Birhan Training Institute

Birhan Training Institute (Services): ሥልጠናዎች, ኮምፕዩተሮችና ሌሎች ,አክሴሰሪዎችን መግ

Welcome to Birhan Training Institute, your go-to YouTube channel for mastering computer skills, IT expertise, soft skills, and cutting-edge technology! Whether you're a beginner looking to navigate the digital world or a pro aiming to level up, our engaging tutorials, practical tips, and in-depth guides cover everything from coding and cybersecurity to communication and productivity. Subscribe now

and unlock your potential in the ever-evolving world of tech!

እንኳን ወደ ብርሃን ማሠልጠኛ ተቋም በደህና መጣችሁ፣ ቻናላችን አዳዲስ ክህሎትና ዕውቀት ለሚፈልጉ ሰዎች ስለ መሠረታዊ ኮምፕዩተር ክህሎት፣ የተሻለ የአይቲ ልምድ፣ የማነቃቂያ ሥልጠናዎች እንዲሁም አነጋጋሪ ስለሆኑ ሰሞነኛ ቴክኖሎጂዎች ላይ በቂ ሥልጠና ይሰጣል። በአይቲ ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድና ዕውቀት ባካበቱ አሠልጣኞች የሚፈልጒትን ሥልጠና መውሰድ ይችላሉ። በጥያቄዎ መሠረትም ማወቅ በሚፈልጒት ርዕስ ላይም ሥልጠና እንሰጣለን። ከእርሱ የሚጠበቀው ቻናላችንን ሳብስክራይፕ ማድረግ ብቻ ነው።

Leadership dilemma``````````````````````````````````The best way to predict the future is to create it.Abraham Lincolnሁል...
07/05/2026

