Sefa Kabu

Sefa Kabu Sefa Kabu

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ በመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በስፍራው ተገኝተው አፅናኑጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ጉዳት ወደ ደረሰበት ስፍራ አቅንተዋል...
27/07/2024

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ በመሬት መንሸራተት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በስፍራው ተገኝተው አፅናኑ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ጉዳት ወደ ደረሰበት ስፍራ አቅንተዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን አውጇል።

የሰፋ መረጃ ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/
ቴሌግራም፡ https://t.me/+V9Taivf1aRLRSCiH
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
እነዚህን የዩቲዩብ እና ቴሌግራም ቻናል ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

አርቲስት ያሬድ ነጉ ደግ ልቡን ይዞ ጎፋ ደርሷል| አርቲስት ያሬድ ነጉ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ምክኒያት የደረሰውን አደጋ ለማቋቋም ...
27/07/2024

አርቲስት ያሬድ ነጉ ደግ ልቡን ይዞ ጎፋ ደርሷል

| አርቲስት ያሬድ ነጉ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ምክኒያት የደረሰውን አደጋ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ ከአዲስ አበባ ተነስቶ ጎፋ ደርሷል።

🛑 ያሬድ ጓደኞቹን በማስተባበርም የተለያዪ ለድጋፍ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን እና ለምግብነት የሚውሉ ግብአቶችን በአይሱዙ አስጭኖ የአደጋው ስፍራ ድረስ በመገኘት በአስክሬን ፍለጋ ስራ ላይም እንደተሰማራ በስፍራው የተገኙ ምንጮች ገልጸውልናል።
ደራሽ ለወገኔ 🙏❤️
📌 ይህቺ ናት ኢትዮጵያ፤
ሰላም ለሀገራችን💚💛❤️
የሰፋ መረጃ ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/
ቴሌግራም፡ https://t.me/+V9Taivf1aRLRSCiH
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
እነዚህን የዩቲዩብ እና ቴሌግራም ቻናል ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

27/07/2024

ቬሮኒካ : -አሁን ደህና ነኝ

1 ሚሊዮን ብር ለገሠ  | ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በጎፋ በመሬት ናዳ ሳቢያ ለተጎዱ ወገኖች መርጃ የሚውል 1 ሚሊየን ብር ለግሷል።ቴዲ አፍሮ ትናንት በማህበራዊ ገጹ ባስተላለፈ...
27/07/2024

1 ሚሊዮን ብር ለገሠ

| ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በጎፋ በመሬት ናዳ ሳቢያ ለተጎዱ ወገኖች መርጃ የሚውል 1 ሚሊየን ብር ለግሷል።

ቴዲ አፍሮ
ትናንት በማህበራዊ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት “ከሰሞኑን በደቡብ የሀገራችን ክፍል (ጎፋ) በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ እና ጉዳት በደረሰባቸው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ በደረሰውም አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ወገኖች በሙሉ ከልብ መፅናናትን እመኛለሁ።” ማለቱም ይታወሳል።

Tewodros_Kassahun (ቴዲ አፍሮ)

የሰፋ መረጃ ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/
ቴሌግራም፡ https://t.me/+V9Taivf1aRLRSCiH
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
እነዚህን የዩቲዩብ እና ቴሌግራም ቻናል ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀከሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሽራተት አደጋ ምክን...
27/07/2024

ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ

ከሐምሌ 20 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ለ3 ቀናት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሽራተት አደጋ ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን በማሰብ ብሔራዊ የሀዘን ቀን ሆኖ እንዲታወጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወስኗል።

በእነዚህ የሐዘን ቀናት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች ፤ በኢትዮጵያ መርከቦች ፤ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈ ቤቶች የሪፐብሊኩ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተወስኗል፡፡



የሰፋ መረጃ ቤተሰብ ይሁኑ!
ቲክቶክ: https://www.tiktok.com/
ቴሌግራም፡ https://t.me/+V9Taivf1aRLRSCiH
ዩቲዩብ: https://www.youtube.com/
እነዚህን የዩቲዩብ እና ቴሌግራም ቻናል ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sefa Kabu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share