ET-Cybers

ET-Cybers We give information on securing your social media

የቴሌግራም አካውንቶን ለመቆጣጠር ብዙ የማጭበርበሪያ ገጾች አሉ። የማታለል ዘዴዎችን በመጠቀም የቴሌግራም አካውንትዎን ለማግኘት እየሞከሩ መሆናቸውን ደርሰንበታል። ያረፉበት ድረ-ገጽ ትክክለኛ ...
18/07/2023

የቴሌግራም አካውንቶን ለመቆጣጠር ብዙ የማጭበርበሪያ ገጾች አሉ። የማታለል ዘዴዎችን በመጠቀም የቴሌግራም አካውንትዎን ለማግኘት እየሞከሩ መሆናቸውን ደርሰንበታል። ያረፉበት ድረ-ገጽ ትክክለኛ የቴሌግራም ድረ-ገጽ አይደለም። ከዛ ውጭም ብዙ የቴሌግራም ቦቶች ተስርተው የስልክ ቁጥራቹን እና activation ኮድ በመጠየቅ ለማታለል ይየሞከሩ ነው። ከጓደኞችዎ ግብዣ ሊደርሰዎት ይችላል ምክንያቱም መለያቸው ስለተጠለፈ።
እራስህን ለመጠበቅ ምርጡ መንገድ የማታውቀውን ሊንክ "አትንካ" ነው።
ሼር በማድረግ ይተባበሩን።

Akkaawuntii Telegram keessan hack gochuuf fuula gowwoomsaa hedduutu jira. Mala sobaa fayyadamuun akkaawuntii Telegram keessan seenuuf yaalaa akka jiran arganneerra. Weebsaayitiin ati irra buute marsariitii Telegram isa dhugaa miti. Kanarraa kan hafe Telegram bots hedduun uumamuun lakkoofsa bilbilaa fi activation code gaafachuun gowwoomsuuf yaalu. Hiriyyoota keessan irraa waamichi argachuu dandeessu sababiin isaas akkaawuntiin isaanii waan hack ta'eef.
Karaan of eeguu dandeessan inni gaariin linkii hin beekne "hin tuqin".
Share gochuun nu gargaaraa.

07/04/2023

" እኛ እንዲህ ዓይነት ዘረፋ ይኖራል ብለንም አስበን አናውቅም " - የዘረፋው መርማሪ

ጠቅላላ ዘረፋውን ለመፈጸም የወሰደው 2 ሰዓት ከ13 ደቂቃ ነው።

ዘረፋው በተመሳሳይ ሰዓት፣ በ28 አገራት ውስጥ ነው የተፈፀመው።

ነገሩን በአጭሩ ለማስቀመጥ ተራ ግለሰቦች ወደ ባንክ ኤቲኤም ማሽን ሄደው ገንዘብ ያወጡበት ዘረፋ ነው።
ይህ እንዴት ሆነ ? የሚለውን እንመልከት።

በሕንድ የተወሰኑ ሰዎች ለአስተኔ ገጸባሕሪ (extra role) ፊልም ቀረጻ ተመለመሉ። ደስም አላቸው።

የተሰጣቸው ሚና ከኤቲኤም ማሽን ብር ማውጣት ነው።

ሕንድ ሀገር ማሃራሽትራ የሚገኙ ምልምል ተዋናዮች ድርጊቱን ሲፈጽሙ ለፊልም ቀረጻ መስሏቸዋል።

የታላቁ የገንዘብ ርቆት አካል እንደተደረጉ በፍጹም አያውቁም።

ይህ የሆነው በሐምሌ 2018 ሰንበት ነበር።

ኮስሞስ ይባላል የተዘረፈው ባንክ።

ጭር ባለው የሰንበት ዕለት ድንገት ዋናው የባንኩ መሥሪያ ቤት ያሉ ሠራተኞች መልዕክት ደረሳቸው። መልዕክቱ የሚመጣው ከአሜሪካ የቪዛ ካርድ ኩባንያ ነበር።

ቪዛ ኩባንያ ለኮስሞስ ባንክ ሰዎች በቀጣይ ደቂቃዎች በርካታ የገንዘብ ጥያቄዎች ሊቀርቡላችሁ ይችላል ሲሉ አስጠነቀቁ። ያልተለመዱ ነገሮች በኤቲኤም አካባቢ እየታዩ እንደሆነ አብራሩ።

