Hadiya Zone Science and Information Technology Department

Hadiya Zone Science and Information Technology Department Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hadiya Zone Science and Information Technology Department, Information Technology Company, Hossana.

11/09/2023
የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለባለሙያዎች አድቫንስድ  ሥልጠና  መስጠት ጀመረሆሳዕና፡ ሰኔ 7/2015 ዓ.ም  የሀዲያ ዞን ሳይንስና ...
15/06/2023

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለባለሙያዎች አድቫንስድ ሥልጠና መስጠት ጀመረ
ሆሳዕና፡ ሰኔ 7/2015 ዓ.ም የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለባለሙያዎች አድቫንስድ ሥልጠና በሆሳዕና ከተማ መስጠት ጀምሯል።
ስልጠናው የሚሰጠው በ Networking, በ Office machine maintenance, በ Software development እና በ Innovation ርዕሶች መሆኑ በመክፈቻው ወቅት ተገልጿል።
ስልጠናውን ከዞን ማዕከል፣ ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ባለሙያዎች የሚሠለጥኑ ሲሆን፤ ስልጠናው የፈጻሚዎችን የክህሎት ክፍተት ከመሙላት ባለፈ የአሰልጣኞች ስልጠና ስለሆነ ታቅዶ መጀመሩ በመድረኩ ተገልጿል።

የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመተባበር ለወጣቶች ሲሰጥ የቆየዉ የኢንኩቤሺን ማዕከል ስልጠና ተጠናቀቀ ሰኔ 2/2...
09/06/2023

የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በመተባበር ለወጣቶች ሲሰጥ የቆየዉ የኢንኩቤሺን ማዕከል ስልጠና ተጠናቀቀ

ሰኔ 2/2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

ስልጠናዉ ከ 3 ማህበራት ለተወጣጡ 15 ወጣቶች ለ12 ወራት ሲሰጥ የቆየ መሆኑ ተጠቁሟል

በስልጠናዉ ማጠቃለያ የምረቃ መርሃ ግብር የተገኙት የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መንግስቱ በየነ በመልዕክታቸዉ የዛሬ ተመራቂ ወጣቶች በክልል ደረጀ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመረቁ በመሆናችሁ የተሻለ ዕድል ይጠብቃችኋል ነው ያሉት።

ዘርፉ እንደ ሀገር ከ10 ዓመት በላይ ያልተሠራበት በመሆኑ ለተመራቂዎቹ ወጣቶች ተከታታይነት ያለዉ ስልጠና ከተሰጣቸዉና የገበያ ትስስር በመፍጠር ባለድርሻ ተቋማት ተቀናጅተዉ ከሠሩ ከዘርፉ የሚፈለገዉን ዉጤት ማስመዝገብ ይቻላል ብለዋል።

የሀዲያ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ካይረዲን ራመቶ ባስተላለፉት መልዕክት በቴክኖሎጂ ዘርፍ የፈጠራ ሥራን በማሳደግ ለህዝባችን የሚሰጠዉን አገልግሎት ማዘመን እንደምገባ ገልፀዋል።

የመንግስት ሠራተኞች ለተገልጋዩ ማህበረሰብ የምሰጠዉን አገልግሎት በተገቢ ሁኔታ ለማቅረብ በቴክኖሎጂ መታገዝ መሆን አለበት ያሉት አቶ ካይረዲን ራመቶ

ዛሬ የሚመረቁ ወጣቶች በሰለጠኑበት ሙያ ለራሳቸዉና ለአካባቢዉ ማህበረሰብ የተሻለና ተመጣጣኝ አገልግሎት በመስጠት በዘርፉ ተምሳሌት መሆን አለባቸዉ ብለዉ ለዚህ ተግባር ምቹ ሁኔታ የፈጠሩትን አካላት ሁሉ አመስግነዉ ይህ አበረታች በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሺን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት አኑሎ በበኩላቸዉ መምሪያዉ ከዚህ ዘርፍ የሚጠበቀዉን ዉጤት ለማስመዝገብ የተቻለንን ሁሉ ጥረት አድርገናል

አሁን በዘርፉ የሳከነዉ ስኬት መነሻ በመሆኑ ጉድለት ቢኖረዉም በቀጣይ ለሚሠሩ ሥራዎች መሠረት መጣል በመሆኑ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል

