እልፍኝ - Elefgn

እልፍኝ - Elefgn All About Technology, gadgets, Apps Store, Andriod, IOS, Games, Media,Fun, Pictures and News Not a dry conventional Tech Blog.

We are fascinated by technology and visualize technology in broader perspective. We roam around the thin boundaries of Nature, Animals, Designs, Art, Information Technology and space to identify and point out the intersections which evolve Technology!! This page is not for people who visualize technology as mobile devices and gadgets. Please do not spam and be relevant to posts. Spamming and irrelevant links will result in permanent ban....

01/12/2024

እናትነት ❤

ለልጆች እና ለአዋቂዎች የሚሆን ቆንጆ ታብሌት አስገብተናል። #ለማንበቢያነት እጂግ የሚመረጥ ሲሆን storage =512Gb Ram =8Gb ሲሆን በበቂ ሁኔታ ይጠቀሙበታል። #በውስጡ አብረው የተ...
27/10/2024

ለልጆች እና ለአዋቂዎች የሚሆን ቆንጆ ታብሌት አስገብተናል።

#ለማንበቢያነት እጂግ የሚመረጥ ሲሆን
storage =512Gb Ram =8Gb ሲሆን በበቂ ሁኔታ ይጠቀሙበታል።

#በውስጡ አብረው የተካተቱት እቃዎች 💤👇

✅power bank
✅ airpad
✅watch
✅keyboard
✅mouse
✅speaker
✅pen
Price=15,500 birr

ይደውሉልን:- 0977778844

ፌስቡክ በስህተት የላክነውን መልእክት በ10 ደቂቃ ውስጥ ለማጥፋት የሚያስችል አገልግሎት ይፋ አደረገ-------------------ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ ሁሉም የፌስቡክ ሜሴንጀር ተጠቃሚዎች...
06/02/2019

ፌስቡክ በስህተት የላክነውን መልእክት በ10 ደቂቃ ውስጥ ለማጥፋት የሚያስችል አገልግሎት ይፋ አደረገ
-------------------
ከትናንትናው ዕለት ጀምሮ ሁሉም የፌስቡክ ሜሴንጀር ተጠቃሚዎች “Remove For Everyone” የሚል አማራጭ ያገኛሉ የተባለ ሲሆን፥ ይህም አንዴ የላክነውን መልዕክት መልሶ ለማጥፋት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

የመልዕክት ማጥፊያ አማራጩን በመጠቀምም ለግለሰብ አሊያም ለቡድን ቻት የላክናቸውን መልዕክቶች ማጥፋት እንችላለን ተብሏል።

አንድ ጊዜ የተላከን መልዕክት መልሶ ለማጥፋትም 10 ደቂቃ የተሰጠ ሲሆን፥ ከዚያ ካለፈ ግን ማጥፋት እንደማይቻል ተነግሯል።

በጠፋው መልዕክት ስፍራም ለላክንለት ሰው መልዕክቱን ማጥፋታችንን የሚያሳይ መልዕክት ይደርሰዋልም ነው ያለው ኩባንያው።

እንደ ፌስቡክ ገለጻ አዲሱ አገልግሎት በተለይም ከዚህ ቀደም ሰዎች በስህተት የላኩትን መልዕከት ለማጥፋት የሚያጋጥማቸውን ችግር የሚቀርፍ ነው።

ፌስቡክ አዲሱን አገልግሎት ካሳለፍነው ጥቅምት ወር ጀምሮ ሙከራ ሲያደርግበት ነበር የተባለ ሲሆን፥ በአሁኑ ጊዜም በፖላንድ፣ ቦሎቪያ፣ ኮሎምቢያ እና ሊቲኒያን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት ጥቅም ላይ መዋል ጀምሯል።
----------------------
ምንጭ፦ www.cnet.com

ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች1. የሀርድዌር መቃረንለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware  መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware...
26/12/2018

ኮምፒዉተር የሚዘጋበት ወይም ክራሽ የሚያደርግበት 5 ምክንያቶች

1. የሀርድዌር መቃረን
ለ Windows ክራሽ የማድረግ ዋነኛው ምክንያት የ Hardware መቃረን ነው፡፡እያንዳንዱ Hardware ክፍሎች ለመግባባት IRQ(interrupt request channel) ያስፈልጋቸዋል፡፡ እነዚህ IRQ ለየሀርድዌሩ የተለዩ ወይም የተነጠሉ መሆን አለባቸው፡፡ ለምሳሌ አንድ ፕሪንተር IRQ 7 ሲኖረው ኪቦርድ ደግሞ IRQ 1፡፡እያንዳንዱ ሀርድዌር የራሱ የሆን IRQ ለመያዝ ጥረት ያደርጋል፡፡ ግን ብዙ የሀርድዌር እቃዎች ስንጠቀም ወይም የሀርድዌሩ ሶፍትዌር በስርዓት ካልተጫነ ሁለት ሀርድዌሮች ተመሳሳይ IRQ ሊጋሩ ይችላሉ፡፡ በዚህም ሰዓት ሁለት የሀርድዌር ዕቃዎች በተመሳሳይ ሰዓት ለመጠቀም ስንሞክር ክራሽ ሊከሰት ይችላል፡፡

