03/17/2024
በ Online (ኦንላይን) ትምህርት ለመማር የሚረዱን ሰድሰት ድረገፆች ጥቆማ
በኦንላይን ኮርስ ለመማር እያሰባቹ ከሆነ እና እንዴት መማር እንዳለባችሁ ግልፅ ካልሆነላቹ ይህ ፅሁፍ ጠቃሚን መረጃን ይስጠቹሃል እና ተጋበዙልን:-
⓵ ዩድሚ (Udemy)
በዩዲሚ የኦንላይን መማርያ ድረገፅ ሲሆን በተለያየ ትምህረት ላይ የሚያተኩሩ ከ 50 ሺ ያላነሱ መማርያ ኮርሶች ሲኖሩት አብዛኞቹን በነፃ የሚገኙ ሲሆን ሌሎቹ በትንሽ ክፍያ በወር በ12 ዶላር ጀምሮ ይገኛሉ፡፡ በዚህ ገፅ ለመማር ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ሙያ ዘርፍ ላይ ባለሙያ ከሆኑ ሰለ ሚያውቁት ሙያ ሆነ ሰለ ሚያውቁት የትምህርት ዘርፍ ማስተማር ከፈለጉ ድረ ገፅ ይህን ዕድል ያቀርብሎታል፡፡
⓶ ኤዴክስ(EDX)
ኤዴክስ መማርያ ድረገፅ እንደ ሀርቫርድ እና ብርክሌ ዩኒቨርስቲዎችን የመሳሰሉ በዓለማችን ያሉ ታላላቅ ዩኒቨርሰቲዎች ጋር የሚሰራ ሲሆን፡፡ በኤዴክስ ኮምፕዩተር ሳይንስ፣ ሳይኮሎጂ፣ ቋንቋ፣ ኢንጅነሪግ፣ ባዮሎጂ፣ ማርኬቲንግን ጨምሮ የተለያዩ የትምህርት ዓይነቶችን ማግኘት እንችላለን ፡፡ ኤዴክስ ለሀይስኩል ተማሪዎችም የሚሆኑ ኮርሶች ያስተምራል፡፡ በኤዴክስ ኦንላይን ኮርስን ሲጨርሱ ለተማሩት ትምህርት ማርጋገጫ ስርተፍኬት ከድረገፁ ይሰጦታል፡፡
⓷ ኦፕን ካልቸር(Open culture)
ኦፕን ካልቸር በኦንላይን ላይ ያለ ትልቅ ላይብረሪ ሲሆን በተጨማሪም ኢ ለርኒግ ትምህርት ይሰጥበታል ፡፡ ኦፕን ካልቸር በወስጡ ከሶስ መቶ በላይ ኮርሶችን እና ከአርባ አምስት ሺ በላይ የምስል እና የድምፅ መማርያ ገባቶችን የያዘ ሳይት ሲሆን፤ ሁሉም ኮረሶች ሙሉ በሙሉ ከክፍያ ነፃ ናቸው፡፡
⓸ ኮርሴራ(Courser)
ኮርሴራ በዓለማችን ካሉ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ይሰራል በገፁም ብዙ የትምህርት ዓይነቶችን ይዟል፡፡ በኮረሴራ ከሁለት ሺ በላይ የነፃ እና መጠነኛ ክፍያ የሚጠይቁ ኮርሶች ሲኖሩ፡፡ በኮምፕዩተር ሳይንስ፥ ቢዝነስ እና ሶሻል ሳይንስን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት ዓይነቶች ያገኛሉ፡፡
⓹ አሊሰን (Alison)
አሊሰን በብዙ ተማሪዎች ዘንድ ተመራጭ የሆነ የነፃ የኢ ለርኒግ መማርያ ድረገፅ ነው፡፡ አሊሰን ከትምህርት በተጨማሪ ስራ ለሚፈልጉ እና ሙያቸውን ለማሻሻል ለሚያሰቡ ብሎም የስኮላር ሺፕ ትምህርቶችን ጨምሮ አዳዲስ ቢዝነሶችን መጀመር ለሚፈልጉ ሰዎች አሊስን በውስጡ የተለያዩ ዕድሎችን ይዟል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም አሊሰን የተለያዩ ዝርዝሮች ያሉት ሲሆን የምንፈልገውን የትምህርት ዓይነትም ሆነ ሌሎች አገልግሎቶች ከድረገፁ ማግኘት እንችላለን፡፡
⓺ ኦፕን ለርን (Open Learn)
ኦፕን ለርን ድረገፁ ላይ በተለያየ ሁኔታ የተቀመጡ የመማርያ ግብአቶችን ማግኘት የምንችል ሲሆን፤ በተጨማሪም የኦፕን ለርን ድረገፅ መማር ለምንፈልጋቸው ትምህርቶች ምንነት እና የሚፈጅብን ጊዜ አያይዞም ሰለ እያንዳንዱ ኮርስ ምንነት እና በምን ዙርያ እንደሚያተኩር አጭር ገለፃ ያድጋል፡፡
https://www.udemy.com/
http://www.openculture.com/
https://www.edx.org/
https://www.coursera.org/
https://alison.com/
http://www.open.edu/openlearn/
Udemy is an online learning and teaching marketplace with over 213,000 courses and 62 million students. Learn programming, marketing, data science and more.