DeritaTech Solution

DeritaTech Solution DeritaTech Solution is a Technology page providing IT tips, Tricks and How to videos.Follow us.

ቴሌግራም Wallet በኢትዮጵያ የሚደረግ የክሪፕቶ ግብይት (P2P Trading) ሊያቆም ነው!በቴሌግራም ላይ ክሪፕቶ ግብይት መድረክ የሆነው ዋሌቴ (Wallet) ከግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ...
30/05/2026

ቴሌግራም Wallet በኢትዮጵያ የሚደረግ የክሪፕቶ ግብይት (P2P Trading) ሊያቆም ነው!

በቴሌግራም ላይ ክሪፕቶ ግብይት መድረክ የሆነው ዋሌቴ (Wallet) ከግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም (ከ June 2, 2026) ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶችን (P2P Trading) እንደሚያቆም አስታወቀ።
ይህ ውሳኔ የተወሰደው የሀገሪቱን የፋይናንስ ህግ መሰረት አድርጎ እንደሆነም ይፋ ተደርጓል።

ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ሁሉም በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ የP2P ትሬዲንግ ማስታወቂያዎች በሙሉ እንዲነሱ ይደረጋል ፤ አዲስ ማስታወቂያዎችንም Post ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል።

ከቀነ ገደቡ በፊት የተጀመሩ ግብይቶች በተለመደው አሰራር መሠረት መፈጸም እንደሚቻል ና ተጠቃአሚዎች በሂደት ላይ ያሉ የትሬዲንግ ስምምነቶችን በፍጥነት እንዲያጠናቅቁ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደምም ፦
- Bitget
- Binance
- Okx
- Bybit የመሳሳሉ መድረኮች በኢትዮጵያን ብር የሚደረጉ የክሪፕቶ ግብይቶች (P2P) ማቆማቸው ይታወሳል።

አሁን ደግሞ በP2P ግብይት በስፋት የሚታወቀው Telegram Wallet ከግንቦት 25,2018 በኋላ በኢትዮጵያ ብር መስራት እንደሚያቆም ታውቋል።

ቴሌግራም ዋሌትም ይሁን ሌሎች ከላይ የጠቀስናቸው በኢትዮጵያ ብር የክሪፕቶ ግብይት ለማቆማቸው እንደምያንያት የተገለጸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (NBE) የአቻ ለአቻ (P2P) የንግድ ልውውጥ ሕገ-ወጥ መሆኑን በመግለጹ ና ከብር ውጪ በቨርቷል ከረንሲ የሚደረጉ ግብይቶች ህጋዊ እንዳልሆኑ በቅርቡ የካቲት 27,2026 ላይ ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ በማውጣቱ እንደሆነም ተነግሯል።

የይለፍ ቃልዎን በቀላሉ ያስተዳድሩ!  ለተለያዩ ጉዳዮች የምንጠቀምባቸውን ጠንከር ያሉ ፓስወርዶች ወይም የይለፍ ቃሎች ለማዘጋጀት ፣ በቀላሉ ና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ሌሎች ሼር ማድረግ ቢያ...
29/05/2026

የይለፍ ቃልዎን በቀላሉ ያስተዳድሩ!

ለተለያዩ ጉዳዮች የምንጠቀምባቸውን ጠንከር ያሉ ፓስወርዶች ወይም የይለፍ ቃሎች ለማዘጋጀት ፣ በቀላሉ ና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ሌሎች ሼር ማድረግ ቢያስፈልገን ፣ ብዙ የይለፍቃሎችን ለማስታወስ ተቸግረን ወረቀት ላይ ከመጻፍ የሚከተሉትን webapps ይጠቀሙባቸው።

1.https://nordpass.com
2.https://bitwarden.com
3.https://1password.com

እነዚህ ዌብ አፕስ አጠቃላይ የይለፍ ቃሎቻችንን ለማስተዳደር እንዲሁም ለግል ወይም ለቢዝነስ ዳታ breach መኖር አለመኖሩን ያጣርልናል።

