ኑሩ ዲሽ እና ሪሲቨር Nuru Dish & receiver

ኑሩ ዲሽ እና ሪሲቨር Nuru Dish & receiver እንኳን ወደ ኑሩ ዲሽ በደህና መጡ በዚህ ፔጅ ላይ የተለያዩ የቴክኖሎጂ መረጃዎችን ለናንተ አንባቢወቼ አደርሳለሁ በፔጁን ላይክ በማለት ናሽናል ጂኦግራፊ ፣ የኳስ፣የፊልም ፣ቻናሎች ፊሪኪዌንሲ ያግኙ

አንድሮይድ ስልክዎት ፍጥነት ጎታታ ሆኖ አስቸገረዎት?የአንድሮይድ ስልክዎን ፍጥነት ወደቀድመው ለመመለስ እነዚህን ቀላል የሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀሙ፡፡1. ችግሩን ለመለየት ይሞክሩየስልክ ፍጥነት ች...
26/09/2020

አንድሮይድ ስልክዎት ፍጥነት ጎታታ ሆኖ አስቸገረዎት?
የአንድሮይድ ስልክዎን ፍጥነት ወደቀድመው ለመመለስ እነዚህን ቀላል የሆኑ ዘዴዎችን ይጠቀሙ፡፡
1. ችግሩን ለመለየት ይሞክሩ
የስልክ ፍጥነት ችግር በበርካታ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል፡፡
እነዚህን ችግሮች ምናልባት የተከሰቱት ኮራብት በሆኑ አፕልከሽኖችና ፋይሎች፤በRAMና በstorage መጣበብ ወይም
በቫይረስ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እነዚህን ችግሮች በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ማወቅ ስንችል latest የሆኑ ስልኮች እራሳቸው cleaner አላቸው።
በነዚህ አፕልኬሽኖች ታግዘው የስልክዎን ብቃት
(performance) ሪፖርት ማየት ይችላሉ፡፡ ቀጥሎም የሚከተሉትን ዘዴዎችን ይሞክሩ፡፡
2. አላስፈላጊ የሆኑ አፕልከሽኖችን ያጥፉ
ተጠቅመው የማያውቅትን አፕልከሽኖችን ያጥፉ ወይም freeze ያርጓቸው(ለ latest ስልኮች)
3. የአፕልከሽኖችን cach data ያጥፉ
ካች ዳታ ማለት አፕልከሽኖች ለሌላ ጊዜ ለፍጥነት እንዲረዳቸው
በራሳቸው የሚያስቀምጡት ዳታ ነው ነገር ግን ይህ ዳታ እየበዛ
ስሄድ የስልኩን የውስጥ storage ቦታ በከፍተኛ ሁኔታ ሊይዝ ይችላል።
ካች ዳታ ለማጥፋት setting =>apps(all application)
ውስጥ ገብተን በየአንዳንዱ አፕልኬሽን ውስጥ እየገባን "clear cache" የምለውን በመምረጥ ካች ዳታ ማጥፋት ይቻላል፡፡
4. የስልክዎን ስቶረጅ( storage ) ያጽዱ
የስልክዎ storage አላስፈላጊ በሆኑ ፋይሎች ተጣቦ ሊሆን ይችላል። እነዚህን ፋይሎች ማጥፋት በተለይም የስልኩን
የውስጥ ስቶሬጅ(internal storage) ማጥፋት ለስልክዎ ስራ ጥሩ የመተንፈሻ ቦታ ይሰጣል፡፡
5. (widgets), በአንመሽን የተሞሉ launcher እና(animated launchers and live wallpapers ) አይጠቀሙ።
ውድጌቶች(widgets), በአንመሽን የተሞሉ ላውንቸረችንና ዋልፔፐሮች(animated launchers and live
wallpapers ) የስልካችንን ራምና ፕሮሰሰር ሊያጣብቡና ሊያጨናንቁ ስለሚችሉ ውድጌቶችን ያለመጠቀም ይምረጣል፡፡
በተጨማሪም ውድጌቶች(widgets), በአንመሽን የተሞሉ
ላውንቸረችንና ዋልፐፐሮች(animated launchers and live
wallpapers ) የባትሪ ጠላቶች ናቸው፡፡
6. በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን አይጠቀሙ
በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን መክፈት ከስልካችን አቅም በላይ
ሆኖ የስልኩን ፕሮሰሰርና ራም ልያጨናንቅና ልያስቸግር
ይችላል፡፡ስለዚህ በአንዴ ብዙ አፕልከሽኖችን አይጠቀሙ፡፡
7. ፎርማት(format) ያድርጉ (ፋክተሪ ሪሲት)
ከላይ የተጠቀሱት መፍትሄዎች አንድሮይድ ስልክዎን ፍጥነት
ልያሻሽሉ ይችላሉ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ልያጠፉ አይችሉም፡፡
ፎርማት(format) ማድረግ ግን ወደ ቀድመው ፍጥንት ልመልስ
ይችላል፡፡ ነገር ግን ስልከዎን ፎርማት ከማድረገዎ በፊት ባክአፕ
(backup) ማድረግ የግድ ነው።
በማድረግ አበረታቱን

Pixel Lab የተሰኘው Application በጣም ጠቃሚ የሆነ App ነው ። በጣም ብዙ እና የሚያስደንቁ (fonts) የፅሁፍ ስታይሎች አሉት። ባጠቃላይ እናንተ የምትፈልጉት ነገር ያሟላል። ...
05/09/2020

Pixel Lab የተሰኘው Application በጣም ጠቃሚ የሆነ App ነው ። በጣም ብዙ እና የሚያስደንቁ (fonts) የፅሁፍ ስታይሎች አሉት። ባጠቃላይ እናንተ የምትፈልጉት ነገር ያሟላል።
👉 ፍቶ ላይ ለመፃፍ ወይም ጥቅስ ለመፃፍ
👉 3D ለመፃፍ
👉የተለያዩ የ 3D የፅሁፍ ስታይሎች
👉አርማ(logo) ለመስራት
👉ለአንድ ፅሁፍ የተለያዩ ቀለማት ለማድረግ የፈለጉትን ያህል
👉ባንዴራዎች ለመስራት
ፔጁን ላይክ ማለት እንዳይረሱ ለጓደኞችዎ ሼር ያድርጉላቸው።

✳️ Artificial Intelligence (AI):◽️ ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) በማሽኖች በተለይም በኮምፒተር ስርዓቶች ውስጥ የሰዎችን የማሰብ ችሎታ በኮዲንግ (Coding) በማስገባ...
29/08/2020

✳️ Artificial Intelligence (AI):