አቶ ታምራት አኑሎ አያይዘዉ ኢንኩቤሺን መንግስት ስራ ኣጥነትን ለመቀነስ የሚያደርገዉ ጥረት በእጅጉ ያግዛል ብለዋል።

ወጣት ላመስግነው ደስታና ኢያሱ አያኖ በኢንኩቤሽን ማዕከል ለአንድ ዓመት በኔትወርክና በኮምፒውተር ጥገና ዘርፍ የተግባር ስልጠና መውሰዳቸውን ገልፀው በቆይታቸው በትንሽ ገንዘብ የመንግስትንና የህዝብን ሀብት ማደን አንደሚቻልና በዘርፉ ጠንክረው ከሰሩ የራሳቸውንም የገቢ አቅም ማሳደግ እንደሚችሉ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ለሰልጣኞች የዕዉቅናና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸም ተገመገመ፤========++=======+++================የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወ...
13/01/2023

የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸም ተገመገመ፤
========++=======+++================
የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወራት አፈጻጸም በዞኑ ሥር ከሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ከመምሪያው ማኔጅመንት አባላት ጋር ገመገመ፡፡
ሆሣዕና፣ ጥር 4/2015 ዓ.ም
መምሪያው በበጀት ዓመቱ የተጣሉ ግቦችን መነሻ በማድረግ በመምሪያው ልማት ዕቅድ አማካይነት የቀረበውን አጠቃላይ የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ከወረዳና ከተማ አስ/ር ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ከዞኑ ማኔጅመንት አባላት ጋር ገምግሟል።
በውይይቱ ወቅት መድረኩን የመሩት የመምሪያው ኃላፊ አቶ ታምራት አኑሎ በቀረበው ሪፖርት መነሻ የውይይቱን ዋና ዋና ነጥቦችንና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት በተለይም በተልዕኮ ተኮር ዘርፎች ላይ በተጣሉ ግቦች ዙሪያ አጽንኦት በመስጠት እንዲሁም በወል ዘርፎች ዙሪያም የሪፎሪም ሥራዎች አፈጻጸምን በጉልህ አንስቷል፡፡
ከኢኮቴ መሰረተ-ልማት ዝርጋታና አስተዳደር ተግባራት አንጻር ዞን ከወረዳዎች ጋር በሚያደርገው የቪዲዮ ኮንፍራንሲንግ አገልግሎት ተግባራዊነት እንዲሁም የኢኮቴ መሳሪያዎች ጥገና አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ በስፋት ተነስቷል፡፡ የማህበረሰብ መረጃ ማዕካላትን በተመለከተ፣የኔትወርክ ዝርጋታና ማሰፋፊያ ስራዎችን፣የኢኮቴ መሳሪያዎች እስፔስፊኬሽን ዝግጅትና አጠቃቀምን የሚመለከቱ ጉዳዮችም የውይይቱ ዋንኞቹ ነበሩ፡፡
የሶፍት ዌርና ድረ-ገጽ ልማት አፈጻጸም በተመለከተም በዞኑ እየለሙ ያሉ አዲስ ሲስተም እና ድህረ-ገጾች አፈጻጸም በዕቅዱ መሰረት እየተከናወኑ መሆናቸው የተገመገመ ሲሆን አንዳንድ ወረዳዎችም አዳዲስ ሶፍት ዌርችንና ድረ-ገጾችን የማልማት ስራ መጀመራቸውን አንስቶ ይህም አበረታች መሆኑ ተነስቷል፡፡
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች በተመለከተም፡- የሳ/ቴ/ክበባት አደረጃጀትና አፈጻጸም ስራዎች፣ በት/ቤቶች የሳይንሰ ሳምንታት አከባበር እና ዝግጅት፣ የግል ፈጠራ ባለቤቶችና ተቋማትን የመለየትና ለማበረታታት እየተደረገያው ዝግጅት፣ እንዲሁም ከባላድርሻ ሴክተሮች ጋር ያለው ቅንጅታዊ ሥራዎች በተሻለ ሁኔታ መፈጸማቸውና በቀጣይም በትኩረት የሚሠሩ መሆናቸው ተገምግሟል፡፡
በተጨማሪነት ከመረጀ አያያዝና ሪፖርት ወቅታዊነት እንዲሁም የሰው ኃይል አደረጃጀትና ቢሮዎችን ለሥራ ምቹ ማድረግ ወዘተ… በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት ተካሄዷል፡፡
በአጠቃላይ የዞኑ ማኔጅመንት አባላትና እና የታችኛው መዋቅሮች ኃላፊዎች በ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖሪት ላይ ሰፋ ያሉ ሀሳቦችን አክለው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ የታዩ ጥንካሬዎች እንዲቀጥሉና ጉድለቶች ደግሞ ተላይተው ኢንዲታረሙ ቀጣይ አቅጣጫ ላይ መግባበት ተፈጥሯል፡፡
በመጨራሻም የመምሪያው ኃላፊ አቶ ታምራት አኑሎ በባኩላቸው ሴክተሩ በአዋጅ እንዲያከናውን የተሠጠውን ተልዕኮ፣ ዓለማና ግብ ለማሳካት የተጀመሩ እንቅስቃሴዎችን አጣናክረን መቀጠል ይኖርብናል ካሉ በኋላ ያለውን የሰው ኃይልና አቅም በማስበሰብ የታዩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማጎልባት በድክማት የተለዩ ተግባራትን ደግሞ በማረም ለቀጣይ እምርታዊ ለውጥ ማስመዝገብ ይኖርብናል የሚል ማጠቃለያ አስተያየት በመስጠትና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዩች ላይ በመግባባት እና የቀጠይ 6 ወራት የተከለሰ ዕቅድ ላይ የግብ ስምምነት በመፈራረም የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ  አጠቃቀም ጽንሳ ሀሳብ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ ህዳር 6/2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)በስልጠናው የሆሣዕና ...
17/11/2022

