Bole Woreda Three Information Technology Group

Bole Woreda Three Information Technology Group To provide fast perfect and comfortable service for the organization

7 ሺህ ኪ.ሜ የሚረዝመው አዲሱ የጉግል መረጃ ማስተላለፍያ ገመድ===============ግሬስ ሁፐር የተሰኘውና በጉግል አማካኝነት አሜሪካን እና አውሮፓ ለማገናኘት የተዘረጋው የመረጃ ማስተላለ...
17/09/2021

7 ሺህ ኪ.ሜ የሚረዝመው አዲሱ የጉግል መረጃ ማስተላለፍያ ገመድ
===============
ግሬስ ሁፐር የተሰኘውና በጉግል አማካኝነት አሜሪካን እና አውሮፓ ለማገናኘት የተዘረጋው የመረጃ ማስተላለፊያ ገመድ ከቀናት በፊት እንግሊዝ መድረሱ ተሰማ፡፡ ወደ ስራ በሚገባበት ወቅት በአንድ ጊዜ 17.5 ሚሊዮን ያህል ሰዎች 4ኬ ጥራት ያላቸው ቪዲዮን ማስተላለፍ እንዲችሉ የማድረግ አቅም ያለው ገመዱ ከአሜሪካኗ ኒው ዮርክ ከተማ ተነስቶ ወደ ስፔኗ ቢልባኦ እና እንግሊዟ በድ ድረስ የተዘረጋ ሲሆን በቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ወደ ስራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡ የአዲሱ ትውልድ አህጉራትን በውቅያኖሶች ወለል የማገናኛ መስመር የሆነው ገመዱ ከህዝባዊው በይነ መረብ በተሻለም ደህንነትን የሚጠብቅ ይሆናል፡፡
ጉግል በግሉ የውቅያኖስ ውስጥ መረጃ ማስተላለፍያ ገመድ ሲዘረጋ ይህ 7ሺህ ኪ.ሜ የሚጠጋ ርዝመት ያለው ገመድ ለአራተኛ ጊዜው ሲሆን የእስካሁኖቹ ተደማምረውም 98 በመቶ የሚሆነውን የዓለማችን በይነ መረብ መረጃ ዝውውር እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡
ከወራት በፊት ገመዱን የብስ ላይ ለማድረስ ተሞክሮ በአስቸጋሪ አየር ፀባይ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቶ ነው አሁን ላይ በስኬት የተጠናቀቀው፡፡ እንደ ጉግል ከሆነ አሜሪካን እና እንግሊዝን የሚያገናኝ የውቅያኖስ ውስጥ ለውስጥ ገመድ ሲዘረጋ ከአውሮፓውያኑ 2003 በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ ይህም በተለይ በባህር ውስጥ የሚያገናኟት ገመዶች እያረጁባት ላሉት እንግሊዝ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
ከቴክኖሎጂ አንፃር ከዚህ ቀደም የተዘረጉት ገመዶች በውስጣቸው ይይዙት የነበሩት ከፍተኛው የፋይበር ገመዶች ብዛት 8 ሲሆን አዲሱ ግን በአንፃሩ 16 የፋይበር ገመዶችን የሚይዝ ነው፡፡
ምንጭ፤ ቢቢሲ

ከጦርነት ቢሊዮኖችን የሚያተርፉት የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች===================ታላላቅ የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ሀገሪቱ የመስከረም 11ዱ...
17/09/2021