◽️ ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) በማሽኖች በተለይም በኮምፒተር ስርዓቶች ውስጥ የሰዎችን የማሰብ ችሎታ በኮዲንግ (Coding) በማስገባት የኮምፒውተሮችን የአስተሳሰብ ሂደት ከሰዎች ጋር የማስመሰል ስራ ነው።

◽️ Artificial Intelligence (AI) የሚሠራው ከፍተኛ መጠን ያላቸውን መረጃዎች ከፈጣን እና ተለዋዋጭ የሥራ ሂደት ጋር በማጣመር ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ ያላቸው ስልተ ቀመሮች በመጠቀም ሶፍትዌሩ ሲስተም ውስጥ ካሉ መረጃዎች ራሱን-በራሱ እንዲያስተምር ያስችለዋል፡፡

🔺የAI ምሳሌ

◽️ በ iPhone እና በ iPad ውስጥ በአፕል ከሚቀርቡት በጣም ታዋቂ የግል ረዳት (Personal Assistant) Siri አንዷ ናት፡፡ ይህች ተግባቢ ሴት የተለያዩ የተቀነባበሩ ድምፆችን በመጠቀም የተጠቃሚዎቾን የእለት ተእለት ኑሮ ለማቅለል ትረዳለች።

◽️ Siriን በመጠቀም ሞባይላችንን በምንም አይነት መልኩ ሳንነካ ከሷ ጋር በመነጋገር ብቻ የተለያዮ መረጃዎችን ማግኘት ፣ የመንገድ አቅጣጫዎችን ማግኘት ፣ መልዕክቶችን መላክ ፣ የስልክ ጥሪዎችን ለማድረግ ፣ አፖችን መክፈት እና ሌሎችም ነገሮችን ለማድረግ እንችላለን።

◽️ Artificial Intelligence ለሰው ልጆች የሚሰጠው ዘርፈ ብዙ ጥቅም እንዳለ ሆኖ በሰው ሰራሽ አጠቃላይ የማሰብ ችሎታ ላይ የሚደርሰው አደጋ በሰው ሰራሽ አጠቃላይ መረጃ (AGI) ውስጥ አንድ ቀን በሰው ልጅ መጥፋት ወይም ሌላ ሊመለስ የማይችል ዓለም አቀፍ ጥፋት ሊያስከትል ይችላል የሚል መላምት አለ።

◽️ የሰው አንጎል ሌሎች እንስሳት የጎደሏቸው አንዳንድ የተለዩ ችሎታዎች ስላሉት በአሁኑ ጊዜ የሰው ዝርያ ከሌሎች ዝርያዎች የበላይ ነው። ነገር ግን የAI አጠቃላይ የማሰብ ችሎታ ከሰው ልጅ የሚበልጥ ከሆነ እና “የላቀ የማሰብ ችሎታ” ያለው ከሆነ ለሰዎች መቆጣጠር ከባድ ወይም የማይቻል ሊሆን ይችላል።

◽️ እንስሳት እጣ ፈንታ በሰው በጎ ፈቃድ ላይ እንደሚመረኮዝ ሁሉ የሰው ልጅም ዕጣ ፈንታ ወደፊት በሚመጣው የማሽን ብልህነት ተግባር (AI) ላይ የተመረኮዘ ሊሆን ይችላል

▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬

   ኮንፒውተራችን ፓስዋርድ ሲጠፋን ኮምፒውተራችን እንዴት መክፈትእንችላለን?☞☞አይበለውና የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴውቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ… አንድ መላ አይጠፋም፡፡የሚያስፈልገው ...
17/05/2020


ኮንፒውተራችን ፓስዋርድ ሲጠፋን ኮምፒውተራችን እንዴት መክፈት
እንችላለን?
☞☞አይበለውና የኮምፒውተርዎ ፓስዋርድ ከነአካቴው
ቢጠፋብዎት ብዙም አይጭነቅዎ… አንድ መላ አይጠፋም፡፡
የሚያስፈልገው ሶፍትዌር “Spotmou Bootsuite.iso”
ሲሆን ቀጣዮቹን 10 ስቴፖች ተከትለው ኮምፒውተርዎን
መክፈትና መጠቀም ይችላሉ፡፡
Step1: መጀመረያ ሶፍትዌሩን በፍላሽ ወይም CD ላይ
እንጭናላን
Step2: ኮምፒዩተራችንን Turn OFF ማድረግ፡፡
Step3: ፍላሹ ን ሰክተን ኮመፒዩተሩን Turn ON ማድረግ፣
ከዛF12 (Boot key) መንካት፡፡
Step4: “Boot Sequence” የሚል ሲመጣልን “USB”
የሚለዉን መርጠን “Enter”ን መንካት ከዛ ትዕዛዙን
መከተል፡፡
Step5: ኮምፒዩተሩ ከከፈተ በኃላ “Spotmou Bootsuite
2012 Application” ይከፈትልናል፡፡
Step6: ከአፕልኬሽኑ ላይ “Password and Key Finder”
የሚለዉን “Menu” እንመርጣለን፡፡
Step7: “Admin Password Resetter” የሚል መንካት፡፡
Step8: “Please select the target widows” ከሚለዉ
ሥር የኮምፒዩተሩን “Window Version (XP/7/8/8.1/
10)” ይመርጣሉ፡፡ ቀጥሎ “please select the target
user” ከሚለዉ ሥር ደግሞ መክፈት የሚፈልጉትን “User
Account” መርጠዉ “Reset” የሚለዉን መጫን፣ ከዛ
“OK” ከዛ “YES” የሚለዉን እንጫናለን፡፡
Step9: መጨረሻ ላይ “Password is reset
successfully” የሚል መልዕክት ይደርሶታል፡፡
Step10: ኮምፒዩተሩን ዘግተዉ ይክፈቱት (Reboot).
በትክክል ይሰራል…
የቴሌግራም ቻናላችን https//t.me/nurudish
ከወደዳቹት ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያድርሱ
ጥያቄዎች በውስጥ መስመር እንቀበላለን ይላኩ እራሳቹን ከገንዘብ ማውጣት ይዳኑ።
አዳዲስ መረጃዎችን ከኑሩ ሳይቴክ like እና share በማድረግ ብቻ

 # sim card  # networkበመጀመሪያ አንድ ስልክ  # ኔትወርኩ_ሲጠፋ የ Sim Card ችግር ወይም የ ኔትወርክ ችግር መሆኑን መለየት ያስፈልጋልእንድ ስልክ የኔትወርክ ችግር ነው ማ...
16/05/2020

