Safaricom Ethiopia

Safaricom Ethiopia Safaricom telecommunications plc is a company supporting Ethiopian's digital

ተስማሚ የሆነ መጋዘን ለኪራይ የሚያቀርቡ ግለሰቦችን ወይንም ድርጅቶችን እንፈልጋለን፡፡ የተጠቀሱትን ቅድመሁኔታዎችየምታሟሉ ከሆነ አስፈላጊዎቹን ሰነዶች እስከ ሐሙስ ጥር 5/ 2014ዓ.ም ከምሽ...
02/01/2022

ተስማሚ የሆነ መጋዘን ለኪራይ የሚያቀርቡ ግለሰቦችን ወይንም ድርጅቶችን እንፈልጋለን፡፡ የተጠቀሱትን ቅድመሁኔታዎች
የምታሟሉ ከሆነ አስፈላጊዎቹን ሰነዶች እስከ ሐሙስ ጥር 5/ 2014ዓ.ም ከምሽቱ 11፡00 ሠዓት ድረስ በኢሜይል አድራሻ
[email protected] በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡
ማሳሰቢያ፦ የኢሜይል መልዕክቱ ተቀባይነት እንዲኖረው፤ “Warehouse Space for Lease” በሚል ርዕስ መላክ
ይኖርበታል፡፡

የቮዳፎን ቡድን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሻሚል ጁሰብ እና የሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፒተር ንዴግዋ የኢትዮጵያ ብሔራዊባንክ ዋና አስተዳዳሪ ከሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ይናገር ደሴ ጋር እና ከተለያዩ...
22/12/2021

የቮዳፎን ቡድን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሻሚል ጁሰብ እና የሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፒተር ንዴግዋ የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ባንክ ዋና አስተዳዳሪ ከሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ይናገር ደሴ ጋር እና ከተለያዩ ምክትል አስተዳደሮች ጋር ተገናኝዋል፡፡
የቮዳኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ድርጅታችን ኢትዮጵያን አካትቶ በመሥራቱ በአህጉራችን ትልቁ የፋይናንስ እና ቴክኖሎጂ
ተቋም የመሆን ዕድሉ ያለው መሆኑን በማንሳት፤ ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቡድን ላደረጉት አቀባበል የተከበሩ ዶ/ር ይናገርን
አመስግነዋል፡፡
የሳፋሪኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፒተር ንዴግዋም የኢትጵያ መንግስት ጥረታችንን ለመደገፍ ያሳየው ፈቃደኝነት የሚያነቃቃ
መሆኑን አንስተው፤ በኬንያ እየተተገበሩ ያሉ የሞባይል የፋይናንስ ሥርዓቶችን ተሞክሮ ለማጋራት ዝግጁ መሆናቸውን
ገልጸዋል፡፡
የተከበሩ ዶ/ር ይናገር በበኩላቸው ለቀጠለ አጋርነታቸው የአመራር ቡድኑን አመስግነው፤ የሞባይል የክፍያ መንገዶች
ለአካታች የፋይናንስ ሥርዓት መንገድ የሚከፍቱ እንደሆኑና በኬንያ ከተገኘው ስኬት ለምድ በመቅሰም ኢትዮጵያ ውስጥ
ያለውን ሥርዓት ለማሻሻል ያላቸውን ጉጉት ገልጸዋል፡፡

የግንባታ (የከፍታ ላይ) ሥራ የደህንነት ሥልጠና የሚሰጡ፣ የከፍታ ደህንነት ቀበቶዎችንና የደህንነት ቁሳቁሶችንየሚያቀርቡ በቂ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶች እንፈልጋለን፡፡ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታ...
19/12/2021

የግንባታ (የከፍታ ላይ) ሥራ የደህንነት ሥልጠና የሚሰጡ፣ የከፍታ ደህንነት ቀበቶዎችንና የደህንነት ቁሳቁሶችን
የሚያቀርቡ በቂ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶች እንፈልጋለን፡፡ የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች እስከ ሰኞ
ታህሳስ 18/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 11 ሠዓት ድረስ አስፈላጊዎቹን ሰነዶች ወደ [email protected] በመላክ
እንድመትዘገቡ እናሳስባለን፡፡

