Nile Tender

Nile Tender we provide you with the latest tender information in Ethiopia.

19/09/2021

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የደ/ጎንደር ዞን ጽ/ቤት

መኪና ጎማ 7.50 በ16 ባለ12 ክር አዲስ ጎማ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን መስፈርት የሚያሟላ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራችሁ ነጋዴዎች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ የጨረታው መመሪያበጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባችሁ መስፈርት፡-የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤የግብር ከፋዮች (ቲን) መክፈያ ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ተጫራቾች ለሚሳተፉባቸው አይነት ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በዋጋ መሙያ መሙላት ይገባቸዋል፡፡ በነጠላ ዋጋና በድምር ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው የሚያዝ ይሆናል፡፡ ዋጋ ሲሞላ ስርዝ ካለ ፊርማ ሊኖረው ይገባል፡፡ ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ከበዛበትና ግልጽነት ከጎደለው ተወዳዳሪው ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የአጠቃላይ የተሞላው ዋጋውን 2 በመቶ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ 60 የቀን በአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ደ/ጎንደር ዞን ጽ/ቤት ትክክለኛ ስም በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታውን በወቅቱ አጠናቆ ያላቀረበ ማንኛውም ማስረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 7ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል አብቁተ ደ/ጎንደር ዞን ጽ/ቤት ህንጻ 4ኛ ፎቅ ዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 402 ዘወትር በስራ ሰዓት 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7ኛው ደ/ታቦር ከሚገኘው አብቁተ ደ/ጎንደር ዞን ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 101 አንደኛ ፎቅ ከቀኑ 6፡00 ድረስ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ኢንቨሎፕ በማሸግ የተወዳደሩበትን ጨረታ አይነት የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመጻፍ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡ ጨረታው በዚህ እለት ከቀኑ 8፡00 ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፡፡ ማስረከቢያ ደ/ጎንደር ዞን ደ/ታቦር ከሚገኘው ንብረት ክፍል የሚገዙ መኪና ጎማ 7.50በ16 ባለ12 ክር አዲስ ጎማ አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 101 የጨረታ ሰነድ ማግኘት ማየት ይቻላል፡፡ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ አማራ ብድርና ቁጠባ ደ/ጎንደር ዞን ቀበሌ 01 ደ/ታቦር ስ.ቁ 0584410659 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

19/09/2021

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የማዕ/ጎን/ዞን/ገን/ኢ/ትብ/መምሪያ

ተጫራቾችና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎችን ባሉበት መሸጥ ይፈልጋል፡፡የቀላል ተሸከርካሪ ያገለገሉ ጎማ በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ፡- ማንኛውም አካል በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የሚሸጡ ያገለገሉ ንብረቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማዕ/ጎን/ዞን ገ/ኢ/ት/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 14 በመምጣት የተሟላ የጨረታውን ዝርዝር ማስታወቂያ እና ሙሉ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ትችላላችሁ፡፡ ጨረታውን በጋዜጣ ከወጣ በኋላ በ16ኛው ቀን በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በተቀመጠው ቦታ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0581111309 /0581110420/ ፋክስ ቁጥር 0581112041 መደወልና ፋክስ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

የማዕ/ጎን/ዞን/ገን/ኢ/ትብ/መምሪያ

19/09/2021

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የጎንደር መም/ትም/ኮሌጅ

የቆርቆሮ መጋዝን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን / ያላቸው፤የግዥው መጠን ብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ከዚህ በፊት በተሰጣቸው አገልግሎቶች ችግር ኑሮባቸው በየደረጃው በተቀመጠው አግባብ ባለውና በሚመለከተው አካል እርምጃ ያልተወሰደበት መሆን አለበት፡፡ተጫራቾች ከ1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 ብር በመክፈል ከ03/01/2014 ዓ.ም እስከ 23/01/2014 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ፡፡ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተጫራቹ የሞላውን ዋጋ በትክክል በማስላት 2 በመቶ በባልክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በአማረኛ የታተመ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ በመቁረጥ ማቅረብ አለበት፡፡ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ /ፖስታ/ በጎንደር መም/ኮሌጅ በግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት ከ03/01/2014 ዓ.ም እስከ 24/01/2014 ዓ.ም 3፡30 ማስገባት ይችላሉ፡፡ ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ኮሌጁ ቫት ሰብሳቢ በመሆኑ የቫትን ሂሳብ /7.5 በመቶ ቆርጠን የምናስቀር መሆኑን እንገልጻለን፡፡በኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ማህበራትን በድጋፍ ደብዳቤ የማንቀበል /የማይጋብዝ/ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ጎ/መም/ትም/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር ጅ 1 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0581121634 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጎንደር መም/ትም/ኮሌጅ

