Ethio Global Mind EGM

Ethio Global Mind EGM ለፈጣን መረጃዎች ፔጃችንን Follow ያድርጉ
Dedicated to providing factual, timely, and non-political Global information.

⚽️🌟 Goals scored by 𝐛𝐢𝐠 𝐬𝐮𝐦𝐦𝐞𝐫 𝐬𝐭𝐫𝐢𝐤𝐞𝐫 𝐬𝐢𝐠𝐧𝐢𝐧𝐠𝐬 for Premier League clubs in all competitions: 🇸🇪 Viktor Gyokeres - 15 GO...
02/24/2026

⚽️🌟 Goals scored by 𝐛𝐢𝐠 𝐬𝐮𝐦𝐦𝐞𝐫 𝐬𝐭𝐫𝐢𝐤𝐞𝐫 𝐬𝐢𝐠𝐧𝐢𝐧𝐠𝐬 for Premier League clubs in all competitions:

🇸🇪 Viktor Gyokeres - 15 GOALS
🇫🇷 Hugo Ekitike - 14 GOALS
🇧🇷 Joao Pedro - 14 GOALS
🇩🇪 Nick Woltemade - 10 GOALS
🇸🇮 Benjamin Sesko - 8 GOALS
🇸🇪 Alexander Isak - 3 GOALS

𝐖𝐡𝐨 𝐢𝐬 𝐭𝐡𝐞 𝐛𝐞𝐬𝐭 𝐬𝐭𝐫𝐢𝐤𝐞𝐫? 👀✨

ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች (እንደ ፌስቡክ፣ ቲክቶክና ዩቲዩብ ያሉት) የግል ተቋማት ቢሆኑም፣ የሚንቀሳቀሱት ግን እንደተመሠረቱበት አገር ሕግና ፖሊሲ ነው። በተመሳሳይም ሲድሮ (SYDR...
02/23/2026

ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች (እንደ ፌስቡክ፣ ቲክቶክና ዩቲዩብ ያሉት) የግል ተቋማት ቢሆኑም፣ የሚንቀሳቀሱት ግን እንደተመሠረቱበት አገር ሕግና ፖሊሲ ነው። በተመሳሳይም ሲድሮ (SYDRO) በአቶ አዶናይ ባለቤትነትና በ Infra Tech Software PLC የበለጸገ አገር በቀል (ቲክቶክ መሰል) መተግበሪያ ሲሆን፣ አሠራሩም የሚሆን በአገራችን ሕግና ፖሊሲ ነው።

እንደማንኛውም አገር፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) የትውልድንና የአገርን ጥቅምና ደህንነት ለማረጋገጥ ሲል፣ የውስጥና የውጪ የመረጃ ስርጭት ጉዳቶችን እንደሚከላከል የሚታወቅ ነው። SYDRO ግን ልክ እንደEBS TV በግል ቁጥጥር የሚመራ እንጂ የመንግስት ተቋም አለመሆኑን ልብ ይሏል።

ሲጠቃለልም፤ ይሄን እንደአገር ያገኘነውን መልካም እድል፣ ሁላችን ተባብረን ሶፍትዌሩን ስራ ላይ በማዋል ከአፍሪካ ቀዳሚ እንሁን። በቀጣይ የሶፍትዌሩን ዝርዝር አሠራር በቀላል አማርኛ ይዤላችሁ እቀርባለሁና ያድርጉ:: በርታልን አዶናይ 💪🏿

  EGM  🇪🇹👌በሰሜን ጎጃም ዞን ባህርዳር ዙሪያና ሰ/ሜጫ አካባቢ በተሰሳተ መንገድ በጫካ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ ተቀበሉ። እነ ቻላቸው አስና...
02/23/2026

EGM 🇪🇹👌

በሰሜን ጎጃም ዞን ባህርዳር ዙሪያና ሰ/ሜጫ አካባቢ በተሰሳተ መንገድ በጫካ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ ተቀበሉ።

