Fanos midea ፋኖስ ሚድያ

Fanos midea   ፋኖስ ሚድያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fanos midea ፋኖስ ሚድያ, Information Technology Company, Maych'ew.

አቶ ጌታቸው ረዳ ምስጋና ቀርቦላቸው ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንትነት ተሰናበቱ።ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ...
07/04/2025

አቶ ጌታቸው ረዳ ምስጋና ቀርቦላቸው ከጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንትነት ተሰናበቱ።

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት አቶ ጌታቸው ረዳ ላለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ላበረከቱት አስተዋጽኦ አመስግነዋል፡፡

በተለይ አቶ ጌታቸው የተገኘው ሰላም እንዲጸና ለነበራቸው ከፍተኛ ጥንቃቄና አመራር የፌደራል መንግስት እውቅና እንደሚሰጥ አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይ ሥራዎች በጋራ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለነበራቸው ቆይታም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜዊ አስተዳደር በመሆን ለሁለት ዓመት መርተዋል። አሁን ላይ አዲስ የክልሉ ፕሬዝዳንት እንዲሰየም ሂደት ላይ ነው።

Fanos midea ፋኖስ ሚድያ

[🖼 ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የተላከላቸውን መልዕት ከደቡብ ሱዳን ምክ...
07/04/2025

[🖼 ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የተላከላቸውን መልዕት ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ቦል ሜል እንደተቀበሉ ተናግረዋል፡፡

ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደቡብ ሱዳን ወቅታዊው የጸጥታና የፖለቲካ ችግሮችን ለመፍታት፣ ሁሉን አቀፍ ቀጣናዊ አካሄድ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት መስጠታቸውን ገልጸዋል
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ያላትን የድጋፍ ቁርጠኝነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የተላከላቸውን መልዕት ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ቦል ሜል እንደተቀበሉ ተናግረዋል፡፡

ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደቡብ ሱዳን ወቅታዊው የጸጥታና የፖለቲካ ችግሮችን ለመፍታት፣ ሁሉን አቀፍ ቀጣናዊ አካሄድ እንደሚያስፈልግ አጽንዖት መስጠታቸውን ገልጸዋል፡፡

07/04/2025

| 🇪🇹📹 ጅብና ሰው ወዳጅ የሆኑባት ሐረር

በምስራቋ ኢትዮጵያ ሐረር በየቀኑ ማለት ይቻላል ጅቦች በጎዳናዎች ሲንቀሳቀሱ ማየት የተለመደ ነው።

media

 #በትግራይ ክልል የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ እየተጨናነቁ እንደሚገኙ አለም አቀፉ ተቋም አስታወቀ‼️በትግራይ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች በተ...
07/04/2025

#በትግራይ ክልል የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ማስተናገድ ከሚችሉት በላይ እየተጨናነቁ እንደሚገኙ አለም አቀፉ ተቋም አስታወቀ‼️
በትግራይ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች በተፈናቃዮች ቁጥር መጨናነቃቸውን አለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አይኦኤም ትላንት መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፤ መጠለያዎቹ በተፈናቃዮች ከመጨናነቃቸው ባለፈ እየፈረሱ ነው፣ በዚህም ሳቢያ ለአስከፊ ኑሮ እየተዳረጉ ነው ሲል ገልጿል።

“በየግዜው ተጨማሪ አዳዲስ ተፈናቃዮች ወደ መጠለያ ጣቢያዎቹ በመግባታቸው እየፈረሱ ነው” ብሏል።
መጠለያዎች ለመጨናነቃቸው በዋናነት የተጠቀሰው ምክንያት ደግሞ ቤት ተከራይተው በአከባቢዎቹ ከሚገኙ ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ተፈናቃዮች የሚከፍሉት በማጣታቸው ወደ መጠለያዎቹ በመግባታቸው መሆኑን ጠቅሷል።

በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ መጠለያ ጣቢያዎች ለማዛወር ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የጠቆመው ተቋሙ አስካሁን 21 ትምህርት ቤቶች ላይ ተጠልለው የነበሩ ተፈናቃዮችን ወደ መጠለያ ጣቢያዎች ማዛወር መቻሉን አመላክቷል።

Address

Maych'ew

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fanos midea ፋኖስ ሚድያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share