# sim card # network
በመጀመሪያ አንድ ስልክ # ኔትወርኩ_ሲጠፋ የ Sim Card ችግር ወይም የ ኔትወርክ ችግር መሆኑን መለየት ያስፈልጋል
እንድ ስልክ የኔትወርክ ችግር ነው ማለት የምንችለው ከታች ያሉትን ምልክት ሲያመጣ ነው
No Service
Emergency Call
Regisretion Failed
Invalid Sim ...
እነዚ በ 3 አይነት ችግር ሊበላሹ ይችላሉ
በ IMEI NO ችግር
Antrna (Hardware Problem)
Network IC ችግር (Hardware Problem)
አብዛኛውን ጊዜ ግን 90% የ IMEI NO ችግር ሰለሆነ IMEI NO መቀየር ነው።
IMEI NO በተን ስልክ ላይ እና ተች ስልክ ላይ አቀያየሩ ስለሚለያይ ዛሬ # እንዴት_በተን_ስልክ_ላይ
_እንደምንቀይር_እናያለን
በተን ስልኮች ላይ ምንቀይረው በ Code ነው በተን ስልኮች ላይ IMEI NO. መቀየሪያ ኮዶች
* #0160 # ብዛት Techno ስልኮች ላይ እንቀይርበታለን
* #0161 #
* #0162 #
* #0066 # ብዛት Isim ስልክ ላይ እንቀይርበታለን
* #0011 # ብዛት Smadel ስልክ ላይ እንቀይርበታለን
* #346 #
* #020* #
* #0120 #
* #1120 #
* #* #601* #* #
* #8378 #1 # ሁሉም በተን ስልክ ላይ ይሰራል
መጀመሪያ የስልካቹን IMEI NO. ለማየት * #06 # ስትነኩት 15 ዲጂት ያለው ቁጥር ያመጣላችዋል ልክ እንዲ 354688225789335 ካመጣላቹ በዋላ እሱን አጥፍታቹ አዲስ IMEI NO. ታስገቡበታላቹ ካዛ ስልኩን አጥፍታቹ ታበሩታላቹ ካዛ Networku ይመለሳል።
Sim Card Hardware Problem
Insert Sim Card # sim_card_እያለው
No Sim Card Present # sim_card_እያለው
No Sim Card Interted # sim_card_እያለው
Sim Card Regitortion Faild # sim_card_እያለው
እነዚ ችገሮች የ Sim Card ማስገቢያው መደብ ችግር ስለሆኑ ወደ ሞባይል ጥገና ቤት ይዞ ሄዶ ማሰራት ነው::
ምንጭ:- Computer and Mobile Maintenance

ለኮምፒዩተሬ የትኛዉን አንቲቫይረስ ልጠቀም ?አንቲቫይረስ ፕሮግራም ወይም ሶፍትዌር ማለት ኮምፒዩተራችንን ከተለያዩ የቫይረስ አይነቶች ለመከላከልና አስቀድመዉ ሲስተማችንን ያጠቁ ቫይረሶችን ለማ...
15/05/2020

ለኮምፒዩተሬ የትኛዉን አንቲቫይረስ ልጠቀም ?
አንቲቫይረስ ፕሮግራም ወይም ሶፍትዌር ማለት ኮምፒዩተራችንን ከተለያዩ የቫይረስ አይነቶች ለመከላከልና አስቀድመዉ ሲስተማችንን ያጠቁ ቫይረሶችን ለማጥፋት ዲዛይን የተደረገ ሶፍትዌር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ኮምፒዩተርን ያለ አንቲቫይረስ መጠቀም የአለም ዋንጫ ጨዋታን ያለበረኛ እንደመጫወት ማለት ነዉ፡፡
የአንቲቫይረስ ሶፍትዌር ለኮምፒዩተራችን ይሄን ያህል አስፈላጊ ቢሆንም የትኛዉን መርጠን መጠቀም እንዳለብን መወሰኑ አስቸጋሪና ወሳኝ ጉዳይ ነዉ፡፡ ምክንያቱም በኢንተርኔት ላይ ያሉ አንቲቫይረሶች ሁሉም እኛ የምንፈልገዉን አይነት ጥበቃ ይሰጡናል ማለት አይደለም፡፡ አብዛኞቹ አዳዲስ ቫይረሶችን መቋቋም አይችሉም ወይም እዉነተኛ የአንቲቫይረስ ሶፍትዌር አይደሉም፡፡
ከዚህ በታች ለኮምፒዩተራችን አስተማማኝ ጥበቃ የሚሰጡ
አንቲቫይረሶችን ዝርዝር አቅርበንላችኋል ተከታተሉን ፡፡
(1) Kaspersky Anti-Virus
መቀመጫውን ሩስያ ባደረገው Kaspersky Lab የተፈጠረው ይህ አንቲ ቫይረስ የኮምፒዩተር ቫይረሶችን በመለየትና በማጥፋት ረገድ ከሌሎች የአንቲቫይረስ ሶፍትዌሮች የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል። ከአመት አመት ልምድ እያካበተ የመጣው ይህ አንቲቫይረስ ለአጠቃቀም ቀላል እና ውጤታማ ጥበቃ ለኮምፒዩተሮች በመስጠት አንደኛ ደረጃን አግኝቷል።
AV-Test Institute = 18/20
(2) McAfee AntiVirus Plus
በሀገራችን ብዙ ልተለመደው ይህ የአንቲቫይረስ ሶፍትዌር አስተማማኝ ጥበቃ ለደንበኞቹ በመስጠትና በየሳምንቱየ
አንቲቫይረሱን ዴፍኒሽን አፕዴት በማድረግ ይታወቃል። ቫይረስ ዴፍኒሽኑን ቶሎ ቶሎ አፕዴት የማድረጉ ዋነኛ ጥቅም ሶፍትዌሩ ከተሰራ በኋላ የተለቀቁ አዳዲስ ባህሪ ያላቸውን ቫይረሶች ለመለየትእንዲያስችለውነው።
AV-Test Institute = 17.4/20
( 3) Bitdefender Antivirus Plus
ከተሻለ የቫይረስ ጥበቃው ላይ እንደተጨማሪ ግልጋሎት የተሰራለት Autopilot Mode አንድጊዜ ከተጫነ በኋላ ያለ ተጠቃሚው እርዳታ ማንኛውንም አይነት ግልጋሎትና ስካንበራሱ እንዲያከናውን ስለሚረዳው Bitdefender 3ተኛ ደረጃን ለመያዝ በቅቷል። የአንቲፊሺንግ ጥበቃው ከሁሉም አንቲቫይረሶች አስተማማኝ በመሆኑ Bitdefender የምንጠቀም ከሆነ የተጭበረበረ ዌብሳይት ላይ የመግባት እድላችን የጠበበነው።
AV-Test Institute = 17.2/20
( 4 ) Avast Pro Antivirus
በሀገራችን ብዙዎች የሚጠቀሙበት Avast በታዋቂው AV-Test Institute የደረጃ ምደባ መሰረት የአራተኛ ደረጃን ማግኘት ችሏል። Avast ቫይረሶችን ከተጠቃሚው ፋይሎች የሚለይበት መንገድና ኮምፒዩተሩን ፉልስካን የሚያደርግበት ፍጥነት በእጅጉ የተሻሻለ ሲሆን አምና ከነበረበት አምስተኛ ደረጃ ወደ አራት ከፍ ማለትችሏል።
AV-Test Institute = 16.9/20
( 5) ESET NOD32 Antivirus 9
በጥንታዊቷ ግብጽ የጤንነት የለምነትና የሰዎች ጠባቂዋ ጣኦት ኢሴት ስም የተሰየመው ይህ አንቲቫይረስ እንደስያሜው ሰዎችን ባይሆንም ኮምፒዩተሮችን በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅን ችሏል : በዚህም ምክንያት 5ተኛ ስፍራይን ይዞል::

ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ ሲጽፉ ምን ያህል ይፈጥናሉ?==============================ካልፈጠኑ የሚከተሉትን አጭር መግላጫ ይመልከቱ።• ሀ ፡ H ሁ ፡Hu ሂ ፡Hዓi ሃ ፡ Ha ...
15/05/2020

ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ ሲጽፉ ምን ያህል ይፈጥናሉ?
==============================
ካልፈጠኑ የሚከተሉትን አጭር መግላጫ ይመልከቱ።
• ሀ ፡ H ሁ ፡Hu ሂ ፡Hዓi ሃ ፡ Ha ሄ ፡Hy ህ ፡He ሆ ፡Ho
• ለ ፡L ሉ ፡Lu ሊ፡Li ላ ፡La ሌ፡Ly ል፡Le ሎ፡Lo
• ሐ፡Shift +h ሑ፡Shift +hu ሒ፡Shift +hi ሓ፡Shift +ha
ሔ፡ Shift + hy ሕ፡Shift +he ሖ፡Shift +ho
• መ፡M ሙ፡Mu ሚ፡Mi ማ፡Ma ሜ፡My ም፡Me ሞ፡Mo
• ሠ፡Shift + s ሡ፡Shift + su ሢ፡Shift + si ሣ፡Shift+sa ሤ፡Shift + sy ሥ፡Shift + se ሦ፡Shift + so
• ረ፡R ሩ፡Ru ሪ፡Ri ራ፡Ra ሬ፡Ry ር፡Re ሮ፡Ro
• ሰ፡S ሱ፡Su ሲ፡Si ሳ፡Sa ሴ፡Sy ስ፡Se ሶ፡So
• ሸ፡Shift s ሹ፡Shift +su ሺ፡Shift+si ሻ፡Shift+sa ሼ፡Shift +sy ሽ፡Shift+se ሾ፡Shift+so
• ቀ፡Q ቁ፡Qu ቂ፡Qi ቃ፡Qa ቄ፡Qy ቅ፡Qe ቆ፡Qo
• በ፡B ቡ፡Bu ቢ፡Bi ባ፡Ba ቤ፡By ብ፡Be ቦ፡Bo
• ተ፡T ቱ፡Tu ቲ፡Ti ታ፡Ta ቴ፡Ty ት፡Te ቶ፡To
• ቸ፡C ቹ፡Cu ቺ፡Ci ቻ፡Ca ቼ፡Cy ች፡Ce ቾ፡Co
• ነ፡N ኑ፡Nu ኒ፡Ni ና፡Na ኔ፡Ny ን፡Ne ኖ፡No
• ኘ፡Shift +n ኙ፡Shift +nu ኚ፡Shift+ni ኛ፡Shift +na ኜ፡ Shift +ny ኝ፡Shift + ne ኞ፡Shift +no
• ከ፡Ka ኩ፡Ku ኪ፡Ki ካ፡Ka ኬ፡Ky ክ፡Ke ኮ፡Ko
• ኸ፡capslock+ Shift+ h ኹ፡capslock+Shift+hu ኺ፡ capslock+Shift +hi ኻ፡Capslock+
Shift +ha ኼ፡ Capslock+ Shift +hy ኽ፡Capslock+ Shift+ he ኾ፡Capslock+ Shift + ho
• ኀ፡ Capslock + H ኁ፡ Capslock + HU ኂ፡ Capslock + HI ኃ፡ Capslock + HA ኄ፡ Capslock + HY ኅ፡ Capslock + HE ኆ፡ Capslock + HO
• አ ፡Capslock X ኡ፡Xu ኢ፡Xi ኣ፡Xa ኤ፡Xy እ፡Xe ኦ፡XoDe
• ዐ፡Shift +x ዑ፡Shift +xu ዒ፡Shift +xi ዓ፡Shift +xa ዔ፡ Shift +xy ዕ፡Shift +xe ዖ፡Shift +xo
• ወ፡W ዉ፡Wu ዊ፡Wi ዋ፡Wa ዌ፡Wy ው፡ We ዎ፡wo
• ዘ፡Z ዙ፡Zu ዚ፡Zi ዛ፡Za ዜ፡Zy ዝ፡Ze ዞ፡Zo
• ዠ፡Shift + Z ዡ፡Shift + Zu ዢ፡Shift + Zi ዣ፡Shift +Zaዤ፡Shift + Zy ዥ፡Shift + Ze ዦ፡ Shift + Zo
• ፈ፡F ፉ፡Fu ፊ፡Fi ፋ፡Fa ፌ፡Fy ፍ፡Fe ፎ፡Fo
• ፐ፡P ፑ፡Pu ፒ፡Pi ፓ፡Pa ፔ፡Py ፕ፡Pe ፖ፡Po
• ገ፡G ጉ፡Gu ጊ፡Gi ጋ፡Ga ጌ፡Gy ግ፡Ge ጎ፡Go
• ደ፡D ዱ፡Du ዲ፡Di ዳ፡Da ዴ፡Dy ድ፡ ዶ፡Do
• ጠ ፡ Shift + t ጡ፡ Shift + tu ጢ፡ Shift + ti ጣ፡ Shift+ta ጤ፡ Shift + ty ጥ፡ Shift + te ጦ፡ Shift + to
• ጨ፡ Shift +c ጩ፡Shift +cu ጪ፡Shift +ci ጫ፡Shift+caጬ፡Shift +cy ጭ፡Shift +ce ጮ፡Shift +co
• ጸ፡Capslock + t ጹ፡Capslock + tu ጺ፡Capslock + ti ጻ፡Capslock + ta ጼ፡ Capslock + ty ጽ፡Capslock + t ጾ፡Capslock + to
• ፀ፡Capslock+ Shift + t ፁ፡Capslock + Shift + tu ፂ፡Capslock + Shift + ti ፃ፡ Capslock + Shift + t ፄ፡Capslock + Shift + ty ፅ፡ Capslock + Shift + te ፆ፡Capslock + Shift + to
• ጀ፡J ጁ፡Gu ጂ፡Ji ጃ፡Ga ጄ፡Gy ጅ፡Ge ጆ፡Jo
• ቨ፡V ቩ፡Vu ቪ፡Vi ቫ፡Va ቬ፡Vy ቭ፡Ve ቮ፡Vo
• ቋ፡Capslock + qwa ቧ፡Capslock + bwa ቷ፡Capslock + twa ኟ፡Capslock + Shift +
nwa ቿ፡Capslock + cwa ሟ፡ Capslock + mwa ቷ፡Capslock + twa ጓ፡Capslock + gwa ፏ፡Capslock + fwa ሯ፡Capslock +• rwa ዷ፡Capslock + dwa ቯ፡Capslock + vwa ኋ፡ Capslock + hwa ዟ፡Capslock + zwa ዧ፡Capslock + Shif +zwa ኗ፡Capslock + nwa ሏ፡ Capslock + lwa ኳ፡Capslock + kwa ሷ፡Capslock + swa ጇ፡Capslock + jwa ጧ፡ Capslock + twa
==================================

