15/05/2026
ሚኤሳ ኤለማ ሮቤ (ዶ/ር) -የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የስራ አመራር ቦርድ አባል
ዶ/ር ሚኤሳ በፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የዶክትሬት ድግሪ አላቸው።
የአዳማ ከተማ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ፣ የሻሸመኔ ከተማ ምክትል ከንቲባ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ፣ እንዲሁም በከተማ አስተዳደሩ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ሆነው አገልግለዋል።
አሁን ደግሞ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ሀላፊ ሆነው እያገለገሉ የሚገኙ ስሆን በተግባቦት እና ሚዲያ ስራ የካበተ ሞያና ልምድ ያላቸው መሪ ናቸው።
ዶ/ር ሚኤሳ ከመደበኛ ስራቸው ጎንለጎን በከተማ እና ሀገር አቀፍ ጉዳዮች ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅምን የተመለከቱ በርካታ ጽሁፎችን በዲጂታል ህትመት ሚዲያዎች የሚፅፉ የፖለቲካ ሳይንስ ባለሞያ ናቸው።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤው ሚኤሳ ኤሌማን (ዶ/ር) የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ስራ አመራር ቦርድ አባል አድርጎ ሾሟል።