ከጦርነት ቢሊዮኖችን የሚያተርፉት የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች
===================
ታላላቅ የአሜሪካን የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ሌሎች መንግስታዊ ተቋማት ሀገሪቱ የመስከረም 11ዱን ሽብር ጥቃት ተከትሎ ከመጣውና አሜሪካን ሽብርተኝነትን የመዋጋት (War On Terror) ብላ ከሰየመችው ጦርነት በርካታ ቢሊዮኖን ዶላሮችን ማግኘታቸውን ባሳለፍነው ሳምንት የወጣ ሪፖርት አመላከተ፡፡ “ቢግ ቴክ ሴልስ ዋር” የተሰኘው ሪፖርቱ ከአውሮፓውያኑ 2004 አንስቶ አማዞን፣ ፌስቡክ፣ ጉግል፣ ማይክሮሶፍት እና ትዊተር በዋናነት በጦርነቱ ላይ ያተኮሩ ትላልቅ ኮንትራቶችን ከመንግስት ወስደው ሲሰሩ እንደነበር ገልጿል፡፡
የአሜሪካን ጦር ኃይል እና ስለላ ተቋማት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጉዜ ወደ ዲጂታል እየተለወጠ መምጣቱን ተከትሎ በክላውድ ኮምፒውቲንግ እና ጂፒኤስ ሶፍትዌሮች ረገድ ፍላጎታቸውም እየጨመረ ቆይቷል፡፡ የመከላከያ ቢሮውን እንኳን ብናይ ከአውሮፓውያኑ 2004 አንስቶ ከትላልቆቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ባደረገው ስምምነት 43.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪን አውጥቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከትላልቆቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ ከሚያወጡት መካከል ከፊት የሚቀመጡት አምስቱ ተቋማት ሀገሪቱ ያወጀችው ይህን ዓለም አቀፍ ጦርነት ተከትለው የተመሰረቱ አልያም ከውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ጋር የተሳሰሩ ናቸው፡፡
በቅርቡ አማዞን እና ማይክሮሶፍት የነዚህ ስምምነቶች ቀዳሚ ተጠቃሚ ወደ መሆን የተሸጋገሩ ሲሆን ከ2015 እስከ 2019 ባሉት ዓመታት ውስጥ ብቻ አማዞን 5 ማይክሮሶፍት ደግሞ 8 ያህል ትላልቅ ኮንትራቶችን ከተቋማቱ ወስደዋል፡፡ ማይክሮሶፍት በተለይ በፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የስልጣን ዘመን የሚያገኛቸው ከመከላከያ ጋር የተያያዙ መንግስታዊ ኮንትራቶች በይበልጥ አድገውለት ነበር፡፡ በሌላ መልኩ ግን ለወትሮ የጦር ኃይሉ ደንበኛ የነበሩት የኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የኮንትራት ድርሻ በማሽቆልቆል ላይ ነው፡፡
መረጃው አሜሪካዊያን መንግስታቸው ውል የሚገባባቸው ኮንትራቶችን እንዲያጋልጡ በሚጠይቅ የበይነ መረብ መንገድ የተወሰዱ ናቸው፡፡ ታድያ መረጃዎቹ እስካሁን ማግኘት የተቻለው መንግስት ለህዝብ ይፋ ያደረጋቸው ስምምነቶች ብቻ እንደመሆኑ እውነተኛው የኮንትራቶቹ መጠን ከተጠቀሰውም በላይ ላቅ ያለ ሊሆን እንደሚችል ተነግሯል፡፡
ምንጭ፤ ቴክስፕሎር
ለተጨማሪ፤ https://techxplore.com/.../2021-09-big-tech-billions-war...

Tech Xplore, a new division of Science X Network, covers the latest engineering, electronics and technology advances

በደፈረሰ ውሃ ውስጥ በጥራት ማየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ**********************************************************በደፈረሰ ውሃ ውስጥ የሚገኙ ነገሮችንና እንቅ...
17/09/2021