#ፓስወርድ

የ2018ቱን ሚሊየን ሎተሪ ለቆረጣችሁ ፤ ዕጣው ዛሬ የወጣ ሲሆን ፤ 50 ሚሊየን ብር የሚያስገኘው የአንደኛው ዕጣ አሸናፊ ቁጥር 0630907 ሆኗል።
28/05/2026

የ2018ቱን ሚሊየን ሎተሪ ለቆረጣችሁ ፤ ዕጣው ዛሬ የወጣ ሲሆን ፤ 50 ሚሊየን ብር የሚያስገኘው የአንደኛው ዕጣ አሸናፊ ቁጥር 0630907 ሆኗል።

Facebook , Instagram እና WhatsApp premium subscription !  ሜታ ኩባንያ እንዳስታወቀው ከእስካሁኑ በማስታወቂያ ላይ ብቻ የተመሰረተው የገቢ ምንጭ ወጣ በማለት  ...
28/05/2026

Facebook , Instagram እና WhatsApp premium subscription !

ሜታ ኩባንያ እንዳስታወቀው ከእስካሁኑ በማስታወቂያ ላይ ብቻ የተመሰረተው የገቢ ምንጭ ወጣ በማለት Facebook Plus ፣ Instagram Plus እና WhatsApp Plus የተሰኙ ና የሚከፈልባቸው ነገር ግን ተጨማሪ ፊቸሮች ያላቸውን Subscription tiers ይፋ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪም ኩባንያው ለንግድ ተቋማት፣ ለይዘት ፈጣሪዎች እና ለአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ምርት ተጠቃሚዎች የሚሆኑ ተጨማሪ የክፍያ ዕቅዶችንም እያዘጋጀ መሆኑን ገልጿል። ይህንን ተከትሎም የኩባንያው የአክሲዮን ዋጋ የ3% ጭማሪ አሳይቷል።

Facebook እና Instagram Plus ላይ ከተካተቱት አዳዲስ ፊቸሮች መካከል የተጠቃሚዎች Story ምን ያህል ግዜ በማን በተደጋጋሚ እንደታየ ማወቅ ማስቻል ፣ ያልተገደበ የስቶሪ ተመልካች ዝርዝር መፍጠር መቻል ፣ Story ከ24 ሰዓት በላይ እንዲቆይ ማድረግ ና ሌሎችም በርካታ ፊቸሮች አሏቸው።

WhatsApp Plus ላይ ካሉት አዳዲስ ፊቸሮች መካከል custom ringtones, additional pinned chats, list customization ና premium stickers ይገኙበታል።

የፌስቡክ ፕላስ ና ኢንስታግራም ፕላስ ተጠቃሚዎች በወር 3.99 ዶላር የሚከፍሉ ሲሆን የWhatsApp ተጠቃሚዎች ደግሞ የፕላስን ፊቸር ለማግኘት 2.99 ዶላር በወር ይጠበቅባቸዋል።

ሜታ ሁሉንም አዳዲስ የsubscription plans ሜታ ዋን (Meta One) በሚል በአዲስ ብራንድ ስር ለማጠቃለል ማቀዱም ታውቋል።

ለውሮ ና ቡቺ አስተርጓሚ!    ድመቶቻችን ሚያው  ሲሉ እና የውሾችን የጩኸት ድምጽ ስንሰማ ምን ማለታቸው እንደሆነ ለመረዳት የሚያስችል የቴክኖሎጂ መፍትሄ ከወደ ቻይና ብቅብሏል።   በቻይናዋ...
26/05/2026

ለውሮ ና ቡቺ አስተርጓሚ!

