LIGHT MEDIA 30

LIGHT MEDIA 30 WELL CAME TO LIGHT MEDIA 30!

''የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ዛሬን እንተጋለን''
#ማስታወቂያ ለማሰራት ከፈለጉ በ ያውሩን
The sun will rise again and I will try again.
(12)

Yana Tafesse (Engineer) Contact:-

13/05/2026
"ኢትዮጵያን የሚመስል መከላከያ ተገንብቷል" ብርሃኑ ነጋኤርትራ በርሃ ለትጥቅ ትግል ገብተው ለአመታት ትግል ያደረጉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ በአነጋጋሪ ቃለመጠይቅ ተከስተዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ ትናንት ከ...
13/05/2026

"ኢትዮጵያን የሚመስል መከላከያ ተገንብቷል" ብርሃኑ ነጋ

ኤርትራ በርሃ ለትጥቅ ትግል ገብተው ለአመታት ትግል ያደረጉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ በአነጋጋሪ ቃለመጠይቅ ተከስተዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ ትናንት ከሻብያ ጋር ሲሰሩ እንዳልነበረ፤ ዛሬ ከሻብያ ጋር የሚሰሩ ኃይሎችን ሲኮንኑ ታይተዋል፡፡ እርሳቸው ከሻብያ ጋር ሲሰሩ ጽድቅ በተቃራኒው ሌሎች ከሻብያ ጋር ሲተባበሩ ሀጢአት ነው በማለት የሚጋጩ ሀሳቦችን ሰንዝረዋል፡፡

በተጨማሪም፣ ስለ ህውሃት፣ ሻብያ እና አማራ ኃይሎች ጥምረት ባነሱት ሀሳብ፣ ‹‹ሶስቱ ኃይሎች የጋራ ህልም ያላቸው አይመስለኝም ምናልባትም፣ የየራሳቸውን አገር ለመመስረት ካልሆነ በስተቀር›› ብለዋል፡፡ አብይ አዞኝ አንድም የሰራሁትን ስራ የለም፤ አሁን ላይ ኢትዮጵያዊነትን የሚያቀነቅን መከላከያ ሰራዊት ተገንብቷል›› የሚል ጉዳይም አንስተዋል፡፡

ታዋቂው ፖለቲከኛ ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑ በአዲስ ቃለመጠይቅ ብቅ ብለዋል፡፡

በዚህ ቃለመጠይቃቸው በዋናነት ከሻብያ ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት እና አሁን ከሻብያ ጋር ስለሚሰሩ ኃይሎች ያነሱት ሀሳብ ትኩረት የሚስብ ነው፡፡ እርሳቸው ከሻብያ ጋር ለአመታት እጅ እና ጓንት ሆነው መስራታቸውን እንደ ጽድቅ እና ልክ እንደሆነ ነገር አድርገው ያቀረቡ ሲሆን፤ ሌሎች ኃይሎች ከሻብያ መስራታቸውን ደግሞ ሲነቅፉ ተደምጠዋል፡፡

የሕውሓት እና ሻብያ፣ እንዲሁም የሕውሓት እና አማራ ኃይሎችን ጥምረትም በውሃ እና ዘይት መስለው ተሳልቀዋል፡፡ ‹‹ሻብያ እና ሕውሓት ውሃ እና ዘይት ናቸው፤ እንዲሁ ህውሀት እና የአማራ ብሄርተኛ ውሃ እና ዘይት ናቸው›› ያሉት ብርሃኑ ነጋ፤ ‹‹ያን ጊዜ ህውሃትን የተቃወምን ኢትዮጵያን ይገነጣጥላታል ብለን ነው፤ ብልጽግና ደግሞ ኢትዮጵያን ይገነጣጥላታል ብለን አናምንም፤ ሻብያ ደግሞ ህውሃትን ይጠላል፤ እነዚህ ኃይሎች ውሃ እና ዘይት ናቸው፤ በተመሳሳይ የአማራ ብሄርተኞችም ጋር ውሃ እና ዘይት ናቸው፤ እነዚህ ሀይሎች ባንድ ተሰብስበው ሲታገሉ ምን የጋራ አላማ ለማሳካት ነው ብለህ ብትጠይቀኝ፤ እነዚህ በጋራ ተሰብስበው የሚገዙት አገር ሳይሆን ሁሉም በየራሳቸው አገር ሊፈጥሩ እና ኢትዮጵያን ሊበታትኗት ነው የሚችሉት፤ እንጂ አንድ አገር ይፈጥራሉ ብዬ አላስብም›› በማለት አብራርተዋል፡፡

