Svenska Tech Group

Svenska Tech Group Software Design Development and Implementation
Svenska Tech Group was founded in Stockholm. It is Svenska Tech Group was founded in Stockholm.

It is an IT company has a regional office in Addis Ababa. The company provide total-solutions in IT related areas. With leading expertise in product development,we contribute with innovative solutions and services that create growth. Svenska Tech Group Stimulates and Implements New Solution and Innovation in the Privet and Public Sector.With Extensive Experience in Systems Development and Integrat

ion is a Company of the forefront in the Development of customized solution. We work with many different types of businesses. Our customers are represented in a wide range of industries. They are both small and large, public and private. We at Svenska Tech Group focus on our customers and strive to deliver highest level of service. For us it is important to offer that little bit extra to make our products and services more attractive. Our employees in the systems development team consists of experienced project managers , architects and system developers with broad competence in modern development tools, databases and integration that today’s system development requires.

24/07/2022

ፌስቡክዎ መጠለፉን ለማወቅና ከጠለፋ እራስዎን ያውጡ!
1. Setting and Privacy ይግቡ
2. Setting ይንኩ
3. Security
4. Security and login
5. Where you are logged in ከዚህ ውስጥ በምን ሞባይል ወይም ኮምፒውተር፣ የት ቦታና ሀገር፣ በምን ብራውዘር፣ ወይም አፕልኬሽን፣ መቼ ቀን ከዚህ በፊት እንደከፈታችሁት ያሳያችኋል። ነገር ግን ደግሞ Active now በሚል በአረንጓዴ የተጻፈው አሁን የከፈታችሁበትን ይነግራችኋል። ከዚህ በታች የተዘረዘረውን Session ስትመለከቱ የናንተ ካልሆነና የሚያጠራጥር ከሆነ ከታች ላይ Logout All Sessions የሚለውን በመጫን Logout የሚለውን በመጫን እራስዎን ከጠላፋ ማውጣት ይኖርብዎታል።
የተጠለፈ መሆኑ ከተጠራጥሩ በፍጥነት Password መቀየር ይኖርብዎታል።
ከአምስተኛው ተራ ቁጥር በመቀጠል ካለው Step Where you are logged in በታች Login ከሚለው በታች Change password የሚለውን በመጫን current password እና New password በማስገባት Save Changes የሚለውን ይጫኑ።

✅ በተጨማሪም Two factor Authentication On ቢያደርጉት ጥሩ ነው። ይህ On መሆኑ ምንም እንኳን የፊስቡክ አካውንትዎን Password ሰው ቢያውቅብዎ በስልካችሁ የሚላከውን Security code እስካላወቁ ድረስ መክፈትና መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ On በማድረግ እንድትጠቀሙ እመክራለሁ። በፈለጋችሁ ሰአት Off ማድረግ የምትችሁ ይሆናል!

እራስዎን ከጠላፊዎች ይከላከሉ!

እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology

21/07/2022

ቫይረስ /Virus/ የኮምፒውተር ቫይረስ እራሱን ሌሎች ፋይሎች ላይ በማጣበቅ የሚያባዛ እና ተላላፊ ማልዌር ነው፡፡ ቫይረስ እራሱን ከተለያዩ ሶፍትዌሮች ጋር ባማጠባቅ እንደ ወርድ ዶኩሜንት ሊሆን ይችላል እኛ ፐሮገራሞቹን ስንከፍት እሱም አብሮ በመቀስቀስ የሚራባ ነው፡፡ በተጨማሪም ኔትዎርክ እና አንተርኔትንም ጨምሮ ማለት ነው፤ በፈላሽ ዲስክ፤ሜሞሪ ካርደ እና ሲዲዎችን በመጠቀም ይተላለፋል፡፡
ቫይረስ እንደሌሎቹ ማዌሮችን ኮምውተራችን በመበከል ኮምውተራችን ፍጥነቱን ይቀንሳል፤ ዳታ ያጠፋል ዋይንም ይሰርቃል፡፡ ከበድ ያሉ ቫይረሶች የክፒውተራችንን ሃረድዋር ጭምር ሊጎዱ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ሃረድ ዲስክን በመጉዳት ኦፐሬቲንግ ሲይሰተማችን ክራሽ እነዲዲርግ ያደርጋሉ፡፡
⭕️ ወርም/Worm/
ወርሞች በአብዛኛው ተንሰራፍተው የሚገኙ ማዌሮች ናቸው፡፡ በኔትዎርክ አማካኝነት እራሳቸውን ችለው የኦፐሬቲንግ ሲይስተማችንን ድክመት በመጠቀም የሚባዙ ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ ኔትዎርክን በማጨናነቅ የእንተርኔት ፍጥነት ይቀንሳሉ ፤ የኮምፒውተራችን ፕሮሰሰር በአላስፋለጊ ትዛዞች በማጨናነቅ ኮምውተራችን ቀርፋፋ ያደርጋሉ፡፡
ከቫይረስ ጋር የሚለያቸው ወርሞች የሰዎችን ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው እራሳቸውን ማባዛት ከመቻላቸው በላይ በኢሜሎች አታች ተደርገው ወደ ኮምፒውተራችን ሊገብ ይችላሉ፡፡ ቫይረስ ግን ለመባዛት የግድ እኛ የተበከለውን ፍላሽ ዲስክ መክፈት ይንም የተበከለ ወርድ ፋይል መክፈት ይኖርብናል፡፡
በማልዌር የተጠቁ ኮምፒውተሮች የሚያሳያቸው ምልክቶች
ማልዌሮች የሚያደርሱት ጉዳት እና ምልክት እንደ ማልዌሩ አይነት፤እንደ ኮምፒውተሩ አይነት እና እነደ ሚጠቀመው የ ኦፐሬቲንግ ሲሰይሰም ቢለያይም አብዛኛው ጊዜ ግን አንድ ኮምፒውተር በማልዌር ሲጠቃ ከስር የተገለጹትን ምልክቶች ያሳያል
⭕️ የኮምፒውተር ፍጥነት መቀነስ
የኢንተረኔት ፍጥነት መቀነስ ( የኢንተርኔ ፍጥነት የቀነሰው ከ ኢንተርኔ አገልግሎት ከሰጠን አካል አለመሆኑን እረግጠኛ መሆን የኖርብናል)
⭕️ የዌብ ብራውሰራችን ማዝገም
ከእኛ እውቅና ውጪ በተለያየ ስም የተፈጠሩ ፈይሎች ወይን የተደበቁ ፋይሎች
⭕️ የማናውቀው አይኮን ዴስክቶፓችን ላይ ሲገኝ
⭕️ ፕሮገራሞች ካለእኛ ትዛዝ ሲከፈቱ ወይንም ሲዘጉ
⭕️ እኛ ያላክነው ኢሜይል ተልኮ ከሆነ
⭕️ ፌስቡክ ላይ እኛ ፖስት ያላደረግነው እና ካልታወቀ ምንጭ በእኛ ስም ፖስት የሚደረግ ከሆነ
⭕️ የዴስክቶፕ ከለር መዛባት
⭕️ አንዳድ ፕሮገራሞች አልከፍት ማለት በተለይ ታስክ ማናጀር አልከፈት ካለ ኮምፒውተራችን በማልዌር ተጠቅቶ ሊሆን ሰለሚችል ከተች የተገለጹትን መፍትሄዎች መተግበር ያስፈልጋል
🛑 እርምጃዎች እና ጥንቃቄዎች
ማልዌሮች ኮምፒውተራችንን በመበከል አደጋ ከማድረሳቸው በፊት አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የሚፈጠረውን ችግር በከፍተኛ መልኩ መቀነስ ይቻላል፡፡ አንዴ ገብተው ጉዳት ካደረሱ በኋላ ግን ወደኋላ መመለስ በጣም አዳጋች ነው የሚሆነው ስለዚህ ቅድመ ጥንቃቅ ማድረገ የተሸለ አማራጭ ነው፡፡
🛑 ምንጊዜም አንቲቫይረስ መጠቀም
🛑 የምንጠቀምባቸው አንቲቫይረሶች ተአማኝነት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል
🛑 በተቻለን መጠን አንቲቪረሳቻንን አፕቱዴት ማድረግ
🛑 ቀላል የሆኑ በነጻ ዶወንሎደ አድርገን የምንጠቀምባቸው አንቲቫይረሶቸ
1️⃣ McCaffe
2️⃣ Avira
3️⃣ Microsoft Security Essential
4️⃣ Avast
🛑ዳውንሎድ የምናደርገው ሶፍትዌር በተለይ ቶረንት ፋይሎችን ከመክፈታችን በፊት ስካን ማድረግ ከማናውቀው አካል በኢሜላችን የሚላኩ የተላያዩ ዳውንሎድ ሊንኮችን ከመክፈት መቆጠብ ፤በተወሰነ ጊዜ ልዩነት ኮምፒውተራችንን ፉል ስካን ማድረግ፡፡

16/07/2022

ቴሌግራምዎን hack እንዳይደረግብዎ ይፈልጋሉ?
መፍትሄውን እነሆ

❖ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatsapp, viber, imo, tango.....etc
📌ቴሌግራም እንደ whatsapp, viber,imo...ሁሉ በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል

⭕ ይህ ዘዴ ሌሎች hack ማድረጊያ hacking Tricks ሳያስፈልገን አፕሊኬሽኖች በመጠቀም
ማለትም የራሳችን ቴሌግራም አፕሊኬሽን ላይ ወይም pc ላይ ቴሌግራም install በማድረግ የምንፈልገውን ቁጥር በማስገባት ኮዱን ካስላክን ብኋላ ኮዱን የምናገኝበት አጋጣሚ ካለ....