ድመቶቻችን ሚያው ሲሉ እና የውሾችን የጩኸት ድምጽ ስንሰማ ምን ማለታቸው እንደሆነ ለመረዳት የሚያስችል የቴክኖሎጂ መፍትሄ ከወደ ቻይና ብቅብሏል።

በቻይናዋ Hangzhou የሚገኝ Meng Xiaoyi የተሰኘ የቴክኖሎጂ startup ከአሊባባ ክላውድ (Alibaba Cloud) ጋር በመተባበር PettiChat የሚል ስያሜ የተሰጠው ና በኤአይ የተደገፈ Pet translator device አስተዋውቋል።

27.2 gram ብቻ የሚመዝነው ይህ አስተርጓሚ መሳሪያ በአንገታቸው ላይ በመታሰር የእንሰሳቱን ድምጽ ሪከርድ ለማድረግ ማይክ ያለው ሲሆን የሚያሳዮትን የአካል እንቅስቃሴ ደግሞ በMotion sensor እንዲሁም በAccelerometer በመረዳት እንደሚሰራ ተነግሯል።

መሳሪያው ይህን ሪከርድ ያደረገውን ድምጽና የአካል እንቅስቃሴ ለመተንተን ወይም ፕሮሰስ ለማድረግ የአሊባባ ክላውድን Qwen AI model የሚጠቀም ሲሆን ካምፓኒው የሰራሁት ተርጓሚ መሳሪያ የረሃብ ስሜት ፣ ፍርሃትን እና ደስታን ጨምሮ ከ20 በላይ ውሾች ና ድመቶች የሚያሳዩትን ስሜታዊ ሁኔታዎች እንስከ 95% በትክክል የመተጎም ብቃት እንዳለው ገልጿል።

ይህ አስተርጓሚ መሳሪያ በ799 yuan ወይም 118 ዶላር ገደማ ለገበያ ሊቀርብ እንደሚችል ና እስካሁን ባለውም በርካታ ትዕዛዞችን እየተቀበለ እንደሆነ ታውቋል።

አዲሱ BYD ያስተዋወቀው ክሪክ ለምኔ ያለው እጅግ ዘመናዊ ተሽከርካሪ!    የቻይናው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ BYD ሰሞኑን ዓለምን እያነጋገረ ያለ አዲስ ነገር ይዞ ተከስቷል ...
21/05/2026

አዲሱ BYD ያስተዋወቀው ክሪክ ለምኔ ያለው እጅግ ዘመናዊ ተሽከርካሪ!

የቻይናው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያ BYD ሰሞኑን ዓለምን እያነጋገረ ያለ አዲስ ነገር ይዞ ተከስቷል ፤ ይሄውም ኩባንያው ሰሞኑን ባስተዋወቀው የBYD leopard Bao 8 የተሰኘ ተሽከርካሪው አዲስ ስሪት ላይ ይፋ ያደረገው Ultra fully active hydraulic suspension ቴክኖሎጂ ፤ ይህ ተሽከርካሪ እያንዳንዱን ጉማዎቹን በየተራ ክፍ በማደግ ክሪክ ሳያስፈልገው በራሱ አየር ላይ በመቆም ጎማ መቀየር እንድንችል ወይም በሶስት ጎማዎች ብቻ ሚዛኑን ጠብቆ መሄድ እንዲችል ያስችላል።

ይህ ግንቦት 13,2026 የተዋወቀው BYD Leopard 8 Flash Charging Edition የሚጠቀመው አዲሱ ultra fully active hydraulic suspension ቴክኖሎጂ ተሽከርካሪው በገደላማ ና እጅግ አስቸጋሪ ቦታዎች ላይ ያለ ችግር ጎማዎቹን በየተራ እስከ 300ሚሊ ሜትር ወይም 30ሴንቲ ሜትር ድረስ በማንሳት እንዲጓዝ የሚያደርግ ሲሆን አሽከርካሪው የፈለገውን ጎማ መርጦ እንዲነሳ ማዘዝ ይችላል።

ይህ ቴክኖሎጂ Yangwang U9 Supercar በተሰኘው እጅግ ቅንጡ በሚባሉ የቢዋይዲ ተሽከርካሪዎች ምድብ በሚካተተው ተሽከርካሪ ላይም እንዳለ ተነግሯል ፤ ይህ ሱፕር ካር በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ላይ የመዝለል አቅም እንዳለውም ታውቋል።