ግን የኮስሞስ ባንክ ሰዎች ምንድነው የምታወሩት በሚል ቸል አሉት ማስጠንቀቂያውን ነገሩ ሊገባቸው አልቻለም። ምክንያቱም እነርሱ ሲስተም ላይ የሚታይ ምንም የተለየ ነገር የለም።

ከግማሽ ሰዓት በኋላ ቪዛ ኩባንያ በድጋሚ ወደ ኮስሞስ ደወለ።

" እኔ ጋ የሚታዩ ምልክቶች ጤናማ አይመስሉም፤ ለማንኛውም ሁሉምን ኤቲኤም ማሽኖቻችሁን ለጊዜው ከጥቅም ውጭ አድርጉ " አላቸው።

ይህ ለኮስሞስ ባንክ ብዙ ዋጋ የሚያስከፍል ውሳኔ ቢሆንም ምክሩን ተቀብለው ኤቲኤም ማሽኖቻቸውን ዘጉ።

እንዲያም ሆኖ ዘግይተዋል። ኮስሞስ ባንክ በዚያች ሁለት ሰዓት ብቻ 14 ሚሊዮን ዶላር ተዘርፈው ነበር።

ይህን ዘረፋ ማን አቀነባበረው ?

ይህ ዘረፋ በ28 አገሮች ውስጥ በሚገኙ ኤቲኤም ማሽኖች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት የተፈጸመ ነው።

- ሩሲያ፣
- አሜሪካ፣
- ካናዳ፣
- ዩናይትድ ኪንግደም፣
- ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ይገኙበታል።

ሂደቱ በሰሜን ኮሪያ ጠላፊዎች መመራቱ እንደተደረሰበት ተነግሯል።

የዝርፊያው አቀናባሪዎች ላይ ከመደረሱ በፊት የባንኩ ሰዎች ለምን በርካታ ሰዎች #በተመሳሳይ ሰዓት ወደ ኤቲኤም ማሽን ሄደው ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚወስዱ ግራ ገብቷቸው ነበር።

የዘረፋው መርማሪ፣ “እኛ እንዲህ ዓይነት ዘረፋ ይኖራል ብለንም አስበን አናውቅም” ይላሉ።

የደኅንነት ካሜራ (ሲሲቲቪ) ምስሎችን በመጠቀም የሕንድ መርማሪዎች ለጊዜው 18 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋል ቻሉ። እነዚህ ሰዎች ተራ ሰዎች ናቸው። ሾፌሮች፣ የቡና ቤት አስተናጋጆች፣ ጫማ ጠራጊዎች ይገኙበታል።

እነርሱ ለፊልም ቀረጻ መመልመላቸውን እንጂ ማን እየተጠቀመባቸውን እንደነሆ አያውቁም ነበር።

በመጨረሻ ከዚህ ጥንቅቅ ካለ ዘረፋ ጀርባ ያለው ‘አልአዛር’ የተሰኘው የሰሜን ኮሪያ ጠላፊዎች ቡድን እንደሆነ ተደረሰበት።

እንዴት ግን ቡድኑ በ28 አገራት ዘራፊ ሊያሰማራ ቻለ ?

ዘራፊና አዘራፊን አገናኝ ደላላ ፦

" አልአዛር " በሚል የሚጠራው የዘራፊዎች ቡድን የሰሜን ኮሪያ የወታደራዊ ደኅንነት መሥሪያ ቤት የሚመራው ነው ይባላል።

" አልአዛር " የሚለውን ስም ያገኘውም ከመጽሐፍ ቅዱስ ሞቶ ከተነሳው አልአዛር ነው።

የእነርሱ የኮምፒውተር ቫይረሶች አንዴ ከገቡ ሁሉን ነገር ይገድላሉ። ኮምፒውተር ሲስተሙን መልሰው መቀስቀስ የሚችሉት እነርሱ ብቻ ናቸው። ከእዚሁ ተግባራቸው ጋር ተያይዞ ነው አልአዛር የሚለው ስያሜ የተሰጣቸው።

