19/03/2022
የመግቢያ ውጤቱ እስኪፈተሽ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ እንዲራዘም የአማራ ትምህርት ቢሮ ጠየቀ
በ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስደው ወደዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ውጤት ተፈትሾ መተማመኛ ላይ እስኪደረስ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ተጠየቀ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ ጠይቋል።
የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሸላቸው እያመለከቱ መሁኑን የገለፀው የክልሉ ትምህርት ቢሮ በተጨማሪ በትምህርት አመራሩና በትምህርት ማህበረሰቡ ዘንድም በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ መሆኑን ቢሮው አትቷል። የተማሪዎች ውጤት በአግባቡ ተፈትሾላቸው ተገቢው መተማመን እስኪፈጠር ድረስ የተማሪዎች መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቢሮው በደብዳቤ ትምህርት ሚኒስትርን ጠይቋል፡፡
ለፈጣንና ለሀቀኛ መረጃዎች ቤተሰባችን ይሁኑ!
የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ👇
https://t.me/FasilAmhara
የፌስቡክ ገፃችንን ይከታተሉ👇
https://www.facebook.com/110194134211057/posts/421046496459151/?substory_index=0&app=fbl
ዝርዝር መረጃዎችን በዩቲዩብ ቻናላችን ይከታተሉ👇
https://www.youtube.com/channel/UC5uxO6rNeYuNCcGXgM2gQHA