BYD የመጀመርያውን Leopard bao 8 በይፋ ያስተዋወቀው April 8,2024 እንደነበር ይወሳል።

የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የ2026 የAI summer Camp ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል ፤ ከአንደኛ እስከ 12 ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ኤአይን ጨምሮ በተለያዩ የቴክኖሎ...
15/05/2026

የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የ2026 የAI summer Camp ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል ፤ ከአንደኛ እስከ 12 ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ኤአይን ጨምሮ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ኮርሶች ልዩ የክረምት ስልጠና በነጻ ማዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል ።

በFundamentals of AI ፣ በProgramming ፣ በMachine Learning ፣ Robotics and IOT ፣በData science ና በሌሎችም የኤአይ ስልጠና ዘርፎች ፍላጎቱ ላላቸው ና መስፈርቱን ለሚያሟሉ ለመጪው ክረምት ስልጠና መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ለዚህ ስልጠና ለመመዝገብ ማስፈንጠርያውን በመጫን ና በgmail አድራሻችን በመግባት ና የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት መመዝገብ እንችላለን ፡ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSf_0QSAISZUjQxEttCFVEBjbWtHrxYQo_XKle_vcqKREsAs9g/viewform

አሁን ላይ በብዙዎቻችን ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ ለእያንዳንዷ ነገር እንደ ግል አማካሪ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ChatGPT እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር November 2022 ላይ ድንገት ተከስ...
13/05/2026

አሁን ላይ በብዙዎቻችን ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ ለእያንዳንዷ ነገር እንደ ግል አማካሪ ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ChatGPT እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር November 2022 ላይ ድንገት ተከስቶ የጉግልን ሰርች ዶሚናንስ ጥያቄ ውስጥ ከቶታል ፤ ቻት ጂፒቲን ወይም ሌሎች ኤአይ ቻት ቦቶችን ሰዎች ከጎግል በበለጠ እንዲመርጧቸው የሆነበት ዋነኛው ምክንያት ፤ Google Search ትንሽ አድካሚ ና ጥረት የሚጠይቅ ነው ፤ ጉግል ላይ ሰርች ላደረግናቸው ነገሮች ለኛ ተስማሚ የሆነውን ና ለፍለጋችን በጣም ቅርብ የሆነውን የፍለጋ ውጤት ጉግል ከሚሰጠን በሺዎች የሚቆጠሩ ውጤቶች መካከል መምረጥ ይጠበቅብናል ፤ ቻት ጂፒቲ ላይ ስንሄድ ያለ ምንም ልፋት ለፍለጋችን ቀጥተኛ ምላሽ ከማግኘታችንም ባሻገር ልክ ሰዎችን እንደምንጠይቀው በውይይት ቃና የምንፈልገውን ነገር መጠየቅ ስለሚያስችለን ነው።

ChatGPT ከ ጉግል አንጻር ሲታይ ምን ልዩነት አለው? ምን አይነት ጥያቄዎችስ መጠየቅ የለብንም? ጉግልን ሊተኩ የሚችሉ አንዳንዴም የተሻሉ አማራጭ search engines የትኞቹ ናቸው ? እነዚህ እና ሌሎች መሰል መረጃዎችን የያዘውን ቪዲዮ ይመልከቱ!

| | | |EthioComputer School| Useful Videos : Exce...

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / INSA አምስተኛውን የINSA cyber talent challenge Summer camp ፕሮግራም ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል !ለዚህ ፕሮግራም መመዝ...
07/05/2026

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር / INSA አምስተኛውን የINSA cyber talent challenge Summer camp ፕሮግራም ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል !

ለዚህ ፕሮግራም መመዝገብ የሚፈልጉ ተሳታፊዎች ፤ ፋይዳ መታወቂያ ወይም የፋይዳ ቁጥር ሊኖራቸው እንደሚገባ ተገልጿል ፤
ለመመዝገብ ፡ https://ctc.insa.gov.et/registration ላይ በመግባት ፎርሙን መሙላት ይኖርብናል።

Keylogger ምንድን ነው?   Keylogger ወይም Key Stroke logger ኮምፒውተራችን ላይ ወይም ስልካችን ላይ የምንጽፋቸውን ሁሉንም key strokes ማለትም ከኪቦርድ ታይፕ የ...
07/05/2026

Keylogger ምንድን ነው?

