Gihon habesha tube

Gihon habesha tube Welcome to my channel I'm Melkamu Ashebir from Ethiopia if you subscribe my channel you get more be

21/05/2025

"ፋኖ እንደ አንበሳ ክንደ ብርቱ፣ እንደ ነብር ቁጡ፣ እንደ እርግብ የዋህ ነው። በዚህ ባሕርዩም አልጋ ላይ የዋለን በሽተኛ ጠያቂ፣ የተጣላውን አስታራቂ፣ የደከመውን አነቃቂ፣ ለእኔ ሳይሆን ለእኛ የሚል ክንደ ብርቱ የዓላማ ሰው ነው። ፋኖ ቁሞ ከሚሸነፍ ሞቶ ማሸነፍን የሥነ ልቡናው መሠረት ያደረገ የአሸናፊነት ምልክት ነው። ፋኖ የዐማራ ሕዝብ ሥሪት ሕያው ምስክር፣ በራሳቸው የሚተማመኑ ሀገር እና ወገን ወዳድ ስመጥር ጀግና ኢትዮጵያዊያን የክብር ስም ጭምር ነው። ፋኖነት በሕይወት እና በሞት መካከል በሚደረግ ብርቱ ትግል የሚገኝ ወርቃማ ስም ነው። ፋኖነት የዕድሜ፣ የፆታ፣ የሃይማኖት፣ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የሙያ፣ የዘር እና መሰል ልዩነቶችን ሳይፈጥርና ሳያጎል ሁሉም በተግባር ተመዝኖ በሚገለጥ እውነታ የሚገኝ እና ራሳቸውን ለሰፊው ሕዝብ ሲሉ አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎች ክብር ስም ነው።"

🌱🌱  የልማት ጥያቄ 🌿🌿🌿""ውዴ እኔ ያልኩት፣ከላይ በርዕሱ ልክ እንደጠቀስኩት፣በድፍረት ቀርቤ  አንቺን የጠየኩት፤ከጭኖችሽ መሃል… ያለውን ለም መሬት፤ለልማት ፈለኩት፡፡ድንግሉ መሬትሽ በዝናብ...
20/05/2025

🌱🌱 የልማት ጥያቄ 🌿🌿🌿
"
"
ውዴ እኔ ያልኩት፣
ከላይ በርዕሱ ልክ እንደጠቀስኩት፣
በድፍረት ቀርቤ አንቺን የጠየኩት፤
ከጭኖችሽ መሃል… ያለውን ለም መሬት፤
ለልማት ፈለኩት፡፡
ድንግሉ መሬትሽ በዝናብ የራሰው፤
ፍቀጂልኝና ክረምቱን ልረሰው፡፡
መንግስት ሳይገባበት ፣ደላላ ሳይሰማ፤
በውል አልባ ፍቅር ፣እኛው እንስማማ ፡፡
መቼም በኛ ሀገር…ታውቂያለሽ አውቃለው፤
ከማንም ከምንም ፣ልማት ነው የሚቀድመው ፡፡
ደግሜ ልነገርሽ… የኔናንቺን ወሬ ፣የኔናንቺን ደባ፤
ሌላ ሰው አይስማው ፣ መንግስት ጆሮ አይግባ፡፡
ነገሬ እስኪገባሽ ፣ ታዲያ ምን ይሻላል፤
ጠንካራ ገበሬ ፣ ባመት ይሸለማል ፡፡
ይሄንን ቢያውቅ አይደል ፣ ምድረ ዲያስፖራ፤
ሀገር ሸሽቶ ሄዶ ፣ ሀገር የሚያኮራ ?!
ወደፊት ለመጓዝ ፣ ለማደግ ስንዳዳ፤
አንዳንዴም ይሆናል ፣ ጠላትም እንግዳ፡፡
በዚህ በኛ ሀገር ፣ እንኳን ድንግል መሬት፤
በሊዝ ከተገዛ ፣ ይፈርሳል የሰው ቤት፡፡
እስቲ አሁን በኔ ሞት፣ ይሄ ይጠፋሻል ?
‹‹ልማት›› ከተባለ ፣ ድንበርም ይሸሻል፡፡
በዚህ በኛ ሀገር…
እኔም አንቺም ሁሉም ፣ቀድሞ እንደምናውቀው፤
ከማንም ከምንም ፣ ልማት ነው ሚቀድመው፡፡
‹‹ሙስና ነው›› ሳንል ፣ መንግስት ሳንፈራ፤
እስኪ እሺ በይና ፣ ሻጥር እንስራ ፡፡
ደግሜ ልንገርሽ ፣ ጥያቄዬ ይህ ነው፤
በውኔም በህልሜም ፣ እኔ እንደማልመው፤
ከጭኖችሽ መሀል… ያለውን ለም መሬት ፣ ፍቀጅልኝ ላልማው ፡፡
እንዲ በቀላሉ… ‹‹እሺ›› ብሎ መስጠት ፣ አውቃለሁ ይከብዳል፤
ግን ደሞ ልማት ነው…
ይህ ድንግል መሬትሽ ፣ ለሚያለማ ሀብታም ፣ ሊሰጠው ግድ ይላል ፡፡
ምክንያቱም….
በዚህ በኛ ሀገር ፣ እኔም አንቺም ሁሉም ፣ በወል የምናውቀው፤
ከማንም ከምንም ፣ልማት ነው ሚቀድመው፡፡
-------------///-------------