የቮዳኮም ዋና ሥራ አሥፈጻሚ የሆኑትን ሻሚል ጁሰብ እና የሳፋሪኮም ኃ/የተ/የግል ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፒተርንዴግዋን ያካተተው የዓለም አቀፍ አመራር ቡድን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽንን ጎብ...
18/12/2021

የቮዳኮም ዋና ሥራ አሥፈጻሚ የሆኑትን ሻሚል ጁሰብ እና የሳፋሪኮም ኃ/የተ/የግል ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፒተር
ንዴግዋን ያካተተው የዓለም አቀፍ አመራር ቡድን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽንን ጎብኝቷል፡፡
በጉብኝቱ ለሁላችንም ጥሩ ልምድ የመቅሰሚያ ጊዜ መሆኑን በመግለጽም አገልግሎት ለመጀመር ስለሚደረገው ዝግጅት
ያላቸውን ቀና ሐሳብ አጋርተዋል፡፡ ኢንጂነር ባልቻ ቡድኑ ላሳየው ተነሳሽነት ምሥጋናቸውን አቅርበው ዕቅዶቻችንን
ለማሳካት ባለው ሂደት ውስጥ እገዛ ለማድረግ ያላቸውን ተነሳሽነት ገልጸዋል፡፡
የአመራር ቡድኑ መንግስት ላደረገው ድጋፍ እና የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ለማበርከት ቃል ስለገባቸው አስተዋጽዖዎች
ሁሉ ምሥጋናውን አቅርቧል፡፡
The Global Leadership Team Vodacom Group CEO Shameel Joosub and Safaricom PLC CEO Peter
Ndegwa visited the Ethiopian Communications Authority. They expressed optimism over the
preparations for launch noting that it was a learning curve for everyone.
Eng. Balcha Reba appreciated the efforts of the group and affirmed his commitment to helping
expedite the progress for us to achieve our goals.
The leadership team appreciated the support given by the Government and facilitation offered by
the ECA to Safaricom Ethiopia.

የሥራ አስፈጻሚዎቻችን ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አመራሮች ጋር ትውውቅ እድርገዋል። የቴሌኮም ገበያው በርካታእድሎች ያሉት እና ብዙ ሊሰራበት የሚችል ዘርፍ በመሆኑ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገ...
18/12/2021

የሥራ አስፈጻሚዎቻችን ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አመራሮች ጋር ትውውቅ እድርገዋል። የቴሌኮም ገበያው በርካታ
እድሎች ያሉት እና ብዙ ሊሰራበት የሚችል ዘርፍ በመሆኑ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በዚህ
ወቅት በመገኘታችን ኩራት ይሰማናል። ሚዲያዎች ደግሞ በሁሉም ቤት በቀላሉ ለመድረስ የሚያስችሉን አጋሮቻችን
ናቸው።
ከተለያዩ የቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያዎች እንዲሁም የዲጂታል እና የኅትመት ሚዲያ አመራሮች ጋር ተገናኝተን እስካሁን
የተሰሩ እና በቀጣይ የታቀዱ ተግባራትን አሳውቀናል።
ወደገበያ ለመግባት በዝግጅት ላይ በምንገኝበት በዚህ ወቅት፤ በተለያዩ የኅትመት ሚዲያዎች ባወጣናቸው የፍላጎት
መግለጫዎች መሠረት አብረውን ለመሥራት ፍላጎት ያሳዩ አገልግሎት ሠጪዎች ተነሳሽነት አስደናቂ ነው፡፡ ከ400 በላይ
ማመልከቻዎችን ተቀብለን መስፈርቶቹን ከሚያሟሉት 25 ጋር ለመሥራት የመረጥን ሲሆን፤ እነዚህንም በቀጣዮቹ 2
ሣምንታት ውስጥ የምናሳውቅ ይሆናል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን በጥር ወር እስከ 100 የሀገር ውስጥ ሠራተኞችን
የመቅጠር ዕቅዳችንን ለማሟላት እየሰራን ከመሆናችን በተጨማሪ በ2014 ዓ.ም መጨረሻ 1000 ኢትዮጵያውያን
ሠራተኞች እንዲሁም በቀጣይ 10 ዓመታት ከ1.5 ሚሊየን በላይ የሥራ ዕድሎችን ለማመቻቸት ስለተያዘው ዕቅድ
አስረድተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት ለተነሱ ጥያቄዎች አመራሮቻችን ዝርዝር ማብራሪያዎችን ሠጥተዋል፡፡
ግብዣችንን አክብረው በውይይቱ የተገኙ መገናኛ ብዙኃን አመራሮችን ከልብ እናመሰግናለን፡፡

የሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም፣ ቮዳፎን፣ ሱሚቶሞ እና ሲዲሲ ጥምረት (የግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ) ልዑካን እናየሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አመራሮቻችን ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዳይሬክተር ...
17/12/2021

የሳፋሪኮም፣ ቮዳኮም፣ ቮዳፎን፣ ሱሚቶሞ እና ሲዲሲ ጥምረት (የግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ) ልዑካን እና
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አመራሮቻችን ከኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ኢንጂነር ባልቻ ጋር
ተወያይተዋል።
ከጥምረቱ አባላት አንዱ የሆነው የቮዳኮም ግሩፕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ዲያን ካስተሊክ፣ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ
ኢንጂነር እስካሁን ላደረጉልን ያልተቋረጠ ድጋፍ እና መልካም ግንኙነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ሚስተር ዲያን፣ “ወደ ኢትዮጵያ ገበያ መግባት አስደሳች ነው፡፡ እንደ ቮዳኮም ሌሎች አገራት ያለንን ልምድ ማካፈል
መቻላችንም ያስደስተናል፡፡ ቮዳኮም ለዲጂታል አካታችነት እና ለፋይናንስ አገልግሎቶች ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ
በኢትዮጵያ ከቴሌኮም አቅርቦት በተጨማሪ ሌሎች እገዛዎችን ለማድረግ እንደሚሰራ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል ፡፡
ኢንጂነር ባልቻ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ወደ አገር ውስጥ ለሥራ የሚያስፈልጉትን
ቁሳቁስ በማስገባት እና የባለድርሻ አካላት ግንኙነትን በማመቻቸት ሳፋሪኮም ጥራት ያለው የቴሌኮም አገልግሎት
ማቅረብ እንዲችል እገዛ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል፡፡
የሳፋሪኮም የውጪ ጉዳዮች እና ሬጉላቶሪ ኃላፊ ሚስተር ማቲው ሃርቬ-ሃሪሰን፣ ድርጅታችን የፈቃድ ግዴታዎችን እና
መመሪያዎችን በመከተል በተቻለው ፍጥነት የኔትዎርክ አቅርቦቱን ለማቀላጠፍ አፅንዖት ሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ሚስተር ማቲው በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በጉምሩክ እና ኢምፖርት ሂደቶች ለሳፋሪኮም
ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
ውይይቱ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሚገኝበትን የዝግጅት ደረጃ እና በቀጣይ የሚሠሩ ሥራዎችን በመግለጽ ተጠናቋል፡፡

በሶፍትዌር ደቨሎፐር ልምድ ያላቸው አገልግሎቶችን የሚያቀርቡልን ድርጅቶችን እንፈልጋለን ። ተፈላጊው የቦታ ዓይነትያላችሁ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ማመልከቻዎቻችሁን ወደ developerbids@...
07/12/2021

በሶፍትዌር ደቨሎፐር ልምድ ያላቸው አገልግሎቶችን የሚያቀርቡልን ድርጅቶችን እንፈልጋለን ። ተፈላጊው የቦታ ዓይነት
ያላችሁ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ማመልከቻዎቻችሁን ወደ [email protected] እስከ ታህሳስ 10 ቀን
2021 ቀን 2014 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ መላክ ትችላላችሁ።

በመሀል አዲስ አበባ ለኪራይ ተስማሚ የሆኑ የቢሮ ቦታዎችን መከራየት እንፈልጋለን። ተፈላጊው የቦታ አይነት ያላችሁግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች ማመልከቻዎቻችሁን ወደ bids@safaricom.et እ...
27/11/2021

በመሀል አዲስ አበባ ለኪራይ ተስማሚ የሆኑ የቢሮ ቦታዎችን መከራየት እንፈልጋለን። ተፈላጊው የቦታ አይነት ያላችሁ
ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች ማመልከቻዎቻችሁን ወደ [email protected] እስከ ቅዳሜ ኅዳር 25 ቀን 2014 ከቀኑ 11፡
00 ሰዓት ድረስ መላክ ትችላላችሁ። .
We are looking for suitable office space for lease in the central area of Addis Ababa. If you have
office space that meets the criteria listed, please send your offer and details to bids@safaricom.
et no later than Saturday, 4th December 2021 at 5:00 pm.

