Ge'ez Computers Clinic

Ge'ez Computers Clinic We are working on Electronics

17/08/2024

Join Us

17/08/2024
Acer Aspire 4736zIntel® Pentium® mobile processor T4400 (1 MB cache, 2.2GHz, 800 MHz FSB)3GB DDR2 RAM 320GB SATA HDDBuil...
17/08/2024

Acer Aspire 4736z
Intel® Pentium® mobile processor T4400 (1 MB cache, 2.2GHz, 800 MHz FSB)
3GB DDR2 RAM
320GB SATA HDD
Built-in Super Multi DVD drive
5-in-1 card reader, supporting Secure Digital™ (SD), MultiMediaCard (MMC), Memory Stick® (MS), Memory Stick PRO™ (MS PRO), xD-Picture Card™ (xD)
14" HD 1366 x 768 pixel resolution, high-brightness

0-hour battery life (only direct)

Price 4500 Birr

Meta Quest 2
17/08/2024

Meta Quest 2

Kyocera DuraXV Extreme E4810 16GB Verizon | Ultra-Rugged Flip Phone IP68 Rated | 4G LTE HD Voice| 5MP Camera | 1770mAh B...
17/08/2024

Kyocera DuraXV Extreme E4810 16GB Verizon | Ultra-Rugged Flip Phone IP68 Rated | 4G LTE HD Voice| 5MP Camera | 1770mAh Battery

17/08/2024

Welcome

11/02/2024

የተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጥቅማ ጥቅሞች

ከኃላፊነት የተነሱ የአገር መሪዎችና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ከኃላፊነት ከተሰናበቱ በኋላ ቀሪ ዘመናቸውን ከመንግሥት የሚያገኟቸው ጥቅማ ጥቅምች በ2002 ዓ.ም. በወጣው አዋጅ ቁጥር 653 ተደንግጓል።

የአገር መሪ ማለት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ወይም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው በአዋጁ የትርጓሜ ክፍል ተደንግጓል።

በመሆኑም አቶ ደመቀ ከኃላፊነት የተነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እንደ መሆናቸው መጠን፣ በተጠቀሰው አዋጅ ላይ የተደነገጉትን ጥቅማ ጥቅሞች በሕይወት እሳካሉ ድረስ የሚያገኙ ይሆናል። በአዋጁ መሠረትም ተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በቀጣዩ የሕይወት ዘመናቸው የሚከተሉትን ጥቅማ ጥቅሞች ከመንግሥት ያገኛሉ።

የግል ወጪና አበል

ተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በኃላፊነት ላይ በነበሩበት ጊዜ ይከፈላቸው የነበረው የወር ደመወዝና አበል ከኃላፊነት ከተሰናበቱ በኋላም ሳይቋረጥ የሚቀጥል ሲሆን፣ መንግሥት በኃላፊነት ላይ ለሚገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የደመወዝና አበል ማስተካከያ ያደረገ እንደሆነም ለተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርም (ለአቶ ደመቀ መኮንን) የግል ወጪና አበል ማስተካከያ እንደሚደረግ በአዋጅ ቁጥር 653 የተደነገገ በመሆኑ ይኼው መብት ይጠበቅላቸዋል።

የመኖሪያ ቤት አገልግሎት

በዚሁ አዋጅ መሠረት ተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው መኖሪያነት የሚያገለግል ከአራት እስከ አምስት መኝታ ክፍሎች ያሉት መኖሪያ ቤት የሚያገኙ ሲሆን፣ የተሟላ የቤት ውስጥ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ደመወዝም በመንግሥት ወጪ ይሸፈንላቸዋል።

የተሽከርካሪ አገልግሎት

በተጨማሪም ተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ደረጃቸውን የጠበቁ ሦስት ለመጓጓዣ የሚያገለግሉ የመንግሥት ተሽከርካሪዎች ይመደቡላቸዋል፡፡