Leadership dilemma
``````````````````````````````````
The best way to predict the future is to create it.
Abraham Lincoln

ሁልጊዜ መሪዎች በሁለት አስቸጋሪ ምርጫዎች መካከል ሚዛን ለመጠበቅ ይገደዳሉ። አንደኛ በሌላኛው የዓለም ጥግ የሚከናወኑ፣ ነገር ግን ውጤታቸው ዓለም ዐቀፋዊ አስከትሉት ያላቸዉ ጒዳዮች ሲሆኑ ሁለተኛው ወደ ፊት ሊከሰቱ ስለሚችሉ ጉዳዮች ወይም በአጭሩ የነገ ጒዳይ ነው። እጃችን ላይ በደርዜን የሚቈጠሩ አንገብጋቢ ችግሮች እያሉ የሩቁን ማሰብ ለምን አስፈለገ? የሚል ጥያቄ ነው። ወይም ዛሬ እጅግ አጣዳፊና ፋታ የሚነሡ ብዙ ችግሮች በዙሪያችን ሞልተው እያለ ስለማንኖርበት ነገ መጨነቊ የጤና ነው? ብሎ አንድ ሰው ሊጠይቅ ይችላል። እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች የሚነሡት አንድም ዓለም ዐቀፋዊ ችግሮች ላይ ውይይት ሲደረግ አሊያም ወደ ፊት ሊከሰቱ ስለሚችሉ ችግሮች ላይ ትኲረት ሲደረግ ነው። ዓለም ዐቀፋዊም ሆነ የነገ ጒዳዮች ላይ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎች መነሣታቸው ብዙ አይገርምም። ይኸ አስተሳሰብ አብዛኛው ሕዝብ የሚጋራው ነው። በርግጥም ለብዙ ዘመናት የነበሩ የሰው ልጆች ጥናት በአመዛኙ ትናንትናና ዛሬ ላይ ያተኮረ ነበር። የምናውቀው ስለ ወደፊት ወይም ነገ ብዙ ትኲረት ሲሰጥ አይስተዋልም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ‘የነገ’ ጥናት ወይም “Future Study” (Futurology) በጣም ታዋቂ እየሆነ መቷል። ከዚህ በተጨማሪ ዓለም ሉላዊ ከመሆኗ የተነሣ ችግሮችን ለመፍታት በተናጥል የሚደረግ ሙከራ ቀርቶ በጋራ መወያየት ላይ ትኲረት ማድረግ የተሻለ አማራጭ እየሆነ ይገኛል። ከነዚህ ሙከራዎች መካከል አንዱ የሮም ክለብ (Club of Rome) የተሰኘ ቡድን በ1972 ዓ.ም ያሳተመው ሪፖርት ነው። በሪፖርቱ ላይ የሰው ልጆች ለሚኖሩበት ዓለም ያላቸው አስተሳሰብ ቀጥሎ ባለው ግራፍ አስቀምጠዋል።

(see the attached graph):-

ግራፉ በጊዜና (Time and Space) በቦታ የተዋቀረ ነው። ቊሙ መስመር (y co-ordinate) ቦታ (Space) የሚያመልክት ሲሆን አግዳሚው መስመር (x co-ordinate) ጊዜን (Time) ያመለክታል። ነጥብጣቦቹ ሰዎች ሲሆኑ በምን ጒዳዮች ላይ ትኲረት እንደሚያደርጒ ያሳያል። ብዙ ነጥብጣቦች ብዙ ሰው የሚያመለክቱ ሲሆን ዘርዘር ያሉ ነጥቦች ጥቂት ሰዎችን ያሳያሉ። ከግራፉ እንደምንረዳው አብዛኛው ሰው የቅርብ ጊዜ ችግሮችንና በአብዛኛው በራሱ ቤተሰብ ዙሪያ ብቻ የሚያውጠነጥን ነው። አብዛኛው ሰው ከጊዜ ዕለታዊ ችግሮች ላይ ብቻ ትኲረት የሚያደርግ ሲሆን ከቦታ አንጻር የራሱ ወይም የራሱ ቤተሰብ ጋር የተያያዙ ጒዳዮች ላይ ብቻ ትኲረት ያደርጋል። ጧት ከእንቅልፉ ተነሥቶ ወደ ዕለት ተግባሩ የሚሰማራው የዕለት ጒርሱን ለማሸንፍ ሊሆን ይችላል። በሌላ ጎን ደግሞ የሚሠራው የአጭር ጊዜ (ምናልባት የዛሬ ወይም የሳምንት) ጉርሻው እንዳይጎድልበት ሊሆን ይችላል። በጣም አሰበ ከተባለ የወሩ ወይም የዓመቱ የኑሮ ዋስትና ለማረጋገጥ ሊሆን ይችላል። ከራሱ ሕይወት አልፎ የሌሎችን ሰዎች ሕይወት በአዎንታዊ መልክ ለመለወጥ የሚያስብ ሰው በጣም ጥቂት ነው። እንዲሁም ከዛሬ አሻግሮ በመመልከት የትውልድ ጉዳይ የሚያሳስበው ሰው ብዙ አይደለም። በአጭር አገላለጽ ከራስና ከራስ ዘመድ አልፎ ለሌሎች የሰው ልጆች ማሰብ እንዲሁም ነገ የሚመጣውን ትውልድ እያሰበ የሚሠራ ሰው በጣም ጥቂት ነው።

እሩቅ የሚያስቡና የብዙ ሰዎች ሕይወት ለማሻሻል የሚጥሩ ሰዎች ቊጥራቸው እጅግ በጣም ጥቂት ነው። ከዛሬ ችግሮች በላይ አሻቅቦ ነገ ሊከሰት ስላለው ችግር ከወዲሁ ዝግጅት እንዲደረግ የሚያሳስብ ሰው ብዙ አይደለም። ከዚህ የተነሣ አንዳንድ ችግሮች በግልጽ ፈጥጠው እየታዩ እንኳን፣ አብዛኛው ሰው በቀጥታ እራሱን ወይም ቤተሰቡን የማይነካ ስለሚመስለው ግድ አይሰጠውም።