በደፈረሰ ውሃ ውስጥ በጥራት ማየት የሚያስችል ቴክኖሎጂ
**********************************************************
በደፈረሰ ውሃ ውስጥ የሚገኙ ነገሮችንና እንቅስቃሴዎችን በጥራት መመልከት የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ መሰራቱ ተሰማ፡፡ ይህ ቴክኖሎጂም የደፈረሰ ውሃ ውስጥን ጥራት ያለው ምስል ማሳየት የሚያችል በመሆኑ በጎርፍ አደጋ ጊዜ ተጠቂዎችን ለማፈላለግ፣ ለስነ ምድር ምርምር እና ለውሃ ውስጥ የግብርና ስራ በጣም ጠቃሚ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡
ድፍርስ ውሃ በውሃው መደፍረስና ባሉት ብዛት ያላቸው ቅንጣቶች ምክንያት ብርሃን በቀላሉ ስላማይተላለፍ ውስጥ ፎቶ ማንሳት እጅግ ከባድ ነው፡፡ በድፍርስ ውሃ ውስጥ የሚያልፍ የብርሃን ጨረር በቀላሉ የሚበታተን በመሆኑ ከሚፈለገው ምስል ላይ ተጋጭቶ የመመለስ እድሉ ዝቅተኛ ነው፡፡ በመሆኑም ተመራማሪዎቹ ይህንን የሚበተን የብርሃን ጨረር ወደራሱ መሰብሰብ የሚችል ቴክኖሎጂን ሰርተው በድፍርስ ውሃ ውስጥ ፎቶ ማንሳት እንደሚቻል አረጋግጠዋል፡፡
ቴክኖሎጂው በተለያዩ ድፍርስ ውሃ አካላት ላይ ሙከራ የተደረገበት ሲሆን ምንም አይነት ነገርን ለማየት በሚያዳግት ድፍርስነት ባለው የውሃ አካልም በቂ መረጃን መሰብሰብ የሚያስችል ብቃት እንዳለው ታውቋል፡፡ የቻይናው ቲያንጂን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ሀዎፌንግ ሁ የውሃን የውስጥ ክፍል በፎቶ መረጃ ለመሰብሰብ የነበረውን ችግር ይህ ቴክሎጂ በእጅጉ እንደቀረፈው ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ የተደረጉት ሙከራዎች ቤተ-ሙከራ ውስጥ የተደረጉ ሲሆን ሙከራውን በወንዞችና በውቅያኖሶች ለማድረግ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን በተጨማሪም ምስልን ከርቀት ላይ የመውሰድ አቅምንም ለማሳደግ መታቀዱን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ phys.org

Researchers have developed a new method that can automatically produce clear images through murky water. The new technology could be useful for searching for drowning victims, documenting submerged archaeological artifacts and monitoring underwater farms.

"ሶላር ፔንት" የወደፊቱ የዓለማችን የሃይል ምንጭ====================== በሶላር የኢነርጂ አማራጮች ውስጥ አዳዲስ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ ቀደም ብሎ...
17/09/2021