20/05/2025

አንድ ሰነፍ ሰውዬ ነበር ከጧት እስከ ማታ ተኝቶ የሚውል። ታዲያ ሚስቱ ሁልጊዜ እየሰራች ትመግበዋለች። አንድ ወቅት ግን እንዲህ አለችው፦
የትም አትንቀሳቀስም እኔ ነኝ ሁልጊዜ የምሰራው እንደዚህ ሆነን እስከመቼ?
እሱም መለሰላት አታስቢ ፍቅሬ ሃብታም እንሆናለን አላት። እሷም ሳትንቀሳቀስ እንዴት ተብሎ ነው ሃብታም የሚኮነው አለችው።
እሱም እንዲህ አላት ከተራራው ጀርባ አንድ ሽማግሌ ሰው አለ እሱን እጠይቀዋለሁ በማለት በሚቀጥለው ቀን መንገድ ጀመረ። መንገድ ላይ አንድ ቀጭን ተኩላ አገኘውና የት እየሄድክ ነው በማለት ይጠይቃል? አንድ ሽማግሌ ጋር እንዴት ሃብታም እንደምሆን ለመጠየቅ ይላል። ለእኔም እየበላሁ አልወፍርም እስኪ ጠይቅልኝ ይላል። እሺ ብሎ ይሄዳል።
መንገዱን ይቀጥላል ከዚያም አንድ የአፕል ዛፍ ያገኛል። እሱም ወዴት እንደሚሄድ ይጠይቀና እሱም ለእኔም እስኪ ፍሬዬ ሳይበስል እየበሰበሰ ነው ጠይቅልኝ ይላል።
ከዚያም ትንሺ እንደሄደ አንድ አሳ ሃይቅ ዳር ያገኝና አሱም የት እንደሚሄድ ጠይቆ እርዳኝ ጉሮሮዬ ላይ የሆነ ነገር ተሰንቅሮብኛል እናም ጠይቅልኝ ይለዋል። ከዚያም ከረጂም ጉዞ በኋላ የተባለውን አዋቂሰው ያገኘውና እንዴት ሃብታም እንደሚሆን አዋቂውን ይጠይቃል። በተጨማሪም መንገድ ላይ ያገኛቸውን ጥያቄዎቻቸውን ጠየቀ?
ሽማግሌው እንዲህ አለ፦
አሳው ጉሮሮ ውስጥ የከበረ ዲንጋይ ነው ያለው የሆነ ሰው ቢያወጣለት ይድናል።
የአፕሉ ዛፍ ስር የተቀበረ ወርቅ አለ ያንን ቆፍረው ቢያወጡት ዛፉ ፍሬው ጤናማ ይሆናል።
ተኩላው በመንገዱ ላይ መጀመሪያ የሚያገኘውን ሰነፍ ሰው ከበላ ይወፍራል ይላል አዋቂው ሰውዬ።
ሰውዬው እሺ እኔስ እንዴት ነው ሃብታም የምሆነው ይላል? አንተማ መልእክቱን ለሁሉም ታደርስና እዚያ ስትደርስ ሃብታም ትሆናለህ ይለዋል። መልእክቱን ለሁሉም እያደረሰ እየሄደ እያለ በመጨረሻ በተኩላው ተበላ። . . ስንፍና እድሎችህን ብቻ አይሰርቅም አንተንም ሊሰርቅህ ይችላል። ስለዚህ ስኬትን ለሚጠብቁ ሰዎች አይመጣም ለሚንቀሳቀሱ ብቻ ነው።
ለህልምህ ምን ያህል ርቀት ትጓዛለህ?