ከዚህ ቀደም፦
- ሆሊውድን፣
- ሶኒ ፒክቸርስን እና ሌሎችንም ግዙፍ መሥሪያ ቤቶች መረጃ ዘርፈዋል።

ከባንግላዴሽ ባንክ አንድ ቢሊዮን ዶላር ለመዝረፍ ሞክረዋል።

ሰሜን ኮሪያ ይህ " አልአዛር " የተሰኘው ቡድን በአገሬ ስለመኖሩ አላውቅም ስትል ታስተባብላለች።

ቡድኑ (አልአዛር) ኮስሞስ ባንክ ላይ ለፈጸመው ዘረፋ የተጠቀመው " ጃክፖት " የሚባለውን ስልት ነው። ይህ ስም የተሰጠው ልክ እንደ መቆመሪያ ማሽን ኤቲኤም ገንዘብ እንዲተፋ ስለሚያደርግ ነው።

" አልአዛር " ቡድን ይህን ስልት በተግባር ከማዋሉ በፊት የተመሳሰለ ኢሜይል ወደ ባንኩ ሰዎች በመላክ እንዲከፍቱት ካደረገ በኋላ ወደ ባንኩ ሲስተም ሰርጎ መግባት ችሏል።

ከዚያም የባንኩን የቁጥጥር ሥርዓትን ካሉበት ሆነው ማዘዘ ቻሉ።

ይህ መቆጣጠሪያ ባንኩ የገንዘብ ወጪ ጥያቄ ሲቀርብለት ማሽኑ ገንዘብ እንዲተፋ የሚያዝ ሥርዓት ነው።

ማለትም ከየትኛውም የዓለም ክፍል ከሚገኝ ኤቲኤም የገንዘብ ትዕዛዝ ቢመጣ ሰርሳሪዎቹ ማሽኑ ገንዘቡን እንዲለቀው ማድረግ ያስችላቸዋል።

የማይችሉት አንድ ማሽን ምን ያህል ገንዘብ መልቀቅ እንዳለበት መወሰን ነበር። ብዙ ገንዘብ ለማውጣት ደግሞ የግድ ብዙ ካርድ ማተም ነበረባቸው።

የሚቀራቸው ተመሳሳይ ነው። ይህን የሚሠራ ሌላ ድርጅት ተገኘ።

አስገራሚው እሱ አይደለም፤ ሰሜን ኮሪያዊያን እንዴት ከ28 አገር በተመሳሳይ ጊዜ ገንዘብ የሚያወጡላቸው ሰዎችን ማዘጋጀት ቻሉ ? ምክንያቱም ቪዛ ለማግኘት ራሱ ብዙ ችግር የሚያዩ ናቸው።

ይህን ሥራ ለሌላ ለሚተባበራቸው ድርጅት ኃላፊነት መስጠት ነበረባቸው።

በበይነ መረብ በተዘረጋው የጠላፊዎች ግንኙነት አንድ ሰው ይህን ሥራ እንደሚሠራ ገለጸ።

ይህ ቢግቦስ በሚል ስም የሚጠራው መረጃ ቦርቧሪ ግለሰብ ኤቲኤም ካርዶችን ማምረት እና ሰዎችንም ማዘጋጀት እንደሚችል ገለጸ።

በካናዳና አሜሪካ ተቀጣሪ ሊሆኑ የሚችሉ እንዲሁም ከኤቲኤም ማሽን ገንዘብ ማውጣት የሚቸሉ ግለሰቦችን እንደሚመለምል አስታወቀ።

ይህ በትክክል አልአዛር ቡድን የሚፈልገው አገልግሎት ነበር። ቢግቦስ እና አልአዛር አብረው ጥምረት ፈጠሩ።

ቢግቦስ ለ14 ዓመታት በስርቆት የተሰማራ ማንነቱ ሳይታወቅ የቆየ ግለሰብ ነበር። የሆነ ወቅት ላይ ማንነቱ ተደርሶበት አሜሪካ ውስጥ በመኖርያ ቤቱ ሳለ ተይዞ አሁን ዘብጥያ ወርዷል። የ35 ዓመት ካናዳዊ ነው።

እርሱን መያዝ ቢቻልም የባንኩ 14 ሚሊዮን ዶላር ግን እስከወዲያኛው ቀልጦ ቀርቷል። እነዚህ የሰሜን ኮሪያ ሰርሳሪዎች በፍጹም ዝቀተኛ ገንዘብ ላይ ጊዜያቸውን አያጠፉም። እንዲያውም አሁን አሁን ላይ ትኩረታቸውን ወደ ክሪፕቶከረንሲ አዞረው ወደ 3.2 ቢሊዮን ዶላር ዘርፈዋል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት አልአዛር የተባለውን የዓለም ግዙፍ የባንክ ዘራፊ ቡድን ብሎ ይጠራዋል ለዚያውም ያለ አንዳች የጦር መሣሪያ።

Credit : BBC AMHARIC

20/02/2023

💻 ኮምፒውተሬ በማልዌር መያዙን እንዴት አውቃለሁ?