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጽንሳ ሀሳብ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ

ህዳር 6/2015 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)

በስልጠናው የሆሣዕና ከተማ አስተዳደር እና ሌሞ ወረዳ አጠቃላይ ሴክተር መስሪያ ቤቶት ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አባለት ተሳትፈዋል።

በስልጠና መድረኩን ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሀዲያ ዞን መንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ እያሱ ሻንቆ በቴክኖሎጂ ያልተገዛ አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማ ስለማያደርግ በዘርፉ የበቃ ኃይል መፍጠር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ዓለም በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የደረሰበትን ለማወቅና ለመጠቀም የኮምፒውተር እውቀት አስፈላጊ በመሆኑ ሁሉም ሰልጣኝ በስልጠናው በሚቀስመው ዕውቀት አገልግሎት አሰጣጡን ማዘመን ይጠበቃል ብለዋል።

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊው አቶ ታምረት አኑሎ እንደተናገሩት ለታቸኛው መዋቅሮች የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እውቀት ጽንሳ ሀሳብ ላይ መስጠት መጀመሩንና በዛሬ ዕለትም ለ390 ወንዶች እና 35ሴቶች በድምሩ 425 ሠልጠኞች ስልጠና መሰጠቱን አንስተው

የስልጠና ዓለማው በሁሉም መስሪያ ቤቶች ሥራን ለማቀላጠፍና በውስን ሰዓት ብዙ ሥራ በመስራት ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያግዝ በመሆኑ ፈይደው የጎላ ነው ያሉት

እንደዞን በሁሉም በትምህርት ቤቶች ክለብ በመቋቋም የተሻለ በፈጠረው ሥራ ተደራጀተው ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እና ባለሙያዎች ማበረታቻ ሽልማት መስጠታቸውንም ተናግሯል።

አክለውም ለቀጣይ የዲጂታል የቴክኖሎጂ በመጠቀም አካባቢው ከሌሎች አቻ ዞኖች ጋር ተፎካካሪ በመሆን አለም የደረሰችበትን እንዳትደርስ አዳዲስ ሶፍትዌሮች እየለሙ እንዳሉም ተነግሯል።

በዕለቱ ያነጋገርነቸው ስልጠና ታሳተፍዎች መካከል የሆሣዕና ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደነ ዘመድኩን እና የሆሣዕና ከተማ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ቦጋለ እንደናሱት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በጥንቃቄ ስንጠቀም ለጠንካራ ኢኮኖሚ መሠረት እንደመሆኑ መጠን ዘርፉ በአከባቢያችን ለኢኮኖሚው መነቃቃት ጉልህ ድርሻ እንዲለው አንስተው