20/05/2025

Mindset Success(የስኬት አስተሳሰብ)
10_የገንዘብ_ሳይኮሎጂ_ትምህርቶች
የገንዘብ_ሳይኮሎጂ መጽሐፍ ስለ ገንዘብ፣ ስለ ሀብት፣ ሰዎች ስለ ገንዘብ እና ስለ ሀብት ስለሚኖሯቸው ባህሪያት፣ ስለ ኢንቨስትመንት እና ገንዘብን በተመለከተ ምን አይነት ውሳኔዎችን መወሰን እንደሚገባን የሚያስተምር መጽሐፍ ነው፡፡ ገንዘብን ስለማሳደግ፣ ሀብት ስለ ማፍራት፣ ሀብታም ሆኖ ስለ መኖር፣ ስግብግብነት ስለሚያስከትለው ጉዳት፣ ስለ ኢንቨስትመንት ወዘተ ጥልቅ ጥበቦች ያሉበት መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ እንደሚገኝ እየጠቆምን አስሩን ነጥቦች እነሆ ለቅምሻ ብለናል፡-
1_ወሳኙ_ለገንዘብ_ያለህ_አስተሳሰብ_ነው፡፡
እጅግ በጣም ወሳኙ ነገር አካላዊ ገንዘቡ ሳይሆን ስለ ገንዘብ ያለህ አስተሳሰብ ነው፡፡ ስለ ገንዘብ ያለህ አእምሯዊ አስተሳሰብ እና አመለካከት ከጥሬ ገንዘቡ ይልቅ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ አእምሯዊ አስተሳሰብህ ምን ያህል ሀብት እንደምትገነባ፣ ምን ያህል ገንዘብ እንደምታገኝ፣ ምን ያህል ገንዘብ መቆጠብ እንደሚገባህ፣ ገንዘብህንና ሀብትህን በምን ያህል እጥፍ ማብዛት እንደምትችል እናም በዋነኝነት እንዴት ደስተኛ እንደምትሆን ይወስናል፡፡ ስለዚህም ስለ ገንዘብ ትክክለኛ አመለካከትን ገንባ፡፡
2_በቃ_ዕድል_ነው፡፡
በህይወትህ ልዩነት የሚፈጥረው አንዳንዴ ተሰጦኦህ፣ ችሎታህና ክህሎትህ፣ የትምህርት ብቃትህ፣ ያሉህ ግንኙነቶችና ትውውቆች፣ አሊያም ምን ያህል ሀብታም መሆንህ አይደለም፤ በቃ ዕድል ነው፡፡ ይህን መቀበል ነው፡፡ የባንክ ባለሙያ፣ ኢኮኖሚስት፣ ስራ ፈጣሪ እና የበርካታ ድርጅቶች ባለቤት ስለሆነው ስለ ናይጄሪያዊው ቢሊነየር ቶኒ ኢሉሜሉ አስብ፡፡ ትሁት ሁን፡፡ ስኬትን ስታገኝ አትኮፈስ፡፡ ራስህን ዝቅ አድርግ፡፡ በስኬትህ ዕድል እንዳለበት አስብ፡፡