የተዘጋ ስልክ ማለት ምን ማለት ነው ?unlock phoneኔትወርክ ሰጪ ድርጅቶች የምንላቸው የሞባይል ኔትወርክ የመስመር ስልክ እናየኢንተርኔት አገልግሎት የመሳሰሉትን ለህዝብ የሚያቀርቡ ድርጅ...
14/05/2020

የተዘጋ ስልክ ማለት ምን ማለት ነው ?
unlock phone
ኔትወርክ ሰጪ ድርጅቶች የምንላቸው የሞባይል ኔትወርክ የመስመር ስልክ እና
የኢንተርኔት አገልግሎት የመሳሰሉትን ለህዝብ የሚያቀርቡ ድርጅቶች ናቸው ። ለምሳሌ
ኢትዮጰያ ውስጥ ያለው የኔትወርክ አገልግሎት የሚሰጠው የኢትዮጰያ ቴሌኮሙኒኬሽን
ኮርፖሬሽን ነው ።
ወደ ሌላ ሀገራት ስንሄድ ከአንድ በላይ የኔትወርክ ሰጪ ድርጅቶች እናገኛለን አንድአንድ
አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መነሻ ካደረጉበት ሀገር በተጨማሪ አለም አቀፍ እውቅና
ያላቸው ናቸው ። ለምሳሌ T-mobile. Verizone.etisal
at.safaricom.me
tropcs.orange.chinamobile.Vodafone.Airtel.QteAt&t እነዚህ አገልግሎት
ሰጪ ድርጅቶች ሲም ካርድ በመስጠት ደምበኞቻቸውን ለመሳብ ከሚጠቀሙባቸው
መንገዶች አንዱ የሞባይል ቀፎ አምራቾች ከሚሸጡበት ዋጋ ቅናሽ ማድረግ ዋነኛው
ነው ቀፎ አምራቾች የምንላቸው ሳምሰንግ አፕል ኖኪያ ሞተሮላና የመሳሰሉት ናቸው
ኔትወርክ ሰጪ ድርጅቶች ከቀፎ አምራቾችየሚወስዷቸውን ቀፎወች በተወሰነ ቅናሽ
ለደንበኞቻቸው ከሲምካርድ ጋር ይሰጧቸዋል በመጀመርያ ላይ የሚያደርጉትቅናሽ
ለድርጅቱ ትክክለኛ ኪሳራ ነው ሆኖም ደንበኞቻቸው የአየር ሰአት በገዟቸው ቁጥር
ተጠቃሚ ይሆናሉ ነገር ግን በዚህ መንገድ የተገዙ ስልኮች የሌላ ኔትወርክ ሰጪ
ድርጅት የሆነን ሲምካርድ መቀበል አይችሉም ይህ የሆነበት ምክንያት ቀድሞ ያደረጉት
ቅናሽ ስላለ ሴኩሪቲ (ይለፍ) ያደርጉበታል ከላይ በተቀሰው መልኩ የተገዛ ስልክ ወደ
ኢትዮጰያ መቶ የኢትዮጰያ ሲም ካርድ ስናስገባበት ሊሰራ አይችልም ይህም የሆነው
ውጪ ሀገር ያለው ኔትወርክ ሰጪ ድርጅት ያስቀመጠው /ያኖረው/ሴኩሪቲ ይለፍ ስላለ
ነው ። በዚህ መንገድ ሲም አልቀበል ያለ ስልክ የተዘጋ ስልክ እንለዋለን ። ኮምፒዩተር
ሶፍትዌር በመጠቀም የተዘጉ ስልኮችን መክፈት እንችላለን
የተዘጉ ስልኮች የሚከተሉትን ፅሁፎች ያሳያሉ
* sim not valid
* wrong sim
* contact service provider
* unknown sim
* phone restricted
ከውጪ ሀገር የገቡ ስልኮች የምንከፍተው ሀገር ስለቀየሩ አይደለም ። መከፈት
የሚፈልጉ ስልኮች በሙሉ ከአምራች ሳይሆን ከኔትወርክ ሰጪ ድርጅቶች በመጠነኛ
ቅናሽ የተገዙ ስልኮች ናቸው ።
ከአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በቅናሽ የተገዛ ስልክ እዚያው ሀገር ሆነን የሌላን
አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ሲም ካርድ ብንከትበት አይሰራም።
ከአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የገዛነው ስልክ ከሌላ ሲም ጋር ለማዋሀድ /ለመክፈት/
ሁለት አይነት መንገድ አለ አንደኛው መንገድ ኮምፒዮተር ፍላሸር ቦክስ እና ፍላሽ ፋይል
በመጠቀም በራሳችን መክፈት ሲሆን ሁለተኛው መንገድ ደሞ ድርጅቱን በማግኘት
መጠነኛ ክፍያ በመፈፀም ማስከፈት ናቸው ። ክፍያው በኢንተርኔት ግብይት ስርአት (e-
commerce) በመጠቀም መክፈል ይቻላል ። ሁለተኛው መንገድ ለመጠቀም ክሬዲት
ካርድ /cridit card/ያስፈልገናል ። ከተመቾት ሼር ያርጉት
አዳዲስ መረጃዎችን ከኑሩ ሳይቴክ like እና share በማድረግ ብቻ

እንዴት ናቹ እስቲ ዛሬ ደሞ ስለ ኔትዎርክ::ስለ ኔትዎርክ ሲነሳ እኛ ሀገር መቼም……………………ለማንኛዉም ሰለ ኔትዎርክ ማቃትን ልበል እስቲ ጂ ማለት(Generation)1G,2G,2.5G,3G,4...
14/05/2020