ዓለም የደረሰችበትን በማየት አካባቢው በሁሉም ሥራ መስኮች በዲጂታል ቴክኖሎጂ መጠቀም አስፈላጊ በመሆኑ ስልጠናው ወደተግባር ተቀይሮ ለሕዝብ ተጠቃሚነት በትኩረት እንደሚሰሩም አንስተዋል።

ሌላኛው ያነጋገርናቸው የሌሞ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሠ ደሚሴ እንደተናገሩት የዲጂታል ሊትሬሲ ምንነትና አጠቃቀም ውስንነት ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራ ከዚህ በፊት ወደኋላ እንደቀረን የሚያሳይ በመሆኑ ለቀጣይ ትውልድ የዕውቀት ሽግግር ለማድረግ ጠንክሮ መስራትን እንደሚጠበቅ አንስተው

መረጃ ሀብት ከመሆኑ የተነሳ በጥንቃቄ እንዲጠበቅ የማድረግ ሥራ ለመስረትም የሚረዳ ስልጠና እንደመሆኑ መጠን ጠንክሮ ለመስራት መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ተነግሯል።

በስልጠና መድረክ ለይ ክቡር የሆሣዕና ከተማ አስተዳደር ከንትባ አቶ ሊሩ ጀማልን ጨምሮ የሆሣዕና ከተማ አስተዳደርና ሌሞ ወረዳ ሁሉም መሳርያ ቤት ኃላፊዎች፣ ማኔጅመንት አባለት እንዲሁም የመምሪያ ማኔጀመንት አባላትና ሠራተኞች ተገኝተዋል።

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክ/-መምሪያ 1ኛ ሆነ።የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ካሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በአጠቃላይ አፈጻጸም 1ኛ ወጥቷል...
13/10/2022

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክ/-መምሪያ 1ኛ ሆነ።
የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ካሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በአጠቃላይ አፈጻጸም 1ኛ ወጥቷል።

የደቡብ ክልል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2014 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2015 እቅድ ላይ ምክክር እያደረገ ነው።

ባላደጉ ሀገራት የኢኮኖሚ ውድቀት አንዱ ምክንያት ያላግባብ የሚባክን ጊዜ ነው ያሉትቴክኖሎጂ የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ገብሬ ጋጌ አንድ ጉዳይ ለማስፈፀም ሁለት ቀንና ከዚያ በላይ ጊዜን እናቃጥላለን ይህ ደግሞ ያለ ስራ ማሳለፋችን ብቻ ሳይሆን ለተጨማሪ ብክነትም እየዳረገን ነው ብለዋል።

ባለፈው አመት የደቡብ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ተቋማት ስራዎቻቸውን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ኢንዲሆን ለማድረግ ባደረገው ጥረት በክልል ፣ዞንና ወረዳ ተቋማት በኔትወርክ በማስተሳሰር እንዲሁም ለባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት የተሻለ ውጤት መመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

ቴክኖሎጂን በትውልድ ውስጥ ለማስረፅ ቢሮው በክልሉ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የአይሲቲ ሴንተር ( የሳይንስ ከበባት)ለመክፈት ጥረት አድርጓል ያሉት አቶ ገብሬ ይህምየመሰረተ ትውልድ ከቴክኖሎጂ ጋር ለማቀራረብ ያግዛል ብለዋል።

በምክት ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር አበባየሁ ታደሰ ተቋማት አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ እንዲደግፉ ማድረግ ከተቻለ የኢኮኖሚ እድገታችንን አሁን ካለው በእጥፍ ማሳደግ ያስችላል ብለዋል።

ዘርፋ ትልቅ ሀብትና የተማረ የሰው ሀይል የሚጠይቅ ቢሆንም ኢትዮጵያ አሁን ለዘርፋ ትልቅ ትኩረት መስጠቷን በቅርቡ በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የተመረቀው የሳይንስ ሙዚየም ማሳያ ነው ብለዋል።