ብዙውን ጊዜ ወቅታዊ ችግሮች ላይ ብቻ አተኩሮ ነገ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመገመት አለመሞከር ችግሮቹ ድንገተኛ አደጋ ሆነው ከተፍ ብለው እንዲከሰቱ ምክንያት ይሆናል። ይኸ አካሄድ አጸፋዊ (Reactive) ምላሶችን ብቻ እንድንሰጥ ያስገድደናል። ችግሮች ይፈጠራሉ፣ ከዚያ በኋላ ለመፍትሔ እንሯሯጣለን። አንዳንድ ችግሮች ደግሞ ችግር ሆነው ሲታዩ ብዙ ብልሽት ካደረሱ በኋላ ስለሆነ መፍትሔያቸው ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፣ መፍትሔው ተገኝቶ ከሆነ።

ተቋማትንም እንደ ሰዎች/ግለሰቦች መውሰድ እንችላለን። ሁልጊዜ በወቅታዊና ደራሽ ሥራዎች ላይ ብቻ ትኲረት የሚያደርግና ስልታዊ ዕቅዶች ላይ ትኲረት የማያደርግ ተቋም በዛሬው ዓለም በሕይወት መቀጠል አይችልም። በዚህ ዘመን ጠንካራና ዘመን ተሻጋሪ ተቋማትን ለመመሥረት ከሚያስፈልጒ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ዓለም ዐቀፋዊ አውድን በተከተለ መልኲ እራሱን ሲያደራጅና ነገን በመገመት የተለያዩ የዕቅድ አማራጮችን ሲይዝ ነው። ይኸ አካሄደ ተለማጭነት (Adaptability) ይሰኛል። በ21ኛው ክፍለ ዘመን እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ የመርነት ክህሎቶች መካከል አንዱ ነው። ዓለም ተለዋዋጭ በመሆኗ በአንድ ስልታዊ ዕቅድና እሳቤ ላይ ብቻ ተቸንክሮ መቆየት ዋጋ ያስከፍላል። ይልቊን ብዙ የይሆናል አማራጮችን ይዞ ሁሌ ለለውጥ መዘጋጀት የተሻለ አማራጭ ሆኖ ተገኝቷል። በአጋጣሚ የመጀመርያ አማራጭ ሳይሳካ ሲቀር ሁለተኛ አማራጭ ይወሰዳል። ይከሰታሉ ተብለው የሚገመቱ ችግሮች ቀድሞ (Scenario) ዝግጅት ስለሚደረግ አስከትሎቶቻቸው (impacts) ይቀንሳል።
ስለ ነገ ማሰብም ሆነ ዓለም ዐቀፋው አውድን ባማከለ መልኲ ችግሮችን መተንተን ማለት ወቅታዊ ችግሮችንና አካባቢያዊ ችግሮችን መዘንጋት ማለት አይደለም። ጊዜ የማይሰጡ አንገብጋቢ ችግሮችን እየፈቱ በዚያ ልክ ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሔ እያበጁ መሄድ የተሻለ አማራጭ ነው። አለበለዚያ በተመሳሳይ ችግሮች ላይ ዘመናትን የመፍጀት አዙሪት ውስጥ ይከታል። አንዳንድ ችግሮች በተፈጥሮአቸው ዓለም ዐቀፋዊ አውድን በመረዳት የሚፈቱ ናቸው።

ስለዚህ በዚህ ዘመን ያለ ማንኛውም ሰው፣ በተለይ በመርነት ደረጃ ያለ ሰው ዓለም ዐቀፋዊ አውድን የተገነዘበ፣ ዘላቂ መፍትሔ ማበጀት የሚችል ሰው መሆን ይኖርበታል። ጎበዝ የሆነ መር ከጠቅላላው ሕዝብ በተሻለ ሁኔታ ነገን አሻግሮ ማየት የሚችልና ከራሱ የግል ጥቅም አልፎ ለሰው ልጆች የጋራ ደህንነትና ሰላም መሥራት የሚችል ነው።

ሁለንተናዊ ደህንነትመግቢያደህና ነህ? ወይም ደህና ነሽ? ደህና ናችሁ? መባባል በኛ አገር ባህል የተለመደ የሰላምታ መለዋወጫ መንገድ ነው። ምላሹ ደግሞ ተጠያቂው/ሰላምታ የቀረበለት ሰው ደህና...
22/03/2026

ሁለንተናዊ ደህንነት

መግቢያ

ደህና ነህ? ወይም ደህና ነሽ? ደህና ናችሁ? መባባል በኛ አገር ባህል የተለመደ የሰላምታ መለዋወጫ መንገድ ነው። ምላሹ ደግሞ ተጠያቂው/ሰላምታ የቀረበለት ሰው ደህና መሆኑን ከተናገረ በኋላ ለዚህ ደህንነት ፈጣሪን የሚያመሰግን ቃል ያስከትላል። እንግልዝኛ ተናጋሪዎች በበኩላቸው ጧት፣ ከሰዓት እና ምሽት ላይ Good የሚለውን ቃል በመጨመር ሰላምታቸውን ይለዋወጣሉ። ግን ደህንነት ምንድን ነው? አንድ ሰው ደህና ነው የሚባለው መቼ ነው? ለመሆኑ ሙሉ ደህንነት አለ? ከፍል ደህንነትስ? በተለምዶ አንድ ሰው በአካል ካልታመመና አልጋ ላይ ካልተኛ በስተቀር ደህና እንደሆነ ይታሰባል። ይህ እሳቤ ደህነንትን በአካላዊ ብቻ ከማድረግ ጋር የተያያዘ ነው። ነገር ግን ሙሉ ደህንነት ሰፊ ጒዳዮችን ያካትታል። ሙሉውን ዝርዝር ከማየታችን በፊት ደህነት ራሱ ምን እንደሆነ መተርጐም ይኖርብናል።
የደህንነት ትርጒሞች
ዓለም ዐቀፉ የደህንነት ተቋም (The Global Wellness Institute) ደህንነትን እንደሚከተለው ይተረጒማል።

ወደ ሙሉ ደህንነት የሚመራ ንቊ እንቅስቃሴዎችን፣ ምርጫዎችንና የሕይወት ዘይቤን የሚያካትት የፈለጋ ውጤት ነው ።