እነ ቻላቸው አስናቀ(ቻቻ) እና ቢኒያም ጋሻው የሚመሩት በጫካ ሲንቀሳቀስ የነበረው የታጣቂው ቡድን አባላት የሰላምን አማራጭ በመቀበል በምህረት ለመንግሰት እጅ ሰጠዋል።

የታጠቁ የቡድኑ አባላት መርዓዊ ከተማ ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን
1ኛ- 10 አለቃ ቻላቸው አስናቀ (ቻቻ) የበፊቱ የ1ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረ የአሁኑ የ109 ኛ ኮር ዘ መቻ መምሪያ ሀላፊ
2ኛ- ቢኒያም ጋሻው የብርጌዱ ዘመቻ መምሪያ፣
3ኛ-ጋሻው መኳንት የ11 ኛ ክ/ጦር የሰው ሀይል ሀላፊ
4ኛ-ዘላለም አዱኛ የቅንባባና አካባቢዋ የሻለቃዋ ኦርዲናስ
5ኛ-እንዳላማው ገብሬ የቅንባቤ ሻለቃ ዘመቻ መምሪያ ሀላፊ
6ኛ-ጋሻ ታደለ -የደጉ በላይ ሻለቃ መሪ እጅ ከሰጡት የቡድኑ ዋና አመራሮች ሲሆኑ 22 የቡድኑ አባላትን በመያዝ በዛሬው እለት ገብተዋል።

የታጠቁ ኃይሎች ለመንግስት እጅ ሲሰጡ ከእነ ሙሉ ትጥቃቸው ሲሆን 1 ብሬን፣ 11 ክላሽ፣2 ስኬስ፣2 ፋል፣ 4 ቦንብ፣1የመገናኛ ሬዲዮ፣9 የደረ ትጥቅ ፣ 242 የክላሽ ጥይት ፣ 95 የብሬን ጥይት ፣32 የክላሽ ካዘና፣2 የፋል ካዘና፣m14ጥይት 19 በመያዝ ነው ለመንግስት እጅ የሰጡት።

በአቀባበል ፕሮግራሙ የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሰፋ ጥላሁን እኳን ደህና ጣችሁ በማለት ወደ ህዝባችሁ መቀላቀላችሁና የሰላምን አማራጭ በመቀበላችሁ ለህዝቡ ትልቅ እፎይታን ይሰጣል ብለዋል።

መንግስት በሚሰጠው አቅጣጫ መሠረት የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ እንድታበረክቱ ይደረጋል ብለዋል።

በብልጽግና ፓርቲ የ ሰሜን ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማስተዋል አሰሙ በበኩላቸው የሰላምን ዋጋ ተረድታችሁ ሰላምን ስትቀበሉ ህዝባችሁን ለመካስ ያላችሁን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

ታጣቂ ቻላቸው አስናቀ በተሳሳተ መንገድ የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርገን የወጣንበት መንገድ ትክክል አለመሆኑን እና ከሻቢያና ህወሃት ጋር አብሮ መስራት ህዝባችንን ይባስ መበደላችንን ስለተረዳን ሰላምን መርጠናል ብለዋል።

ስለሆነም መንግስት በሚሰጠን አቅጣጫና ተልዕኮ መሠረት የበደልነውን ህዝባችን ለመካስ ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል።

በአቀባበል መርሃ ግብሩ የሰሜን ግጃም ዞን ዋና አስተዳዳራ አቶ አሰፋ ጥላሁን፣የሰሜን ጎጃም ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ማስተዋል አሰሙ፣የሰ/ጎጃም ዞን ም/አስተዳዳሪ እና ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ በለጠ ጥጋቡ፣የዞኑ ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ አንዷለም ፈንቴ፣የዞኑ ሰላምና ፀጥታ ሀላፊ አቶ ገብረስላሴ ታዘብ፣እንዲሁም የአድማ መከላከል አመራር ኮሚሽነር አንዷለም አስረስ፣የመርአዊ ከተማ ከንቲባ አቶ ብርሀኑ አበረና የከተማ ስራ አስፈፃሚና አመራሮች ተገኝተዋል።

የጀርመንኛ ቋንቋ ካልተማረ ደሞዝ ሚቀንስበት ተጫዋች! ቢልድ የተሰኘው የጀርመን ጋዜጣ በክረምቱ ሊቨርፑልን ለቆ ባየርሙኒክን ስለተቀላቀለው ሊውስ ዲያዝ ለየት ያለ መረጃን አጋርቷል። እንደጋዜጣ...
02/23/2026

የጀርመንኛ ቋንቋ ካልተማረ ደሞዝ ሚቀንስበት ተጫዋች!