2. የተበላሸ ራም

ራም Ram (random-access memory) ችግሮች ዋናው የብሉ እስክሪን ኦፍ ዴዝ (blue screen of death) ዋና መንስኤ ሲሆን የሚያሳየው መልእክት ፋታል ኤክሰብሽን ኢረር( Fatal Exception Error) የሚል ነው፡፡ ፋታል ኢረር የሚነግረን አሳሳቢ የሀርድዌር ችግር አለ ማለት ነው፡፡ አንዳንዴ የሀርድዌር ክፍል ስለተጎዳ መቀየር እንዳለበት ይናገራል፡፡ በራም የሚመጡ ችግሮች ብዙ ግዜ የራሙ ከኮምፒዉተሩ ጋር ሳይጣጣም ሲቀር ነው፡፡ ይህም ማለት ለኮምፒዉተር የራም ስሎት ጋር ሳይመጣጠን ሲቀር ፤ የራሱ ያልሆነ ሞዴል ስንጠቀም እና የተለያየ አይነት ራም በአንድ Computer ውስጥ ስንጠቀም ነው፡፡ለምሳሌ 70ns ለይ 60ns ራም ስንጠቀም ኮምፒተሩን ፍጥነት ይቀንሳል፡፡ይሄ ደግሞ ራሙን ከአቅሙ በላይ ይጫነዋል በዚህ ግዜ window ክራሽ ያደርጋል፡፡

3. ባዮስ ሴቲንግ( BIOS settings)

እያንዳንዱ ማዘር ቦርድ ሲመረት የራሱ የሆነ የተለያዩ ቺፕሴት ሴቲንግ አብሮት ይጫናል፡፡ እነዚህን ሴቲንግ ለመጠቀም በኮምፒውተራችን ኪቦርድ ላይ F2 ወይም F10 (እንደ ኮምፒዉተሩ ይለያያል) ኮምፒዉተሩ ስንከፍት ከጥቂት ሰከንድ በኻላ በመንካት ሴቲንጉን አክሰስ ማድረግ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዴ ባዮስ ዉስጥ ከገባን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ማንኛውንም ሴቲንግ ከመቀየራችን በፊት ፎቶ ወይም ወረቀት ለይ ሴቲንጎቹን ማኖር አንድ ያበላሸነው ነገር ካለ በቀላሉ መቀየር ያስችለናል፡፡ብዙን ግዜ የባዮስ ችግር የራም ላተንሲ ችግር ነው፡፡ የድሮ ኮምፒዉተር ራም ላተንሲ 3 ሲሆን የቅርብ ግዜ ራሞች ደግሞ ላተንሲ 2 ናቸው፡፡ ይሄንን ሴቲንግ በምንቀይርበት ጊዜ ኮምፒዉተሩ ክራሽ ያደርጋል ወይም ፍሪዝ ይሆናል፡፡

4. ቫይረስ
ቫይረሶች የኮምፒዉተር ፕሮግራም ሲሆኑ እራሳችውን በማብዝት ወይም ኮምፒዉተር ፋይሎች ላይ በማጣበቅ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡ ቫይረሶች የትእዛዞች ስብስብ ሆኖ እራሱን በሌላ የኮምፒዉተር ፕሮግራም ያጣብቃሉ(ብዙ ግዜ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን)፡፡ ኮምፒዉተራችን ውስጥ ቫይረስ ሲያጠቃ የኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ፋይል የመቀየር ሀይል ስላለው ኮምፒዉተሩን ክራሽ ወይም ፍሪዚ ሊያረግ ይችላል፡፡

