10/08/2021
"መንጋውን ንብ ለመያዝ ሠራተኛውን ንብ በሙሉ ማሳደድ ሳይሆን ዘዴው አውራውን መያዝ ነው።"ከሰንፔር ግድግዳው እልፍኝ ለማደርና የውስጡን ምሥጢራት ለማግኘትም መፍትሔው ቁልፉን መቀጥቀጥ ሳይሆን መፍቻውን ከያዘው ፈልጎና ጠይቆ ማግኘት ነው።ገነት ለመግባት መፍትሔው ጉልበት ማፈርጠም ሳይሆን መልካም መሥራት ነው፤በጉልበት ቢሆን ኑሮ እስክንድር ጠቢብ በአሞራ ፈረሱ ዘው ብሎ በገባ ነበር።
አስተዋይ ዓይነ ልቦች ከተከለሉ ቀንም ሌሊትም ጨለማ ናቸው።ከበሩ ደግሞ ሌሊቱም ቀኑም ብርሃን ናቸው።ሰው ጥንትም ሆነ ዛሬ የሚሸወድ ከተሰጠውና በቀላሉ ከሚያገኘው ይልቅ ግብ ግብ መግጠሙና ዙሪያ ጥምጥም ጉዞውን መምረጡ ነው።ቃኤል አቤል ወንድሙን በበቀል ገድሎ ቆንጆ ሚስት ለማግኘት ከመሞከር ይልቅ የአምላኩንና የአባቱን ፈቃድ ቢከተል ኑሮ መፍትሔ በኖረውና የኖድ ሽፍታ የምድር ተቅበዝባዥ ሁኖ ባልቀረ ነበር። ቁልፍ ካለ መፍቻም አለ።ካለመፍቻም የሚቆለፍ በር የለም፤አይኖርምም።ሁለቱም በእጅህ አሉ፤ካልታየህ ከያዘው መጠየቅና ፈልጉ ማግኘት ነው።ሰዶ ማሳደድ ፣ መፍቻ ጥሎ ቁልፍ ለመስበር መታገል ሁለተኛ እዳ ጥበብ ሳይሆን ከራስ መጣላት ነው።"እሳትና ውሃ ቀርቦልሃል፤እጅህን ወደ መረጥከው አስገባ።"...
፠ሰማያዊ መፍቻ