የተሽከርካሪው ሹፌር ደመወዝ፣ የነዳጅና የጥገና፣ እንዲሁም ሌላ ወጪ በመንግሥት ይሸፈናል፡፡ እንዲሁም ለአቶ ደመቀና ለቤተሰቦቻቸው ጥበቃ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎች ጥበቃውን በሚያካሂደው ሪፐብሊካን ጋርድ (የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል) የሚመደብ ይሆናል።

የግል ደኅንነት ጥበቃ አገልግሎት

ተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው የግል ደኅንነት ጠባቂዎች በመንግሥት እንደሚመደብላቸውም የአዋጁ ድንጋጌ ያመለክታል። ጥበቃውን የሚያካሂደው የሪፐብሊካን ጋርድ (የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል) ሲሆን፣ ለአቶ ደመቀና ቤተሰቦቻቸው የሚመደበው የጥበቃ ኃይል መጠን ጥበቃውን በሚያካሂደው አካል የሚወሰን ይሆናል፡፡

የሕክምና አገልግሎት

በአዋጅ ቁጥር 653 ድንጋጌ መሠረት ተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀና ቤተሰቦቻቸው በመንግሥት ወጪ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የተሟላ የሕክምና አገልግሎት ያገኛሉ፡፡ የሕክምና አገልግሎቱ እንደ ሁኔታው በመንግሥት ወይም በግል የጤና ተቋም የሚሰጥ ሲሆን፣ ባለመብቱና ቤተሰቦቻቸው በአገር ውስጥ የጤና ተቋም ለሕክምና አገልግሎት የሚተኙ ከሆኑ አገልግሎቱን የሚያገኙት በአንደኛ ደረጃ ማዕረግ ይሆናል፡፡

የቢሮ የስልክና የፕሮቶኮል አገልግሎት

ከኃላፊነት የተሰናበቱት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ቀሪ ዘመናቸውን በተለያዩ ሕዝባዊ አገልግሎቶች በመሰማራት የሚያሳልፉ ከሆነ፣ መኖሪያ ቤታቸው በሚገኝበት ከተማ የቢሮ አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን፣ ራሳቸው መርጠው ለሚቀጥሯቸው አንድ ጸሐፊና አንድ ባለሙያ ደመወዝ በመንግሥት የሚሸፈን ይሆናል።

በተጨማሪም ለቢሮ የሚያስፈልጉ ኮምፒዩተር፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ ፖስታና የመሳሰሉትን አገልግሎቶች መንግሥት ወጪያቸውን ሸፍኖ ያሟላል። ተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ቀሪ ዘመናቸውን የሚገለገሉበት የዲፕሎማቲክ ፓስፖርትና የቪአይፒ አገልግሎት የሚያገኙ ሲሆን፣ የቀድሞ ኃላፊነታቸውን የሚመጥን ሙሉ የፕሮቶኮል አገልግሎት በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ያገኛሉ።

መብቶችንና ጥቅሞቹ የሚቋርጡባቸው ሁኔታዎች

ከኃላፊነት የተነሱ የአገር መሪዎችና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ከኃላፊነት ከተሰናበቱ በኋላ ቀሪ ዘመናቸውን የሚያገኟቸው ጥቅማ ጥቅምች ሊቋረጥ የሚችልበት ሁኔታም በዚሁ አዋጅ ቁጥር 653 ተደንግጓል።

በዚህም መሠረት ተሰናባቹ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርም ሆኑ ሌሎች መሰል መብት የሚያገኙ የአገር መሪዎች መንግሥታዊ ሥርዓትን ለማፍረስ የሞከሩ እንደሆነ፣ የአገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ በሚጥል ተግባር ከተሳተፉ፣ የአገር ክህደት ወንጀል ከፈጸሙ፣ በኃላፊነት ላይ በነበሩበት ወቅት ያገኟቸውን አገራዊ ጉዳዮች የሚመለከቱ ሚስጥራዊ መረጃዎች ካልጠበቁ፣ ወይም ሕገ መንግሥቱንና በሕገ መንግሥቱ መሠረት የተቋቋሙትን ተቋማት ካላከበሩ የሚያገኟቸው ጥቅማ ጥቅሞች የሚቋረጡ ይሆናል።