በዚህ ትርጒም ውስጥ የምናገኘው ዋና ሐሳብ ደህንነት ሰው ቊጭ ብሎ የሚጠብቀው ሳይሆን በብርቱ ፈለጋ (Pursuit), በምርጫና በተግባር የተደገፉ እርምጃዎችን በመውሰድ የሚመጣ ነገር ነው። በዚህ እሳቤ ደህንነት አንድ ነገር ላይ ብቻ የሚያተኲር ሳይሆን ሁለንተናዊ ማንነትን (holistic) የሚያካትት ነገር ነው።
ደህንነት የሕመም አለመኖር ሳይሆን ንቊ የሆነ የደህንነት አስተሳሰብ፣ የሕይወት ዘይቤና ያንን ያማከለ ተግባራዊ ድርጊቶችን የተከተለ የሕይወት ዘመን ትምህርት ነው።
የዓለም ጤና ድርጅት ደህንነት (Health) ሙሉ የሆነ አካላዊ፣ አእምሮአዊ እና ማኅበራዊ ብልጽግና (Wellbeing) ላይ መገኘት እንደሆነ ያስረዳል። ስናጠቃልለው ደህንነት ማለት፥-
 ንቊ (Conscience) የሆነ፣ በራስ ተነሳሺነት የሚተገበር የሕይወት ዘመን ጒዞ ነው
 በአንድ ሰሞን ተሞክሮ የሚተው ሳይሆን የሕይወት ዘይቤ (Life Style) ነው።
 ደህንነት በባህሪው አዎንታዊ የሆነ፣ አንድ ሰው እምቅ ዐቅሙን እንዲጠቀም የሚያስችል ረጅም ዕድሜን ከጤና ጋር የሚያጎናጽፍ ሥራ ነው።
 ደህንነት ሁሉን ዐቀፍና ሁሉን የሕይወት ክፍል የሚያጠቃልል ነገር ነው።

ስለ ትርጒም ይኸን ያህል ካልን አሁን ሙሉ ደህንነት የሚያካትታቸው የሕይወት ክፍሎችን ወደ መዘርዘር እንሄዳለን።
1. አካላዊ ደህንነት 5. ማኅበራዊ ደህንነት
2. ስሜታዊ ደህንነት 6. አካባቢያዊ ደህንነት
3. አእምሮአዊ ደህንነት 7. የኢኮኖሚ ደህንነት
4. መንፈሳዊ ደህንነት 8. የሥራ ቦታ ደህንነት

አዲሱ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) 666 ነውን?
30/01/2026

አዲሱ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) 666 ነውን?

ጥያቄ፡ ፋይዳ ከ 666 ጋር ይያያዛል?

ምንም እንኳን ፋይዳ ዓላማው የግለሰብ መለያ ሥርዐት ቢሆንም፣ መታወቂያውን በፍራቻ የሚመለከቱ ሰዎችም አልታጡም፡፡ የፍራቻቸው ምንጭም ዲጂታል መታወቂያው የአውሬው ቁጥር ሊሆን ይችላል ከሚል ጥርጣሬ የመነጨ ነው፡፡ “ይመጣል የተባለው የአውሬው ምልክት (666) እሱ ነው” ብለው የሚሞግቱ ሰዎች እዚህም እዚያም አሉ፡፡ ግና የአውሬው ቁጥር ማለት ምን ማለት ነው? ፋይዳ የአውሬው ቊጥር ብሎ ለመፈረጅ ቅድሚያ የአውሬው ቊጥር ምን እንደሆነ መረዳት ተገቢ ነው።

አውሬውና ቁጥሩ (666)

ስለ 666 ለኢትዮጵያውን መንገር ለቀባሪ ማርዳት ያህል ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ተብለናል፣ በየቦታው የሚወጡ ሰይጣኖችም ስለ ቊጥሩ ብዙ አስተምረውናል፡፡ 666 እየመጣባችሁ ነው ተጠንቀቁ ተብለናል፣ ከቁጥሩ ጋር ተያይዞ የሚነሡ ምልክቶች በልብሳችን ላይ ድንገት ሲገኝ የእሳት ሲሳይ አድርገናል…. ብዙ ብዙ። የአውሬው ቊጥር ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰው በዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ነው።
አእምሮ ያለው የአውሬውን ቍጥር ይቍጠረው፤ ቍጥሩ የሰው ቍጥር ነውና፥ ቍጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው። ራዕይ. 13፡18
በዚህ ጥቅስ ላይ ሁለት ዋና ዋና ነገሮችን መገንዘብ አስፈላጊ ነው፡፡ አውሬና ቁጥሩ፡፡ ለመሆኑ አውሬው ማን ነው? ቁጥሩስ?

አውሬው ማን ነው?

ይህንን ለመረዳት የዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 13 ሙሉውን መረዳት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ በዚህ በተጠቀሰው ምዕራፍ ዮሐንስ አንድ ልዩ አውሬ ከባህር ሲወጣ ይመለከታል፡፡ ያየው አውሬ እንዲህ ብሎ ይገልጸዋል፡፡
አንድም አውሬ ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፥ በቀንዶቹም ላይ አሥር ዘውዶች በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ነበረ። ራዕ. 13፡1
ከአውሬው ጋር የተያያዙ ሌሎች ጉዳዮች፦
• አሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች (የቀንድና የራስ ብዛት አለመመጣጠን አለ)