"ሶላር ፔንት" የወደፊቱ የዓለማችን የሃይል ምንጭ
======================
በሶላር የኢነርጂ አማራጮች ውስጥ አዳዲስ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ ቀደም ብሎ የሚታወቀው የፓኔል የሶላር ቴክኖሎጂ በአስር አመታት ውስጥ ብቻ ለአለማችን የኤሌክትሩክ ሃልይ አቅርቦት ላይ ትልቅ አስተዋፅዕ የደረገ ሲሆን ከሱ በኋላ ተከትለው የመጡት ልዩ ልዩ የሶላር የኢነርጂ አሰራሮችና ቴክኖሎጂዎች የወደፊቱን የሃይል አቅርቦት ይበልጥ ያሳድጉታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንደአውሮፓውያኑ በ1939 ለመጀመሪያ ጊዜ በሩሲያው ሚኒራሎጂስት ሌቭ ፔሮቭስኪ ሙከራ የተደረገበት የሶላር ፔንት (Solar Paint) ቴክኖሎጂ ወይም አሰራር ከቅርብ አመታት ወዲህ በሶላር የኢነርጂ አማራጮች ውስጥ ትልቅ ተስፋን ያሳየ ግኝት ነው፡፡ የሶላር ፔንት ከስሙ እንደምንረዳው በግርግዳዎች፣ በጣሪያዎች አልያም በወለሎች ላይ በቀላሉ ሊቀባ የሚችል እና ከፀሃይ የሚመጣን ኢነርጂ ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል ለማቀየር የሚስችል ዘመናዊ የሶላር ኢነርጂ አሰራር ነው፡፡ በዚህ የምርምር ዘርፍ ውስጥ ብዙ ዩኒቨርስቶች እና የጥናት ተቋማት ሰፊ እንቅስቃሴዎች እየደረጉ ቢሆንም ግኝቱን ይበልጥ ወደ መሬት እንዲወረድ ያስችሉት በቅርቡ በሮያል ሜልቦርን የጥናት ተቋም እና በሼፍልድ ዩኒቨርስቲ የተሰሩት የምርምር ስራዎች ናቸው፡፡ ከዚህ ባለፈም የሚሰጠውን የኢነርጂ አቅም ይበልጥ ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እንዲቻል በቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ እና በባፍሎ የቴክኖሎጂ ተቋም የተሰሩ የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ቴክኖሎጂውን ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደተጠቃሚዎች እንዲቀርብ ያስቻለ ነው፡፡
ሶላር ፔንት ወይም በሳይንሳዊ አጠራሩ (Perovskite Solar Paint) በተለያዩ የቀለም ባህሪያት ውስጥ እንደ ሴንቴቲክ ሞሊቤድነም ሰልፋድ እና ቲታኒየም ኦክሳድ ያሉ የኬሚካል አፀግብሮቶችን በመጠቀም በግድግዳዎች አልያም በጣሪያዎች ላይ የሚቀቡት ቀለሞች በአየር ላይ የሚገኘውንና በትነት ደረጃ ያለን ውሃ ወደ ኤሌክትሪክ ሃይል ለመቀየር የሚያስችል ግኝት ነው፡፡ በዚህ የሶላር ቴክኖሎጂ አሰራር እንደቀለም የሚያገለግለው ኬሚካል ከአየር ላይ በቀላሉ እርጥበትን በመሳብ ያገኛቸውን የውሃ ሞሎኪዩሎች በሃይድሮጅን እና በኦክስጂን መልክ ለይቶ በማስቀመጥ ለኤሌክትሪክ ሃይል ሊውል የሚችለውን ንፁህ የሃይድሮጅን ኢነርጂ ለይቶ የሚያወጣ ይሆናል፡፡ በቴክኖሎጂው የአሰራር ሂደት የተገኙትን የውሃ ሞሎኪዩሎች በሃይድሮጅን እና በኦክስጂን መልክ ከፋፍሎ በማስቀመጥ ንፁህ የሆነውን የሃይድሮጅን ኢነርጂ ለይቶ ማውጣት እንዲቻል የፀሃይ ብርሃን እጅግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ በቅርብ በተከናወኑ የምርምር ስራዎች ሶላር ፔንት ከዚህ አተገባባር በተጨማሪ የናኖ ስኬል ሰሚኮንዳክተሮችን በመጠቀም ከቀለም ቅቡ የሚሰበሰበውን የጸሃይን ብርሃን ቀጥታ ወደኤሌክትሪክ ሃይል ለመቀየር የሚያስችል ተስፋ ሰጪ ግኝቶችም እንደተገኙ በዘርፉ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች ሲገልፁ ይሰማል፡፡
ሶላር ፔንት በምርምር ሂደት ውስጥ ገና እያለፈ የሚገኝ ቴክኖሎጂ ቢሆንም በወደፊቱ የአለማችን የኢነርጂ ፍላጎት ላይ ትልቅ እድል ይዞ የሚመጣ ግኝት ነው፡፡ አሁን ጥቅም ላይ እየዋሉ ካሉት መደበኛ የሶላር ፓኔሎች በተለየ በቀላሉ በግርግዳዎች፣ በጣሪያዎች አልያም በወለሎች ላይ ተቀብቶ የኤሌክተሪክ ሃይልን ማስገኘት መቻሉ እጅግ ጠቃሚ ግኝት ያደርገዋል፡፡
https://solaractionalliance.org/solar-paint/

