የጉባ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት /Guba woreda Civil service sector

  • Home
  • Ethiopia
  • Asosa
  • የጉባ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት /Guba woreda Civil service sector

የጉባ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት /Guba woreda Civil  service sector Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የጉባ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት /Guba woreda Civil service sector, Computer Company, Guba, Asosa.

lct የኮምፕዩተር እውቀቶን ያሳድጉ
ከyoutube ላይ ቪድዮ ወይም ፊልም ዳውንሎድ ማድረግ ይፈልጋሉ? አሁን የምናየው ከyoutube ላይ ቪድዮ እንዲሁም የሙዚቃ ክሊፕ ወይም ፊልም እንዴት ዳውንሎድ ማድረግ እንደሚቻል ነው። የሚከተሉትን 5 እስቴፓች ይጠቀሙ። step1: መጀመሪያ ወደ www.youtube.comይሂዱ። step2: ከዚያም የሚፈልጉትን ቪድዮ ይምረጡና ያጫውቱት ወይም Play ያድርጉትና ከላይ Adress bar ውስጥ ያለውን የቪድዮውን ሊንክ copy ያድርጉት። step3: ከዚያም አዲስ ታብ(New tab) ይክፈቱና ወደ www.en.savefrom .netይሂዱ። step4: ከዚያም የዌብሳይቱ ሰርች ኤንጅን ውስጥ የቪድዮውን ሊንክ past ያድርጉትና Enterን ይጫኑ። step5: በመቀጠልም የሚፈልጉትን የቪድዮ format ይምረጡና ዳውንሎድ ያድርጉ። plus

19/04/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ ትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን! በባዓሉ ለት ተራርቀን ሳይሆን ተቀራርበን
☑ ተበታትነን ሳይሆን ተሰባስበን
☑ ተነቃቅፈን ሳይሆን ተደጋግፈን
☑ ተገደን ሳይሆን ወደን ለጋራ ስኬት እጅ ለእጅ ተያይዘን ለነገ ጉዟችን የምንዘጋጅበት ፣
ውበትና ቁንጅናችን ጎልቶ የሚታይበት በዓል የአንድነት ፣ የሠላም ፣
የፍቅር ፣ የመከባበር ፣ የመረዳዳት ፣ የእድገት እንዲሆንላችሁ የጉባ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት
መልካም ምኞቱን ይገልፃል

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን! በባዓሉ ለት ...
29/03/2025

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር እና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን! በባዓሉ ለት ተራርቀን ሳይሆን ተቀራርበን
☑ ተበታትነን ሳይሆን ተሰባስበን
☑ ተነቃቅፈን ሳይሆን ተደጋግፈን
☑ ተገደን ሳይሆን ወደን ለጋራ ስኬት እጅ ለእጅ ተያይዘን ለነገ ጉዟችን የምንዘጋጅበት ፣
ውበትና ቁንጅናችን ጎልቶ የሚታይበት መጪው የኢድ አልፈጥር በዓል የአንድነት ፣ የሠላም ፣
የፍቅር ፣ የመከባበር ፣ የመረዳዳት ፣ የእድገት እንዲሆንላችሁ የጉባ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት
መልካም ምኞቱን ይገልፃል

Please
29/01/2025

Please

በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !!!!!!!!!!!!!
07/01/2025

በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ

እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም

አደረሳችሁ !!!!!!!!!!!!!

ይነበብ
20/12/2024

ይነበብ

በጉባ ወረዳ  የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ ።ጉባ ህዳር 10/2017 ዓ.ም / ጉባ ወረዳ ሲ /ሰ/ጽ/ቤትየጉባ ወረዳ  አመራሮች ፣  መንግሥት ስራተኞች ፣ከማንኩሽ ቀበሌ የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች...
19/11/2024

በጉባ ወረዳ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ ።

ጉባ ህዳር 10/2017 ዓ.ም / ጉባ ወረዳ ሲ /ሰ/ጽ/ቤት
የጉባ ወረዳ አመራሮች ፣ መንግሥት ስራተኞች ፣ከማንኩሽ ቀበሌ የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት በከተማው ውሰጥ የፅዳት ዘመቻ ተካሄዷል ።

በዕለቱ የተገኙት የጉባ ወረዳ ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሪት ቢሴና ረጀብ የከተማውን ፅዳት መጠበቅ የሁሉም ድርሻ መሆኑን ገልጸው።

በዛሬው ዕለት በአመራርና በሠራተኛው ግንባር ቀደምትነት የተካሄደው በአርአያነት ማህበረሰቡን ለማነቃቃት መሆኑን አፈ-ጉባኤዋ በመግለጽ በጽዳቱ ለተሳተፉት ሁሉንም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ይነበብ
08/11/2024

ይነበብ

05/11/2024

ይህ ድህረ ገፅ የጉባ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት ትክክለኛ ድረ ገፅ ሲሆን በዚህ ፔጅ የሚለቀቁ ማንኛውም ወቅታዊ መረጃ ትከታተሉ ዘንድ ተጋብዛችኋል። ፅ/ቤቱ
እዲሁም መስተካከል ያለበት ነገር ካል በደዕረ ገፁ ላይ ማንኛውንም አሰተያየት የምነቀበል ይሆናል እናመሰግናለን።

ለኑሮ ውድነት መቋቋሚያ የሚሆን የደመወዝ ጭማሪ ተፈቅዶና በጀቱም ጸድቆ ክፍያው ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም.  ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል።  ከገንዘብ ሚኒስቴር የተፈቀደውን በጀት፣ የአፈጻጸም ...
21/10/2024