የኢንተርፕራይዝ ትሥሥር ቁሳቁሶችን ሥርጭት፣ጥገና እና የድጋፍ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡልን ድርጅቶችንእንፈልጋለን። የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ከሆነ የተጠቀሱትን አስፈላጊ ሰነዶች በ eb...
27/11/2021

የኢንተርፕራይዝ ትሥሥር ቁሳቁሶችን ሥርጭት፣ጥገና እና የድጋፍ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡልን ድርጅቶችን
እንፈልጋለን። የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ከሆነ የተጠቀሱትን አስፈላጊ ሰነዶች በ [email protected]
እስከ ዓርብ ኅዳር 24 ቀን 2014 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
We are looking for a reputable firm/s to provide Enterprise connectivity solutions, deployment,
maintenance, and support services. If you meet the stated requirements please submit the
requested documents to [email protected] no later than Friday, 3rd December 2021 at 5:00
pm.

የሰነድ ትርጉም አገልግሎት የሚሰጡ አጋሮችን እንፈልጋለን። ከታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ባለሙያዎች እናድርጅቶች የተጠየቁትን ሰነዶች በ bids@safaricom.et ከረቡዕ ኅዳር 2...
26/11/2021

የሰነድ ትርጉም አገልግሎት የሚሰጡ አጋሮችን እንፈልጋለን። ከታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ባለሙያዎች እና
ድርጅቶች የተጠየቁትን ሰነዶች በ [email protected] ከረቡዕ ኅዳር 22 ቀን 2014 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ
ትችላላችሁ፡፡
We are looking for suitable partners for the provision of document translation services. If you meet
the stated requirements please submit the requested documents to [email protected] no later
than Wednesday, 1st December 2021 at 5:00 pm

የድርጅታችን ሥራ አስፈጻሚዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ሥርዓት ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ወ/ሮ ማርታኃይለማርያም እና የክፍያ ሥርዓት ቁጥጥር እና ልማት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደስታ ጋር ስለ...
26/11/2021

የድርጅታችን ሥራ አስፈጻሚዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የክፍያ ሥርዓት ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ወ/ሮ ማርታ
ኃይለማርያም እና የክፍያ ሥርዓት ቁጥጥር እና ልማት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደስታ ጋር ስለንግድና አገልግሎታችን
የማስጀመሪያ ምዕራፍ ሥራዎች እንዲሁም የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ግብ በመደገፍ ዙሪያ ተነጋግረዋል፡፡
Officials of our company met with W/ro Martha Hailemaria (Director of Payment Settlement) and
Ato Solomon Desta (Principal payment systems oversight & Development) of the National Bank of
Ethiopia to discuss our commercial launch, supporting Ethiopia’s digital transformation objectives.

የሥራ አመራሮቻችን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ከሆኑት ከክብርት ሌሊሴ ነሜ ጋር ተገናኝተው፤ በንግድእና አገልግሎቶቻችን የመጀመሪያ ምዕራፍ ሂደት እና የዲጂታል ኢትዮጵያ ዕቅድን...
25/11/2021

የሥራ አመራሮቻችን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ከሆኑት ከክብርት ሌሊሴ ነሜ ጋር ተገናኝተው፤ በንግድ
እና አገልግሎቶቻችን የመጀመሪያ ምዕራፍ ሂደት እና የዲጂታል ኢትዮጵያ ዕቅድን እውን ለማድረግ ስላለን ደጋፊ ሚና
ተነጋግረዋል፡፡
Our officials met with H.E Lelise Neme, Ethiopia Investment Commission Commissioner, to give
updates on our preparations for commercial launch, supporting digital Ethiopia objectives.

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Safaricom Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share