ቢልድ የተሰኘው የጀርመን ጋዜጣ በክረምቱ ሊቨርፑልን ለቆ ባየርሙኒክን ስለተቀላቀለው ሊውስ ዲያዝ ለየት ያለ መረጃን አጋርቷል። እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነም ዲያዝ በባየርሙኒክ በፈረመው ኮንትራት ላይ ቋንቋ መልመድ እንደግዴታ የተቀመጠበት ሲሆን የቋንቋ ትምህርት እየተማረ በየጊዜው በሚደረግ ምዘና ለውጥ ካላሳየ ከደሞዙ ላይ ከ5000 እስከ 50,000 ዩሮ ድረስ እንደየሁኔታው እንደሚቀጣ ተቀምጧል።

ተጫዋቹ በሳምንት ለ2 ወይም ለ3 ጊዜ የጀርመንኛ ቋንቋ ትምህርትንም እየወሰደ ይገኛል። ሊውስ ዲያዝ በ21 የቦንደስሊጋ ጨዋታዎች 13 ጎሎች እና 10 አሲስቶች በማስመዘገብ በ23 ቀጥተኛ የጎል ተሳትፎ ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ እንደሚገኝ ይታወቃል።

✍️ EGM

(EGM) ብራዚላዊው የማንቼስተር ዩናይትድ ኮከብ ካስሚሮ…አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018  በማንቼስተር ዩናይትድ ቤት ምርጥ ብቃታቸውን እያሳዩ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው ብራዚላ...
02/23/2026

(EGM) ብራዚላዊው የማንቼስተር ዩናይትድ ኮከብ ካስሚሮ…

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2018 በማንቼስተር ዩናይትድ ቤት ምርጥ ብቃታቸውን እያሳዩ ከሚገኙ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው ብራዚላዊው ተጫዋች ካስሚሮ፡፡

የእግር ኳስ ሕይወቱን በሀገሩ ክለብ ሳኦፖሎ የጀመረው ካስሚሮ የቡድኑን ሚዛን በመጠበቅ ችሎታው ይታወቃል፡፡

በወቅቱ በተከላካይ አማካይ ስፍራ ላይ ባሳየው ድንቅ እንቅስቃሴ የሪያል ማድሪድን ቀልብ የሳበ ሲሆን÷ በ2013 በውሰት ውል ሎስብላንኮቹን መቀላቀል ችሏል፡፡

ካስሚሮ ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ በኋላ በዋናው ቡድን ውስጥ የመጫወት ዕድል ባለማግኘቱ በውሰት ለፖርቶ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡

በፖርቶ ቆይታው ካስሚሮ አስደናቂ እንቅስቃሴ በማድረግ ቡድኑን በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ለሩብ ፍፃሜ ማብቃቱ አይዘነጋም፡፡

ካስሚሮ በፖርቶ ባሳየው ምርጥ ብቃት ሪያል ማድሪድ በ2015 ተጫዋቹን ወደ ሳንቲያጎ ቤርናባው መልሶ አምጥቶታል፡፡

ካስሚሮ ወደ ክለቡ ከተመለሰ በኋላ ለሪያል ማድሪድ ስኬት ወሳኝ ሚና በመጫወት ዓለም ላይ ካሉ ምርጥ የተከላካይ አማካዮች አንዱ መሆን ችሏል፡፡

ብራዚላዊው ተጫዋች በሪያል ማድሪድ በነበረው ቆይታ አምስት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ፣ የስፔን ላሊጋ፣ የዓለም ክለቦች፣ የኮፓ ዴል ሬይን ጨምሮ የተለያዩ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡

በሪያል ማድሪድ ቤት በቆየባቸው ዓመታት ከክሮሺያዊው ሉካ ሞድሪች እና ከጀርመናዊው ቶኒ ክሩስ ጋር የነበረው ጥምረት አስደናቂ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በሦስቱ ተጫዋቾች አስገራሚ ጥምረት የሪያል ማድሪድ የመሀል ሜዳ ክፍል ለዓመታት አስፈሪ ሆኖ መቆየትም ችሏል፡፡

ካስሚሮ ሪያል ማድሪድን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀላቀል በቂ የመሰለፍ ዕድል ማግኘት ባይችልም በድጋሚ ቡድኑን ከተቀላቀለ በኋላ ግን የቡድኑ አይነኬ ተጫዋች ለመሆን በቅቷል፡፡

ካስሚሮ ለሪያል ማድሪድ በሁሉም ውድድር 336 ጨዋታዎችን አድርጎ 31 ግቦችን አስቆጥሮ 29 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡

በስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ በዋንጫ የታጀቡ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ በ2022 የእንግሊዙን ክለብ ማንቼስተር ዩናይትድን ተቀላቅሏል፡፡

ካስሚሮ ማንቼስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለ በኋላ የካራቦ ካፕ እና የኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫዎችን አሳክቷል፡፡

በዚህ ወቅት ለማንቼስተር ዩናይትድ አስፈላጊ እና ወሳኝ ከሆኑ የቡድኑ ተጫዋቾች መካከል ካስሚሮ አንዱ ነው፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ የካስሚሮን ግልጋሎት በማያገኝባቸው ጨዋታዎች በመከላከሉ እና የቡድኑን ሚዛን በማስጠበቅ ረገድ ሲቸገር ይስተዋላል፡፡

ካስሚሮ በሚሰልፍባቸው ጨዋታዎች የቡድኑን ሚዛን በመጠበቅ፣ ለተከላካዮች ሽፋን በመስጠት እና የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ በመሳተፍ ለማንቼስተር ዩናይትድ ትልቁን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ሀገሩን ከፈረንጆቹ 2011 ጀምሮ እያገለገለ የሚገኘው ካስሚሮ ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን እስካሁን ባደረጋቸው 82 ጨዋታዎች 8 ግቦችን ያሳቆጠረ ሲሆን÷ በ2019 የኮፓ አሜሪካ ዋንጫ አሳክቷል፡፡

አሁን እያሳየ በሚገኘው ምርጥ እንቅስቃሴ ለ2026 የዓለም ዋንጫ ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን እንደሚጠሩ በአሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ ዋስትና ካገኙ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው።

በሪያል ማድሪድ በዋንጫ የታጀቡ ስኬታማ ዓመታትን አሳልፎ በማንቼስተር ዩናይትድ ምርጥ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው ካስሚሮ በፈረንጆቹ 1992 በዛሬዋ ዕለት ነው የተወለደው፡

A Viktor Gyokeres and Eze rocket 🚀Arsenal win 4-1 at Tottenham Hotspur Stadium!
02/23/2026

A Viktor Gyokeres and Eze rocket 🚀

Arsenal win 4-1 at Tottenham Hotspur Stadium!

Some are asking why I wrote my appeal to peace in Amharic. I chose Amharic as it is the primary working language of Ethi...
02/23/2026

Some are asking why I wrote my appeal to peace in Amharic. I chose Amharic as it is the primary working language of Ethiopia and widely understood. Including all five working languages - Tigrigna, Amharic, Afaan Oromo, Somali, and Afar - would be beneficial. Here you go…

ጦርነት ትርፉ ሞት፣ ጥፋት፣ መፈናቀልና ረሃብ ብቻ ነው! ፖለቲካዊ መፍትሄ ሁሌም አለ። እውነተኛ ጀግኖች ሰላምን ይመርጣሉ። ለሰላም ዕድል እንስጥ! 🕊️