በኮምፒተርዎ ላይ የሚከተሉትን ምልክቶች ካገኙ ኮምፒውተርዎ በማልዌር ተበክሏል፡-

- የእርስዎ PC ፍጥነት ይቀንሳል
- ብልሽቶች ይከሰታሉ
- ያልተለመዱ የስህተት መልዕክቶች
- የሚረብሹ ማስታወቂያዎች ይታያሉ
- Pop-up መልዕክቶች
- Control Panel መክፈት አትችልም

🤝 በጣም የተለመዱት የማልዌር ጥቃቶች የትኞቹ ናቸው?

በጣም የተለመዱት የማልዌር ጥቃቶች Trojan Horse,Virus, Spyware, Ransomware እና Worm ናቸው።

✅ የማልዌር እንዴት ማስወገድ ይቻላል?

የማልዌር ማስወገጃ መሳሪያን ተጠቅመን እነዚህን ማልዌርዎችን ማስወገድ እንችላለ።
ምርጥ የማልዌር ማስወገጃ ሶፍትዌሮች በጥቂቱ፦
- TotalAV
- Restoro
- Outbyte PC Repair
- Avira
- Malwarebytes
- HitmanPro
- Malware Hunter
- Malwarefox

☑️ እንዴት መጠቀም እንዳለብን ከታች ማየት ይቻላል፡-

1) ከላይ ከተሰጠው ዝርዝር የሚወዱትን ማንኛውንም የማልዌር ማስወገጃ መሳሪያ ያውርዱ እና ይጫኑ

2) ከጫኑ በኋላ ምርቱን Activate ያድርጉ ፤ ወይም crack የሆኑ ተጠቀሙ(but risk አለው)
3) ሶፍትዌሩን ይክፈቱ

4) አሁን መላውን system ከማልዌር፣ ቫይረሶች እና ሌሎች ስጋቶች ለመፈተሽ scanning ያስጀምሩ።

5) Scanninጉ እንደተጠናቀቀ፣ ሶፍትዌሩ system ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን ከሚያስፈልጉ solution ጋር ያሳያል።

6) አንዴ ካረጋገጡ በኋላ፣ action ያስጀምሩ እና ማልዌሮቹን ማጥፋት ይጀምራል።

Please Join Our Telegram Channel

27/10/2022

አሁን ባለንበት ዓለም እንደ ዳታ የሚፈለግ ነገር የለም። ምክንያቱም እናንተን በደንብ ለማወቅ ይረዳቸዋል።

በቅርብ አንድ የታዘብኩት ነገር፣ ለስራ apply ስናረግ CVችነ ላይ ስላለው data ምንም አንጨነቅም። እስቲ መለስ ብላችሁ check አድርጉ። እናንተ የት እንደ ተወለዳችሁ፣ መቼ እንደ ተወለዳችሁ፣ ስልክ ቁጥር፣ hobbieችሁ፣ እና ብዙ dataዎች እንሰጣለን። ይሄ ደግሞ እኛን target ለሚያደርጉ ሰዎች ብዙ ጠቀሜታን ይሰጣል።

እባካችሁን ለስራ ስታመለክቱ ጥንቃቄ ብታደርጉ የተሻለ ነው። እዛ ላይ ማስቀመጥ ያለባችሁን ዳታ ሁሌም check አድርጉ።

21/10/2022

ዛሬ ላይ እንደ ቀልድ የምናያቸው፣ የስልክ ፣ የባንክ፣ የመታወቅያ ቁጥሮች እኛን ማጥቃት ለሚፈልጉ በcyber ዓለም ውሰጥ በጣም ብዙ ጥቅም ይሰጣቸዋል።

ለምሳሌ፣ የስልክ ቁጥራችሁን አንድ ሰዉ ቢያገኝ እናንተ ምትጠቀሙት አገለግሎቶች እነደነ ቴሌብር፣ ወይም ከባንክ ነው ምንደውለዉ ይያሉ ሊያሳስቷቹ ይችላሉ።