⭕በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉ
❶Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።

■Note: እራስዎ በሌላ አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል ስለዚህ በደንብ ይመልከቱ።

📌ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት።
☛ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ የእናንተን አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።

⓶ Security ደግሞ ለማጠናከር
seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password ***..ግን የ gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።

❖ ይህ ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።

❖ የሚጠቅመው እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።
====================
❖ ሌላ ሰው በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።
====================
❖ ማንም ሰው ለመግባት በኢሜል የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ መግባት አይችልም።

⚠️የፃፋችሁትን password እንዳትረሱት።
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology

01/07/2022

📌 SSD and HDD ምንድንነው ልዩነታቸው?
✅ SSD ማለት Solid State Drive ማለት ሲሆነ HDD ማለት Hard Disk Drive ማለት ነው።

✅ HDD ኤችዲዲ ወይም ሃርድ ዲስክ ከመግነጢሳዊ ቴፕ የተሰራ እና በውስጡም ሜካኒካል ክፍሎችን የያዘ የመረጃ ማከማቻ መሳሪያ ነው።
ኤችዲዲ መረጃን ለማንበብ(Read) እና ለመፃፍ(Write) በሚሽከረከር ዲስክ ወይም በብረት ፕላስተር ማግኔቲክ የተሸፈነ ነው።

✅ መረጃውን ለመድረስ በክንድ ላይ የተነበበ/የፃፈ ጭንቅላት ከተሽከረከረው ሳህን በላይ ይንሳፈፋል።
ሳህኑን ለማሽከርከር እና ክንዱን ለማንቀሳቀስ የሚያገለግል ሞተርን ያካትታል።

✅ ለHDD ላፕቶፖች 2.5 ኢንች መጠን ያላቸው ሲሆን ለዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች 3.5 ኢንች ነው።
HDD በብዛት SATA («stands for "Serial Advanced Technology Attachment," or "Serial ATA") ኢንተርፊስን ይጠቀማሉ።

✅ SDD ከHDS ጋር አንድ አይነት ተግባራትን ያከናውናል፣ ነገር ግን SDD መረጃን ለማከማቸት interconnected flash-memory chips (እርስ በርስ የተያያዙ ፍላሽ-ሜሞሪ ቺፖችን) ይጠቀማሉ።

✅ ስሙ እንደሚያመለክተው solid-state drive ፣ ይህ ማለት በSSD ውስጥ ምንም ተንቀሳቃሽ ክፍሎች የሉም ወይም እንደ HDD የሚሽከረከር ዲስክ የለም።

✅ SSD ከSATA Ports እና 2.5 ኢንች ፎርማት በHDS ምትክ በቀላሉ ከኮምፒውተር ጋር ማገናኘት ይቻላል።

✅ እንዲሁም በሚኒ-PCI (Peripheral Component Interconnect) ኤክስፕረስ ማስገቢያዎች ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሚኒ-SATA (mSATA) ያላቸው ትናንሽ SSDs አሉ።

✅ አብዛኞቹ ዘመናዊ ላፕቶፖች SSD በ PCI Express Expansion slot ከገባ ወይም በቀጥታ በማዘርቦርድ ላይ በማገናኘት መጠቀም ይቻላል።

✅ HDD ከSSD ርካሽ ነው
✅ HDD ከSSD ዝቅተኛ የሆነ መረጃን Read/Write የማድረግ አቅም አለው
✅ HDD ከSSD በይበልጥ ሀይል(ባትሪ) ይጠቀማል
✅ HDD ከSSD ዲስኩ ስለሚሽከረከር ድምጽ የማሰማት ሁኔታ ይታያል
✅ HDD ከSSD በጥንካሬ/ በቆይታ የተሻለ ነው
✅ HDD ከSSD በክብደትና በአካላዊ ግዝፈት ይበልጣል

⚠️ ኮምፒውተራችን SSD ወይም HDD Disk መሆኑን ለማርጋግጠ የWindows key + R ቁልፍ ስትጫኑ Run box ይመጣል ከዛም, dfrgui በመጻፍ Enter ይጫኑ.
Drive Media Type የሚል ቦክስ ይመጣል ከዛም የኮምፒውተር ዲስክ HDD ከሆነ Hard Disk Drive ወይም SSD ከሆነ Solid State Drive የሚል ይመጣል።
እንዲሁም ከዚህ በፊት የለቀቅኳቸውን ቪዲዮዎችን ብትከታተሉ ምርጥ እውቀትን ልታገኙ ትችላላችሁ
አሁንም የቴሌግራምና የYouTube ቻናሌን Subscribe በማድረግ ድጋፋችሁን አሳዩኝ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅

የ YouTube ቻናል ሊንክ 👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCZBIP6PqUdmmagdTjbyp_AQ

ቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇👇👇 https://t.me/MuhammedComputerTechnology

24/06/2022
13/05/2022

ፍላሽ ዲስክ ከኮምፒውተራችን ጋር ተጠቅመን ከጨረስን በኋላ eject ማድረጋችን ምንድን ነው ጥቅሙ? አስበውት ያውቃሉ እስኪ ሀሳባችሁን አጋሩኝ?
✅ ፍላሽ፣ External Hard Disk፣ እንዲሁም CD/DVD ከኮምፒውተራችን ሰክተን ተጠቅመን ስንጨርስ በቀጥታ የሚታየን ነገር ቢኖር በቶሎ ፍላሹን፣ External Hard Disk መልቀል ወይም CD/DVD ከሆነ ደግሞ ሲዲው እንዲወጣ መጫን ነው።
✅ ነገር ግን አብዛኛዎቻችን ፍላሼ፣ External ሀርዲ ዲስኬ፣ የምጠቀምበት ሲዲ አልሰራልኝ አለ? ኮራፕት አደረገብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ Write Protected ሆነብኝ፣ ፍላሽ ዲስኬ ከነጭራሹ ከኮምፒውተሬ ጋ ብሰካው እይሰራም፣ ፍላሽ ዲስኬን ከኮምፒውተሩ ጋ ስሰካው ድምጽ ያሰማኛ ግን My computer ጋ ስሄድ የለም የሚል በብዛት የሚነሳ ጥያቄ ነው። ለዚህ ሁሉ ችግር ተጠያቂዎቹ እኛው ነን።
✅ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ።
በመጀመሪያ ደረጃ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ስብሰካና ስናስገባ ኮምፕዩተሩ Read/ Write process ያደርጋል። ይህ ማለት ስራ እየሰራ ነው ማለት ነው።
✅ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ወደ ኮምፒውተር ሰክተንና አስገብተን ፋይል ለምሳሌ ከኮምፒውተር ወደ ፍላሽ፣ ከፍላሽ ወደ ኮምፒውተር, ከExternal Hard Disk ወደ ኮምፒውተር .......... መረጃ ስናገላብጥ አሁን ሁሉም ስራ ላይ ናቸው ማለት ነው። ስለሆነም መረጃ እያላላክን ሳለ ከተሰካበት ብንነቅለው። ከገባበት ብባወጣው። ስራውን ሳይጨርስ አቋረጥነው ማለት ነው። በዚህ አጋጣሚ የመበላሸት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው በተለይ ደግሞ ለExternal Hard Diskና CD/DVD እንዲሁም ፍላሽ ዲስኮች።
✅ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተር ጋ ተሰክተው እያለ ዝም ብለን የምነቅለው ከሆነ ይህም የመበላሽት አጋጣሚው በጣም ሰፊ ነው።
✅ ስለሆነም ማንኛውንም ከኮምፒውተር ጋ የሚሰኩ Storage Device በጥንቃቄ በሚከተለው ፕሮሰስ ፍላሽ ዲስክ፣ External ሀርድ ዲስክ፣ ሲዲ/ዲቪዲ ከኮምፒውተራችን ሳንነቅለው በፊት Eject ማድረግ አለባችሁ።
✅ Start -> All Program -> Computer or This PC -> ወደ ፍላሻችን ወይም External Hard Disk..... በመሄድ Right click በማድረግ Eject የሚለውን ይጫኑ። ከዛም ቢያንስ ለ5 ሰከንድ ይጠብቁ በቅድሚያ ግን ከፍላሽ ዲሳክችን....... የተከፈተ ማንኛውንም ፕሮግራም መዝጋት አስፈላጊ ነው።
ምስሉን ይመልከቱ!⁉️
✅ Eject ጥቅም ከኮምፒውተር ጋ የተሰካን ማንኛውንም ነገር ግንኙነቱን ያቋርጣል ማለት ነው። እንደገና ግንኙነቱ እንዲቀጥል ከፈለጋችሁ እንደአዲስ በመንቀል መሰካት ያስፈልጋል።
✅ይህ ተግባር የሁልጊዜ ስራችንና ተግባራችን ይሁን።
✅ ከተመቻችሁ ለሌሎች ሰዎች እንዲደርሳቸው #ሼር ይደረግ!
✅ ለፔጁ አዲስ የሆናችሁ ሰዎች ይደረግ።

Address

Addis Ababa
28655/1000

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 17:00

Telephone

+251911173350

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Svenska Tech Group posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share