13/03/2026
ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ ምርቶቹ ያወጣውን ማዘመኛ በመተግበር ራስዎን ከሳይበር ጥቃት ይጠብቁ
ማይክሮሶፍት በመጋቢት ወር የሶፍትዌር ማሻሻያ መርሃ ግብሩ፣ ለዊንዶውስ ተጠቃሚዎች ለሳይበር ጥቃት አጋላጭ ለሆኑ ክፍተቶች መፍትሔ የሚሰጡ 79 መጠገኛዎችን (Patches) ይፋ አድርጓል።
ይህ የማሻሻያ እርምጃ በተለይ በስፋት ጥቅም ላይ በሚውሉ የዊንዶውስ ምርቶች ላይ የታዩ የደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ የታለመ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች መረጃዎቻቸውን ከጥቃት ለመከላከልና የሥርዓታቸውን ደህንነት ለማረጋገጥ እነዚህን ዝመናዎች በአፋጣኝ እንዲጭኑ ተመክሯል።
በዚህ ወር ማሻሻያ ከተደረገላቸው ክፍተቶች መካከል በዋናነት የሚጠቀሱት ሁለቱ ቀድመው ያልተለዩ የ"Zero-day" ተጋላጭነቶች ናቸው።
የመጀመሪያው መረጃዎችን በሥርዓት ለመያዝ እና ለማስተዳደር በሚያገለግለው SQL Server ላይ የተገኘው ነው። ሁለተኛው ደግሞ የተለያዩ የሶፍትዌር ዓይነቶችን ለመሥራት የሚያገለግል ነጻ እና የጋራ የቴክኖሎጂ መድረክ በሆነው በ .NET ሶፍትዌር ላይ የተገኘ የአገልግሎት መቋረጥ (DoS) ስህተት ነው።
ይህም የደህንነት መቆጣጠሪያ ወኪሎችን ለጊዜው በማሰናከል አጥቂዎች ሳይታወቁ ሥርዓቱ ውስጥ ዘልቀው እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ምንም እንኳ መጋቢት ወር "በጣም አደገኛ" (Critical) ተብለው የተመደቡት ሦስት ተጋላጭነቶች ብቻ ቢሆኑም፣ አብዛኞቹ ክፍተቶች ግን የመረጃ መንታፊዎች የሲስተሙን ሙሉ ቁጥጥር እንዲያገኙ መንገድ የሚከፍቱ መሆናቸው ታውቋል።
የቀረበውን ማዘመኛ በመተግበር መረጃዎችዎ እንዳይሰረቁ እና የኮምፒውተርዎ ፍጥነት እንዳይቀንስ፣ ወደ Settings > Windows Update በመግባት "Check for updates" የሚለውን በመጫን የዚህን ወር አዳዲስ ዝመናዎች እንዲጭኑ ይመከራል።
ተጨማሪ የሳይበር ደህንነት መረጃዎችን ለማግኘት፡-
• ድረ ገጽ፦ https://www.insa.gov.et
• ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/INSA.ETHIOPIA
• ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/?_t=8qBKkyp092r&_r=1
• ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com//featured
• ቴሌግራም፦ https://t.me/insagovet
• ትዊተር (X) ፦ https://twitter.com/INSAEthio
• ሊንክድኢን:- https://www.linkedin.com/.../information-network.../
• የሳይበር ጥቃት ጥቆማ ለመስጠት፡- ነጻ የስልክ መስመር 933