ኲናት ትርፉ ሞት፣ ጥፍኣት፣ ምዝንባልን ጥሜትን ጥራይ እዩ! ፖለቲካዊ መፍትሒ ወትሩ ኣሎ። ናይ ሓቂ ጀጋኑ ሰላም ይመርፁ። ንሰላም ዕድል ንሃብ! 🕊️"

Waraanni bu’aan isaa du’a, badii, buqqa’insaafi beela qofa! Furmaanni siyaasaa yoomiyyuu jira. Goonni dhugaan nagaa filata. Nagaadhaaf carraa haa kenninu! 🕊️

Dagaalku waxa laga dhaxlaa oo kaliya dhimasho, burbur, barakac iyo macaluul! Xal siyaasadeed mar walba waa uu jiraa. Geesiyaasha dhabta ahi waxay doortaan nabadda. Aan fursad siinno nabadda! 🕊️

Carbi dubuk rabaay, finqaay, dufuu kee qululu bahta! Umman way siyaasâ fidga tan. Numma agiira salaam doorita. Salaam saami nacay! 🕊️

Courage for Peace.
Peace is the best medicine.
by WHO president Tedros

ሰበር መረጃ!!ያልተጠበቀ ግጥምጥሞሽ የሶስቱ መሪዎች ጥምረት! የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት እና የአዲሱ ቀጠናዊ ጥምረት ግጥምጥሞሽ!!የእስራኤሉ ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ አዲስ ጥምረት ይዘው...
02/23/2026

ሰበር መረጃ!!
ያልተጠበቀ ግጥምጥሞሽ የሶስቱ መሪዎች ጥምረት!

የኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎት እና የአዲሱ ቀጠናዊ ጥምረት ግጥምጥሞሽ!!

የእስራኤሉ ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ አዲስ ጥምረት ይዘው መጥተዋል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የጀመረችው ጥረት፣ እስራኤል በቀይ ባሕር ላይ ከምትዘረጋው አዲስ የኢኮኖሚ እና የደህንነት ኮሪደር ጋር ስትራቴጂካዊ ውህደት እየፈጠረ መሆኑ ተመልክቷል።

እስራኤል፣ ህንድ እና አውሮፓን የሚያስተሳስር የኢኮኖሚ መስመር ለመጠበቅ በቀይ ባሕር ላይ እንደ ኢትዮጵያ ያለ ጠንካራ አጋር ትፈልጋለች።

እስራኤል ከሶማሌላንድ ጋር የምታደርገው መቀራረብ፣ ኢትዮጵያ በዚያው ቀጠና የባህር ኃይል ለመገንባት ካላት ዕቅድ ጋር በቀጥታ ይገጣጠማል።

የሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባሕር ላይ የሚፈጥሩትን ስጋት ለመመከት፣ የኢትዮጵያ በባህር ዳርቻው ላይ መገኘት ለምዕራባውያን እና ለእስራኤል ስትራቴጂካዊ ፋይዳው የጎላ ነው።

ሂደቱ ግልፅ ነው። አዲስ ዓለም አቀፍ አሰላለፍ እየተፈጠረ ነው። ኢትዮጵያ የባህር በር ትፈልጋለች፤ እስራኤል እና አጋሮቿ ደግሞ ቀይ ባሕርን የሚጠብቅላቸው ጠንካራ ሀገር ይፈልጋሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ በሐዋሳ በነበረ የልዩ ዘመቻ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር
" ከሶማሊያ ጫፍ እስከ ምጽዋ ጫፍ በባሕር የሚያጋጥሙ ሽብሮችን ወንድም ሕዝቦችን ደግፈን ሽብርን ለማስቀረት ልማት ብልጽግናን በቀጠናችን ለማረጋገጥ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጠናው በቂ የሆነ ኤሊት ፎርስ ገንብተናል። ቀይ ቦኔት ለባሾቹ ውጊያ የሚጨርሱ እና ውጊያ የሚያስቀሩ ናቸው።የእኛ ዝግጅት በድፍን አፍሪካ ሰላም ለማረጋገጥ ነው። በቀጠናችን ላሉ አገራት አለኝታ፣ መከታ፣ ጋሻ ለመሆን ነው።" ማለታቸው በጥምረቱ ውስጥ ኢትዮጵያ እንዳለችበት አመላካች ነው።

