ራዳር RADAR

ራዳር RADAR Honest Media et

26/01/2026
የሞዛምቢክ ፓስተር እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት ለመጾም ሲሞክር ህይወቱ አለፈአንድ የሞዛምቢክ ፓስተር በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸዉ ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ለ40 ቀና...
16/02/2023

የሞዛምቢክ ፓስተር እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ 40 ቀናት ለመጾም ሲሞክር ህይወቱ አለፈ

አንድ የሞዛምቢክ ፓስተር በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተገለጸዉ ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ለ40 ቀናት የጾመዉን ጾም ክብረወስን ለመጋራት ሲሞክር ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።በሞዛምቢክ ማዕከላዊ ማኒካ ግዛት ውስጥ በሚገኘው የሳንታ ትሪንዳድ ቤተ ክርስቲያን ፓስተር እና መስራች የሆኑት ፍራንሲስኮ ባራጃህ ረቡዕ እለት ህይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል።

በከባድ ሁኔታ የጤና ችግር ዉስጥ ከወደቀ በኃላ ወደ ቤይራ ሆስፒታል ተወስዶ ሲታከም ቢቆይም ህይወቱ አልፏል።ከ25 ቀናት ጾም በኋላ መቆም፣ መታጠብና መራመድ እስከማይችልበት ደረጃ ድረስ ክብደት ከድቶት እንደነበር መገለፁን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

ከቀናት በኋላ፣ በዘመድ አዝማድና በአማኞች ግፊት፣ ወደ ሆስፒታል ቢወሰድም ወደ ጤናው ለመመለስ የተደረገው ሙከራ ግን አልተሳካም።በቤተክርስቲያኑ አማኞች ዘንድ እና በጎረቤቶቹ ያሉ አማኞች በሁኔታዎች ለውጥ አልተገረሙም ፣ምክንያቱም ከቅርብ ቀናት ወዲህ የታየበት የሰውነት አካል ለዉጥ በህይወት ለመትረፍ አስፈሪ እንደነበር ተናግረዋል፡፡


#ራዳር

15/02/2023

"ሰበር ዜና
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በንግግርና ውይይት ተፈታ"
Zehabesha

#ራዳር

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ ተከታዮች እና የተለያዩ ሚዲያ አባላት እስር በእጅጉ እንደሚያሳስብ ገለጸ!የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ ከየካቲት 4 ...
15/02/2023

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች፣ ተከታዮች እና የተለያዩ ሚዲያ አባላት እስር በእጅጉ እንደሚያሳስብ ገለጸ!
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)፣ ከየካቲት 4 ቀን 2015 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ በተለያዩ የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተፈጸሙ እስሮችን በተመለከተ የአዲስ አበባን፣ የፌዴራል እና የኦሮሚያ ክልል ፖሊስና የጸጥታ አካላት፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤትን፣ ምስክሮችን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በማነጋገር እንዲሁም በአዲስ አበባ የተለያዩ ማቆያ ቦታዎችን በመጎብኘት ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል።

የተወሰኑ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች በፍርድ ቤት ወይም በፖሊስ ጣቢያ ዋስትና እየተለቀቁ መሆናቸውን ኮሚሽኑ ያረጋገጠ ቢሆንም አሁንም ብዙ ሰዎች ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በተለያየ ዓይነት ወንጀል ተጠርጥረዋል በሚል ዋስትናም ተከልክለው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር ተያይዞ የዚህ ዓይነቱ እስር የዘፈቀደ እስር ሊሆን ስለሚችል የመንግሥት የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር አካላት በሙሉ በበቂ ምክንያት በወንጀል የተጠረጠረን ሰው በሕጉ መሠረት ሰብአዊ መብቶችን ያከበረ በተለይም በቅድመ ምርመራ ወቅት የዋስትና መብት አጠባበቅ ሥርዓትን ባከበረ መንገድ ምርመራ ከማድረግ ውጪ ተገቢ ያልሆነ እስር እንዲያስወግዱ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አሳስበዋል፡፡
ምንጭ :zehabesha

#ራዳር

የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ ኹለት ሰዎች ተገደሉ======= #=======ረቡዕ የካቲት 8 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በወልቂጤ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባ...
15/02/2023

የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ ኹለት ሰዎች ተገደሉ
======= #=======

ረቡዕ የካቲት 8 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በወልቂጤ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመጣዉ የውሃ ችግር የተነሳ፣ ብሶታቸውን ለማሰማት አደባባይ በወጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ የኹለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነግሯል፡፡

የከተማዋን የንጹህ መጠጥ ዉሃ ችግር ለማሰማት በከተማው የዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ፅ/ቤትና በጉራጌ ዞን አስተዳደር በር ላይ በተጀመረ ሠላማዊ ሰልፍ ላይ፣ በተፈጠረ አለመግባባት ከደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ወደ ሰልፈኞች በተተኮሰ ጥይት የኹለት ወጣቶች ሕይወት ማለፉንና ከፍተኛ የአካል ጉዳት ማጋጠሙን የአካባቢው አዲስ ማለዳ ምንጮች ተናገረዋል፡፡

