12/07/2023
በማህበራዊ ሚዲያ ለሚደርስ የሳይበር ጥቃት አጋላጭ የሚያደርጉ የአጠቃቀም ክፍተቶች
በአለማችን በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ማህበራዊ ሚዲያ በርካታ መልካም አጋጣሚዎችን የማስገኘታቸውን ያህል በአግባቡ ካልተጠቀምን በግለሰብም ሆነ በተቋም ደረጃ የሚያስከትሏች ጉዳቶች በርካታ ናቸው፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ለሚደርስ የሳይበር ጥቃት አጋላጭ ከሚያደርጉን የአጠቃቀም ክፍተቶች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1.ትክክለኛ ወዳልሆነ አገኛኝ መግባት
የማህበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች ላይ መረጃዎችን ከማስባታችን በፊት ትክክለኛ አድራሻ መምረጣችንን ማረጋገጥ፡፡ ለምሳሌ Facebook .com በሚለው አድራሻ ፋንታ facebooke .com የሚሉ ሀሰተኛ አድራሻዎችን ልንጠቀም ስለምንችል ጥንቃቄ ማድረግ፡፡
2.ያልዘመነ (update) ባለሆነ መቃኛ (browser) መጠቀም
የኢንተርኔት መጠቀሚያና መቃኛዎችን (browser) በአግባቡ ማዘመንያስፈልጋል፤ ምክንያቱም ያልዘመኑ መተግበሪያዎችና መቃኛዎች ለጥቃት አጋላጭ ስለሆኑ፡፡
3.ደካማ የይለፍ ቃል አጠቃቀም ባህል
• እጅግ ተገማች የይለፍ ቃልን መጠቀም፤
• ለበርካታ አካውንቶች ተመሳሳይ የይለፍ ቃል መጠቀም፤
• የይለፍ ቃልን ለሌሎች አሳልፎ መስጠት፤
4.የማይታወቁ አባሪዎችን (Attachments) ወይም ማስፈንጠሪያዎ (Links) መክፈት
• የምንከፍታቸውን ሊንኮች ትክክለኛ አድራሻ ማወቅ፤
• የምንከፍታቸውን አባሪዎች ትክክለኛ የፋይል ፎርማት እንዳላቸው ማረጋገጥ ፤
• ቫይረሶችና ሌሎች አጥቂ ፕሮግራሞች ከአባሪዎች ጋር ሊመጡ ስለሚችሉ ጥንቃቄ ማድረግ ፤
5.መረጃዎችን በወረቀት ጽፎ መያዝና በአግባቡ አለማስወገድ
• የይለፍ ቃሎችን (pass word ) በወረቀት መዝግቦ መያዝ ፤
• በወረቀት የፃፍነውን መረጃ በሚገባ አለማስወገድ፤
6. አካውንታችንን ዘግተን አለመውጣት (logout) አለማድረግ
• አካውንታችንን ተጠቅመን ስንወጣ አለመዝጋት ለጥቃት ተጋላጭ ያደርጋል ፤
• በሌሎች ሰዎች መጠቀሚያ ተጠቅመን ስንጨርስ (log out ) አለማድረግ፤
7. በሌሎች እይታ ውስጥ ሆኖ የይለፍ ቃልን ማስገባት (shoulder surfing)
• የይለፍ ቃል ስናስገባ አካባቢያችንን መቃኘት ያስፈልጋል፤ ባጠቃላይ ሌሎችም የማህበራዊ ሚዲያ ደህንነት አጋላጭ የአጠቃቀም ባህሎች በመሆናቸው ጥንቃቄ ልንወስድ ይገባል ፡፡