Hageregna-ሀገረኛ Hub

Hageregna-ሀገረኛ Hub Hageregna hub provides tips and tricks of new technologies that related to computer and mobile system throughout the world.

EBC-መዝናኛ Ethiopian Broadcasting Corporation   ,
08/01/2026

EBC-መዝናኛ Ethiopian Broadcasting Corporation ,

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

17/07/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Suffa Buzinesh, Destawu Des

17/07/2025

እመንገድ ላይ አየኋት ። ወፍራለች ፣ ጡቷ እንድድሮው አይደለም ። ቦርጫም ሆናለች፣ ትልቅዬ የጭቃ መከላከያ ጫማ ተጫምታለች

ልጅ አቅፋለች ። ብዙ አመት አብረን ተንዘላዝለን ተጨቃጭቀን ..
ተዋደን ...
ተዳርተን...
ተማምተን፣ ተሳስበን ሙሉ ቀን ተጠፋፍተን ምነው የት ጠፋህ የት ጠፋሽ ተባብለናል ። ተለያየን ብለን ታርቀናል ፣ተበዳድለን ይቅርታ ተባብለናል

ትክዝ አልኩ ፦

ልጅነቷ ውስጥ ልጅነቴ ነበር። ጠረኗ ውስጥ ትዝታዬ ተወሽቋል ። እንድተለያየን ሁለት ወር ሳንቆይ ከኔ ጋ እያለች ከሚጀነጅናት ጋ መሰለኝ
አብራው መኖር ጀመረች አራት ወር እንደቆዩ ተለያዩ ሲጣሉ አርግዛ ነበር መሰለኝ ብዙ ሳትቆይ ወለደች ልጁም የሱ ነው ተባለ ።

ምን አለ ልጁ የኔ ቢሆን ...!

አባትህ እንዲ መጥቶ፣ ሰርቶ ፣ሄዶ ፣በድሎኝ፣ ጠቅሞኝ፣ ገለመሌ እንዲ ሆነን ተጣብሰን ተዋደን ብዙ ግዜ ቆይተን ገለመሌ ትላለች

እኔም የልጄ እናት እንዲ አድርጋ እንዲ ሄደን፣ ወጥተን ወርደን እንዲ አቶድም እሷ እንዲ ናት እያልኩ ለልጄ እነግረው ነበር ።

ምን አለ እኔጋ እያለች ሙሉ እንድሆንላት ተመስጣ ባትደምር ባትቀንስ ፣ ምናለ እኔስ ባልፈለሳሰፍ ዝም ብዬ ገፋፍቼ አታልዬ አስርግዣት ቢሆን ።

ህፃን ልጅ አቅፋ ጎስቁል ብላ ልጅነቷን በልጇ ተሸሽጋ እየሸኘችው ነው ።

ውዱን ጊዜያችንን አብረን ነበርን ። ምን አለ ያቀፈችው ልጅ ከኔ ቢሆን፣ ምን አለ ያረገብኩት ጡቷ በኔ ልጅ ምክንያት ቢወድቅ ።

ልጇ እሷን አይመስልም። ምን አለበት ሌላው ይቅር ልጆ እሷን ቢመስል ።
ውድድ ...ሳምምም... እቅፍፍ ...ባደርገው ።

አብሮነታችን ምንም ቋሚ የሚናገር ነገር ሳይገነባ አለፈ ።

እሷ ግን ታድላ መኖርያ ምክንያት አገኘች ።

በድርበቡ ሰላም ብያት ልጆን እጁን ስሜው አይን አይኖን እያየሁ ከላይ ከላይ ካወራን ቀጥሎ

"ለኔም ውለጂልኝ" አልኳት ሳቀች ሳቋ ውስጥ ልጅነቷ ወጣ ፣

በማርያም.... እ....?🙏

ስለት አሳዘንኳት መሰለኝ ፊቷ ቅር አለው፣ "በዚህ ልጅ የበላውት ፍዳ ብታቅልኝ ኖሮ.... "አለች

መንገዷ አባጣ ጎርባጣ እንደነበረው ብዙ ነገሯ ይናገራል

ግዴለም ሁን ያለው ነው የሚሆንው ።እኔም ስንት መከራ ሳይገለኝ ምሮኛል ፣ሰንት ሞት አምልጫለሁ

መጥፎ ነገር ብቻ የሚያልፈኝ በእውነቱ እኔ ማነኝ?!

ባይልልን ነው !
© Adhanom Mitiku

ህዝቤ ሆይ ደመወዝህን አብቃቅተህ ተጠቀም ተብለሀል
11/05/2025

ህዝቤ ሆይ ደመወዝህን አብቃቅተህ ተጠቀም ተብለሀል

ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ መነሻው፣ ምልክቶቹ እና ህክምናው_____▪ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ምን ማለት ነዉ?ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ በረጅም ዓመታት ቀስ እያለ ኩላሊታችንን እየጎዳ ...
06/05/2025

ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ መነሻው፣ ምልክቶቹ እና ህክምናው
_____

▪ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ ምን ማለት ነዉ?