በደቡብ ክልል በተለይ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
በሁለተኛ ቀን ውሎው የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የእውቅናና ሽልማት መርሃ-ግብር የተከናወነ ሲሆን በዚህም:
1) የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መመሪያ 1ኛ፤
2) የወላይታ ዞን ሳ/ኢ/ቴ/መ 2ኛ፤
3) የጉራጌ እና ጌዴኦ ዞን መምሪያዎች በእኩል 3ኛ ጀረዳ በመውጣት ጉባኤው ተጠናቋል።

MELKAM ADDIS AMET
12/09/2022

MELKAM ADDIS AMET

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጥገና በእደሳትና በመጓጓዣ ሊወጣ የሚችለውን ከ7 መቶ 73 ሺህ ብር በላይ የመንግሥት ሀብት ማስቀረቱን የሀዲያ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ አስታወቀሚያዝያ 27/201...
06/05/2022

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጥገና በእደሳትና በመጓጓዣ ሊወጣ የሚችለውን ከ7 መቶ 73 ሺህ ብር በላይ የመንግሥት ሀብት ማስቀረቱን የሀዲያ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ አስታወቀ
ሚያዝያ 27/2014 ዓ.ም (የሀዲያ ዞን መ/ኮ/ጉ/መምሪያ)
ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጥገና በእደሳትና በመጓጓዣ ሊወጣ የሚችለውን ከ7 መቶ 73 ሺህ ብር በላይ የመንግሥት ሀብት ማስቀረቱን የሀዲያ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ አስታውቋል።
መምሪያው የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን የወረዳና የከተማ አስተዳደር የዘርፉ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሆሳዕና ከተማ ገምግሟል።
የሀዲያ ዞን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት አኑሎ በዚህ ወቅት እንደገለፁት መምሪያው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ መቆየቱን ገልጸዋል።
በተለይም በኢኮቴ ዘርፉ ተቋማት ውጤታማ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እና በተማከለ የዲጂታል መሠረት ልማት የመረጃ ልውውጥ የማሳለጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ለተቋማት የጥገና፣ የቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት በመስጠት ለጥገና ለመጓጓዣና ለልዩ ልዩ ወጪዎች ሊወጣ የሚችለውን ሀብት ማስቀረቱን ገልጸዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ከ7 መቶ 73 ሺህ ብር በላይ ሀብት ማስቀረቱን ነው ኃላፊው የጠቆሙት።
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፉ በዘጠኝ ወሩ ለህዝብ ተጠቃሚነት ባላቸው ፍይዳ ተለይቶ ለ18 የፈጠራ ባለሙያዎች የዕውቀትና መሰጠቱን ጠቅሰዋል።
ዕውቅና የተሰጠባቸውም የግብርና ቴክኖሎጂ የከተማ ልማትና ማስዋብ እንዲሁም ሌሎች የፈጠራ ስራዎችን ያካተቱ ናቸው ብለዋል።
በሶፍትዌርና በድረ ገጽ ልማት ዘርፍ የተለያዩ የለሙ ድህረገጾችን ማስተዳደርና ማሻሻል ስራ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ኃላፊው።
በተያዘው በጀት ዓመት በዞኑ ከወረቀት የፀዳ የሰው ሀይል አስተዳደር ስርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ይህም በአሁን ወቅት አፈጻጸሙ 60 ከመቶ መድረሱን ጠቁመዋል።
በተቋሙ የቀጣይ ጊዜያት የትኩረት አቅጣጫዎች በ90 ቀናት ዕቅድ ተለይተው ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑንም ኃላፊው አብራርተዋል።
ለአብነትም የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል የሴክተሩን አገልግሎት ለህብረተሰቡ ማዳረስ፣ በቴክኖሎጂው ዘርተፍ ከመንግሥት የሚወጡ ወጪዎች መቀነስ የአይሲቲ መሠረት ልማቶችን ማሟላት የቀጣይ የትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የሀዲያ ዞን ምክር ቤት አባላት የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢነፎረሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ያለበትን ሁኔታ ጉብኝት አደረጉ፡፡ ---------------------------------------------...
01/04/2022