እንዴት ናቹ እስቲ ዛሬ ደሞ ስለ ኔትዎርክ::
ስለ ኔትዎርክ ሲነሳ እኛ ሀገር መቼም……………………
ለማንኛዉም ሰለ ኔትዎርክ ማቃትን ልበል እስቲ ጂ ማለት(Generation)
1G,2G,2.5G,3G,4G,5G ድረስ ያሉትን በ አጭሩ
1ጂ
ከ1980-1990 ፍጥነቱ 2.4Kbps ሚሰራዉ በ አንድ ሀገር ዉስጥ ብቻ ነዉ ሚጠቀመዉ የ ሞገድ አይነት አናሉግ ነዉ መጀመሪያ ዩኤሰኤ(USA)ዉሰጥ ነዉ ደካማ ጎኑ የድምፅ ጥራት የለዉም ባትሪ ይጨርሳል ስልኩ ትልቕ ነዉ ሴኪዩሪቲ የለዉም
2ጂ
የተጀመረዉ ፊንላንድ ነዉ በ 1991 ዲጂታል ሞገድ ነዉ ሚጠቀመዉ እስከ 64kbps ደርስ ፍጥነት አለዉ መልእክት መላላኪያ አለዉ(SMS,MMS) ጥሩ የድምፅ ያሰማል
ደካማ ጎኑ ጠንካራ ሞገድ ይፈልጋል አንድ ቦታ ከተበላሸ ሌላ ቦታ ሞገዱ ይደክማል ብዙ ዳታ መላክ እና መቀበል አይችልም
2.5 ጂ
በ 2ጂ እና 3ጂ መካከል ይገኛል ኢሜል መላክ እና መቀበል ያስችለናል ኢንተርኔት ማስጠቀም ይችላል ፍጥነት64Kbps-144Kbps
3ጂ
በ 2000 አከባቢ ነዉ የተጀመረዉ ፍጥነቱ 144Kbps-2Mbps ትልቅ መጠን ያለዉ ኢሜል መላክ እና መቀበል ያስችላል እየተያዩ መደወል ይቻላል/3ዲ ጌሚንግ(3D GAMING) ቀጥታ ቲቪ ማየት/የስልክ ቲቪ ደካማ ጎኑ ዉድ ነዉ መስመሩን መዘርጋት ከባድነዉ ስልኮቹ ትልቅ/ዉድ ናቸዉ ብዙ ሞገድ ይጠቀማል
4ጂ
ፍጥነቱ ከ100Kbps-1Gbps ሌላ ስሙ (MAGIC) MAGIC
(M)obile Multimedia
(A)nytime Anywhere
(G)lobal Mobility Support
(I)ntegrated Wireless Solution
(C)ustomized Personal Services
ደካማ ጎኑ ባትሪ በጣም ይጠቀማል ዉስብስብ የሆነ ስልክ ያስፈልጋል ዉድ አቃዎች ያስፈልጋሉ መስመሩን ለመዘርጋት
5ጂ
ከ 2010 ጀምሮ ነዉ ኢሄ ሁሉን ነገሮች አሉት አንከን የለዉም ብዙ ነገር ይሰራል እያንዳንዱን ነገር ጥርት አርጎ ያሳያል (HD) ከሁሉም በጣም ፈጣን ነዉ በ አንድ ግዜ ብዙ ነገር ያስጠቅማል እስከ 1 Tbps ደርስ ፍጥነት አለዉ ምን እንዳልኩ ሰማቹ በ ሰከንድ እስከ 1000 ጂቢ ፍጥነት አለዉ ለ ማንኛዉም አገልግሎት በ 2020 ይቀርባል ተብሎ ይታሰባል:: መቼም ከዛሬ ጀምሮ ስለ ኔትወርክ ሲወራ ግራ አይገባቹም ቀኝ ነዉ ሚገባቹ
አስተያየት፣መጠየቅ፣ማወቅ የፈለጋቹት ነገር ካለ ኮሜንት ወይም inbox ጥያቄ ካለ ኮሜንት
ከተመቻቹ ላይክ እና ፍሬንዶች እንዲያዩት ሼር በማድረግ እንማማር፡፡

ያለ ምንም መሸወድ Smart ስልኮ እንተርኔት ሲጠቀሙ በጣም ብዙ የአየር ሰዓት እንዳይበላብዎ ማድረጊያ ትክክለኛው ቀላል ዘዴ!!!