5. መጋል
በኮምፒዉተራችን ዉስጥ ካሉ ሀርድዌሮች በጣም አስፈላጊው እና ዋናው ሲፒዩ ነው፡፡ ሲፒዩ በኤሌትሪክ ሃይል የሚሰራ ሲሆን ካለው ውስብስብ የትራዚስተር ብዛት አማካኝነት የሚፈጥረው ከፍተኛ ሙቀት ሲፒዩን ሊያበላሸው ወይም ከጥቅም ውጪ ሊያደርገው ይችላል፡፡ ሲፒዩ ብዙ ጊዜ ከማቀዝቀዣ ቬንትሌተር ከኮምፒዉተራችን አንድ ላይ ይመጣል፡፡ እነዚህ ቬንትሌተር ከተበላሹ ወይም ሲፒዩ ካረጀ የኮምፒዉተራችን ሲፒዩ መጋል ይጀምራል፡፡ ይህ ደግሞ በኮምፒዉተራችን ላይ የከርንል ኢረር ያስከትላል፡፡ ይሄ ችግር ብዙ ጊዜ የሚታየው በኦቩር ክሎኪንግ ጊዜ ነው፡፡ ይህ ማለት ሲፒዩን ከሚገባው በላይ በማሰራት ወይም ከፍተኛ ፍጥነት እንዲገባ በማድረግ ነው፡፡ሲፒዩ በጣም ሲግል ኮምፒዉተራችን ሳናስበው እራሱን ይዘጋል ወይም ክራሽ ያደርጋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮምኢትዮ ቴሌኮም እንደ  #ዋትሳፕ፣ ሚሴንጀር፣ ቫይበር፣ ኢሞ፣ ዊቻትና ቴሌግራም አይነት  መሰል ማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ልዩ ታሪፍ ከማውጣት እስከ መዝጋት የሚያስችለውን የቴክኖሎጅ...
26/12/2018

ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም እንደ #ዋትሳፕ፣ ሚሴንጀር፣ ቫይበር፣ ኢሞ፣ ዊቻትና ቴሌግራም አይነት መሰል ማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ልዩ ታሪፍ ከማውጣት እስከ መዝጋት የሚያስችለውን የቴክኖሎጅ መሳሪያ ግዥ መፈፀሙን ዋዜማ ራዲዮ ጉዳዩን ከሚያውቁ ምንጮች አረጋግጧል።
-----------------
ራድዮ ጣቢያው እንዳሰባሰብነው መረጃ ፣ ኢትዮ ቴሌ ኮም እንደ ዋትሳፕ፣ ሚሴንጀር፣ ቫይበር፣ ኢሞ፣ ዊቻትና ቴሌግራም አይነት የኢንተርኔት መገናኛዎች አጠቃቀም ላይ የተለየ ታሪፍ ለመጣልና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ እነዚህ መተግበሪያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ አገልግሎት ላይ እንዳይውሉ #ለመዝጋት የሚያስችለውን የቴሌ ኮም ሲስተም ለመዘርጋት ያሰበው ከሁለት አመት በፊት ጀምሮ ነበር። ሆኖም በወቅቱ ባጋጠመው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ከመሳርያው አቅራቢ ኩባንያ ጋር ተነጋግሮ ቢጨርስም ግዥው ዘግይቷል።

አሁን ግን ኩባንያው የውጭ ምንዛሬ በማግኘቱ ግዥውን ፈጽሟል። የማህበራዊ ሚዲያዎቹን መተግበሪያ ከታሪፍ ጀምሮ ለመቆጣጠር የሚያስችለው መሳርያ ወይንም ስርአት ; policy charging rule function and traffic detection function, pcrf/tdf ; የሚባል ሲሆን አቅራቢው ደግሞ ዋና መቀመጫውን ጀርመን ያደረገ ባይት የተባለ ኩባንያ ነው።

ኢትዮ ቴሌኮም በዋነኝነት ይሄንን የቁጥጥር ስርአት ለመዘርጋት የፈለገው ከአለማቀፍ ጥሪ ያገኘው የነበረው ገቢ በቢሊየን ብሮች እየቀነሰበት በመምጣቱ ነው። እንደ ዋትሳፕ :ቫይበርና ሚሴንጀር አይነት መተግበሪያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በሰፊው ጥቅም ላይ መዋል ከጀመሩ በሁዋላ ዜጎች በቀላሉ ውጭ ሀገር ካሉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ወይንም የስራ አጋሮቻቸው ጋር መገናኘት ችለዋል። ይህም የቴሌን መደበኛ አገልግሎት ለአለማቀፍ ጥሪ የሚጠቀሙ ደንበኞችን በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶታል።