ይሁን እንጂ እነዚህ መብቶችና ጥቅሞች ሊቋረጡ የሚችሉት ባለመብቱ የተላለፈው ድርጊት ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ቀርቦ የጥፋተኛነት ውሳኔ ከተሰጠና ይኼውም በኋላ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከተወሰነ በኋላ ነው።

ምንጭ:- ሪፖርተር

13/11/2023

ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉት Real Estates (የጋራ የመኖሪያ ቤት ገንቢዎች) ህዝብና መንግስት ላይ የሚጫወት የለም። በተለይ ለኑሮ ግሽበት ዋናውን ሚና እየተጫወቱ ያሉት እነዚህ አካላት ናቸው። እነሱ ቤቶችን ሲሸጡ በዕለቱ ባለው የዶላር ምንዛሪ ነው ከዛም በሁለት ወይም በሶስት ዓመት እናስረክባችኋለን ይላሉ ነገር ግን በቀጠሯቸው አይገኙም። ችግሩ ይሄ ብቻ አይደለም ባሉት ጊዜ ሳያስረክቧቹ ቀርተውም ለወሰዱባችሁም ጊዜ የሚያስከፍሏቹ እናንተኑ በዕለቱ ባለው ምንዛሬ ነው። እነሱ አሥር ዓመት ሥራውን ቢያዘገዩት እናንተ እስከሆናቹ ድረስ የዶላሩን ልዩነት የምትከፍሉት እነሱን ምንም አይጨንቃቸውም ለዚህ ደግሞ የትኛውም ፍርድ ቤት ሄዳችሁ አትረቷቸውም ምክንያቱም ከመጀመሪያው ውሉን ሲያስፈርሟቹ አስበውበት እና ብትከሱም ምንም እንዳታመጡ አድርገው ነው የሚያዘጋጁት። እናም ለብራችን በዚህ መጠን ማሽቆልቆልና ለከፍተኛ የኑሮ ግሽበት የመጀመሪያ ተጠያቂዎች ናቸው። እኔምለው? መንግስት ግን ይሄንን ሳያውቅ ቀርቶ ነው እንዲህ ህዝቡ ላይ ሲጫወቱ ዝም የሚላቸው? ሀገራችንስ የራሷ የተከበረ መገበያያ ገንዘብ እያላት በዶላር መሸጡ ለምን አስፈለገ? እሺ መጀመሪያ ሲያዋውሉ ይሁን እንበል ነገር ግን የክፍያ ጊዜ በደረሰ ቁጥር በዶላር መከፈሉ አግባብ ነው? በዚህ ላይ ደግሞ ውሽት እና ቅጥፈታቸው? የከርሰምድር ውሀ አለው ይሉሃል መጨረሻ ላይ ባይኖረው እመኑኝ ምንም አታመጡም ይሄን ያህል ሊፍት አለው ፣ ጀነሬተር አለው ይሏቹሃል ፣ በቂ የባርኪንግ ቦታ አለው ይሏቹሃል ፣ መዋኛ ገንዳ አለው ይሏቹሃል ፣ የልጆች መጫወቻ እና ጂም አለው ይሏቹሃል ........በአጠቃላይ አለው የማይሏቹ ነገር የለም።ነገር ግን አለው የተባላችሁት ሁሉ ባይኖረው እመኑኝ ምንም አታመጡም።
እባካችሁ ገዢዎች ከማንኛውም ሪልስቴት ቤት ከመግዛታችሁ በፊት በጣም ተጠንቀቁ ውላቸውን በደንብ አንብቡ ብትችሉ ከጎበዝ ጠበቃ ጋር ተመካከሩ። ለሚያጋጥማችሁ ማንኛውም ችግር መንግስትም ህግም ምንም አይረዷችሁም።

ታማኝ ነን የምትሉ አልሚዎች ካላቹ ደግሞ የገዢ ደንበኞቻችሁን ሙሉ መብት የሚያስከብር የውል አንቀጽ ካላቹ እስኪ ማስታወቂያዎቻችሁ ላይ አሳውቁን።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911623192

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ge'ez Computers Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ge'ez Computers Clinic:

Share