ከ90 ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ምድር የተመለሱት የቻይና ተመራማሪዎች********************************************************************በቻይና ታሪክ ው...
17/09/2021

ከ90 ቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ምድር የተመለሱት የቻይና ተመራማሪዎች
********************************************************************
በቻይና ታሪክ ውስጥ ብዛት ያላቸው የህዋ ሳይንስ ተመራማሪዎች ለረጅም ጊዜ ያደረጉትን የህዋ ላይ ቆይታ አጠናቀው ወደ ምድር መመለሳቸው ተነገረ፡፡ እነዚህ ተመራማሪዎች ቲያንጎንግ በተሰኘው የቻይና የህዋ ላይ ምርምር ጣቢያ ለ90 ቀናት ያክል ቆይተው የተለያዩ የምርምር ስራዎችን ከሰሩ በኋላ በሙሉ ጤንነት ወደ ምድር ተመልሰዋል፡፡ በቆይታቸውም የህዋ ላይ እንቅስቃሴ (spacewalks) እና የተለያዩ ሳይንሳዊ ሙከራዎችን አካሂደዋል፡፡
12ቱም ተመራማሪዎች ወደቤታቸው ከመሄዳቸው በፊት ለ2 ሳምንታት በለይቶ ማቆያ ተቀምጠው ክትትል እንደሚደረግላቸው ተሰምቷል፡፡ ይህ ተልዕኮ እያደገ የመጣው የቻይና የህዋ ላይ ምርምር አካል ሲሆን ሀገሪቱ ማርስ ላይ የአሰሳ ሮቨር ማምጠቅና ወደ ጨረቃም የተለያዩ የምርምር ግብዓቶችን መላኳ በዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አመላካች ነው፡፡
ቲያንጎንግ ሰማያዊ ስፍራ ("heavenly palace") ማለት ሲሆን ለ10 ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተሰራ የህዋ ላይ የምርምር ጣቢያ ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ 3ቱም ከሀገሪቱ የመከላከያ ሀይል የተገኙ ሲሆኑ አንደኛው ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ የህዋ ላይ ጉዞን በማድረግ ልምድ ያለው መሆኑ ተነግሯል፡፡
የቻይና ስፔስ ኤጀንሲ በቀጣዩ አመት ብቻ 11 የህዋ ላይ ጉዞ ያቀደ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 3ቱ ተመራማሪዎችን ይዘው የሚጓዙ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም 70 ቶን የሚደርሱ ሁለት የቤተ ሙከራ መገንቢያ ቁሶችም እንደሚላኩ ታውቋል፡፡ ቻይና የህዋ ላይ ምርምሯን የመከላከያ ሀይሏን መሰረት ባደረገ መልኩ እያከናወነች ትገኛለች፡፡
ምንጭ phys.org
ተጨማሪ ንባብ https://phys.org/.../2021-09-chinese-astronauts-earth-day

21/07/2021

♻️ የኤሌክትሮኒክስ አብዝቶ መጠቀምና ጉዳቱ:-

💻📱🖥 እንደ ላፕቶፕ ፣ ታብሌት እና ስማርት ስልኮችን አዘውትረው የሚጠቀሙ ከሆነ ለተለያዩ የጤና ጉዳቶች ይዳርጋሉ፡፡

👉ይህም በተጠቃሚዎቹ ላይ የትምህርት ፣ የስራ እንዲሁም የማህበራዊ ተጽዕኖ እና የባህሪ ችግር እንደሚያጋጥማቸው የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

