Rediet Marufa Mekuria

Rediet Marufa Mekuria Execellent

ፈጣሪ አቅም ይሁንላችሁ!
07/06/2026

ፈጣሪ አቅም ይሁንላችሁ!

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ተስፋ፣ ሀደራና ኃላፊነት...

ምስጋናና ክብር ላከበሩን ለመሎ ማህበረሰብ ይድረስላቸው!!

ሀገራችን ኢትዮጵያ የመንግስት አስተዳደርን በህዝቦች ይሁንታና በዴሞክራሲያዊ አሰራር ማዕቀፍ ለመምራት ከጀመረችበት ወድህ የዘንድሮ ምርጫ 7ኛ ዙር መሆኑ ይታወቃል።

እንደ ሀገር 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ግብ ተደርጎ የተወሰደው በሀገራችን የዴሞክራሲ ልምምዳችን ለማጽናት የሚያስችሉ በርካታ ተቋማዊ ሥራዎች ተሰርቷል። አመርቂ ውጤትም ተመዝግቧል።

በዚህ ታሪካዊ ምርጫ የመሎ ኮዛ ምርጫ ክልል ህዝብ ወክለን ስንወዳደር ከህዝቡ በዋናነት ከተነሱት ውስጥ ውስጣዊና ውጫዊ ጉዳዮችን በጥልቀት በመመልከት ወቅታዊና በሂደት የሚፈቱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች መንግስት እንደምፈታ በማመን በምርጫ ክልሉ ጊዜያዊ ውጤት መሰረት ድምጹን ሰጥቷል፣ ቃሉንም ጠብቋል።

አስተዋይ ማህበረሰባችን ባለፉት ጊዜያት ለተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ዕውቅና በመስጠት ቀሪ ሥራዎች የዕቅድ አካል እንዲሆን ከመንግስት ጋር መሆኑን ከምርጫ ክልሉ ጊዜያዊ ውጤት መሰረት በምርጫ ካርዱ አረጋግጧል።

አሁን እየታየ ያለውን ለውጥ ተስፋ በማድረግ፣ በቀሪ ጉዳዮች ላይ ሀደራውንና ተጨማሪ ኃላፊነት በመስጠቱ በግሌና በፓርቲያችን ብልፅግና ስም እያመሰገንን በጉድለቶች ላይ በትብብር፣ በቅንጅት፣ በመደጋገፍና በመርህ ለመስራት ዝግጁ ነን።

በምርጫ ውድድሩ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ወቅታዊ ችግሮችን ይሁን ጊዜ የወሰዱ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ የማዋጣት ጉዞ ጀምራችኃል፣ ህዝቡን በምጠቅሙ ጉዳዮች ላይ በጋራ የመስራት ልምድ ማካበትና መተባበር ያስፈልጋል። ከዚህ አኳያ በፓርቲያችን እሳቤ መሰረት የሚንከተለው የመግባባት ዴሞክራሲ በመሆኑ በትብብር፣ በቅንጅት፣ በመደጋገፍና በሀሳብ የበላይነት ለመስራት ከወድሁ መዘጋጀት ይጠብቅብናል።

ፓርቲያችን ብልፅግና በአፍላ ዕድሜው የኢትዮጵያን መልክ የሚመስል በተግባር ተፈትኖ ውጤት እያመጣ ያለ የፖለቲካ ስርዓት በመከተሉ የተለያዩ ሀሳቦችን ወደ መድረክ በማምጣት የመግባባት፣ የአቃፊነትና የገብር-ነበብነት እሳቤ ውጤት ከዚህ ምርጫ ሌላ ማሳያ አይኖርም።

ስለሆነም በምርጫ ክልሉ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ዕቅድ ለመመለስ በፓርቲያችን ፕሮግራምና ማኒፌስቶ ላይ በተቀመጠው አግባብ መሰረት ከመላው ህዝብ፣ ከተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ስቭክ ተቋማትና ሌሎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የምንሰራ ይሆናል።

የህዝቡ እምነትም የልማትና የመልካም አስ/ር ጉዳዮዎችን የሚመልሰው መንግስትና መሪው ፓርቲ እንደሆነ እምነታቸውን ያሳዩ በመሆናቸው በመንግስትና በፓርቲያችን መርህ ማዕቀፍ ላይ በመቆም የሚናሳካው ይሆናል። ለዚህ ፈጣሪ ይረዳናል!!

መጪው ጊዜ የብሩህ፣ የስኬት፣ የአንዲነትና የመበልፀግ ጊዜ እንዲሆን ተግተን በጋራ የሚንሰራ ይሆናል።

"ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ልጆቿን ይባርክ"!
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር"!

 !
21/05/2026

!

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሻገር
ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ

የብልጽግና ፓርቲ የ2040 ራዕይ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ ቀዳሚ የብልጽግና ተምሳሌትና ማዕከል ማድረግ ላይ ያተኮረ ነው።

ይህ የረጅም ጊዜ እቅድ በሦስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ የተገነባ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም ሀገሪቱን ተምሳሌትነት ከሚጠቀሱ ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው፦

ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና፦ ግብርናን ማዘመን፣ የኢንዱስትሪ ልማትን ማስፋፋት እና የዲጂታል ኢኮኖሚን በመገንባት ሁሉን አቀፍና ቀጣይነት ያለው እድገት ማረጋገጥ።

ማህበራዊ ፍትህና እኩልነት፦ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣ ጥራት ያለው ትምህርትና ጤና ተደራሽ ማድረግ፣ እንዲሁም ድህነትን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ።

ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ፦ ጠንካራ ተቋማትን መገንባት፣ የሕግ የበላይነትን ማስፈን እና ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር የተረጋጋች ሀገር መፍጠር። ይህ ራዕይ "በመደመር" የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፍልስፍና እንደ መሪ መርህ ይጠቀማል።

!
!