ለኑሮ ውድነት መቋቋሚያ የሚሆን የደመወዝ ጭማሪ ተፈቅዶና በጀቱም ጸድቆ ክፍያው ከጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል። ከገንዘብ ሚኒስቴር የተፈቀደውን በጀት፣ የአፈጻጸም መመሪያውንና የክፍያ ትዕዛዙን ለ12ቱ ክልሎች፣ ለሁለቱ የከተማ አስተዳደሮችና ለፌደራል ተቋማት ዛሬ አስተላልፈናል።

የተከበራችሁ የመንግስት ሰራተኞች:-
የኑሮ ውድነቱ በሰራተኞቻችን ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት መንግስትና ዜጋው ተጋግዞ እንዲቋቋመው በማሰብ የደመወዝ ክፍያ እስኬሉ ማስተካከያዎችን ከጥቅምት 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተደርጓል። በዚህም ደስተኛ ነኝ። ይህ ማስተካከያ ሁሉም የመንግስት ሠራተኞች በእነዚህ የኑሮ ውድነት ፈታኝ ጊዜያት ኑሯቸውን በተወሰነ ደረጃ እንዲቋቋሙት ያግዛቸዋል። በተለይ የውጭ ምንዛሪ የሚመራበት የግብይት ሥርዓት ሲቀየር የተመራበት ሁኔታ ጥሩ በመሆኑ የደመወዝ ማስተካከያው በተለይ ለዝቅተኛ ተከፋይ ለነበረው ሰራተኛ የሚኖረው ፋይዳ መልካም የሚባል ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በተነጻጻሪ የተሻለ ክፍያ ለምታገኙ ሰራተኞቻችን የተደረገው ማስተካከያ መጠነኛ መሆኑ መንግስት ይገነዘባል። ለደመወዝ ማስተካከያው መንግስት በተለይ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችን በወሰዱት ቁርጠኛ ውሳኔ ከሌሎች ብዙ ሥራዎች ተሸጋሽጎ የተመደበ ከአገራችን የመክፈል አቅም ጋር ሲመዛዘን እጅግ ግዙፍ በጀት ነው። የአገሪቱ የመክፈል አቅምንም በከፍተኛ ደረጃ የሚፈትንም ነው። በመሆኑም መጠነኛ ጭማሪ ያገኛችሁ የመንግስት ሰራተኞችም ብትሆኑ መደሰትና መንግስትን ማመስገን ተገቢ ይሆናል።

በሚሆንም በማይሆንም ጉዳይ የሲቪል ሰርቪስ ተቋምን መርገም ተገቢ አይደለም። ሴክተሩ የብዙ ዘመናት የተጠራቀመ ችግር ያለበትና ከተተበተበበት ፈርጀ ብዙ ውስብስብ ችግር ለማውጣት መንግስት ቁርጠኛ አቋም መውሰድ ጀምሯል። በተያዘው መንግድ ከቀጠልን መልካም ህልም ከፊት ለፊታችን ወገግ ብሎ ይታያል። እሴት ከማይጨምር መወቃቀስ ይልቅ ፈተናውን በጋራ ተጋፍጠን ሪፎርሙን ብናሳካ እላለሁ።

በየደረጃው ያለው የንግዱ ህብረተሰብ ይህ የደመወዝ ጭማሪ በጥቅል ሲታይ ብዙ ይሁን እንጂ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ በእጁ የሚደርሰው ብዙ የሚባል አይደለም። የደመወዝ ማስተካከያ ተደረገ ብሎ ያለምክንያት ዋጋ መጨመር ተገቢ አይደለም። ተቆጣጣሪ አካላትም ይህንን በሚያደርጉት ላይ አስተማሪ እርምጃ መውሰድ ይገባል።

በቀጣይ በሚኖረው የመንግስት ሪፎርም ሁላችንም በየተመደብንበት ሥራ በጽናትና በትጋት ለአገራችን እድገት ከሰራን ጥሩ ውጤት በፍጥነት እናስመዘግባለን። በጋራ ተባብረን በአገልግሎት አቅርቦት ላይ ህዝቡ የሚያቀርበውን እሮሮ ተቀናጅተን እንፍታው። ዜጎች አገልግሎት ለማግኘት ወደየመስሪያ ቤቶቹ ሲሄዱ ክብር እንዲሰማቸው ማድረግ ይጠብቅብናል። መንግስት አሁን የጀመረውን የሠራተኛውን የክፍያ ሥርዓት የማስተካከሉ አንጀዳ በቀጣይ ተገማችና የመንግስት ሠራተኞች ህይወት የሚያሻሽል እንዲሆን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በርትቶ ይሰራል።

የሀዘን መግለጫ                                         ***የጉባ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት የሰራ ባልደረባ  የሆኑት ወ/ሮ ፅሀይ አለማየሁ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመ...
18/10/2024

የሀዘን መግለጫ
***
የጉባ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት የሰራ ባልደረባ የሆኑት ወ/ሮ ፅሀይ አለማየሁ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ህይወታቸው አልፏል።

በፀሀይ አለማየሁ ህልፈተ ህይወት የሲቪል ሰርቨሰ ጽ/ቤት አመራርና ሰራተኞች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለመላው ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።
ነብስዎ በሰላም ትረፍ!!

የውይይት መድረክ ጥሪ
12/09/2024

የውይይት መድረክ ጥሪ

Address

Guba
Asosa

Telephone

+251937696972

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጉባ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት /Guba woreda Civil service sector posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share