✅ ከችግሮቹ መካከል፡- 👇

1⃣. የአህምሮ ዕድገት እክል:-
- ህፃናት ከተወለዱ ጊዜ አንስቶ እስከ 21 ዓመታቸው ድረስ የአህምሮአቸው ዕድገት ፈጣን ሲሆን በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ታዳጊዎች ጊዜያቸውን በብዛት እንደ ላብቶፕ ፣ ታብሌት እና ስርማት ስልኮችን📱 ጋር የሚያሳለፉ ከሆነ የአህምሮአቸው ዕድገት ፍጥነት ላይ እክል ሊገጥም ይችላል፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት ከኤሌክትሮኒክስ የሚወታጣው ጨረር ታዳጊዎቹ የአህምሮ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው፡፡

2⃣. የተዛባ ማህበራዊ ግንኙነት:-
- ጊዜያቸውን እንደ ላብቶፕ፣ ታብሌት እና ስማርት ስልኮችን📲 ጋር የሚያሳለፉ ታዳጊዎች በማህበራዊ እና በትምህርት ላይ ከፍተኛ ችግር ሲያጋጥማቸው ይስተዋላል፡፡ እነዚህ ታዳጊዎች ጊዜያቸውን ከኤሌክትሮኒክስ ጋር ሲያሳልፉ ከማህበረሰብ መማር ያለባቸውን ክህሎት ሳይማሩ ይቀራሉ፡፡

3⃣. ከመጠን ያለፈ ውፍረት:-
- ጊዜያቸውን ለረጅም ሰዓት ቁጭ ብለው ስለሚያሳልፉ አነስተኛ ለሆነ እንቅስቃሴ ይጋለጣሉ፤ ይህ ደግሞ ከመጠን ላለፈ #ውፍረት (Obesity) በቀላሉ ሊያጋጥማችው ይችላሉ፡፡

4⃣. የእንቅልፍ ማነስ:-
- በስልክ📲 መጫወት በጣም ስለሚያስደስት ለጫወታው ሲሉ የእንቅልፍ ሰዓታቸውን ያሳልፋሉ በዚህም ምክንያት በእንቅልፍ እጦት ይሰቃያሉ🤦‍♂ በአስተኛኘታቸው ላይ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል፡፡

5⃣. ለጨረር መጋለጥ:-
- የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች አዘውትረው የሚጠቀሙ ከሆነ ከቁሳቁሱ የሚመነጨው ጨረር #ለአህምሮ እድገት/ለአይን ችግር.... ላይ ከሚያስከትለው በተጨማሪም ለከፋ የጤና ችግር ሊያጋልጣቸው ይችላል፡፡

6⃣. ለአይን ጉዳት:-
- እስክሪን ለረጅም ሰዓት እያዩ የሚቆዩ ከሆነ ለእይታ ችግር👁 ሊጋለጡ ይችላሉ ይህም ከሚያነቡት የጽሁፍ መጠን ማነስ ፣ ለረጅም ሰዓት አይንን በአንድ ነገር ላይ ማተኮር እና ከእስክሪን በሚወጡ ጨረሮች አማካይነት ለአይን ህመም ይዳረጋሉ፡፡
👉 ስለዚህ ለምናደርገው ነገር በሙሉ ጥንቃቄ መውሰድ አለብን በተለይ ወላጆች ለልጆች ቢበዛ ለ30 ደቂቃ ብቻ እንዲጫወቱ መፍቀድ ብዙም ወደ ሚጎዳቸው ነገር ባናስጠጋ ጥሩ ነው፡፡

