02/01/2024
ቴሌግራም ላይ ሀክ እንዳትደረጉ ማድረግ ያለባችሁ ጥንቃቄዎች
✅ 1. Device Passcode ተጠቀሙ። ማንኛውም ሰው ስልካችሁን አንስቶ የተላላካችሁትን ሚሴጅ እንዳያይ ወይም ቴሌግራም የሚልከውን የሚስጠር ቁጥር እንዳያገኝ እናንተ ብቻ የምታውቁት የሚስጢር ቁጥር ይኑራችሁ።
ይህን ለማስተካካል
Settings - privacy and security - passcode
✅ 2. 2-step verification ተጠቀሙ።
2-step verification የማይጠቀም ሰዉ ሀክ የመደረግ እድሉ ከፍተኛ ነው።
Settings - privacy and security - 2-step verification ላይ በመግባት on አድርጉት።
ምናልባት ሀክ ብትደረጉ አካውንታችሁን መልሳችሁ ለማግኘት recovery email መሙላት አለባችሁ።
✅ 3. ከ2 በላይ device ላይ አትጠቀሙ። Login ያደረገችሁበት device በጨመረ ቁጥር ሀክ የመደረግ እድላችሁ ይጨምራል።
ስለዚህ privacy and security -device ላይ ግቡና የተዘረዘሩት ዲቫይሶችን terminate secc ቀንሷቸው።
✅ 4. በDesktop ስትጠቀሙ official የDesktop ሶፍትዌሩን ተጠቀሙ እንጂ web ላይ አትጠቀሙ።
✅ 5. ከofficial የtelegram አፕሊኬሽኖች ውጪ ሰዉ በላከላችሁ Link ላይ login ለማድረግ አትሞክሩ።
✅ 6. የቴሌግራም ኮንታክታችሁን ለሰዎች ስትሰጡ username ወይም የአካውንታችሁን qr-code Share አድርጉ እንጂ ስልክ ቁጥር አትስጡ።
✅ 7. ለማታቁትና ለማታምኑት ሰዉ ፎቷችሁን፣ የድምፅ መልዕክት እንዲሁም ሌሎች ሚስጢራዊ የሆኑ መጃዎችን በፍፁም መላክ የለባችሁም። የግድ መላክ ካለባችሁም በsecret message ወይም self destruct ( የተላከለት ሰው ካያቸው በኋላ የሚጠፉ) ሚሴጆችን ላኩ።
✅ 8. የስልካችሁ status bar ላይ notification እንዳይታይ off አድርጉት።
✅ 9. በመጨረሻም የPrivacy settings ላይ በዚህ መልኩ አስተካክሉ።
Phone number - Nobody
Last seen & online - My contacts
Profile photos - My contacts
Forwarded message - Nobody
Calls - My contacts
Group & channels - My contacts