የአካል ጉዳት ያጋጠማቸው ሰዎች ቁጥር ከ15 በላይ መድረሱና ተጎጂዎቹ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል። ከቆሰሉት ሰዎች መካከል ኹለቱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውም ሥማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ልዩ ኃይሉ የከፈተው ተኩስ ባለመቆሙ የተጎጂዎች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እንደሚችልም ተመላክቷል፡፡

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 2ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 36ኛ መደበኛ ጉባኤ፣ የከተማው የዕለት ተዕለት ችግር የሆነው የውሃ አቅርቦት ለማስተካከል ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡ በከተማው ለወራት ውሃ በመጥፋቱ ሕዝቡ ለከፋ ችግር እየተዳረገ መሆኑንና በዚህም ለማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች እያጋለጠ ስለመሆኑም በጉባኤው ተነስቷል፡፡
ምንጭ
#ራዳር

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተወሰደ======= #=======ማክሰኞ የካቲት 7 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ ቴዎድሮስ አስፋው በዛሬው ዕለ...
14/02/2023

ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ተወሰደ
======= #=======

ማክሰኞ የካቲት 7 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ ቴዎድሮስ አስፋው በዛሬው ዕለት በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች መወሰዱን ወንድሙ ቢኒያም አስፋው ለአዲስ ማለዳ ገልጿል።

ቴዎድሮስ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ቱሉዲምቱ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ አራት ሲቪል በለበሱና ኹለት የፌደራል ፖሊስ መለዮ በለበሱ የጸጥታ አካላት መወሰዱን የገለጸው ቢኒያም፤ ሜክሲኮ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዱንም አስታውቋል።

ጋዜጠኛ እና የፖለቲካ ተንታኝ ቴዎድሮስ አስፋው በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የፖለቲካ ትንታኔዎች በመስጠትና አግባብነት የሌላቸውን ፖለቲካዊ ሂደቶች በመተቸት ይታወቃል።
ምንጭ :
#ራዳር

የማኅበረ ቅዱሳን ጭሮ ማዕከል አገልጋይ የሆነው ዶ/ር እንደሻው ዘርፉ በጸጥታ ኃይሎች መታሠሩ ተገለጸ።ምንጭ:                                     #ራዳር
14/02/2023

የማኅበረ ቅዱሳን ጭሮ ማዕከል አገልጋይ የሆነው ዶ/ር እንደሻው ዘርፉ በጸጥታ ኃይሎች መታሠሩ ተገለጸ።
ምንጭ:


#ራዳር

በአዲስ አበባ በሚካሄደዉ የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ  ላይ 35 ፕሬዝዳንቶችና 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ተገለጸ======= #=======ማክሰኞ የካቲት 7 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከ...
14/02/2023

በአዲስ አበባ በሚካሄደዉ የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔ ላይ 35 ፕሬዝዳንቶችና 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ ተገለጸ
======= #=======

ማክሰኞ የካቲት 7 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚካሄደው 36ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ እና 42ኛው የሕብረቱ የስራ አስፈፃሚዎች ስብሰባ ላይ 35 ፕሬዝዳንቶችና 4 ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንደሚሳተፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፤ በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ላይ የ51 አገራት ልዑካን ቡድኖች እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል፡፡

በመድረኩ ላይ 35 ርዕሰ-ብሔሮች፣ አራት ጠቅላይ ሚኒስትሮች፣ 11 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ 13 ቀዳማዊ እመቤቶችና 10 የዓለም አቀፍ ድርጅት ኃላፊዎች እንደሚታደሙም ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው፤ መድረኩ በአንድ ጊዜ በአንድ ቦታ የሚካሄድ እና አገራት ጥቅማቸውን ለማስከበር የኹለትዮሽና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ሥራዎች የሚከናወንበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

አክለውም ጉባኤው የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ጉዳይ ላይ በስፋት እንደሚመክርም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በጉባኤው ስኬታማ የዲፕሎማሲ ሥራዎችን ለማከናወን የነቃ ተሳትፎ ለማድረግ መዘጋጀቷን የገለጹት አምባሳደር መለስ፤ ኢትዮጵያ የገጠማትን የሰላም ችግር በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ እንዲፈታ ለተደረገው ጥረት ምስጋና ታቀርባለች ብለዋል።

በጉባኤው የፀጥታ ምክር ቤት ማሻሻያ እና የተለያዩ የሕግ ሰነዶች ይጸድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የተገለጸ ሲሆን፤ ቀጣዩን የአፍሪካ ሕብረት ፕሬዝዳንት ኮሞሮስ ከሴኔጋል እንደምትረከብም ተነግሯል።
ምንጭ

#ራዳር

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ራዳር RADAR posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share