ሌላው የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ይስሐቅ ሄርዞግ በዚህ ሳምንት በኢትዮጵያ የአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ መዘገቡ ነገሩን ለእውነት የቀረበ ያደርገዋል።

EGM

(EGM) የቴክኖሎጂ እያደር መምጠቅ ዕድል ብቻ ሳይሆን ስጋትንም ይዞ መጥቷል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት (የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኤአይ) እድገት የዓለም ኃያላን መንግሥታትን ጭምር ስጋት ው...
02/23/2026

(EGM) የቴክኖሎጂ እያደር መምጠቅ ዕድል ብቻ ሳይሆን ስጋትንም ይዞ መጥቷል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት (የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ኤአይ) እድገት የዓለም ኃያላን መንግሥታትን ጭምር ስጋት ውስጥ ከትቷል። እንዴት ልንቆጣጠረው እንችላለን? ካልተቆጣጠርነው ምን ሊያስከትል ይችላል? ዓለምስ ወደፊት ምን መልክ ይኖራታል? የሚሉ ጥያቄዎች መነጋገሪያ ከሆኑም ሰነባብተዋል። በተለይ ባደጉት አገራት በሰው ሰራሽ አስተውሎት ምክንያት ሥራችንን ልናጣ እንችላለን በሚል በርካታ ሰዎች ካሁኑ ጭንቀት እየተዳረጉ ነው።

(EGM) #በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ  ቤንዚን በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰማ።የካቲቲ 12 ቀን 20 ዓ.ም በህገ ወጥ መንገድ በባለ ሶስት እግር ባጃጅ ሲዘዋወር  የነበረ ከ400(አራት መ...
02/22/2026

(EGM) #በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ ቤንዚን በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰማ።
የካቲቲ 12 ቀን 20 ዓ.ም
በህገ ወጥ መንገድ በባለ ሶስት እግር ባጃጅ ሲዘዋወር የነበረ ከ400(አራት መቶ) ሊትር በላይ የሆነ ቤንዚን ከነአሽከርካሪው መያዙን የገረሴ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ።

ግለሰቦች ህገ ወጥ ንግድን በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚፈልጉበት መንገድ አድርገው የሚወሰዱ በመሆናቸው ህጋዊ ከመሆን ይልቅ ህገ ወጥነትን ይመርጣሉ ያሉት የገረሴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢ/ር መለሰ ቃውሳ ዛሬ ላይ የተያዘውም ይህ ህገወጥ ቤንዚን የዚሁ ማሳያ ነው በማለት ተናግረዋል።

አያይዘውም አዛዡ እንደገለፁት ህገ ወጥ ንግድ በአገር ዕድገት ላይ የሚያመጣው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ክትትልና ቁጥጥሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በመጨረሻም በማንኛውም ህገ ወጥ ተግባር ላይ በሚሠማሩ አካላት ላይ ህጋዊ ርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ጠቁመው በህገ ወጥ ተግባር ላይ የምገኙ አካላት ከእኩይ ተግባራችሁ እድትቆጠቡ ሲሉም የበኩላቸውን መልዕክት አስተላልፈዋል።

በአሽከርካሪው ላይ ምርመራ እየተጣራ መሆኑንም ገልፀዋል። መረጃው የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው

Big win Liverpool
02/22/2026

Big win Liverpool

Former British PM Boris Johnson calls on the U.K. and European allies to deploy noncombat troops to Ukraine immediately,...
02/22/2026

Former British PM Boris Johnson calls on the U.K. and European allies to deploy noncombat troops to Ukraine immediately, signaling Western commitment to the country’s freedom and independence.

Address

Lake Los Angeles, CA

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Global Mind EGM posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share