21/02/2023
~~~~~ስማርት ስልክ ስንገዛ በልዩነት ማስተዋል ያለብን 7 መሰረታዊ ጉዳዮች~~~~~
1. ራም (RAM)
***********
RAM የሚለው ምህጻረ ቃል ሲተነተን Random Access Memory የሚል ትርጓሜ ይይዛል፡፡ እንግዲህ የራም ስራ ከማዕከላዊ የስልኩ ማቀነባበሪያ ክፍል የሚመጡ አፕሊኬሽኖችን ተጠቃሚው በሚጠቀምባቸው ጊዜ እንዲሁ እንዲጠቀማቸው ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ ማስቻል ነው፡፡ ታዲያ ኪቦርዱ፣ ሆምስክሪኑ እና አንዳንድ የስልኩ መሰረታዊ ክፍሎች ከዚህ ራም መጠን ግማሽ ያህሉን ስለሚወስዱ ስማርት ስልክ ስንገዛ ፈጣን እና የተሻለ አገልግሎት እንድናገኝ ቢያንስ 2 ጊጋ ባይት ራም (2GB) ያለው ስልክ ቢሆን ይመረጣል፡፡
2. የመረጃ ማከማቻ (Storage)
**********************
ይህኛው የስልክ መገለጫ ደግሞ ልክ እንደ ራም ሁሉ መጠኑ በ ጊጋ ባይት (GB) ይለካል፡፡ እዚህ የመረጃ ማከማቻ ላይ ነው ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች፣ ሙዚቃዎች፣ ዶክመንቶች እና የተለያዩ መረጃዎችን የምናስቀምጠው የምናጠራቅመው፡፡ እንግዲህ ምንም እንኳን ኤክስተርናል የመረጃ ማከማቻዎች (SD CARD) እና ክላውድ (CLOUD) ላይ መረጃዎቻችንን በማስቀመጥ ያልተገደበ የመረጃ ማከማቻ መጠን ማግኘት ብንችልም የስልካችን የመረጃ ማከማቻ ግን ከፍ ያለ ቢሆን በጊዜና በቦታ እንዲሁም በኢንተርኔት ግንኙነት ባለመገደብ መረጃዎቻችንን በየትኛውም ጊዜና ቦታ ለማጠራቀምና ለማግኘት ያስችለናል፡፡
3. ባትሪ (Battery)
*************
የባትሪ ህይወት የሚለካው በ milliampere hours (mAh) ነው፡፡ mAh ስልካችን ምን ያክል ሀይል አለው የሚለውን ይነግረናል፡፡ ጠቅለል ባለ አረዳድ ብዙ mAh ያለው ባትሪ ስልካችን ረዘም ላለ ጊዜ አገልግሎት እየሰጠን እንዲቆይ ያስችለዋል ማለት ነው፡፡ በርግጥ ይሄ የጊዜ ርዝማኔ ስልካችን አንድ ሰአት ለመቆየት ምን ያክል ሀይል ያስፈልገዋል በሚለው ጥያቄ ይወሰናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የስልካችን አጠቃላይ ቅልጥፍና ራሱ የስልካችን ባትሪ የሚቆይበትን ጊዜ ይወስነዋል፡፡ በአሁኑ ሰአት እስከ 10,000 mAh የሀይል አቅም ያላቸው ባትሪዎች ገበያውን እየተቀላቀሉ ስለሚገኙ ከፍ ያለ የስልክ መጠቀሚ ጊዜ እንዲኖረን ከፍ ያለ የሀይል አቅም ያላቸውን ባትሪዎች እንምረጥ፡፡
4. ኦፕሬቲንግ ሲስተም(Operating System)
***********************************
ኦፕሬቲንግ ሲስተም ማለት ስልኩን የሚያንቀሳቅሰው ሶፍትዌር ማለት ነው፡፡ ልክ ኮምፒዩተሮች ዊንዶስ አልያም ሊኑክስ የመሳሰሉት ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች እንዳሏቸው ሁሉ ስልኮች የራሳቸው ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች አሏቸው፡፡ እንግዲህ በስማርትስልክ ረገድ በስፋት የሚገኙት ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች አንድሮይድ (Android) እና አይኦኤስ (IOS) ናቸው፡፡ አንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በርካታ ስልኮች ላይ መስራት ስለሚችል በርካታ የስልኮች አማራጭ እንዲኖረን የሚያስችለን ሲሆን አይኦኤስ ግን በአፕል ምርቶች ላይ ብቻ የሚሰራ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ስለሆነ ልክ እንደ አንድሮይድ ሰፊ የስልክ አማራጭ አይሰጠንም፡፡ እንግዲህ እኛ ለአጠቃቀም የሚቀለንን በየጊዜው ለሚወጡ ማሻሻያዎች ክፍት የሆነው ኦፕሬቲንግ ሲስተም የተጫነበትን ስልክ ብንመርጥ ብልህነት ነው፡፡
5. የስክሪን መጠን (Screen Size)
*************************
ብዙ ጊዜ ስማርት ስልኮች በአነስተኛ፣ በመካከለኛ እና በትልቅ የስክሪን መጠን ስለሚመጡ ለእኛ የሚስማማውን መርጠን መግዛት እንችላለን፡፡ ጥያቄው ግን ለእኛ የሚስማማንን የስክሪን መጠን በምን እናውቃለን? የሚለው ነው፡፡
6. ካሜራ (Camera)
**************
በዚህ ዘመን ስማርትስልክ ይዞ መንቀሳቀስ ማለት ቆንጆ ካሜራ ይዞ እንደመንቀሳቀስም ጭምር ነው፡፡ ጥሩ ካሜራ ካለን ጥሩ ጥሩ ፎቶዎችን ማንሳት ጥሩ ጥሩ ቪዲዮዎችን መቅረጽ እንችላለን ማለት ነው፡፡ እንግዲህ አንድ ካሜራ ጥሩ ምስል እንዲያነሳ ብርሀን ወደ ውስጡ ማስገባት አለበት፡፡ ይህም በቴክኖሎጂው ቋንቋ f-stops ብለን እንጠራዋለን፡፡ ለምሳሌ f/1.8 እንኳን ከቤት ውጪ ለሚነሱ ቤት ውስጥም ለሚነሱ ፎቶዎች ጥሩ ጥራት ያስገኛል፡፡
7. የስክሪን ጥራት (Display Quality)
*****************************
ብዙ ጊዜ የስክሪን ጥራት ስንል ስክሪኑ ላይ ምስሎች ምን ያክል ብርሀናማ ሆነው ይታያሉና የመመልከቻ አንግሉ ምን ያክል ሰፊ ነው ማለታችን ነው፡፡ ለምሳሌ ቀለሞችን በማሳየት በማመጣጠንና በሚያሳዩበት አንግል ስፋት AMOLED ስክሪኖች ከ LCD የተሻሉ ናቸው፡፡