ሁሌም ብሆን ስልካቹን ከመስጠታቹ በፊት ለምን እንደ ሚፈልገው እርግጠኛ ሁኑ።

ባለማወቅ የሳይበር ተጋላጭ አንሁን።

02/05/2022

Bitcoin Kan itii fuufe... Kutaa 2ffaa

Ergaa Kiriiptookaarensii argatanii booda akkamitti eeggattu?
Qaabenyii kiriipto furtuu dhuunfaa(private key) kan itiin adda isin baasu barbaada. Yoo furtuu keessan dagatan kiriiptookareensii keessan ni dhabdu. akkasumas namni adda biraan yoo furtuu keessan kana baree kooyini keessan isin jalaa fayyadamuu ni danda'a.

Namoonni hedduun kooyini isaanii eeguuf waaleetii dijitaalaa fayyadamu. Waaleetii kana iddoo kooyini keessan argataan irraa argaachuu dandeessuu. Inni kuni garuu, yoo daldala kooyini keessa seentan deebistanii waan gurgurtaaniif filannoo gaarii tahuu danda'a. Garuu, kooyini keessan yeroo dheeraaf of harka tursuu barbaaddu taanan kuusaa mataa keessanni isin barbaachisa jeechudha.

Yeroo jalqabaaf biyyi Bitcoin seera isee keessatti fuudhate El Salvador yeroo taatu, amma garuu biyyoonni akka Kuubaa (Cuba) fi Chaayinaa(Chaina) seera isaani keessatti eyyamanii jiru.

Akka gabaa amma jiruutti gaatiin kooyini bebbeekamo kana fakkaata.
Biitkooyini 1 = Doolaara 38,781.53
Iteeriiyemi(Ethereum ) = Doolaara 2,814.38

Teekinoloojii adda biraan walitti deebina.

02/05/2022

Kiriiptookaarensii - Cryptocurrency

Kutaa 1ffaa
"Cryptocurrency"n maaliidha?

Yeroo ammaa kanatti teekinoloojiwwan bayy'ee bebbeekamoo keessaa "Cryptocurrency"n isa tokkodha. Kiriiptookaarensiin mallaqa dijitaalaa yeroo tahu, neetiwoorkii kompiitaraa fayyadamuun to'annaa giddu-galeessa kan akka Mootummaa yookaan Baankii tokko malee sochii isaa kan geggeessudha. Yeroo ammaa kanatti gosoota kiriiptookaarensii hedduun kan jiran yoo tahus, bayy'ee beekamoo kan ta'an keessaa tokko biitkooyinidha. Biitkooyini(bitcoin) bu'uurri isaani teekinoloojii biilook-chayin(bilokchian) jedhamu kan tarree bilookota waliitti fuufinsaan guddaata adeeman irraa kan ijaarameedha. Bilookoonni kun daataa dhabbataa baasii fi galii kuusuu akkasumas kooyinichii kan eenyuu akka tahe enyuumaasa adda baasuun kuusee ka'a. Kana jechuunis namoonni koyiinii qaban koppii gochuu fi irra deddeebiin akka hin fayyadamnee kan dhorkuudha.

Karaa salphaan kiriiptookaarensii itti argachuu dandeenyu kara "mining" (kooyin daddabarsuu) jedhamuunidha. 'Mining'n humna hedduu kan barbaadudha, jechuunis koompiteera guyyaa guyyaatti fayyadamnuun rawwachuun kan danda'amu miti. Kanaafuu, 'Data Center' hojjeechuun koompiteeronni hedduun akka isaan akka tokkotti hojjettan gochuun yeroo daddabarsa kooyini rawwaatan abbuummaa kooyinichaa neetiwoorkii irraatti qulqulleessuun bakka daddabarsa rawwaatu koompiitarri keenya badhaasa kooyinii haaraa uumaamu argaata jechuudha. Namoota meeshaa kana hunda qopheessuu hin dandeenyeef karaa salphaan itti kooyinii argatan warreen qaba irraa bituunidha.

Yeroo ammaa kanatti gosoota kooyinii 19,000 oltu jiruu, isaan keessa muraasin:- Bitcoin, Ethereum, Cardano, Litecoin, Solana, Dogecoin, Stablecoin fi kkf ni jiruu. Kana keessaa tokkoo irraatti inveestii gochuu ni dandeessuu.