19/09/2021

የመኪና መለዋወጫ እቃ ግዥ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 5/2014

በአብክመ በምዕ/ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት

በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የመኪና እቃ ሎት 1 LN166 LPRMDS TOTA ሞዴል ሎት 2 ኒሳን X980012649 ሞዴል መኪና ሎት 3 ላንድ ክሮዘር ሞዴል HZJ761 መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁር /ቲን/ ያላቸው፤የግዥው መጠን ብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-2 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1፣2 እና 3 ብር 5,000/ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥ እና ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳችሁ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ሀሳባቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በእያንዳንዱ ፖስታ ስምና አድራሻ በመጻፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታቸው ላይ የሚወዳደሩበትን የጨረታ አይነት ወይም ሎት በመጻፍ ሞጣ ከ/አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት አለባቸው፡፡ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ ሆነ በ16ኛው ቀን እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ላይ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሞጣ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡የጨረታ አሸናፊው ውል የሚይዘው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ነው፡፡ የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት በመሆኑ ሁሉንም የሎት ዋጋ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡

ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ለመጠየቅ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 18 በአካ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0586611890/0221 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

የሞጣ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት

19/09/2021

የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የምዕ/ጎጃም ዞን የስናን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ያገለገሉና አገልግሎት የሚሰጡ ንብረቶችን ባሉበት መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በጨረታው የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡የሚሸጡ ያገለገሉ ንብረቶችን ሎት 1 የደብረ ኤልያስ አሸዋ፣ ሎት 2 ለግንባታ የሚያገልግል ብረት ሎት 3 ለማገዶ የሚያገለግል እንጨት ሎት 4 ያገለገሉ የተሸከርካሪ ጎማና ካለመዳሪ ሎት 5 ያገለገሉ ኮምፒውተሮችን መሸጥ ይፈልጋል፡፡የሚሸጡ ያገለገሉ ንብረቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን የሽያጭ ጠቅላላ ዋጋ 7 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ዋናውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ን/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ መግዛትና ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን 4፡00 ይከፈታል፡፡በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 0582880122 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ ለሽያጭ የሚቀርቡ ያገለገሉ እቃዎች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚህ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ በተገለፀው ቦታ ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ በመሄድ ንብረቶችን ባሉበት ማየት ይቻላል፡፡ የጨረታው አሸናፊዎች በገቡት ውል መሰረት ያሸነፉበትን የንብረቶች ዋጋ ውሉን ከፈረሙበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ለመ/ቤቱ ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡በጨረታው ያሸነፉ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች የሚረከቡት ንብረቶቹ በተቀመጡበት /ሻጭ መ/ቤት በሚጠቅሰው/ ቦታ ይሆናል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-የጨረታ መክፈቻ ቀን የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎበተመሳሳይ ሰዓተት ጨረታው ይከፈታል፡፡ አድራሻችን ከደ/ማርቆስ በ27 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንገኛለን፡፡

የስናን ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

19/09/2021

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያበምዕ/ጎጃም ዞን የአዴት ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ስራ ላይ የሚውል የተለያዩ እቃዎች እና መገጣጠሚያዎች በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች ያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጨረታውም በሎት የሚታይ ይሆናል፡፡ ሎት 1 ፊቲንግ/መገጣጠሚያ፣ ሎት እስቴሽነሪ/ አላቂ እቃዎች/ ሎት 3 የኤሌክትሪክ እቃዎች በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይገልፃል፡፡ በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የ2013 ዓመተ ምህረት ግብር ከፍሎ ፈቃድ ያሳደሰ እና እቃው 50 ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑትን የሚያሳትፍ ይሆናለል፡፡የግብር ከፋይ ለመሆኑ መለያ ቁጥር /የምስክር ወረቀት/ አብሮ ማስያዝ አለበት፡፡የጨረታ ማስከበሪያ ሂሳብ ሲፒኦ /በጥሬ ገንዘብ/ የጠቅላላውን ዋጋ 1 በመቶ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡ ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡ተጫራቹ ድርጅት እቃውን በተጠየቀው ስፔስፊኬሽን እና ጽ/ቤቱ ውስጥ ባሉ ሳምፕሎች መሰረት ማቅረብ የሚችል፡፡በሌላ ተጫራች ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ተጫራቹ ዋጋ መሙያ የራሱ ማህተም፣ስም ፣ፊርማ፣ ስልክ ቁጥር ማስቀመጥ አለበት፡፡ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት በአየር ላይ ይቆያል፡፡ በዚሁ ቀን 5፡30 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ክፍት ሆኖ 6፡00 የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡ በ7፡30 ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾቹ ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት ጽ/ቤቱ ወደ ኋላ አይልም፡፡ የጨረታ መክፈቻ የበዓል ቀን ከሆነ ያንኑ ሰዓት ጠብቆ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ማንኛውም ወጭ ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ተጫራቾች የበለጠ ለመረዳት ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0985895037/0583380793 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሰነዱን ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዘርፉ የሚመለከታቸው ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 ከፍሎ ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ፡፡አሸናፊው ድርጅት እቃውን አዴት ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ሊያቀርብ ነው፡፡የሚገዙ የእቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፖስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዟል፡፡ ሳፕል ከጽ/ቤት ማየት ይቻላል፡፡ የሚቀርቡ እቃዎች በእኛ የጥራት ኮሚቴ እቃው ታይቶ ጥራቱ ዝቅተኛ ከሆነ /ጥራት ከሌላቸው/ ጽ/ቤቱ የማይረከብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የአዴት ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት

Address

Bahir Dar

Telephone

+251912890707

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nile Tender posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Nile Tender:

Share