ስር የሰደደ የኩላሊት በሽታ በረጅም ዓመታት ቀስ እያለ ኩላሊታችንን እየጎዳ ከጥቅም ውጪ የሚያደርግ በሽታ ነው። ከግዜ በኋላ የታማሚው ኩላሊት ሙሉ በሙሉ ስራ ያቆማል። የኩላሊት በሽታ በማህበረሰቡ የተንሰራፋ በሽታ ሲሆን ስር እስኪሰድ ድረስ ለረጅም ግዜ ሳይታወቅ ኩላሊታችንን የሚያጠቃ በሽታ ነው።

▪ስር የሰደደ የኩላሊት ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

• የደም ማነስ
• ደም የተቀላቀለበት ሽንት
•የጠቆረ ሽንት
• ንቁ አለመሆን
• የሽንት መጠን መቀነስ
• የእግር፣ የእጅ እና የቁርጭምጭሚት ማበጥ
• የድካም ስሜት
• የደም ግፊት
• እንቅልፍ እጦት
• የሚያሳክክ ቆዳ
• የምግብ ፍላጎት መጥፋት
• በሌሊት ቶሎ ቶሎ ለሽንት መመላለስ
• የትንፋሽ እጥረት
• ሽንት ላይ ፕሮቲን መገኘት
• በፍጥነት የሚቀያየር የሰውነት ክብደት
•ራስ ምታት ዋና ዋና ዎቹ ናቸው።

ለኩላሊት በሽታ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በየግዜው የኩላሊታቸውን ጤንነት እየተመረመሩ ማረጋገጥ አለባቸው። በሽታው እንዳለብን በግዜ በማወቅ እራሳችንን ከከባድ የኩላሊት ጉዳት ማዳን እንችላለን።

▪የኩላሊት በሽታ ህክምናው

ስር የሰደደ ኩላሊት በሽታ ያላቸው ሰዎች የተለያዩ መድሃኒቶችን መውሰድ ይገባቸዋል። የተለያዩ ህክምናዎች በሽታውን ለመቆጣጠር አገልግሎት ላይ ይውላሉ።
የደም ማነስ፣ ፎስፌት ባላንስ እንዲሁም የደም ግፊት መድሃኒት በሃኪም ምርመራ ከተደረገ በኋላ መድሃኒት መውሰድ ይኖርብናል።

▪ የመጨረሻ ደረጃ ህክምናዎች

ኩላሊት አቅሙ ተሟጦ በ10-15 ፐርሰንት ደረጃ መስራት ሲጀምር ከላይ የተዘረዘሩት ህክምናዎች ብቻቸውን በቂ አይሆኑም። የመጨረሻ የኩላሊት ደረጃ የደረሱ ታካሚዎች ሰውነታቸው ውስጥ የሚከማቸውን ቆሻሻ እና ፈሳሽ ያለ እገዛ መቋቋም አይችሉም። ታካሚው በህይወት ለመኖር የኩላሊት እጥበት/dialysis/ ያስፈልገዋል።

ኩላሊት መጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሶ አስፈላጊ ካልሆነ ሀኪሞች ዳያሊሲስ እና ንቅለ-ተከላን ለማድረግ አይመርጡም። እነዚህ ህክምናዎች በኢንፌክሽን ምክንያት መወሳሰብ ሊፈጥሩ ይችላሉ።

▪የኩላሊት እጥበት /dialysis/ ህክምና

ዳያሊሲስ በማሽን የሚደረግ የሰውነት ቆሻሻን ማጥራት ስራ ነው። ሁለት አይነት የዳያሊሲስ አይነት አለ፣ አንደኛው ሂሞዳያሊሲስ ነው። ይህ የዳያሊሲስ አይነት ደም ከሰውነታችን ፓምፕ እየተደረገ በማሽን ውስጥ አልፎ እየተጣራ እንዲገባ የሚደረግበት ህክምና ነው። 3 ሰአት የሚፈጅ ህክምና ሲሆን ህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህን ህክምና በተደጋጋሚ ማድረግ ለታካሚው ጤና ጥሩ ነው።

ሌላኛው የዳያሊሲስ አይነት ፔሪቶኒያል ዳያሊሲስ ሲሆን የታካሚው ደም በራሱ ሆድ ውስጥ እንዲጣራ ይደረጋል። ሆድ ውስጥ በሚገባ ካቴተር ውስጥ የዳያሊሲስ ውህድ በመጨመር ቆሻሻ እና ፍሳሽ እንዲወጣ ይደረጋል።