እንደ ዋትሳፕ ያሉ መተግበሪያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቅም ላይ ሲውሉ ኢትዮ ቴሌኮም የሰራቸውን መሰረተ ልማቶች ተጠቅመው ነው የሚሰሩት። በዚህም በተለያየ ሀገር እንደታየው የመተግበሪያዎቹ ባለቤቶች ገንዘባቸውን በተለያየ መልኩ ያገኙታል። ኢትዮ ቴሌ ኮም ከዚህ የሚያገኘው ታድያ የመተግበሪያዎቹ ተጠቃሚዎች ኢንተርኔት ኮኔክሽን/አገልግሎት ስለከፈቱ ብቻ ነው። ይሄ ደግሞ መተግበሪያዎቹ የአለማቀፍ ጥሪ ገቢዬንም ቀንሰው የሰራሁትን መሰረተልማት ተጠቅመውም የሚገባኝን ጥቅም እንዳላገኝ አድርገውኛል ብሎ ኩባንያው አስቧል።

ስለዚህም በምጽሀረ ቃሉ pcrf/tdf የተባለው ስርአት የማህበራዊ ሚዲያ የድምፅና የፅሁፍ አገልግሎት መተግበሪያዎችን የተለየ የአገልግሎት አከፋፈል ስርአት /special tariff zone/ ውስጥ እየጨመረ ከኢንተርኔት ኮኔክሽን ባሻገር የተወሰነ ክፍያ እንዲጠየቁ እንደሚያደርግ ከኩባንያዎቹ ምንጮቻችን ሰምተናል።

ስርአቱ መተግበሪያዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሰሩ የማድረግ አቅምንም ለኢትዮ ቴሌ ኮም ይፈጥርለታል።ሀገራት እንደዋትሳፕ ያሉ መተግበሪያዎች በተመሳሳይ ስርአት ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች መነሻነት በግዛታቸው ውስጥ እንዳይሰሩ ሲያደረጉ ታይቷል።የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን የማድረግ አላማ ይኑረው አይኑረው ለጊዜው ያገኘነው መረጃ የለም።

pcrf/tdf የተባለውን ስርአት በኢትዮጵያ የቴሌ ኮም ሲስተም ውስጥ ለመዘርጋት ከ10 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወጭ በማድረግ ግዥ መፈጸሙንም ዋዜማ ራዲዮ ከምንጮቿ መረዳት ችላለች።

በሌላ በኩል የቁጥጥር ስርአቱ የኢንተርኔት አቅርቦትን እንደተጠቃሚዎች የሚጠቀሙበት ዘርፍ አስፈላጊት ፍጥነት ለመገደብ ያስችለኛል ብሏል የቴሌኮም ኩባንያው።

እንዲሁም ኩባንያው መቆጣጠር ያቃተውን በውጭ ሀገር ያሉ ሰዎች በኢትዮጵያ ቁጥር እየተጠቀሙ ሀገር ውስጥ የሚደውሉበትን የቴሌኮም ማጭበርበርን በተሻለ መልኩ ለመቆጣጠር እንደሚያስችለው አምኗል። ኩባንያው በዚህ ማጭበርበር ብዙ ገቢ እያጣ መሆኑን ሲናገር ቆይቷል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ

..."'በኔ ብቻ' በሽታ - ጥበት እየቀጣን፣በ'ናታችን ርስት፣ ባባታችን መሬት፣ መደገፊያ እያጣን፤ቁልቁል እያሰቡ - ምንድነው ከፍታ፣መብት እየነጠቁ - ምንድነው ግዴታ?እስከ መቼ ተረት - ግ...
26/12/2018

...
"'በኔ ብቻ' በሽታ - ጥበት እየቀጣን፣
በ'ናታችን ርስት፣ ባባታችን መሬት፣ መደገፊያ እያጣን፤
ቁልቁል እያሰቡ - ምንድነው ከፍታ፣
መብት እየነጠቁ - ምንድነው ግዴታ?
እስከ መቼ ተረት - ግዴለም ይነጋል፣
መንገድ እየቀሙ - ምርኩዝ ምን ያደርጋል?"..
#ህሊና

የAndroid ሚስጢራዊ ኮዶች🗝-----------1) Phone information code: * #* #4636 #* #*2) Factor data reset code: * #* #7780 #* #*3) F...
29/11/2018

የAndroid ሚስጢራዊ ኮዶች🗝
-----------
1) Phone information code: * #* #4636 #* #*

2) Factor data reset code: * #* #7780 #* #*

3) Format android phone code:*2767*3855 #

4) Phone camera update code:* #* #34971539 #* #*
-Update camera firmware in image
-Update camera firmware in SD card
-Camera firmware version
-Firmware update count

5) End call power
code:* #* #7594 #* #*
6) File copy for creating backup code:* #* #273283*255*663282* #* #