በተንቀሳቃሽ ስልካችሁ እንተርኔት ሲትጠቀሙ 3G (ሦስቱ ጅቦች) የሞላችሁትን ካርድ ወዲያውኑ እየጨረሰባችሁ ፤ ደግሞም መላ አመጣን የሚሉ ፖስቶች እየሸወዷችሁ ለተቸገራችሁ… እውነተኛው መፍትሔ እነሆ፡፡ እነዚህን 10 ስቴፖች ብቻ በመከተል የእንተርኔት ወጪ መቆጠብ ትችላላችሁ። ይከተሉ፡-
Step 1. Open settings→Data usage
በአንዳንድ Samsung ስልኮች ላይ Settings→More→Data usage
Step 2. Touch the "Options" key ይንኩ።
Step 3. Check (✔) “Restrict background data” ከዚያም Pop-Up ሲመጣ “Ok" ይንኩ፡፡
Step 4. Go back to settings→Mobile networks→Network mode
በአንዳንድ Samsung ስልኮች ላይ Settings→More→Mobile networks→Network mode
Step 5. ከዚያም “GSM only“ የሚለውን (•) ይምረጡ፡፡
Step 6. ቀጥሎ “Use only 2G networks” የሚለውን Check (✔) ያድርጉ።
☞ እዚህ ላይ "Enable always-on mobile data" የሚለውን አትምረጡ (✔ አታድርጉ።)
Step 7. አሁን ደግሞ Go back to settings
Step 8. Scroll down to “Developer options” ከታች በኩል ያገኙታል፡፡
Step 9. Scroll down to “Background process limit”
Step 10. Select “No background processes” የሚለውን (•) ያድርጉ።
እዚህ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ፦
★Settings ውስጥ ስንገባ "Developer Options" የሚለው ቦታ (ከላይ Step 8) ለስልካችል በትክክል ተግባራቱን እንዲያከናውን አስፈላጊ የሆኑ ማስተካከያዎችን የያዘ ስለሆነ ከBackground process limit ውጪ ሌላ ነገሮችን መንካት የለብንም።
ደግሞም Developer Optionsን "OFF" ስናደርግ Background... በራሱ ወደ "Standard limit" ስለሚመለስ "ON" እንደሆነ መቆየት አለበት። ግን ሌላ ነገር ሳይነካ።
ተጨማሪ Tips
1. ☞ልብ ይበሉ፡- ሁሌም ስልካችንን አጥፍተን ስናበራ ወይም Power ON ስናደርግ (Restart/Rebootም ቢሆን) ምንም ነገር ከመክፈታችን በፊት Settings ውስጥ ገብተን Step 7-10 በመከተል “No background processes” የማለውን መምረጥ ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም ሁሌም ስልካችን ተዘግቶ ሲከፈት በራሱ “standard limit” ስለሚል ነው፡፡
2. ሁልጊዜ በሞባይል እንተርኔት ስንጠቀም (Google, Facebook, Viber, E-mail, Chat... ሁሉም ዓይነት ይሁን) በየመካከሉ ለአፍታ ቆም ብለን ጽሑፍ ስናነብ ፣ ፎቶዎችን ስናይም ሆነ መልዕክት ወይም Post የሚደረግ ነገር ስንጽፍ የስልኩን Notifications Pannel ከላይ ወደ ታች Flick አድርገን Data connection መዝጋት ፤ ከዚያም የጻፍነውን መልዕክት መላክ ፣ Post ማድረግ ስንፈልግ ወይም እንተርኔት ላይ ሌላ ቦታ ገብተን ሌላ ነገር ከፍተን ማየት ስንፈልግ እንደገና Notifications Pannel ከላይ ወደ ታች Flick አድርገን Data connection መክፈት አለብን፡፡ ይህም ከብክነት ይታደገናል፡፡
3. የተወሰኑ የስማርት ስልክ አፖች አንዳንዴ ያለፍቃዳችን ራሳቸውን በBackground አፕዴት (Update) ለማድረግ ስለሚሞክሩ ሳይታወቀን ገንዘባችንን በዚያው ይጨርሳሉ፡፡ ለዚህም መከላከያው Step 3 ነው፡፡
4. በተለይ 3G እየተጠቀማችሁ ብር በጣም ለሚበላባችሁ አበቃላችሁ። Step 5 እና 6 መፍትሄ ናቸው::
5. Play Store በWi-Fi ካልሆነ በስተቀር ፍጹም መክፈት የለብንም፡፡
6. 3G እንድትጠቀሙ ግን አልመክራችሁም!!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
አዲስ የቴሌግራም ቻናል ከፍተናል ይህ ቻናል የተከፈተዉ ለኑሩ ሳይቴክ ተከታታዩች ብቻ ነዉ
የቻናሉ አላማ የኑሩ ሳይቴክ ተከታታዮችን መጥቀም ነዉ ጥቅሙ እዉቀት ብቻ ሳይሆን ገንዘብም ነዉ ይህ ቻናል እኛጋ መስራት ለሚፈልጉ ብቻ ነዉ የተከፈተዉ እዚህ ቻናል ላይ መቀላቀል ወይም ገንዘብ ማግኘት የሚችሉ የዩቱብ ቻናል ወይም Gmail ያላቸዉ ብቻ ናቸዉ በዚህ ቻናል ላይ ማስተናገድ የምንችለዉ 1000 የኑሩ ሳይቴክ ተከታታዮችን ብቻ ነዉ

ስልክዎት በጣም busy ይሆንብዎታልአሪፍ መፍትሔ.. ..አሁን የማሣያችሁ ስልካችሁ አልፈጥን ወይም እየዘገየ ላስቸገራችሁ አሪፍ መፍትሔ ነው።...................................
14/05/2020

ስልክዎት በጣም busy ይሆንብዎታል
አሪፍ መፍትሔ.. ..
አሁን የማሣያችሁ ስልካችሁ አልፈጥን ወይም እየዘገየ ላስቸገራችሁ አሪፍ መፍትሔ ነው።.............................................
*መጀመሪያ setting ውስጥ ትገባላችሁ ...በመቀጠል *developer option ውስጥ ትገባላችሁ አንዳንድ ስልኮች ላይ developer option በቀጥታ ስለማናገኘው *about phone ውስጥ ገብተን build number የሚለየውን ደጋግመን ስንነካው developer option ይመጣልናል በመቀጠልም *window animation scale # transition animation scale & animation duration scale 3ቱንም off እናደርጋቸዋለን.....
አሁን ስልካችን ፈጠነ ማለት ነው።

ስልካችንን ስንጠቀም ማድረግ የሌለብን ነገሮችበዝናብ ሰዓት Networking የሆኑ ነገሮችን ማጥፋት (Airplane Mode ላይ ማድረግ) (ምክንያቱም ራዲየሽኑ መብረቅ ይስባል) | off wi...
14/05/2020