በዚህ ቃለመጠይቅ ፕሮፌሰሩ ሌላው ያነሱት ነጥብ የ2010ቱን ለውጥ በተመለከተ ነው፡፡ ለውጡ በመጣ ሰሞን የፖለቲካ ኃይሎችን አሰላለፍ በተመለከተ ጥናት እና ትንተና ማደረጋቸውን ጠቅሰው፤ በመጨረሻም የእነአብይ የኢትዮጵያ ሀሳብ የተሻለ በመሆኑ ያንን አሰላለፍ መምረጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ከደርግ ዘመነ መንግስት በኋላ ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ኢትዮጵያ የሚያስብ መከላከያ ሰራዊት አለን የሚሉት ፖለቲከኛው፤ ‹‹ከአምስት አመት በፊት ልዩ ኃይል ተብሎ በየመንደሩ በዘር የታጠቀ ሰራዊት ነበር አገሩን የሞላው፤ አሁን ግን በመንግስት ተቋም ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር አይታይም፤ አሁን ያለው መከላከያ ሰራዊት ግን በትጥቅ እና ሰው ኃይል ብቻ ሳይሆን፤ በእሳቤ ደረጃም ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ ነው፤ ይህ ከረጅም አመት በኋላ አሁን የሆነ ነው፤ ኢትዮጵያ ስትገነጣጠል ዝም ብሎ የማያይ ይህን ማስቆም የሚችል ሀይል አለ ብዬ አምናለሁ›› በማለት ተደምጠዋል፡፡

ሌላው በዚህ ቃለመጠይቅ ያነሱት ሀሳብ የትምህርት ሚኒስቴርነት ሹመታቸውን የተመለከተው ነው፡፡ በወቅቱ የሹመት አማራጭ ሲቀርብላቸው ከሌሎች ዘርፎች የትምህርት ሚኒስቴር መሆንን እንደመረጡ ተናግረዋል፡፡ ‹‹የትምህርነት ሚኒስቴር ሆኜ ማገልገል ከጀመርኩ አንስቶ አንድም ነገር ሳላምንበት ያደረኩት ነገር የለም፤ ወይም ዶክተር አብይ አዞኝ የሰራሁት አንድም ነገር የለም፤ ሙሉ ነፃነቴ ተጠብቆ ነው የሰራሁት›› ብለዋል፡፡

11/05/2026

ለማክሰኞ ተራውን የማይሰጥ
ሰኞ የለም።
በርታልኝ አምበሳዬ 💪

በምስሉ ላይ የሚታየው ህንጻ ዘ ገርኪን (The Gherkin) በመባል የሚታወቀውና በለንደን ከተማ የሚገኝ ታዋቂ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ነው። ስለ ህንጻው ዋና ዋና መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦✅ ...
11/05/2026

በምስሉ ላይ የሚታየው ህንጻ ዘ ገርኪን (The Gherkin) በመባል የሚታወቀውና በለንደን ከተማ የሚገኝ ታዋቂ ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ነው። ስለ ህንጻው ዋና ዋና መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦

✅ ስያሜ፦ ህንጻው በይፋ 30 ሴንት ሜሪ አክስ (30 St Mary Axe) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ቀደም ሲል ደግሞ የስዊዝ ሪ (Swiss Re) ህንጻ በመባል ይታወቅ ነበር።

✅ ንድፍ፦ ህንጻው በታዋቂው አርክቴክት ኖርማን ፎስተር (Norman Foster) እና በፎስተር ኤንድ ፓርትነርስ ድርጅት የተነደፈ ነው።

✅ መጠን፦ ቁመቱ 180 ሜትር ሲሆን በውስጡ 41 ፎቆችን ይይዛል።

✅ አካባቢ፦ የሚገኘው በለንደን ዋና የፋይናንስ ማዕከል (City of London) ውስጥ ነው።

✅ ታሪክ፦ የህንጻው ግንባታ በ2003 ዓ.ም ተጠናቆ በ2004 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ ተከፍቷል።

✅ ልዩ ባህሪ፦ ህንጻው ባለው ልዩና ዘመናዊ ቅርጽ ይታወቃል፤ ይህም ለለንደን ከተማ አንዱ መለያ ምልክት እንዲሆን አድርጎታል።

ግንባታዎን የሚያዘምን - አማንዞን
አማን ዞን ትሬዲንግ

WAR WARNING: US President Donald Trump has claimed the United States could strike “every single target” in Iran within t...
11/05/2026

WAR WARNING: US President Donald Trump has claimed the United States could strike “every single target” in Iran within two weeks, saying the country has already been “militarily defeated” following recent US and Israeli attacks.

