30/08/2025
30 ተቋማትን ያስተሳሰረው መተግበሪያ በድሬዳዋ…
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ አስተዳደር 30 ተቋማትን በማስተሳሰር የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያቀላጥፍ ''ቼቼ'' የተሰኘ መተግበሪያ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡
የአስተዳደሩ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኤጀንሲ ኃላፊ አብዱላዚዝ ሻፊ እንዳሉት÷ ወጣቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ከማብቃት ባለፈ የሥራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው።
በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና 7 ሺህ 832 ወጣቶችን ለማሰልጠን ታቅዶ ከ14 ሺህ በላይ ወጣቶች ሥልጠናውን እንደወሰዱ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናውን የወሰዱ ከ11 ሺህ በላይ ወጣቶች ከኢንዱስትሪና ከፋይናንስ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር የሥራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡
በአስተዳደሩ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች በተለይም በመንግስት ተቋማት የሚሰጥ አገልግሎት እንዲሻሻል እያገዙ ነው ብለዋል፡፡
ዜጎች ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ''ቼቼ'' የተሰኘ መተግበሪያ በልጽጎ አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም አመልክተዋል፡፡
መተግበሪያው 30 ተቋማትን በማስተሳሰር 500 የሚጠጉ አገልግሎቶችን መስጠት እንደሚያስችል ነው የተገለጸው፡፡
በተስፋዬ ሃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/ በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!