05/02/2019
Protect yourself from cyber attack
====እራስዎን ከኢንተርኔት ላይ ጥቃት ይከላከሉ!(PROTECT YOURSELEF FROM CYBER ATTACK)!=====
ከኢንተርኔት እና የድጅታል ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ እያደጉ ከመጡ ጉዳይዎች ዋነኛው የመረጃ ደህንንነት ጉዳይ ነው።እንድ ቴክኖሎጂው ሁላ የመረጃ ስርቆቱም በአይንት፤በብዛት እና በሚጠቀሙት ስልት እየተወሳሰበ መጥቶል።መረጃ የዘመናችን እና የቀጣዮ ዘመን ትልቅ ሃብት ነው።ለዚህም ነው መረጃ የቀጣይ ዘመን ነዳጅ የሚባለው።ስለዚ የመረጃ ደህንንት በሚገባ ካልተጠበቀ በግልሰብ፤በድርጅቶች እና በመንግስት ላይ የሚያመጣው ጉዳት ከባድ ነው። የመረጃ ደህንነት ለምን ያስፈልጋል?መረጃ ሀብት ነው ካልን ሀብትን ደሞ ከወድመት እና ከቀማኛ መጠበቅ አለበት።የኢንተርኔት ሶሳይቲ 2018 ሪፖርት እንደሚያመለክተው አለማችን በ2018 ኢንተርኔትን ተመርኩዞ በተፈጸመ የመረጃ ጥቃት 600 ቢሊዮን የአሜርካ ዶላር ከስራለች።ይህን በዛሬው እለት በነበረው ማለትም 28/05/2011 በብሀሄራዊ ባንክ በነበረው የምንዛሬ ዋጋ ብናሰላው 600,000,000,000 * 28.20=16,920,000,000,000 ይህም 16 ኮትሪሊየን 920 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ማለት ነው።ይህን ቁጥር ለማነጻጸር ዘንድሮ ኢትዮጵያ መንግስት ከመደበው የ2011 በጅት ማለትም 346.9 ቢለየን ብር ጋር እናነጻጽረው መንግስት ለዘንድሮ በመደው በጀት ላይ ጭማሪ ሳያደርግ ቢቀጥል የመንግስትን የ48 አመት በጅት መሸፈን ይችላል ማለት ነው።ይህም ማለት መንግስት እስከ 2059 ዓ.ም ደረስ ያለውን ወጪ ሸፈነ ማለት ነው። ችግሩ ይህን ያልህ ሰፊ ከሆነ እራሳችን እንዴት እንከላከል?
1.ለሚጠቀሙባቸው እያንዳንዱ ዲጂታል መሳሪያ ፤ድህረ ገጽ እና መተግበሪያ(Application) ጠንካራ የይለፍ ቃል ወይም password ይጠቀሙ።
2. የይለፍ ቃል ወይም password ለማንም አይናገሩ
3.የታደሰ አንቲ ቫይረስ ሁሌም ይጠቀሙ
4.ሶፍትዌር ከማትታወቅ እና ታማኝ ካልሆነ ዌብ ሳይት አይጫኑ
5.ፓስወርድዎን በፍጹም በማስታወሻ ወረቀት አይጻፍ
አንድ የይለፍ ቃል ወይም password ጠንካራ ነው የሚባለው ምን ምን መመዘኛዎችን ሲያሞላ ነው?ጠንካራ የይለፍ ቃል ወይም password እንዴት መፍጠር እንችላለን?የሚለውን እና የተቀሩት 4 ጉዳዮች በቀጣይ ጽሁፋችን እንመለስበታልን።ማንኛውም የቴክኖሎጂ ዜና እና የቴክሎጂ እውቀቶን ለማበልጸግ ይህን ገጽ ላይክ ያድርጉ።እኛ ለቴክኖሎጂ ባይተዋር እንዳይሆኑ እንረዳዎታለን።
ከዛ በፊት ለሚኖራችሁ ማንኛውም ጥያቄም ሆነ አስተያያየትም
በINBOX,
COMMENT ወይም
[email protected]
ያድርሱን አፋጣኝ ምላሽ እንሰጣለን።
SHARING IS CARING ይህን ጽሁፍ በማጋራት ያወቁትን ያሳውቁ።ከወደዱት ላይከ እና ኮመንት ያርጉት ለበለጠ እና ለተሻለ ጽሁፍ ይግዘናል።
እናመሰግናለን።