XIWAN AT

XIWAN AT discussing politics, good governance, justice, equity, human and democracy right, moral value

17/11/2017

"መኖር አልፈራም"
1, ያለማስመሰለል ሀሳብ በነጻነት እየገለጽኩ መኖር አልፈራም
2, ሙስና, የተዛባ እና የዘገየ ፍትህ እየተቋወምኩ መኖር አልፈራም
3, በቀጠናበቀበሌ, በጎሳ በብሔር, በቋንቋ በሀይማኖት, በቀለም ተከፋፍሎ መገዳደል መዘራረፍ መጨቆን በመቃወም መኖር አልፈራም

08/11/2017

"world is becoming flat"

04/11/2017

በአዕምሮ መሰልጠናችን ስለሰው መጨነቅ ነው!!!!.
በሀገራችን "ሰለሰው ስለሰው ቀድጄ ልልበሰው " የሚባል አባባል አሁን የሰው ልጅ ከደረሰበት ስልጣኔ አንጻር ስህተት ነው። ስለአንድ ሰው ምቾት፣ፍትህ የማግኘት፣የግል ነጻነቱን ማክበር፣በህይወት የትም መኖር ተፈጥሮ የሰጠችው መብት እውቅና መስጠት መሰልጠን ነው። እነዚህ ለማክበርም ሆነ እውቅና ለመስጠት በቡድን(ማለት በብሔር፣በትውልድ ቦታ፣በሀይማኖት፣በቋንቋ፣ በቀለም....) ሁለትና ከዛ በላይ ሁኖ መደራጀት አይጠበቅም። ሰውኛ አካል ይዘው ግን አውሬያዊ አስተሳሰብና ጠባይ አስበውም ሆነ ባለማወቅ በውስጣቸው የሞላ ለሰው አሳቢ ሚመስሉ ግን ስለሰው በእኔ አውቅልሀለሁ ትቢት ተሞልተው ቀድሞ የሚወስኑ ፣ትምህርት የተማሩም ያልተማሩም አለም የደረሰችበት የስልጣኔ ጸሀይ ያልሞቃቸው ግለሰቦችና ቡድኖች በመበራከታቸው ይመስለኛል የርስ በርስ ግጭት በሀገራችን የሰፈነው። ስለዚህ ስለአንድ ሰው መጨነቅን፣ በጥሩ ነገር መወዳደር፣ መከባበር፣ መቻቻል የስልጣኔ ጥግ ላይ መድረስ ነው። ከመቶ ሰው ቢያንስ ዘጠና ዘጠኙ ሀይማኖታዊ በሆነበት ሀገር መገዳደል ስለግል እምነታችን ጥንካሬና ምንከተለው ፍልስፍና መመርመር ይጠበቅብናል የሚል መልእክት አለኝ።

07/10/2017
17/09/2017

Balance...
_________________
(‘እናውጋ' ብለሽ ብትመጪ እንኳ)
ስለሰው - ፍቅሬን ገፍትረሽ
ስለሰው - ስሜትሽን ገትተሸ
እንደምትመለሽ ...
አውቃለሁ!
~
(መውደዴ ውስጥሽ ቢዘራም)
እንዳይበቅል - ከነፍስሽ ማሳ
እንዳይሰርግ - ስሩ እንዲከሳ
ልብሽ እንደማይሳሳ ...
አውቃለሁ!!
~
(ስለ ፍቅር ብዙ ብታውቂም)
የመስፈሪያሽ ዳር - ሁልቆ
የሚዛንሽ ልክ - ድርጎ
መጠን እንዳጣ - መጥቆ ...
አውቃለሁ!!!
~
(ዓይኖችሽ ቀዬ ቢያደምቁም)
በሌሎች ብሌን - አሻግረው
ሌሎች ያዩትን - አምነው
ውበት እንዳልገባቸው ...
አውቃለሁ!!!!
~
ደግሞም…
(ቅርብኝ ብለሽ ስትገፊኝ)
ልጠላሽ - አቅም እንዳነሰኝ
ልረሳሽ - ወኔ እንደከዳኝ
አውቃለሁ!!!!!
~
ብቻ እንዳትይኝ ጅላጅል
… ጊዜዬ ሲሞት ከደጅሽ
ምላሴ ስምሽን ሲያላምጥ
… ልቤ ሲጠፋ በፍቅርሽ፣
በማወቄ ላይ ዘምቼ
… ዘገር ልነቅንቅ ያላልኩት
በቃሽኝ ብዬ ገፍቼ
… ለመተው አቅም ያጣሁት፣
ባንቺና በኔ አምድ ላይ
… ተዋቅሮ የተገነባው
በኪዳን የቆመው ዋልታ
… ስትሄጂ ላዬ ፈርሶ ነው፡፡
---------------------------------------

Address

Addis Ababa

Telephone

+251922415047

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when XIWAN AT posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to XIWAN AT:

Share