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
18/05/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!

ብልፅግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች መነቃቃት የፈጠረ ፓርቲ በመሆኑ ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት የተሰሩ ስራዎች የሁለንተናዊ ብልፅግና ስኬት አይቀረ ያደርጋል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
!

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !ውድ አባቴ መልካም ዕድል!
09/05/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር !
ውድ አባቴ መልካም ዕድል!

በጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ምርጫ ክልል ብልፅግና ፓርቲን በመወከል ለክልል ምክር ቤት የቀረቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች፦




ተነስቷል!ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ መታሰቢያ በዓል እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ! ስለእኛ መከራና ሞት ተቀብሎ የህይወት ተስፋን የሰጠን አምላካችን ስሙ ብሩክ ይሁን!...
11/04/2026

ተነስቷል!

ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ መታሰቢያ በዓል እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ! ስለእኛ መከራና ሞት ተቀብሎ የህይወት ተስፋን የሰጠን አምላካችን ስሙ ብሩክ ይሁን!!
ሚያዚያ 4/2018

06/01/2026

ኢየሱስ ተወልዷል!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ በዓል አደረሰን!!
ታህሳስ 28/2018

HBD to my bro!
30/12/2025

HBD to my bro!

በመደመር መንግስት እሳቤ በየዘርፉ እመርታን ለማስመዝገብ የመሪነት ሚናችንን እንወጣለን - አመራሮች  ህዳር፤ 26/2018 በመደመር መንግስት እሳቤ በየዘርፉ እመርታን ለማስመዝገብ የመሪነት ሚ...
05/12/2025

በመደመር መንግስት እሳቤ በየዘርፉ እመርታን ለማስመዝገብ የመሪነት ሚናችንን እንወጣለን - አመራሮች


ህዳር፤ 26/2018

በመደመር መንግስት እሳቤ በየዘርፉ እመርታን ለማስመዝገብ የመሪነት ሚናቸውን እንደሚወጡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ''በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ'' በሚል መሪ ሃሳብ ለከፍተኛ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠናና የሥራ አቅጣጫ መስጠታቸው የሚታወስ ነው።

በዚህም አመራሩ በየአካባቢው ያሉ አቅሞችን በማስተባበር፣ በመፍጠርና መፍጠን ለላቀ እመርታና ሀገራዊ ማንሰራራት ተግቶ መስራት እንዳለበት ማስገንዘባቸውም እንዲሁ።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች ቀደምት የስልጣኔ ታሪክ ያላትን ኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበት ደረጃ ለማድረስ በመፍጠን፣ በመፍጠርና በጥራት መስራት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በመሆኑም በመደመር መንግስት እሳቤ በየዘርፉ እመርታ ለማስመዝገብ በሚከናወኑ ተግባራት የመሪነት ሚናቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ማሩፋ መኩሪያ እንደገለጹት ለአመራሩ የተሰጠው ስልጠና አመራሩ ወቅቱን የዋጀ ተቀራራቢ እውቀትና ክህሎት እንዲኖረው ያስቻለ ነው።

በሀገር በቀል እሳቤ በመታገዝና ከተለመደው አሠራር በመውጣት ህዝቡን በማቀናጀት በሁሉም መስኮች እመርታ ለማስመዝገብ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

በሀገር በቀል እሳቤ በተከናወኑ ተግባራት ያልተለመደ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ የገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ተጨባጭ ምስክር ናቸው ብለዋል።

በተጨማሪም የከተማ ኮሪደር፣ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና አረንጓዴ አሻራ ኢንሸቲቭ ሥራዎች ፈጣን ልማት ለማስመዝገብ ከተከናወኑት እንደሚጠቀሱ አቶ ማሩፋ ጠቅስዋል።

በክልሉ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት መኖሩን የተናገሩት ሃላፊው፤ በመፍጠርና በመፍጠን እሳቤ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በከተማ ልማትና በኢንዱስትሪ ላይ ሽግግር ለማድረግ አመራሩ ተልዕኮ መውሰዱን ተናግረዋል።

እንደ ሀገርና ህዝብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን ምርጫ ሳይሆን ግዴታ በመሆኑ አዳዲስ እሳቤዎችን ፈጥኖ በመተግበር ለሁለንተናዊ እመርታ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እመቤት ወንድሙ በበኩላቸው፣ የለውጡ መንግስት በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ሽግግር ለማድረግ ባከናወናቸው የሪፎርም ሥራዎች ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

በመደመር መንግስት እሳቤ በመፍጠንና በመፍጠር ከዘመኑ ጋር መጓዝ የሚችል አመራርና ህዝብ ለመገንባት የተለያዩ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

እስከዛሬ ያመለጡ የልማት ዕድሎችን በፍጥነት ለማረጋገጥ በመፍጠንና በመፍጠር ፍልስፍናዊ መርህ በመስራት እንደክልል የተያዙ ግቦችን ለማሳካት ተግተው እንደሚሰሩም ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የግብርና፣ የቱሪዝም፣ የማዕድንና ሌሎችም ሀብቶች በስፋት እንዳሉ ያነሱት ሰብሳቢዋ፤ በቀጣይም የመንግስትና የህዝብን አቅም በማስተባበር የብልጽግና ጉዞን ለማፋጠን በትኩረት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ልማትን ማፋጠን የአመራሩ ሃላፊነት ብቻ ሳይሆን የመላው ህዝብ በመሆኑ አርሶ አደሩ፣ ነጋዴው፣ ምሁሩ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሌሎችም የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አመልክተዋል።
#ኢዜአ

22/11/2025

የማል-ኤሶች ምድር

12/10/2025

ዝማሬ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Rediet Marufa Mekuria posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category