3_ስግብግብ_አትሁን፡፡
ይበቃኛልን ተማር፡፡ በህይወትህ ደስታን የምታገኘው የይበቃኛል ስሜት ሲኖርህ ነው፡፡ ስግብግብ ከሆንክ ሕግን ትተላለፋለህ፤ ለሌሎች ማሰብን ትተዋለህ፡፡ ይህም ብዙ ነገር ያሳጣሃል፡፡ በዓለም እጅግ ስኬታማ የነበሩ ሰዎች ስግብግብ ስለሆኑና ይበቃኛል ስላሉ ውድቀት እና ክስረት ገጥሟቸዋል፡፡ ይበቃኛል በል፡፡ በምታገኘው ትርፍ፣ በስኬትህ እና በምትደርስበት ደረጃ ተደሰት፡፡ ወደፊት ስለምታደርገው አስተዋጾ እና ለማህበረሰብህ እና ለሌሎች የሰው ልጆች ስለምትሰጠው ጠቀሜታ አስብ፡፡ ደስታ፣ ክብርና ሞገስ የሚገኘው ማህበረሰብን በማገልገል እና ሌሎች ሰዎችን በመጥቀም ነው፡፡ እናም ስግብግብ አትሁን፡፡
4_ሀብት_መገንባት_ጊዜ_ይፈልጋል፡፡
ከምናስበው እና ከምንጠብቀው በላይ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ስለ ዋረን በፌት አስቡ፡፡ አብዛኛውን ሀብቱን ያገኘው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው፡፡
5_ለጉራ_ስትል_ውድ_ነገርን_አትግዛ
ከሰዎች አድናቆት እና ክብር ለማግኘት ስትል ነገሮችን ከመግዛት ተቆጠብ፡፡ ማንም በምትገዛቸው ውድ ነገሮች አይደነቅም፡፡ ውድ የሆኑ ነገሮችን መግዛት ከሰዎች አድናቆትንና ክብርን አያስገኝልህም፡፡ ውሳኔዎችህ መሆን ያለባቸው በውስጥ ፍላጎትህ እና በሚያስፈልጉህ ነገሮች ነው፡፡ ጎረቤቶችህን ወይም ጓደኞችህን ለማስደነቅ ስትል በገንዘብህ ምንም ነገር አታድርግ፡፡ ውድ መኪና፣ ቅንጡ ቤት፣ ውድ ቁሳቁሶች፣ ውድ አልባሳት መግዛትህ አያስደንቃቸውም፡፡ እንዲያደንቁህ እና እንዲያከብሩህ አያደርጋቸውም፡፡ ይልቁንም ማንነትህ እና ደግነትህ ያለህ ባህሪ በእነርሱ ዘንድ የሚኖርህን ስፍራ ይወስናል፡፡