ስልካችንን ስንጠቀም ማድረግ የሌለብን ነገሮች
በዝናብ ሰዓት Networking የሆኑ ነገሮችን ማጥፋት (Airplane Mode ላይ ማድረግ) (ምክንያቱም ራዲየሽኑ መብረቅ ይስባል) | off wi-fi | Bluetooth | Main Network
FM(ኤፍ.ኤም) በEarphone አለማዳመጥ | ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ስማርት ስልኮች FM Antenna ስለሌላቸው ኢርፎኑን እንደ አንቴና ነው የሚጠቀሙት - ስለዚህ በኢርፎን ስናዳማጥ Eectromagnetic ራዲየሽኑ ጭንቅላታችን ላይ ጉዳት ያደርሳል።
ስልክን Charge እያደረጉ ማንኛውንም ነገር አለመጠቀም በተለይም | አለመደዋወል - Calling | Wifi አለመጠቀም | Gaming - ጌም አለመጫወት።
በEarphone ሙዚቃ ስናዳምጥ Equalizer በመጠቀም ድምፁን Bass ላይ ማድረግ (ምክንያቱም በNormal ድምፅ ስንጠቀም ያለው ለጆሯችን ቀጭን ድምፅ ስለሚያወጣ ያሳምመናል - የHz አለመጣጣም።
ትልልቅ Magnet (Magnetic field) ያላቸው ነገሮች አቅራቢያ ስልካችሁን አታስቀምጡ።
የስልክ ስክሪን Blue Light የሚባል አደገኛ ጨረር ይለቃል በተቻለ መጠን የስልካችንን Brightness መቀነስ / Blue Light Filter App መጠቀም።
የባትሪ ቻርጅ በጣም Low ሲሆን ወይም ሲቀንስ ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ | ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው የጨረር መጠን ይጨምራል።
ሞባይል ተጠቃሚ ከሆኑ ሲነጋገሩ ወደ ጆሮዎ እና ጭንቅላትዎ እጅግ በጣም አያስጠጉ | ቢያንስ ከ5 Centimetre በላይ ራቅ ማድረግ Electromagnetic Radiation ከተባለው አደገኛ ጨረር ራስዎን ይጠብቃሉ፡፡
የሞባይል ስልኮን ታቅፈው አይተኙ | በእንቅልፍ ወቅት ባትሪውን ያጥፉ ወይም ከአልጋዎ 1.8 metre በማራቅ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው Electromagnetic ራስዎን በተቻለ መጠን አያጋልጡ፡፡
ነፍሰጡር እናቶች ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ | የጽንሱ ሕዋሳት ለElectromagnetic radiation እጅግ በጣም አለርጂክ ናቸው | ስለዚህ አቀማመጡንም ሆነ አጠቃቀሙን ከጽንሱ ራቅ ባለ ሥፍራ ይሁን | አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረጅም ሰዓት ማውራት እና ቶሎ ቶሎ መደዋወል መቀነስ አለበዎት፡፡
ብረት ነክ ነገሮች ባሉበት ሥፍራ ሞባይል አይጠቀሙ | ብረት የኤሌክትሮማግኔቲክ ራድየሽኑን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል | ስለዚህ መኪና ውስጥ፣ አውሮፕላን ውስጥ፣ ሊፍት ውስጥ፣ ባቡር ውስጥ፣ ብረት አጥር ወይም በር አካባቢ፣ የብረታብረት ወርክሾፕ ውስጥ፣ ጋራዥ ውስጥ ወዘተ አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙ | የሚጠቀሙም ከሆነ ለአጭር ደቂቃ ብቻ ይሁን፡፡
በተለይ!!! በተለይ!!! ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ወጣት ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይሻላል | ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎቻቸውን እጅግ በጣም ይጎዳዋል፤ ለካንሰርም ያጋልጣቸዋል፡፡
በበለጸጉት አገሮች ከ15 ዓመት በታች ባሉ ልጆች ውስጥ ለሚከሰተው ሞት በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ምክንያት የጭንቅላት እጢ ነው | ወላጆች ይህንን እውነታ በመገንዘብ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ሞባይል መጠቀምን በመደበኛነት ልጆች አዘውትረው እንዳይለምዱት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ዕድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑት ሁሉ የጭንቅላታቸው ራስ ቅል በጣም ስስ ነው | ስለዚህ ጨረሩ ሙሉ ለሙሉ በስሱ አጥንት በኩል ወደ አንጎላቸው ሰርፆ ስለሚገባ ጥንቃቄ አድርጉ፡፡
ጨቅላ ሕፃናትና ትናንሽ ልጆች አጠገብ ሁነው ሞባይል አዘውትረው የሚነጋገሩ ከሆነ ለአደጋ ስለሚያጋልጣቸው አጠቃቀሙንና አቀማመጡ ከእነርሱ ራቅ ባለ ሁኔታ ላይ ያድርጉት፡፡
Smartphone አብዝተን ስንጠቀም የሚመጣው በሽታ
-Premature Death
-Diabetes
-Heart disease
-የተለያዩ የCancer በሽታዎች
-Discomfort
-Musculoskeletal Symptoms
ቴክኖሎጂ የራሱ የሆነ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ የራሱም የሆነ ከፍተኛ ጉዳት አለው ስለዚህ በተቻለን መጠን የSmartphone አጠቃቀማችንን እንቀንስ የዛሬው መልዕክታችን ነው።
Stay Tuned
══════❁✿❁ ══════
➹share &Join Us

ኦርጂናል እና ፌክ ሚሞሪ እንዴት መለየትይቻላልሚሞሪ ለመግዛት አስበዋል? አዎ!!!እና ታዲያ ሚሞሪ ሲገዙ ኦርጂናል ና ፌክ እንዴ መለየት እንደሚቻል ማወቅያለቦትአይመስሎትም?እንጀምር ..... ...
14/05/2020

ኦርጂናል እና ፌክ ሚሞሪ እንዴት መለየት
ይቻላል
ሚሞሪ ለመግዛት አስበዋል? አዎ!!!
እና ታዲያ ሚሞሪ ሲገዙ ኦርጂናል ና ፌክ እንዴ መለየት እንደሚቻል ማወቅ
ያለቦት
አይመስሎትም?
እንጀምር ..... ኦርጂናል ሚሞሪ ከፌኩ በምን ይለያል?
==============================
================
1ኛ. ኦርጂናል ሚሞሪዎችን የምናረጋግጥበት የመጀመሪያው ና ቀላሉ መንገድ
የሚሆነው ሚሞሪውን ስልካችን ውስጥ በማስገባት ፎርማት(Format)
ማድረግ
ነው። ሚሞሪውን ፎርማት(Format) ስናረገው ኦርጂናል ከሆነ ፎርማቱን ያለ
ምንም
ችግር ይጨርሳል
ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ፎርማት መሆን ስለ ማይችል ኢረር(Error) ቦክስ
ያሳያቹና
ይቋረጣል
==============================
===============
2ኛ.ሁለተኛው መንገድ ደሞ በ ኮምፒውተሮ ወይም በስልኮ ወደ ሚሞሪው
ፍይሎችን ኮፒ በማድረግ ማረጋገጥ ይቻላል ለምሳሌ አንድ 1GB የሚሆን
ፊልም
ወይም ሌላ ፍይል ወደ ገዛነው ሚሞሪ ኮፒ ስናደርግ በሚወስደው ሰዐት
ማወቅ
ይቻላል ኦርጂናል ከሆነ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ በጣም በዛ ከተባለ 5 ደቂቃ
ይወስዳል
ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ 1GB ፍይል ኮፒ ለማረግ 10 - 30 ደቂቃ ሊወስድ
ይችላል ይህ ማለት ሚሞሪው በጣም ደካማ ነው ማለት የው
3ኛ.ሶስተኛው መንገድ ደሞ ስልካችን ውስጥ በማስገባት ይህን SD insight
የተባለ አፕፕ(App) ተጠቅመን ማወቅ እንችላለን
አፑን ከዚህ ዳውንሎድ መድረግ ይችላሉ
https://www.apkmirror.com/apk/humanlogic/sd-insight-2/
sd-
insight-2-1-5-9-release/sd-insight-1-5-9-android-apk-do
wnload/
ስልካችን ውስጥ ሚሞሪ አስገብተን ይህን አፕፕ ስንከፍተው ስለ ሚሞሪው
ምርት
መረጃ ካሳየን ሚሞሪው ኦርጂናል ነው ማለት ነው
ለምሳሌ ሲሪያል ቁጥር እና የትአይነት እንደተመረተ እናም ሌሎችን ማለቴ ነው
ፎርጂድ(ፌክ) ከሆነ ደሞ ምንም መረጃ አያሳየንም ይህ ማለት
ሚሞሪው
የት እንደተመረተ እና ሲሪያል ቁጥር የለውም ማለት ነው ስለዚህ የማይታወቅ
ሚሞሪ ነው ማለት ነው
Like እና Share ማድረግ አይርሱ!

Address

ሁሌም አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት ይህን ፔጅ ላይክ ያድርጉ
Filakit

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኑሩ ዲሽ እና ሪሲቨር Nuru Dish & receiver posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኑሩ ዲሽ እና ሪሲቨር Nuru Dish & receiver:

Share