ♥




13/09/2026

እፎይ ጄግናችን

📖 «የጽልመቱ ጥላ» — ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር 📖መምህር እፎይ ለአዲሱ ዓመት ይዞልን የመጣው «የጽልመቱ ጥላ» የሚለው መጽሐፍ ርዕስ፣ በውስጡ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊና ነገረ-መኮታዊ (T...
13/09/2026

📖 «የጽልመቱ ጥላ» — ከመጽሐፍ ቅዱስ እይታ አንጻር 📖

መምህር እፎይ ለአዲሱ ዓመት ይዞልን የመጣው «የጽልመቱ ጥላ» የሚለው መጽሐፍ ርዕስ፣ በውስጡ ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊና ነገረ-መኮታዊ (Theological) ምስጢርን የያዘ ነው።

ለመሆኑ «ጨለማው» ምንድነው? «ጥላውስ» ማንን ያመለክታል? ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያ ሲመረመር የሚከተሉትን ዋና ዋና እውነቶች እናገኛለን፦

1. ጽልመት (ጨለማው) ምንድነው?
በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ «ጨለማ» የተባለው የእውነተኛው አምላክ እውቀት የሌለበት፣ የጣዖት አምልኮ፣ የሐሰት ትምህርት እና የሰይጣን አታላይ አሰራር የነገሰበት መንፈሳዊ ድንቁርና ነው።
👉 «እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም» (1 ዮሐንስ 1:5)
👉 «እኛ ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሙሉ በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።» (1 ዮሐንስ 5:19)

ያለ ምንም መመርመር፣ ጥያቄ ሳይጠይቁና እውነትን ሳይሹ በዕውር ድንብሩ በሐሰተኛ አስተምህሮዎችና በጣዖት አምልኮ ውስጥ መቆየት እውነተኛው መንፈሳዊ ጨለማ ነው።

2. ጥላው (የብርሃን አምላክ ክርስቶስ) ማነው?
በአንጻሩ «ጥላ» የተባለው የጥላዎች ሁሉ ባለቤት፣ የብርሃን አምላክና የእውነት ምንጭ የሆነው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥላ የሚለው ቃል ጥበቃን፣ እውነተኛ ዕረፍትንና መጠጊያን ያመለክታል፦
👉 «በልዑል መሸሸጊያ የሚኖር ሁሉንနိုင် በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ይደደራል።» (መዝሙር 91:1)
👉 ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ፡ «እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም» ብሏል። (ዮሐንስ 8:12)

3. ከጨለማ ወደ ብርሃን የመውጣት ጥሪ
የዚህ መጽሐፍ ዋና ዓላማ ሰዎችን ከጥራዝ ነጠቅና ከዕውር አምልኮ አውጥቶ፣ በእውቀትና በጥያቄ የታገዘ የእውነት መንገድን ማሳየት ነው። እውነተኛ እምነት በዕውር ድንብር የሚከተሉት ሳይሆን የሚመረመርና የሚታወቅ ነው!

👉 «በብርሃን ይመላለሱ ዘንድ የእግዚአብሔርን እውነት መመርመር ይገባል።» (ኤፌሶን 5:8-11)

✨ አዲሱን ዓመት በእውቀት፣ በጥያቄ እና በብርሃኑ አምላክ በእየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ መንገድ እንጀምር! ✨

#ቻለንጀር

Address

No
Awassa

Telephone

+251937826061

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tewahido posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tewahido:

Shortcuts

Share