Kutaa 2ffaan itti aanee jira dubbiisaa.

04/04/2022

Kompiitarri Akkamitti Hojjeta? Nama Waliinoo Akkamitti walii gala?


Kompiitarri akkuma namaa Afaan mataa isaa qaba. Akkuma namni afaanoota gosa adda addaa qabu kompiitarris afaanoota bayyee qaba. Kompiitaara keenya ajajuu gaafa barbaadnu saganteessu qabna kuniis 'programming' jedhamuun bekaama.

💠 'Programming' Maaliidha?
Programming n ogummaa karaa oggeessa kompiiteeraatin kan argamu yoo tahu , Innis dandeetii kompiitaarri wanta barbadame tokko akka hojjetu taasisuuti.
💠Afaan Programming Jechuunhoo?
Afaan programmingn Abbaa barreesurraatti huunda'uun bakka bu'eewwaan adda addaa fayyadaamuun qaamni kompiiteeraa hojii barbadamu akkaanni hojjetuu gochuudha.

💠'Programming' gosa sadiitu jiru:

1: Procedural Programming( waldura dubaan kan hojjetuu)
2: Structured Programming ( 'function' irraa deddeebiin fayyadaamuu dandenyudha fkn : c language...)
3: Object Oriented programming (OOP) (kuun piroogiramichi yuuniitoota ofdanda'an irraa kan ijaaramuufi wanti hundii kan wantootati (objects) fakkeeffamuudha. Fkn: c++,java,c #...)

>>> to learn more please join ET-Cybersers

01/04/2022

የስልኮ ዳታ ከመጥፋት ይታደጉ - Save your private data from being lost
You can save your device data including photos, messages, contacts and others even if your mobile device is lost or damaged.
join us at https://www.youtube.com/watch?v=ECOlRisJFjc

31/03/2022

Join our YouTube and TikTok channel

(Classifications of Hacker)     ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️🔸ባላቸው የአመለካከት እና የክህሎት ደረጃ ላይ በመመርኮዝ, ጠላፊዎች የሚከተሉትን ዓይነቶች ይመደባሉ.🔰 wh...
28/03/2022

(Classifications of Hacker)

⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️

🔸ባላቸው የአመለካከት እና የክህሎት ደረጃ ላይ በመመርኮዝ, ጠላፊዎች የሚከተሉትን ዓይነቶች ይመደባሉ.

🔰 white hat hacker (ነጭ ኮፊያ ጠላፊ ): እንደ ጥቃተኛ ጠላፊ የሚታወቀው ስሆኑ እንደ ምርመራ የመሳሰሉት ለድጋፍ ዓላማዎች ብቻ የሚጠቀም ሰው ነው. እንደ እነዚህ አይነት ጠላፊዎች የመረጃ ስርዓታቸው ደህንነት ለማረጋገጥ በብዙ ድርጅቶች ይከራያሉ.

🔰Black hat Hacker: ጥቁር ኮፊያ ጠላፊ (እንደ crackም ይታወቃል) እሱ ማለት ነው
ሁልጊዜ ክህሎቹን ለጥቃት አላማዎች ይጠቀማል. የጥቁር ጠረፍ ጠላፊዎች ዓላማ የመረጃ ሥርዓቶችን በማበላሸት ገንዘብ ለማግኘት ወይም የበቀል እርምጃ መውሰድ ነው.

🔰Gray hat hacker: ግራጫ ነጭ ኮፊያ ጠላፊ ከ White hacker
እና Black hat hacker መካከል ይመደባል. እንዲህ ዓይነቱ ጠላፊ ለመከላከልና ለጥቃት ዓላማዎች ክህሎቱን ሊጠቀም ይችላል.

🔰Script Kiddie: የስክሪፕት ኪዲ ሀከሮች ኮምፕዩተሮች እንዴት እንደሚሰሩ እውቀት የሌላቸው ናቸው, ነገር ግን ኮምፒዩተሮች ውስጥ ለመግባት ዝግጁ የሆኑ ፕሮግራሞችን, መሳሪያዎችን እና ስክሪፕቶችን ይጠቀማሉ.

⏩⏩⏩⏩⏩⏩⏩⏩⏩⏩
join our channel➡️➡️

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ET-Cybers posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share