• ለሞት ሊያበቃ የሚችል ቊስል፣ ግን ወዲያው በመፈወሱ ምክንያት ዓለም ሁሉ መደነቊን
• ከመደነቃቸው የተነሣ የሚሰግዱለት
• እግዚአብሔርን መሳደቡን
• ከቅዱሳን ጋር በቀጥታ የሚዋጋ፣ ሥልጣንም የተሰጠው።
• ቀድሞ የተገለጠውን አውሬ የሚያግዝ ሌላኛው አውሬ መገለጡ፣
• ታላላቅ ምልክቶችን ያደርጋል
• የአውሬው ስም ወይም ቊጥር ለሁሉም ሰዎች የሚሰጥ መሆኑ
• ቊጥሩ ወይም ምልክቱ በቀኝ እጅ ወይም በግንባር ላይ የሚለጠፍ ነው።

ጥያቄዎች
1. ለመሆኑ ዛሬ እንደዚህ ዓይነት ክስተቶች በዓለም አሉ?
2. ለመሆኑ ይኸ ቊጥር እንደሚባለው 666 ነው ወይስ ሌላ?
3. 666 በርግጥ ቊጥር ነው ወይስ ለውክልና የገባ ሌላ ሐሳብ?
4. እንደዚህ ዓይነት የዓለም ሥርዐት ከመታወቂያ ጋር እንዴት ሊገናኝ ይችላል?
የአውሬው ቊጥር የተባለው 666 ነው፣ ይኸ ቊጥር በሥነ መለኮት ተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ውዝግብ ያስከተለ ቊጥር ነው። ይኸ ከራዕይ መጽሐፍ ባህሪይ የሚመጣ ነው። የራዕይ መጽሐፍ በብዛት ምልክቶችን ስለሚጠቀም፣ ምልክቶች ደግሞ የሚወክሉት ሌላ ሐሳብ ስላላቸው ነው። ለምሳሌ ከላይ እንዳየነው አውሬ መንግሥትን ወይም መንግሥትን የሚመራ ክፉ ሰውን ይወክላል።
ስለ 666 ምሁራን ምን ይላሉ፦
• ቀደምት ቅጂዎች 666 በሚለው ፈንታ 616ን ተጠቅመዋል።
• 666 በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖችን ካሰቃየው የሮም ንጉሥ ቄሳር ኒሮ ጋር ያያይዙታል፣ ቄሳር ኒሮ ስሙ ተደምሮ 666ን ያስገኛል።
• 666 የሰው ቊርጥ፣ ፍጹም ያልሆነ ነገር ለማመልከት፣ በተቃራኒው 7 (777) ፍጹም የሆነ ነገር፣ አዲስ የተፈጠረው በ6ኛው ቀን ነው፣ እግዚአብሔር ከሥራው ያረፈው በ7ኛው ቀን ነው።
• የመላእክት ቊጥር (Luck Number)

666 አሁን በኢትዮጵያ እየተተገበረ ካለው የመታወቂያ ሥርዐት ጋር የሚያገናኝ አንዳችም ነገር ስለሌለ አላስፈላጊ ፍርሃቶችን ማስወገድ ያስፈልጋል።

የአርባ ምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች በተዘረዘረው የትምህርት ዓይነት መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡
14/10/2024

የአርባ ምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች በተዘረዘረው የትምህርት ዓይነት መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

Posted inVacancy ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ Posted by admin October 14, 2024No Comments የአርባ ምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች በተዘረዘረው የትምህርት ዓይነት መምህራንን አወዳድሮ መቅጠር .....

አዲሱ የፌስቡክ ደህንነት ማስጠበቂያ ስልት````````````````````````````````````````````````ሰሞኑን ፌስቡክ End-to-end encryption የተሰኘ አዲስ የደህንነ...
29/09/2024

አዲሱ የፌስቡክ ደህንነት ማስጠበቂያ ስልት
````````````````````````````````````````````````
ሰሞኑን ፌስቡክ End-to-end encryption የተሰኘ አዲስ የደህንነት (Security) ማስጠበቂያ ዘዴን እያስተዋወቀ ነው። የዚህ ደህነነት ማስጠበቂያ ዘዴ ማንኛውም ሰው በ Messenger (ቻት) በኩልል ያስተላለፍናቸው ማናቸውንም መልእክቶች ከኛ ውጪ ማንም ማየት እንዳይችል የሚያደርግ ነው። የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤቶች (Meta) እንኳን ሳይቀር ከሰዎች ጋር የተቀያየርናቸውን መልእክቶች ማየት እንዳይችል የሚያደርግ ነው።
መረጃው ወደ ኔትዎርክ ሥርዓት ከመግባቱ በፊት በመልእክት ፈጣሪው ኮምፕዩተር ወይም ስልክ ላይ እንክሪፕት (አመሳጥሮ) ይደረጋል። መልእክቱ ወደ ተቀባዩ ሲደርስ የታተመው (የተቆለፈው ነገር ይፈታል) ወይም decrypt ይደረጋል።

