03/08/2026
በአሶሳ ዞን ኡንዱሉ ወረዳ ዞናዊ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እየተካሄደ ነው
በመርኃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት፦ የቤኒሻንጉል ብሐረሰብ ምክር ቤት አፈ ጉባኤና የዞኑ መስተዳድር ተወካይ አቶ ዑመር አብዱልቃድር እንዳሉት፦ አረንጓዴ አሻራ የጠቅላይ ሚኒስተሩ እንዱ ኢንሸቲቭ መሆኑን ገልጸው።
ዛሬ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ሀሳብ ችግኝ ስንተክል መሪ ቃሉን በመገንዘብ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።
ችግኝ መተከል ብቻውን ግብ አይደለም ያሉት አቶ ዑመር በተለይ ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸውን ጨምሮ እንደ ልጅ ቆጥሮ በመንከባከብ ለፍሬ ለማብቃት ሁሉም በኃላፊነት ስሜት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
የኡንዱሉ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታጀዲን አጀሊ እንዳሉት ፦ በዞኑ መሪነት ዛሬ በኡንዱሉ ወረዳ የችግኝ ተከላ መከናወኑመልካም ዕድል መሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህ ቀደም ላለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች አሁን ላይ ተጨባጭ ውጤት ማስገኘቱንም ተናግረዋል።
በዘንድሮው የአረንጎዴ አሻራ መርኃ ግብር 300 ሺህ በላይ ልዩ ልዩ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ የወረዳው ግብርና ጽህፈት ኃላፊ ሀሊፋ ታጀስር ናቸው
በችግኝ ተከላ መርኃ ግብሩ የዞን የመንግስትና የፀጥታ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎችች በቦታው በመገኘት ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አሳርፈዋል።