▪ኩላሊት ንቅለ-ተከላ

ከኩላሊት መስራት ማቆም በቀር ሌላ ኩላሊትን የሚጎዳ በሽታ ለሌላቸው ታካሚዎች ኩላሊት ንቅለ-ተከላ ከዳያሊሲስ የተሻለ አማራጭ ነው። ቢሆንም ግን ንቅለ-ተከላ ከማድረጋቸው በፊት ታካሚዎች የዳያሊሲስ ማሽን እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

ኩላሊት ለጋሹ እና ተቀባዩ ተመሳሳይ የደም አይነት፣ የሴል ሰርፌስ ፕሮቲን እና አንቲቦዲ ሊኖራቸው ይገባል። ካልሆነ የተቀባዩ ሰውነት ኩላሊቱን ላይቀበለው ይችላል። ብዙ ግዜ የዘመድ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች የተሻለ ለጋሽ ይሆናሉ።

ክብርት ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ ከሚያዝያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ተሹመዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሰሃረላ

 የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2026 አሸናፊዎች ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ/ም ይፋ ይደረጋሉ።ለዲቪ (Diversity Visa) 2026 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram...
30/04/2025



የአሜሪካ ዲቪ ሎተሪ (Diversity Visa) 2026 አሸናፊዎች ቅዳሜ ሚያዚያ 25/2017 ዓ/ም ይፋ ይደረጋሉ።

ለዲቪ (Diversity Visa) 2026 ማመልከቻ የሞሉ በ dvprogram.state.gov ብቻ የማረጋገጫ ቁጥራቸውን በማስገባት ውጤቱን ወይም ማሸነፍ አለማሸነፋቸውን መመልከት ይችላሉ።

NB. የማረጋገጫ ቁጥር ማመልከቻው ሲሞላ የተሰጠ ነው። ይህ ቁጥር የጠፋበት Forgot Confirmation Number በማለት አስፈለጊ መረጃ በመሙላት በኢሜል አዲስ ቁጥር ማግኘት ይቻላል።

ለ2026 የፊስካል ዓመት እስከ 55,000 የሚደርስ የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ተዘጋጅቷል። ይህ ቁጥር ብቁ የሆኑ ሀገራትን ሁሉ የሚጠቃልል ሲሆን #ኢትዮጵያም አንዷ ናት።

የዲቪ ሎተሪ መውጫ መድረሱን ተከትሎ " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል ፣ ከአሜሪካ ኤምባሲ ነው ምንደውለው / ይህን ኢሜል / ቴክስት የምንልከው " በማለት የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች ሊጠነቀቁ ይገባል።

አንድ አመልካች ዲቪ 2026 ደርሶት እንደሆነ እና እንዳልሆነ ማወቅ የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ከላይ የተጠቀሰው ድረገጽ ብቻ ነው።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ (ኢትዮጵያ ጨምሮ) ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 55 ሺህ ሰዎችን በዲቪ (DV) ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።
አዲስ አበባ

27/04/2025

“የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል። ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ፤ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ተኩል ዝናብ አልዘነበም። እንደ ገናም ጸለየ፤ ዝናብም ከሰማይ ዘነበ፤ ምድርም ፍሬዋን ሰጠች።”
‭‭ያዕቆብ‬ ‭5‬:‭16‬-‭18‬ ‭

This is how women think 🤔🤩🤩
27/04/2025

This is how women think 🤔🤩🤩

21/02/2025

ይደውሉልን 0964686617

 #ምላስ የሰው ምላስ በአጉሊ መነጽር  ሲታይ ይህን ይመስላል ወጣ ብለው ሚታዩት  ነገሮች(taste bud) ጣእም ሚለዩልን ህዋሶች ናቸው👅 የሰው ምላስ ጣፋጭ፣ጎምዛዛ ፣ ጨዋማ እና መራራ ምግ...
02/10/2024

#ምላስ
የሰው ምላስ በአጉሊ መነጽር ሲታይ ይህን ይመስላል ወጣ ብለው ሚታዩት ነገሮች(taste bud) ጣእም ሚለዩልን ህዋሶች ናቸው👅
የሰው ምላስ ጣፋጭ፣ጎምዛዛ ፣ ጨዋማ እና መራራ ምግቦችን የመለየት ኃላፊነት ያላቸው ከ2,000 እስከ 8,000 የሚደርሱ የጣዕም መለያ taste bud ይዟል።
እያንዳንዱ ሰው ከሌላው የሚለይ #ልዩ የምላስ #አሻራ አለው
የምላስ የላይኛው ክፍል ልዩ የሆነው ክፍል ሲሆን
ሁለት ሰዎች አንድ አይነት የምላስ ቅርፅ ፈፅሞ አይኖራቸውም።
በነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hageregna-ሀገረኛ Hub posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hageregna-ሀገረኛ Hub:

Share