የሀዲያ ዞን ምክር ቤት አባላት የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢነፎረሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ያለበትን ሁኔታ ጉብኝት አደረጉ፡፡ -------------------------------------------------------
ሆሳዕና ፡ መጋቢት 22/2014 ዓ.ም
የሀዲያ ዞን ምክር ቤት አባላት በዞኑ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ እንደ መምሪያ ከተቋቋመበት ከአንድ አመት ጀምሮ እየተሰሩ ያሉ አዳዲስ ተግባራት አፈፃጸምን ለመመልከት ችለዋል፡፡የመምሪያዉ ኃላፍ አቶ ታመራት አኑሎ ለምክር ቤት አባላት በ1 ዓመት ቆይታ የመምሪያዉ ዋና ዋና ተገባረትንና የመምሪያዉን አደረጃጀት ፤በሦስት ዋና ስራ ሂደትና በ 3 ደጋፍ ስራ ሂደት እየተሰራ ያለዉን ተግባራትን በአብነት ከኢኮቴ ልማት አንፃር የቪዲ ኮንፍረንስ ቁሳቁስና ሰፍ አደረሽን በዞን ማንግሰት መመቻቻቱን፣ከሶፍትዌር ልማት አንጸር የዞኑ ድረገጽ የዞኑን ገፀታ በሚያሳይ መልኩ አገልግሎት እየሰጣ እንደሆና የሶፍትዌር ልማት ተግባርም እየተሰራ እንደሆነ፤ስራ አጥ ወጣቶችን በማደረጀት የብዝነስ ኢንኩቤሽን መዕከል በማቋቋም ስረዎች እየተሰሩ እንደሆነ፣በሳይንስ ፈጠራ ዘርፍም ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ለምክር ቤት አባላት የመምርዉ ኃለፍ አቶ ታምራት አኑሎ ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
በተጫማሪም የዞኑ ምክር ቤት አባላት በዞኑ አስተዳደር በሆሳዕና በህብረተሰብ ተሳትፎ በሆሳዕና ከተማ እየተገነቡ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች የስራ እንቅስቃሴ አፈጻፀምን ተዟዙረው የመስክ ምልከታ አደረጉ።
የዞኑ ምክር ቤቱ አባላት ተዟዙረው የመስክ ምልከታ ያደረጉት በሆሳዕና ከተማ በስድስቱም ቀበሌያት እርስበርስ በእርስ በማገናኘት ረገድ ትልቅ ፋይዳ የሚያበረክት የውስጥ ለውስጥ ኮንክሪት እስፓልት መንገድ ግንባታ፣ ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፓርት አገልግሎት መስጫ አዲስ መናኻሪያ ግንባታ፣ የሆሳዕና ከተማ የንፁህ መጠጥ ውኃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት፣ የጎፈር ሜዳ የህዝብ መዝናኛ ፓርክ፣ የሀዲይ ነፈራ ልማት ግንባታ ፕሮጀክት፣ የሀዲያ ቴሌቪዥን ተግባራት አፈፃጸምንና እንዲሁም የሊች ጎጎ የልህቀት ማዕከል አዳሪ ት/ቤት የሥራ እንቅስቃሴን ይገኙበታል። ከዚህ በተጨማሪም በፌደራል መንግስት እየተገነባ ያለውን የስትራቴጅክ የእህል መጋዘን(ዴፓን) በመስክ ምልከታው ታይቷል።
ከላይ የተገለፁት የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች የግንባታ አፈፃጸም ሂደት ላይ በተደረገው የመስክ ምልከታ የታዩት ተግባራት የሥራዎች እንቅስቃሴዎች አበረታች መሆናቸውን የዞኑ ምክር ቤት አባላት በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።
የምክር ቤቱ አባላት አያይዘው በሰጡት አስተያየት በመስክ ምልከታ ተዟዙረው በተመለከቷቸው የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች የስራ እንቅስቃሴ አፈፃጸም ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው የልማት ፕሮጀክቶቹ የግንባታ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ተጠናቀው ለህዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ልዩ ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በሆሳዕና ከተማ ተጀምረው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች እንቅስቃሴ በዞኑ ሁሉም አካባቢ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አንስተዋል።
የሀዲያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ እቴነሽ ሙሉጌታ በበኩላቸው ምክር ቤቱ በዓመቱ መጀመሪያ የመንግስት አስፈፃሚ አካላትን በአዲስ መልክ አዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱን ገልፀው።
በመንግሥት ምስረታ ወቅት አስፈፃሚ አካላት አቅማቸው በሚፈቅደው ሁሉ ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት በምክር ቤቱ ቃል መግባታቸውን ጠቅሰዋል።
የመስክ ምልከታ ያደረጉት የዞኑ ምክር ቤት አባላት ለህዝብ ተጠቃሚነት እተሠሩ ያሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሆነ አንስተዋል።
ይህም ያስፈለገበት ምክንያት የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለይቶ በቀጣይ ለማረም ታስቦ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ በበኩላቸው በዞኑ በመንግስት በጀትና በህዝብ ተሳትፎ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች በዕለቱ በዞኑ ምክር ቤት አባላት ምልከታ የተካሄደባቸው ብቻ እንዳልሆኑ አንስተዋል ።
በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች እተሠሩ ያሉ የመንገድ ግንባታ ሥራዎች፣ የሆስፒታልና የጤና ጣቢያ ግንባታ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ተቋማት፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊናና ሌሎች አዳዲስ ፕሮጀክቶች እየተገነቡ የሚገኙ መኖራቸውን ጠቁመዋል።
በተለይም በዞኑ የሚገኙ ወጣቶች ሥራ ፈጣሪ ዜጎች እንዲሆኑ የሚያስችሉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ተቋማትን ማለትም በአመካ፣ ፎንቆ፣ ሆመቾ፣ ሀብቾ፣ አንሾ እና ዳነማ ላይ በድምሩ ስድስት ተቋማት በዞኑ አስተዳደርና በህብረተሰብ ተሳትፎ ለመገንባት ወደ ተግባር መገንባቱን ጠቅሰው ይህም በዞኑ የሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ቁጥርን 15 ለማድረስ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው፤
የህብረተሰብን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በዞኑ በተለያዩ ምክንያቶች በመንግስት በጀት ግንባታቸው ተጀምሮ ያልተጠናቀቁ ሆስፒታሎችን ግንባታን አስቀጥሎ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑንና በሌሞ ወረዳ የተጀመረውን የበሌሳ ሆስፒታል ግንባታ ሥራን እንቅስቃሴን ለአብነት አንስተዋል ።
ለእነዚህ የልማት ሥራዎች ማከናወኛ በጀት ህብረተሰቡንና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትን በማሳተፍ የተቀናጀ እንቅስቃሴ በማድረግ እና ያለውን ውስን ሀብት በአግባቡ ለታለመለት አላማ እንዲውል ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል።

በሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተባባርነት ከደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሰት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የተሰጣ ዘመናዊ የቪዲዮ ኮንፍራንስ ዕቀዎች ከስሩ ላሉ 5 ወረዳዎች ዕ...
17/03/2022

በሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስተባባርነት ከደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሰት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የተሰጣ ዘመናዊ የቪዲዮ ኮንፍራንስ ዕቀዎች ከስሩ ላሉ 5 ወረዳዎች ዕደላ ተደረገ፡፡
መጋቢት 8/2014 ዓ.ም
የዘመኑን ቴክኖሎጂ የምመጥን በከፍተኛ ዋጋ የተገዙ ከደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከሥሩ ያሉ ዞኖችንና ወረዳዎችን ለማጠናከር በተያዘዉ ዕቅድ መሠረት በሀዲያ ዞን ከሉ ዎረደዎች 5ቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡
በዚህ መሰረት ዕቃዉ ታደላለቸዉ ወረደዎች፡-አንሌሞ ወረዳ፣ሻሾጎ ወረዳ፣ምሻ ወረዳ፣ሌሞ ወረዳና ግቤ ወረዳ ናቸዉ፡፡

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ለተመረቁ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠናቀቀ--------------------...
16/03/2022

የሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ለተመረቁ ተማሪዎች ሲሰጥ የቆየው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠናቀቀ
------------------------------------------------------
ሆሳዕና ፡ መጋቢት 7/2014 ዓ.ም
የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ጋር በጋራ አዘጋጅነት ላለፉት በሰባት ተከታታይ ቀናት በኔትወርክ ዲዛይን፣ በሶፍትዌርና በኤሌክትሮኒክስ ጥገና ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው የተግባር ስልጠና ተጠናቋል።
በማጠናቂያው ስነስርዓትም የሀዲያ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት አማካሪ አቶ ገብረየስ ጡሞሮ፣ የዞኑ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታምራት አኑሎ፣ የዞኑ
የስራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት
መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ግርማ ኤርበሎ፣ አሰልጣኞችና ሠልጣኞች ተገኝተዋል።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ ታምራት አኑሎ በመዝጊው ስነስርዓት እንደተናገሩት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሰለጠና ዜጋ በማፍራት አላስፈላጊ የመንግስት ወጪዎችን ከማደን ባሻገር የተፈለገውን ጉዳይ በአጭር ጊዜ ለመፈፀም የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት የመምሪያው ቀዳሚ ተልዕኮ መሆኑን ገልፀው፤ ይህ ስልጠና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ተመርቀው ስራ አጥ የነበሩ ተመራቂ ተማሪዎች ስራ ፈጥረው እራሳቸውን እንዲጠቅሙና ብሎም የአገሪቱን ብልጽግና እንዲያፋጥኑ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።
ሰልጣኞች ያገኙትን የዕውቀት ሀብት ወደ አገልግሎት ሰጭነት በመቀየር ሀብት እንዲያፈሩ መምሪያው በቅንጅታዊ አሰራር ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸው፤ ስልጠናው ቀጣይነት እንዳለውም ጠቁመዋል።
ስልጠናው በሀዲያ ዞን ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ በኢ.ኮ.ቴ. ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች የተዘጋጃ መርሃ-ግብር መሆኑን ተናግረው፤ በመርሀ-ግብሩም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ዘርፍ ትምህርታቸውን ጨርሰው ስራ አጥ የሆኑ ወጣቶች ከቀበሌ ጀምሮ በዞኑ
የስራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት
መምሪያ ምልመላ ተደርጎ ወደ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ጠቁመዋል።
የዞኑ የስራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት
መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ግርማ ኤርበሎ እንዳሉት ይህ ስልጠና ለመነሻነት በክልሉ በሶስት ማዕከላት የሚሰጥ መሆኑን ገልጸው፤ የስልጠናውን ዕድል ተጠቃሚዎች ለመለየት ተቸግረው እንደነበር ገልጸዋል።
ይህ ድጋፍ መሸጫና ማምረቻ ቦታዎችን በማዘጋጀት፣ በሂሳብ አያያዝ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር እና በመሳሰሉት መምሪያው ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል።
የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት አማካሪ አቶ ገብረየስ ጡሞሮ በበኩላቸው እንዳሉት ተማሪዎች ትምህርታችሁን በስኬት ብታጠናቁም ማህበረሰቡ ውስጥ ስትገቡ ፈተናዎች እንደሚገጥሟችሁ ማወቅ አለባችሁ ብለው አሁን የሰለጠናችሁት ስልጠና ወድቆ መቅረት የለበትም፤ ውጤታማ ለመሆን የራሳችሁ ጥረት ወሳኝነት አለው ብለዋል።
ዛሬ ላይ የትኛውም ስራ ወደ ቴክኖሎጂ እየመጣ ስለሆነ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመስራት በጣም ታታሪና ትኩረት መስጠት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
በመጨረሻም የአንድ ዓመት ዕድሜ ያለው የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ይሄን ያህል ከሰራ ከአሁን በኋላ መምሪያው ብዙ ይሰራል ብለን እንጠብቃለን ብለው፤ የዞኑ አስተዳደር ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚሸጥል አቶ ገብረየስ ገልጸዋል።
ሰልጣኞችም በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት በዩኒቨርስቲ ሲሰጥ ከነበረው ኮርስ በበለጠ በዚህ ስልጠና ለተግባራዊ ስራ የሚያግዛቸውን ዕውቀት እንደጨበጡ አስተያየታቸውን ሰጥተው የመምሪያ ማኔጅመንት ስታፍ ላደረጉላቸው መስተንግዶ ምስጋናቸውን ሰጥተዋል።

Address

Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya Zone Science and Information Technology Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share