12/02/2021

CTRL+A. . . . . . . . . . . . . . . . . Select All
CTRL+C. . . . . . . . . . . . . . . . . Copy
CTRL+X. . . . . . . . . . . . . . . . . Cut
CTRL+V. . . . . . . . . . . . . . . . . Paste
CTRL+Z. . . . . . . . . . . . . . . . . Undo
CTRL+B. . . . . . . . . . . . . . . . . Bold
CTRL+U. . . . . . . . . . . . . . . . . Underline
CTRL+I . . . . . . . . . . . . . . . . . Italic
F1 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Help
F2 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Rename selected object
F3 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Find all files
F4 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Opens file list drop-down in dialogs
F5 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Refresh current window
F6 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Shifts focus in Windows Explorer
F10 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Activates menu bar options
ALT+TAB . . . . . . . . . . . . . . . . Cycles between open applications
ALT+F4 . . . . . . . . . . . . . . . . . Quit program, close current window
ALT+F6 . . . . . . . . . . . . . . . . . Switch between current program windows
ALT+ENTER. . . . . . . . . . . . . . Opens properties dialog
ALT+SPACE . . . . . . . . . . . . . . System menu for current window
ALT+¢ . . . . . . . . . . . . . . . . . . opens drop-down lists in dialog boxes
BACKSPACE . . . . . . . . . . . . . Switch to parent folder
CTRL+ESC . . . . . . . . . . . . . . Opens Start menu
CTRL+ALT+DEL . . . . . . . . . . Opens task manager, reboots the computer
CTRL+TAB . . . . . . . . . . . . . . Move through property tabs
CTRL+SHIFT+DRAG . . . . . . . Create shortcut (also right-click, drag)
CTRL+DRAG . . . . . . . . . . . . . Copy File
ESC . . . . . . . . . . . . . . . . . . . Cancel last function
SHIFT . . . . . . . . . . . . . . . . . . Press/hold SHIFT, insert CD-ROM to bypass auto-play
SHIFT+DRAG . . . . . . . . . . . . Move file
SHIFT+F10. . . . . . . . . . . . . . . Opens context menu (same as right-click)
SHIFT+DELETE . . . . . . . . . . . Full wipe delete (bypasses Recycle Bin)
ALT+underlined letter . . . . Opens the corresponding menu
PC Keyboard Shortcuts
Document Cursor Controls
HOME . . . . . . . . . . . . . . to beginning of line or far left of field or screen
END . . . . . . . . . . . . . . . . to end of line, or far right of field or screen
CTRL+HOME . . . . . . . . to the top
CTRL+END . . . . . . . . . . to the bottom
PAGE UP . . . . . . . . . . . . moves document or dialog box up one page
PAGE DOWN . . . . . . . . moves document or dialog down one page
ARROW KEYS . . . . . . . move focus in documents, dialogs, etc.
CTRL+ > . . . . . . . . . . . . next word
CTRL+SHIFT+ > . . . . . . selects word
Windows Explorer Tree Control
Numeric Keypad * . . . Expand all under current selection
Numeric Keypad + . . . Expands current selection
Numeric Keypad – . . . Collapses current selection
¦ . . . . . . . . . . . . . . . . . . Expand current selection or go to first child
‰ . . . . . . . . . . . . . . . . . . Collapse current selection or go to parent
Special Characters
‘ Opening single quote . . . alt 0145
’ Closing single quote . . . . alt 0146
“ Opening double quote . . . alt 0147
“ Closing double quote. . . . alt 0148
– En dash. . . . . . . . . . . . . . . alt 0150
— Em dash . . . . . . . . . . . . . . alt 0151
… Ellipsis. . . . . . . . . . . . . . . . alt 0133
• Bullet . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0149
® Registration Mark . . . . . . . alt 0174
© Copyright . . . . . . . . . . . . . alt 0169
™ Trademark . . . . . . . . . . . . alt 0153
° Degree symbol. . . . . . . . . alt 0176
¢ Cent sign . . . . . . . . . . . . . alt 0162
1⁄4 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0188
1⁄2 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0189
3⁄4 . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . alt 0190
PC Keyboard Shortcuts
Creating unique images in a uniform world! Creating unique images in a uniform world!
é . . . . . . . . . . . . . . . alt 0233
