21/05/2026
በ$19 ቢሊዮን ዶላር ሶፍትዌር የሸጠው ሊቅ🙄
ይህ ታሪክ በትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ውድቅ የተደረገ፣ ነገር ግን ሳይንበረከክ በአለም ላይ ትልቁን እና ተፅዕኖ ፈጣሪውን ሶፍትዌር የሰራ አንድ እውነተኛ ጀግና ታሪክ ነው።
የታሪኩ ባለቤት ብራያን አክተን (Brian Acton) ይባላል። ብራያን እ.ኤ.አ በ2009 ዓ.ም በህይወቱ ትልቅ ውድቀት ገጥሞት ነበር። ለረጅም ዓመታት ሲሰራበት የነበረውን ያሁ (Yahoo) ኩባንያ ለቆ አዲስ ስራ በመፈለግ ላይ ነበር።
በወቅቱ ገና በጉልበት እየተነሳ ወደነበረው ፌስቡክ (Facebook) ኩባንያ ሄዶ ለስራ ቃለ-መጠይቅ (Interview) አደረገ። ነገር ግን የፌስቡክ ባለስልጣናት የብራያንን እውቀት ዝቅ አድርገው በመመልከት ለእኛ ኩባንያ አትመጥንም ብለው አባረሩት። ብራያን ተስፋ አልቆረጠም፤ ወደ ትዊተር (Twitter) ሄደ፣ እዚያም በተመሳሳይ መልኩ ውድቅ ተደረገ።
ብራያን ግን በወቅቱ በትዊተር ገጹ ላይ እንዲህ ሲል ጻፈ፦ ፌስቡክ ውድቅ አድርጎኛል። ከአስደናቂ ሰዎች ጋር ለመስራት ጥሩ እድል ነበር። ወደ ቀጣዩ የህይወት ምዕራፍ እጓዛለሁ!
ይህ ውድቅ መደረግ ግን በዓለም ላይ ትልቁን የቴክኖሎጂ አብዮት እንደሚፈጥር ማንም አላወቀም ነበር!
ከአይፎን መምጣት ጋር የተወለደው ታላቁ ሶፍትዌር
ብራያን ከጓደኛው ከጃን ኮም (Jan Koum) ጋር በመሆን የሰዎችን የዕለት ተዕለት የኮሙኒኬሽን ችግር የሚፈታ አንድ ቀላል ሶፍትዌር (App) ለመስራት ወሰኑ። ስልኮች ላይ በጣም ውድ የነበረውን የፅሁፍ መልእክት (SMS) የሚያስቀር እና በኢንተርኔት ብቻ በፍጥነት መልእክት የሚለዋወጡበትን ሶፍትዌር ሌት ተቀን ኮድ ማድረግ ጀመሩ።
ይህ የሰሩት ሶፍትዌር በአጭር ጊዜ ውስጥ መላውን ዓለም አናወጠ። ስሙም WhatsApp (ዋትስአፕ) ይባላል!
ዋትስአፕ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ስልክ ላይ እንደ ሰደድ እሳት ተሰራጨ። በጣም ቀላል፣ ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ በመሆኑ፣ በዓለም ላይ ካሉ ሶፍትዌሮች ሁሉ ፈጣኑን እድገት አስመዘገበ።
ታሪካዊው በቀል እና የ$19 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት
ዋትስአፕ እያደገ ሲሄድ፣ ከጥቂት ዓመታት በፊት ብራያንን አትመጥነንም ብሎ ያባረረው ፌስቡክ (ማርክ ዙከርበርግ) በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ወደቀ። ዋትስአፕ የፌስቡክን ህልውና አደጋ ላይ እየጣለበት መሆኑን ተረዳ።
እ.ኤ.አ በ2014 ፌስቡክ ዋትስአፕን ለመግዛት ታሪካዊ ጥያቄ አቀረበ። ከ5 ዓመታት በፊት ለስራ እንኳን አልቀጥርህም ያለው ፌስቡክ፣ አሁን የብራያንን ሶፍትዌር በእጁ ለማስገባት በአለም የቴክኖሎጂ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ዋጋ $19 ቢሊዮን ዶላር (19,000,000,000$) ከፍሎ ለመግዛት ተገደደ.
ብራያን አክተን በአንድ ጀምበር ከዓለማችን ቢሊየነሮች ተርታ ተሰለፈ። በአንድ ወቅት ውድቅ ያደረጉት ኩባንያዎች በእግሩ ስር ወድቀው ሶፍትዌሩን ለመለመን ተገደዱ።