ድንገት የምንጠቀመው ዕቃው (ስልክ ወይም ኮምፕዩተር) ከኛ እጅ ቢወጣ/ቢጠፋ ያገኘ ሰው የተቀያየርናቸውን መልእክቶች ማየት እንዳይችል ያደርገዋል። መልእክቱ ስላክ እኛ ብቻ በምናውቀው ምስጢራዊ ኮዶች ስለሚቆለፍ።

ከዚህ በፊት የነበረው ሁኔታ በቻት ወይም መልእክት መለዋወጫ በኲል የተቀያየርናቸው መልእክቶች ያልተቆለፉ በመሆናቸው ስልካችንን ወይም ኮምፕዩተራችንን ያገኘ ማንኛውም ሰው ማንበብ ይችላል (ምናልባት ሁልጊዜ ማኅበራዊ ሚዲያዎቻቸውን Log out ከሚያደርጉ ጥቂት ሰዎች በስተቀር)። ሌላው የፌስቡክ ድርጅት የኛን መልእክት በቀላሉ ማንበብ ይችላል። መልእክቱ በኔትዎርክ ሥርዓት ሲሄድ ድንገት መሃል-ጠላፊዎች እጅ ቢገባ እንኳን ማንበብ አይችልም። አሁን የተፈጠረው ዘዴ ግን ይኸንን ሁሉ ያስቀራል።