Speaking in an interview aired Sunday, Trump said about 70 percent of the targets the US wanted had already been hit, while describing any additional strikes as “final touches.” He added that although Iran may not admit it publicly, he believes the country knows it has suffered major military setbacks.

Trump also criticised NATO, calling the alliance a “paper tiger” and accusing Washington’s allies of failing to assist in the campaign against Tehran.

The comments come as reports indicate Iran has responded to a new US proposal aimed at ending the conflict that began on February 28 following coordinated US and Israeli strikes.

ሰበር ዜና‼️የ"ፊንቴክ" ማጭበርበር ወንጀል ተጠርጣሪዎች በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ::ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም | አዲስ አበባበኢትዮጵያ የጥበብ እና የማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ታዋቂነት ያላቸው...
11/05/2026

ሰበር ዜና‼️

የ"ፊንቴክ" ማጭበርበር ወንጀል ተጠርጣሪዎች በዋስ እንዲፈቱ ተወሰነ::

ግንቦት 3 ቀን 2018 ዓ.ም | አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ የጥበብ እና የማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ ታዋቂነት ያላቸው ግለሰቦች የተሳተፉበት የ1.9 ቢሊዮን ብር የፋይናንስ ማጭበርበር ክስ ዛሬ አዲስ ምዕራፍ ይዟል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ዝግ ችሎት፣ በተጠርጣሪዎቹ ላይ የዋስትና መብት ውሳኔ አስተላልፏል።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ የፈቀደ ሲሆን፣ የተቀመጡት የገንዘብ ዋስትናዎችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡

* አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፣
* አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣
* አርቲስት ይገረም ደጀኔ እና
* አርቲስት ዳንኤል ተገኝ፦

እያንዳንዳቸው በ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር ዋስ እንዲፈቱ።

* አብርሃም ግዛው እና
* ካሊድ ናስር፦

እያንዳንዳቸው በ 400,000 (አራት መቶ ሺህ) ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ።

ተከሳሾቹ በዋስ ቢፈቱም፣ ፍርድ ቤቱ የሚከተሉትን ጥብቅ ትዕዛዞች አስተላልፏል፡

1. ሁሉም ተጠርጣሪዎች ጉዳዩ ተቋጭቶ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ከሀገር እንዳይወጡ እገዳ ተጥሎባቸዋል።

2. የክስ ሂደቱን በማንኛውም መልኩ እንዳያስተጓጉሉ ጥብቅ ክትትል ይደረግባቸዋል።

አምስተኛ ተከሳሽ የሆነው መንሱር ጀማልን በተመለከተ፣ በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበውን ጠንካራ መቃወሚያ ለመመርመር ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቷል። የመንሱር የዋስትና ጥያቄ ተቀባይነት ያግኝ ወይም አይግኝ ከሰዓት በሚሰጠው ብይን የሚታወቅ ይሆናል።

የተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ አበባው አበበ እንደገለጹት፣ ደንበኞቻቸው ከዚህ ቀደም ሚያዝያ 28 ቀን በነበረው ችሎት ዐቃቤ ህግ የዋስትና መብታቸውን ባለመቃወሙ መነሻነት ዛሬ ከእስር እንደሚፈቱ ይጠበቃል።

ዘገባው የገዛ ጌታሁን ነው
ሸገር ኤፍ ኤም

የእረፍት ሰዓት ! አርሰናል ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር እያደረጉ የሚገኙት የሊግ ጨዋታ 0ለ0 ወደ መልበሻ ቤት አምርቷል። 🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ? - በመጀመሪያው ...
10/05/2026

የእረፍት ሰዓት !

አርሰናል ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር እያደረጉ የሚገኙት የሊግ ጨዋታ 0ለ0 ወደ መልበሻ ቤት አምርቷል።

🟨 የቢጫ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በዌስትሀም ዩናይትድ በኩል ሰመርቪሌ እና ካስቴላኖስ የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል

⚽ የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ አርሰናል 66% - 34% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

Address

Gimbi
PAPY_17

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when LIGHT MEDIA 30 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share