Keylogger ወይም Key Stroke logger ኮምፒውተራችን ላይ ወይም ስልካችን ላይ የምንጽፋቸውን ሁሉንም key strokes ማለትም ከኪቦርድ ታይፕ የምናደርጋቸውን characters/Text ሁሉ ፓስወርዳችንን ሳይቀር ከትቦ የሚይዝ በHardware ወይም በSoftware መልክ የተዘጋጀ tool/መሳሪያ ነው። ሶፍትዌር ኪይሎገር ለስልክም ለኮምፒውተራችንም በቀላሉ online ልናገኝ እንችላለን።

Keylogger ብዙ ግዜ እና በአብዛኛው የሚታወቀው በሃገሮች ወይም በሳይበር ጥቃት አድራሾች የሰዎችን ወይም የተቋማትን መረጃ ለመስረቅ ወይም ለስለላ (Espionage) ተግባር በመዋል ሲሆን ከዚህ ባለፈም ለበጎ አላማ ጥቅም ላይ እንደሚውል ይነገራል።


Keylogger ጥቅም ላይ ከሚውልባቸው በጎ አላማዎች / Legitimate uses የተወሰኑትን ስንመለከት ፡

1. Employee Monitoring ፡ ቀጣሪዎች በሰራተኞቻቸው ኮምፒውተር ላይ Keylogger ጭነው የመረጃ ስርቆትን ፣ የሰራተኛውን ምርታማነት እንዲሁም ለፖሊሲዎች ተገዢ መሆነቸውን ለመከታተል ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

2. Parental Control : ወላጆች ለልጆቻቸው ደህንነት ኪይ ሎገር ያለው የሞኒትሪንግ ሶፍትዌር ሊጠቀሙ ይችላሉ።

3. IT Support & Troubleshooting : የአይቲ ባለሞያዎች የሶፍትዌር ወይም የሃርድዌር ችግሮችን ለማወቅ ና ለመፍታት እንዲረዳቸው keylogger ጭነው የተጠቃሚዎችን input ሊከታተሉ ይችላሉ።

4. Software Debugging & Testing ፡ **ሶፍትዌር አልሚዎች ለቴስቲንግ ና logical errorsን ለመለለየት ይጠቀሙበታል።

5. CyberSecurity Research : የሳይበር ደህንነት ባለሞያዎች እና ethical hackers ለpenetration testing ይጠቀሙበታል።

6. Law Enforcement : የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በወንጀል ምርመራ ወቅት ሊጠቀሙበት ይችላሉ። ለሌሎችም በርካታ ጉዳዮች ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል።

ኮምፒውተራችን ላይ ወይም ስልካችን ላይ keylogger ይኖራል ብለን ከጠረጠርን ምን እናድርግ?

Software Keylogger ይኖራል ብለን ከፈራን ፤ ኮምፒውተራችን Task manager ላይ ሄደን ለየት ያሉ ና የማናውቃቸው እንግዳ ፕሮሰሶች ካሉ ምንነታቸውን አጣርተን ማስቆም ፣ ከኛ እውቅና ውጪ በራሳቸው የሚነሱ Startup ፕሮግራሞች ካሉ እነሱን ማስቆም ፤ ኮምፒውተራችን ላይ ወይም ስልካችን ላይ የተጫኑ የማናውቃቸው ሶፍትዌሮች ካሉ ምንነታቸውን አጣርቶ እርምጃ መውሰድ እኒዱም ኮምፒውተራችንን full virus እስካን ማድረግ።

Hardware Keylogger ይኖራል ብለን ከጠረጠርን በኪይቦርድ ና በኮምፒውተሩ USB port መካከል የተሰካ የማናውቀው ነገር ካለ መጠርጠር ወይም ነቅሎ ሌላ ኪይቦርድ መጠቀም።


Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when DeritaTech Solution posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to DeritaTech Solution:

Share