ውስንነቶች
• በውስጥ መስመር የተቀያየርናቸው የቪዲዮ ወይም የድምጽ መልእክቶች ለፌስቡክ ድርጅት ርፖርት ማድረግ አንችልም
• ከኛ ጋር ሲነጋገር የነበረ ሰው ድንገት መልእክቶቹን ለሌላ ሦስተኛ ሰው ቢያጋራ ሦስተኛው ሰው ማንበብ ይችላል።

እራሳችሁን ጠብቊ!!

አንድ ሰው በተከታታይነት የቲክቶክ ቪዲዮችን የሚያይ ከሆነ የትኲረት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ እንደሚሄድ ጥናቶች ያሳያሉ። በአሁን ጊዜ የሰው ልጅ የትኲረት መጠኑ ከ 8 ሴኮንዶች በታ...
23/09/2024

አንድ ሰው በተከታታይነት የቲክቶክ ቪዲዮችን የሚያይ ከሆነ የትኲረት መጠኑ በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ እንደሚሄድ ጥናቶች ያሳያሉ። በአሁን ጊዜ የሰው ልጅ የትኲረት መጠኑ ከ 8 ሴኮንዶች በታች መውረዱ በዘርፉ የተደረጒ ጥናቶች አመልክተዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የቲክቶክ ቪዲዮች በብዛት የሚያስቊ በመሆናቸው በአእምሮአችን ውስጥ ዶፓሚን የተሰኘ የደስታ ሆርሞን በከፍተኛ ደረጃ እንዲመረት ያደረጋል። የዶፓሚን በተደጋጋሚ ከፍ ብሎ መቆየት ሱስ ከማስያዙም በላይ ሌሎች ዶፓሚን የማያመነጩ (የማያስቊ) ጒዳዮች ላይ ያለን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል።

12/08/2024

``````````````````ፖለቲካችን ሥራ ነው!````````````````
ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ

ምቀኝነትና ኢትዮጵያውያን``````````````````````````ብዙውን ጊዜ ከኢትዮጵያውያን ጋር ተያይዘው የሚነገሩ የምቀኝነት ተረኮች አሉ። ከነዚህ ውስጥ አንዱ እንደሚከተለው ነው፦'እግዚአ...
07/08/2024

ምቀኝነትና ኢትዮጵያውያን
``````````````````````````
ብዙውን ጊዜ ከኢትዮጵያውያን ጋር ተያይዘው የሚነገሩ የምቀኝነት ተረኮች አሉ።
ከነዚህ ውስጥ አንዱ እንደሚከተለው ነው፦

'እግዚአብሔር ለሰዎች የሚፈልጒትን እንዲጠይቊ ዕድል ሰጣቸው አሉ፣ የሚሰጣቸው ነገር ለጓደኛቸው እጥፍ ተደርጎ ይሰጣቸዋል ተባል። የሁሉም አገር ዜጋ የሚጠቅመውን መሻቱን ጠየቅ፣ ቤት፣ መኪና፣ ቆንጆ ሚስት/ባል፣ ዕውቀት. . . ወዘት። እንደተባለውም ለጓደኛቸው የነሱ እጥፍ ተሰጣቸው፣ ኢትዮጵያዊ መጣና ፈጠሪን ምን ቢጠይቅ ጥሩ ነው፣ "የኔን አንድ ዓይን አጥፋ'። የሱ አንድ ዓይኑ ከጠፋ የጓደኛው ሁለት ዓይኖች ይጠፋሉ የሚለውን ስሌት አስልቶ መሆኑ ነው እንግዲህ'። ምቀኛ ሰው ከራሱ ስኬት ይልቅ የጓደኛው ውድቀት ያስደስተዋል ይባላል። እንደዚህ የመሰሉ ብዙ ተረቶች አሉን።

ምንም እንኳን ይኸ ነገር እንዲሁ የሚነገር ተረት ቢሆንም፣ ይኸንን ተረት በሳይንሳዊ መንገድ የሚያረጋግጥ አንድ ጽሑፍ አንብቤ በጣም ተገረምኹ። ለካስ የሚነገርብን ተረት ብቻ ሳይሆን በገቢር የምንኖረው ሕይወት ኖሯል።

ጉዳዩ እንደዚህ ነው፦
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ተመራቂ ተማሪዎች ላይ ጥናት ተደረገ። የጥናቱ ዓላማ "የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በብዛት የሚፈጽሙት የሥነ-ምግባር ችግሮች ምንድን ናቸው?" (What do you think are the most common problems observed among student researchers?) የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ነው።

እኔ ብዙ ነገር ገምቼ ነበር፣
ግምቶቼም፦
፥- የሰውን ሀሳብ ዕውቅና ሳይሰጡ መገልበጥ (plagarism)፣ የሌላ ሰው ሪሰርች የራስ አድርጎ ማቅረብ፣ ዳታ ሳይሰበስቡ እንደሰበሰቡ አድርጎ ማቅረብ. . . ወዘተ ግምቶቼ ነበር።
በጥናቱ መሠረት ግምቶቼም የተወሰነ ዋጋ አላቸው።
ዋናው ግኝት ግን እሱ አልነበረም።

ትልቊን ድርሻ የሚይዘው ችግር እንደሚከተለው ይነበባል፦
'Hide materials that can be useful to others'። ለሌሎች ሊጠቅሙ የሚችሉ ነግሮችን መደበቅ። 59.8% የዚህ ችግር መጠን ነው። በጥናት የተዘረዘሩ ሌሎች ችግሮች በሙሉ ከዚህ በታች ናቸው። አያሳፍርም?