6_ዋጋ_ያለውን_ነገር_ለይ
ስምህና ክብርህ፣ ቤተሰብህ፣ ዘመዶችህ፣ ሰራተኞችህ፣ ጓደኞችህ እና የስራ አጋሮችህ ከምንም በላይ ዋጋ አላቸው፡፡ ገንዘብ ለማግኘት ብቻ ስትል እነዚህን አደጋ ውስጥ መጣል አይኖርብህም፡፡
7_ሁሌም_ተስፈኛ_ሁን፡፡
ጨለምተኛ መሆን አንዳች ነገር አያስገኝም፡፡ ተስፈኛ ሰው ብቻ በአላማው ላይ ሆኖ በረጅም ጊዜ ሂደት ስኬትን ይጎናጸፋል፡፡ የአሁን ሁናቴዎችህ ምንም ይሁኑ የወደፊት ጊዜህ የተሻለ እንደሚሆን ማመን ይኖርብሃል፡፡ ይህ ወደፊት እንድትቀጥል ጥረትህን እንዳታቋርጥ እና የተሻለ ነገር እንድታደርግ ያስችልሃል፡፡
8_የጊዜ_ነጻነት_እጅግ_ስኬታማ_እንድትሆን_ያስችልሃል፡፡
የጊዜ ነጻነትን የሚሰጥህን ስራ ምረጥ፡፡ ሙሉ ጊዜህን የሚቆጣጠር ስራ የራስህን አላማ እንዳትኖር፣ የራስህን ዕቅድ እንዳትተገብር ያደርግሃል፡፡ ስለዚህም የምትመኘውንና የምትፈልገውን ስኬት ለማግኘት የጊዜ ነጻነትን የሚሰጥህን ስራ በጉዞህ የሚያግዝህን ስራ በጥንቃቄ ምረጥ፡፡ የምትሰማራበትን ስራ በተግባር አይተኸው ወደፊት ሃያ እና ሰላሳ ዓመት ብቆይበት እደሰትበታለሁ ወይ ፍላጎቶቼን አሳካበታለሁ ወይ ብለህ ምረጠው፡፡ የጊዜ ነጻነት እና በራስህ ላይ የበላይነትን የሚሰጥህ ስራ ለስኬትህ እጅግ በጣም ጠቃሚ እና ተፈላጊ ነው፡፡
9_የምታገኘውን_መረጃ_ሁሉ_አትጠቀም፡፡
የምታገኘውን መረጃ ሁሉ በህይወትህ አትተግብር፡፡ ለሌላው ሰው የሰራው ለአንተ ላይሰራ ይችላል፡፡ ለሌሎች የሰራው ለአንተ ጎጂ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህም ለግል አላማህ የሚያግዝህ የትኛው መረጃ እና እውቀት እንደሆነ በጥንቃቄ ለይተህ እወቅ፡፡
10_ማንኛውም_ነገር_ዋጋ_አለው፡፡
ምንም ነገር ያለ ዋጋ አይገኝም፡፡ ሀብት ማግኘት ዋጋ ይጠይቃል፡፡ የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ፍቃደኛ መሆን ይኖርብሃል፡፡ መቆጠብ፣ ጥሩ ኢንቨስትመንት ማካሄድ፣ እውቀት ማግኘት፣ ክህሎት ማግኘት ይኖርብሃል፡፡ ሀብት ማግኘት ከፈለግክ ዋጋውን ለመክፈል ፍቃደኛ መሆን ይኖርብሃል፡፡ በሀብት እና በገንዘብ የተደላደለ እና የተሟላ ህይወት ለመኖር ዋጋ ክፈል፡፡ ምንም ነገር ነጻ አይደለም፡፡ አንዳች ነገር ያለ ምንም ነገር አይገኝም፡፡

28/03/2024
27/03/2024

የፋሽስቱ የኦሮሞ ብልጽግና ሰዎች ሜ/ጄኔራል ጋዲሳ ዲሮ ከመሞቱ በላይ ያስጨነቃቸው ነገር የቀብር ስርዓቱ ሲፈፀም ህዝብ ሊያውቅ ነው የሚለው ነው።
ከዚህ ሁሉ ጭንቀት የሚገላግል አንድ ምጡቅ ሃሳብ አለን…
ለምን ትንሽ ጊዜ ጠብቃችሁ ሰብሰብ አድርጋችሁ፣ አደራጅታችሁ ጋዲሳ ዲሮን ሆስፒታል ካሉት ጋር ከኮሎኔል ሸዋ፣ ኮሎኔል ይመር እና ኮሎኔል አባይ ጋር በአንድ ላይ የቀብር ስነስርዓታቸውን አትፈፅሙላቸውም?¡ ወጭም ትቆጥባላችሁ አንድ ሰው ነው የሞተው ማለትም ትችላላችሁ 😋

Address

Addis Ababa
BOLE

Telephone

+251967214917

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gihon habesha tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share