7) Service mode code:* #* #197328640 #* #*
* #* #232338 #* #* show Wi-Fi Mac address
* #* #1472365 #* #* GPS test
* #* #1575 #* #* another GPS test
* #* #232337 #* #* show Bluetooth device
* #* #232331 #* #* bluetooth test
√ Firmware version information code:
* #* #4986*2650468 #* #*
* #* #1234* #* # PDA and phone
* #* #1111 #* #* FTA SW version
* #* #2222 #* #* FTA HW version
√ Code to launch various factory test
* #* #0283 #* #* packet loop back
* #* #*0* #* #* LED test
* #* #0673 #* #* or * #* #0283 #* #* melody test
* #* #0842 #* #* Device test (vibration and backlight test)
* #* #2663 #* #* Touch screen version
* #* #2664 #* #* Touch screen test
* #* #0588 #* #* Proximity sensor test
* #* #3264 #* #* RAM information

 ---------------- በዛሬው ፕሮግራማችን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች  ሎጎዎችን ትርጉም እንዲሁም ከዛም ወጣ ብለን የ አንዳንድ ታዋቂ ካምፓኒዎችን ሎጎ  ትርጓሜ በጥቂቱ እናያለን።...
29/11/2018


----------------
በዛሬው ፕሮግራማችን የተለያዩ የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች ሎጎዎችን ትርጉም እንዲሁም ከዛም ወጣ ብለን የ አንዳንድ ታዋቂ ካምፓኒዎችን ሎጎ ትርጓሜ በጥቂቱ እናያለን።

1. Apple
የ computer science አባት ተብሎ የሚጠራው Alen Turing በ ሁለተኛው የ አለም ጦርነት ወቅት enigma code (በሌላ ፕሮግራም እንመለስበታለን) በመባል የሚታወቀውን የ German military command የሚስጥር ኮድ በመስበር ሚሊየኖችን ከሞት ለመታደግ ችሏል ነገር ግን ለደህንነት ስጋት ነው ተብሎ ስለታሰበ በ cyanide የተለወሰ apple በመስጠት አንዴ ከመጉመጡ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በዚህም ምክንያት Apple ካምፓኒ እሱን ለመዘከር ሎጎው አድርጎታል።

2. Amazon

የ online መገበያያ የሆነው አማዞን ሎጎ አይታቹት ከሆነ ከ A ተነስቶ እስከ Z ድረስ የሚሄድ ቀስት አለው። ይሄም የሚያሳየው ምንም ነገር አማዞን ላይ ተፈልጎ እንደማይታጣ ሲሆን ፤ Amazonየሚለው ስም ደሞ ከ አለማችን ትልቁ ደን እና ወንዝ ከሆነው ከብራዚሉ Amazon የተወሰደ ሲሆን የድርጅቱን ግዝፈት ለመግለጽ የተጠቀሙበት ነው።

3. Nike known as " SWOOSH "

የ ራይት ምልክት በ ግሪክ አፈታሪክ ውስጥ የ እንቅስቃሴ ፣ የመብረር ፣ የ ድል እና የፍጥነት ምልክትን ነው። የተወሰኑት እንደሚያስቡት የ check mark ምልክት አይደለም። ናይክም ይሄን ለመግለጽ ነው ምልክቱ ያደረገው።

4. Facebook

የፌስቡክ ምልክት small capital " f " ነው። ይሄም ፌስቡክ የሚለውን የሚገልጽ መሆኑን ብዙዎቹ ያምናሉ ነገር ግን ከዚህ በተጨማሪም ሰው አጎንብሶ ሲጠቀም ያሳያል የሚል መላምንትም አለ። ሰማያዊ የሆነው ደሞ ከዚህ በፊት ስለ ፌስቡክ እውነታዎች እንደነገርናቹ የ fb ፈጣሪ የሆነው zuckerberg color blindness ስለሆነ ነው።

5. IBM

የተለያዩ የ electronics ምርቶችን የሚያመርተው international business machine IBM ሎጎው ላይ ያለው ነጫጭ ወደ ጎን የተሰመሩ መስመሮች የሚያመለክተው ከምንም በፊት እኩልነት ይቅደም የሚለውን ነው።

Lecture 4 C++ Programming Identifiers, Variables, Datatypes in Amharic በአማርኛ---------------------
25/11/2018

Lecture 4 C++ Programming Identifiers, Variables, Datatypes in Amharic በአማርኛ
---------------------

Lecture 3 This is to strengthen C++ Hello World Program in Amharic በአማርኛ---------------
25/11/2018

Lecture 3 This is to strengthen C++ Hello World Program in Amharic በአማርኛ
---------------

Lecture 2 C++ Hello World in Amharic----------------
25/11/2018

Lecture 2 C++ Hello World in Amharic
----------------

Address

Ethiopia
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እልፍኝ - Elefgn posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share