ድሮ ተማሪ እያለው ተፈላጊ መጽሐፍትን ከላይብራሪ የሚደብቊ ተማሪዎች ትዝ አሉኝ።
ታዲያ ኢትዮጵያውያን ምቀኞች ናቸው ቢባል እውነትነ የለውም ትላላችሁ?

ምንጭ፡ Belay Tefera and Abdinasir Ahmed: Research Methods (Mega printing press) Addis Ababa. p.43

ግርንቢጥ ዐለም!ወንድን ከሴት ታደባድባለች። ሰው ወንድ ነኝ ስላለ ወንድ አይሆንም፣ ሴት ነኝ ስላለም ሴት አይሆንም። የተፈጠሩበትን ማንነት መቀበል ነው ሐቊ!
02/08/2024

ግርንቢጥ ዐለም!
ወንድን ከሴት ታደባድባለች።
ሰው ወንድ ነኝ ስላለ ወንድ አይሆንም፣ ሴት ነኝ ስላለም ሴት አይሆንም። የተፈጠሩበትን ማንነት መቀበል ነው ሐቊ!

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ የሚደግፉ ቡድኖች የደመቁበት የፓሪስ ኦሎምፒክሊዎናርዶ ዳቭንቺ በ15ኛ መቶ ክፍለ ዘመን 'የመጨረሻ እራት' ብሎ የሠራት ሥዕል ለዘመናት የክርስቲናን አስተምህሮን ስትወክል...
28/07/2024

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ የሚደግፉ ቡድኖች የደመቁበት የፓሪስ ኦሎምፒክ

ሊዎናርዶ ዳቭንቺ በ15ኛ መቶ ክፍለ ዘመን 'የመጨረሻ እራት' ብሎ የሠራት ሥዕል ለዘመናት የክርስቲናን አስተምህሮን ስትወክል ቆይታለች። ኢየሱስ ክርስቶ ከደቀ-መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻ እራት እንዴት እንዳሳለፈ የሚያሳይ ሥዕል ነው።

ሰሞኑን የተጀመረው የፓሪስ ኦሎምፒክ ተሳለቀበት። ኢየሱስ ክርስቶንስን በሴት ወክለው ደቀመዛሙርትን በግራ አጋቢ አለባብስ እንዲሁም ያልተለመደ የሰውነት ምልክቶች ለመቀየር ሞክሩት። ጽም ያላት ሴት፣ ግማሽ ራቊት የሆኑ ሴቶችና ሕጻን ልጅ ያጠቃለለ ስብስብ የጌታን ደቀመዛሙርት እንዲወክሉ ተደርገዋል።

ይኸ ትይእንት በኦሎምፒክ ኮሜቴው ላይ ብዙ ወቀሳ እንዲሰነዘር አድርጓል። ነገር ግን ጒዳይ ሆነ ተብሎ የታቀደና የክርስቲያን እሴቶችን ለማራከስ የታሰበ ይመስላል። በተለይ ተገልብጦሽ የጾታ እሳቤ ያላቸውን ሰዎች ለማካተት በሚል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚከተሉን ሃይማኖት ዋጋ ለማሳጣት ሙከራ ተደርጓል።

በርግጥ ይኸ ድርጊት አዲስ አይመስለኝም። ዳን ብራውን የተሰኘ ደራስ 'ዳቭንቺ ኮድ' ብሎ በጻፈው የፈጠራ ድርሰት ላይ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጎን ያለው ምስል ሴት ናት በማለት ኢየሱስ ክርስቶስ ትዳር እንደመሰረተና ሴት ልጅ እንደወለደ ያልታወቀ ታሪክ በአዲስ መልክ ለመጻፍ ሙከራ አድርጓል።

ዛሬም ተመሳሳይ ነገር ታዝበናል።

የሚዲያ አካላታ ታዲያ እየጎረፈ ያለውን ተቃውሞ 'የቀኝ ዘመም' የፖለቲካ አይዲዮሎጂ ያላቸው ሰዎች የሚሰነዝሩት ትችት እንደሆነ ይገልጻሉ።

ማስታወሻ፡ የቀኝ ፖለቲካ ባህላዊ እሴትን በማስጠበቅ የሚያምን ነው።

Address

Arbaminch Gamo Zone, Konso Zone
Arba Mintch

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Birhan Training Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Birhan Training Institute:

Share