É . . . . . . . . . . . . . . . alt 0201
ñ . . . . . . . . . . . . . . . alt 0241
÷ . . . . . . . . . . . . . . . alt 0247
File menu options in current program
Alt + E Edit options in current program
F1 Universal help (for all programs)
Ctrl + A Select all text
Ctrl + X Cut selected item
Shift + Del Cut selected item
Ctrl + C Copy selected item
Ctrl + Ins Copy selected item
Ctrl + V Paste
Shift + Ins Paste
Home Go to beginning of current line
Ctrl + Home Go to beginning of document
End Go to end of current line
Ctrl + End Go to end of document
Shift + Home Highlight from current position to beginning of line
Shift + End Highlight from current position to end of line
Ctrl + f Move one word to the left at a time
Ctrl + g Move one word to the right at a time
MICROSOFT® WINDOWS® SHORTCUT KEYS
Alt + Tab Switch between open applications
Alt +
Shift + Tab
Switch backwards between open
applications
Alt + Print
Screen
Create screen shot for current program
Ctrl + Alt + Del Reboot/Windows® task manager
Ctrl + Esc Bring up start menu
Alt + Esc Switch between applications on taskbar
F2 Rename selected icon
F3 Start find from desktop
F4 Open the drive selection when browsing
F5 Refresh contents
Alt + F4 Close current open program
Ctrl + F4 Close window in program
Ctrl + Plus
Key
Automatically adjust widths of all columns
in Windows Explorer
Alt + Enter Open properties window of selected icon
or program
Shift + F10 Simulate right-click on selected item
Shift + Del Delete programs/files permanently
Holding Shift
During Bootup
Boot safe mode or bypass system files
Holding Shift
During Bootup
When putting in an audio CD, will prevent
CD Player from playing
WINKEY SHORTCUTS
WINKEY + D Bring desktop to the top of other windows
WINKEY + M Minimize all windows
WINKEY +
SHIFT + M
Undo the minimize done by WINKEY + M
and WINKEY + D
WINKEY + E Open Microsoft Explorer
WINKEY + Tab Cycle through open programs on taskbar
WINKEY + F Display the Windows® Search/Find feature
WINKEY +
CTRL + F
Display the search for computers window
WINKEY + F1 Display the Microsoft® Windows® help
WINKEY + R Open the run window
WINKEY +
Pause /Break
Open the system properties window
WINKEY + U Open utility manager
WINKEY + L Lock the computer (Windows XP® & later)
OUTLOOK® SHORTCUT KEYS
Alt + S Send the email
Ctrl + C Copy selected text
Ctrl + X Cut selected text
Ctrl + P Open print dialog box
Ctrl + K Complete name/email typed in address bar
Ctrl + B Bold highlighted selection
Ctrl + I Italicize highlighted selection
Ctrl + U Underline highlighted selection
Ctrl + R Reply to an email
Ctrl + F Forward an email
Ctrl + N Create a new email
Ctrl + Shift + A Create a new appointment to your calendar
Ctrl + Shift + O Open the outbox
Ctrl + Shift + I Open the inbox
Ctrl + Shift + K Add a new task
Ctrl + Shift + C Create a new contact
Ctrl + Shift+ J Create a new journal entry
WORD® SHORTCUT KEYS
Ctrl + A Select all contents of the page
Ctrl + B Bold highlighted selection
Ctrl + C Copy selected text
Ctrl + X Cut selected text
Ctrl + N Open new/blank document
Ctrl + O Open options
Ctrl + P Open the print window
Ctrl + F Open find box
Ctrl + I Italicize highlighted selection
Ctrl + K Insert link
Ctrl + U Underline highlighted selection
Ctrl + V Paste
Ctrl + Y Redo the last action performed
Ctrl + Z Undo last action
Ctrl + G Find and replace options
Ctrl + H Find and replace options
Ctrl + J Justify paragraph alignment
Ctrl + L Align selected text or line to the left
Ctrl + Q Align selected paragraph to the left
Ctrl + E Align selected

world becomes village because of network technology
27/12/2020

world becomes village because of network technology

Address

Bole Atlas Area
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 02:30 - 11:30
Tuesday 02:30 - 11:30
Wednesday 02:30 - 11:30
Thursday 02:30 - 11:30
Friday 02:30 - 11:30

Telephone

+251116624713

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole Woreda Three Information Technology Group posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Bole Woreda Three Information Technology Group:

Share